Wednesday, May 9, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛው የርክበ ካህናት ስብሰባ ተጀምሯል


ትናንት ጧት አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ በመሰየምና የፓትሪያሪኩን የመክፈቻ ንግግር በመስማት ይጀመራል ተብሎ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛው የርክበ ካህናት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በዓል ምክንያት ወደ ዛሬ ጠዋት ተቀይሯል፡፡

  • ማኅበረቅዱሳን የመምህር ዕንቁባህርይ ተከሰተ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪ ዋና ሃላፊነት ሹመት ህገወጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡
  • የአቡነ ጳውሎስና የአቡነ ሣሙኤል ውዝግብ የአሁኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ እንደሚሆነ እየተነገረ ነው፡፡
  • ጥንተ አብሶንና የተሃደሶ መናፍቃን አስተባባሪዎችን አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖድስ ሃይማኖታዊ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • የገዳማትንና የሰሜን አሜሪካን አስመልክቶ በስፋት እንደሚነጋገር ይጠበቃል፡፡

(አንድ አድርገን ግንቦት ልደታ 2004ዓ.ም)፡- የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሃላፊነት ሹመት ህገወጥ የአዲስ አበባ ንበት /ቤቶች ህብረትም የተቃወመው ሲሆን ተቃውሟቸውን የፊታችን ቅዳሜ ይገልጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተቃወሟቸውን አንዳይገልጹ የተለያዩ አካላት ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ በቤተክህነቱ እየተስተዋለ ለመጣው ህገወጥነትና የማፍያ ተግባር በምክንያትነት እንዲሁም ህገ ቤተክርስቲያን በመጣስ፣ ለታህድሶ መናፍቃን መሸሸጊያ በመሆን ቤተክርስቲያኗን ለማፍረስ ለጨለማው ቡድን ወግነዋል፣ አባታዊ ግዴታቸውን አልተወጡም ተብሎ የሚታመነው የፓትሪያሪኩ ጉደይ የመጨረሻ ውሳኔ እደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡


መደበኛው የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ትናንት ሚያዚያ 30 ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት በተገኙበት በጸሎት ተጀምሯል፡፡ በህገወጥ የጨለማው ቡድን አቀነባባሪነት ቤተክህነቱ ሲታመስ በመሰንበቱ ጉባኤው በደራሽ አጀንዳዎች አንዳይጠመድ ተፈርቷል፡፡ጉባኤው ዛሬ ጠዋት አጀንዳ አርቃቂ ኮሜቴ ሰይሞ ከሰዓት በኋላ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ ቤተክርስተያን አሁን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታና ቤተክህነቱ ሰሞኑን ሲያስተናግደው ከነበረው ትዕይንት አንጻር የሚከተሉትን አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚነጋገር ይጠበቃል::

1. የአቡነ ጳውሎስና የአቡነ ሣሞኤል ውዝግብ፡-ከሀምሌ 2001 ዓ.ም ተጀምሮ የነበረው የአቡነ ጳውሎስና የአቡነ ሣሙኤል ውዝግብ ለጊዜው ጋብ ያለ ቢመስልም ከአንድ ወር በፊት አቡነ ጳውሎስ በጻፉት ደብዳቤ አቡነ ሣሞኤል በልማት ኮሚሽኑ ለሚወጣ ወጭ ቼክ ላይ እንዳይፈርሙ የከለከሏቸው ሲሆን በአጸፋው አቡነ ሣሙኤል በፓትሪያሪኩ የተሾሙት የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር አግደውን ያለርሳቸው ፈቃድ ምንም እንዳያደርጉ አዘዋቸዋል፡፡ ፓትሪያሪኩ ይህን ያደረጉት አቡነ ሣሙኤል ለመበቀል ካላቸው ፍላጎት ባሻገር የልማት ኮሚሽንን ገንዘብ በርሳቸው ቁጥጥር ስር ለማስገባት ያላቸውን ፍላጎት እውን ለማድረግ ነው፡፡ ይሄንን ለመከላከል ብጹዕ አቡነ ሣሙኤል በአቡነ ጳውሎስ የተሸሙትን ዶክተር አግደውን የሚፈጹሙትን ማንኛውን ስራ ያለርሳቸው ፈቃድ እንዳያከናውኑ በማድረግ የአቡነ ጳውሎስ ፍላጎትን በተዘዋዋሪ መንገድ አክሽፈውታል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በተመሳሳይ ሰዓት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል በተመሳሳይ መንገድ ቼክ ላይ እንዳይፈርሙ አግደዋቸዋል፡፡ይህ ፓትሪያሪኩ ከህገ-ቤተክርስቲያን በተጻራሪ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ በእርሳቸው ቁጥጥር እንዲሆን ያላቸውን ፍላጎት ፍንትው አድረጎ ያሳያል፡፡በህገ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪኩ በገንዘብ አስተዳደር እንዳይሳተፉ ይከለክላል፡፡ይህ ስልጣን የጠቅለይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ህገ ቤተክርስቲያንን የሚያስጠብቅ ውሳኔ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡.

2. የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ ህገወጥ ሹመትን አስመልክቶ :- ማህበረቅዱሳን ያቀረበውን ጥያቄ መልስ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ማኅበረቅዱሳን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለሁሉም ሊቃነጳጳሳትና ለጠቅላይ ቤተክህነት በ30/08/2004ዓ.ም  በጻፈው ድብዳቤ የመምህር ዕንቁባህርይ ተከሰተ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪ ዋና ሃላፊነት ሹመት ህገወጥ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት አብሮ ለመስራት እንደሚቸገርገልጾል፡፡ማኅበሩ የሹመቱን ህገወጥነቱ ሲያብራራ ህገወጥ የሆኑትን  ቢራዋችንበመቃወማቸው ቆሞስ መላእከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንዲፍራው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውና የህገወጥ ቡድኑ አጋፋሪ የነበረው የመምህር ዕንቁባህርይ ተከሰተ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሃላፊነት ሹመት ህገወጥ በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጠው ይጠይቃል፡፡ ብጹዕ አቡነ ቀለምንጦስ የማደራጃ መምሪያው ሊቀ ጳጳስም እርሳቸው የማያውቁት በመሆኑ እንደማይቀበሉት ገልጸው እንደነበር ይታወቃል፡፡የመምህር ዕንቁባህርይ ተከሰተ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሃላፊነት ሹመትን የአዲስ አበባ ስንበት ት/ቤቶች ሕብረትም የተቃወመው ሲሆን ተቃውሟቸውን የፊታችን ቅዳሜ ይገልጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተቃውሟቸውን አንዳይገልጹ የተለያዩ አካላት ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣሩ ይገኛሉ

3. የጥንተ አብሶ ጉዳይ፡- አባ ሠረቀ ብርሃን ባሳተሙት መጽሐፍእመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባትበማለታቸውና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በፕሪስተን ቲዎሎጅ ሴሚናር ፒኤችዲ መመረቂያ ወረቀታቸው (dissertation) ላይእመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባትብለው መጻፋቸውን ውስጥ ውስጡን በቤተክህነቱ ይወራ የነበረውንእውነትና ንጋትበሚለው በአባ ሠረቀ መጽሐፍ በአስረጅነት በመጥቀሳቸውና ከቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የቤተክርስቲያኒቱን መሠረት እምነት እንደሚያጸና ይጠበቃል፡፡


‹‹ ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ (የአዳም የውርስ ሀጥያት) ጥላ ስር የተወለደች ናት››(To read click here)  በማለት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  እና አባ ሰረቀ ብርሀን እንደሚደግፉት የዛሬ ወር አካባቢ ማስነበባችን ይታወቃል ፤ ይህን ጉዳይ በእኛ ገጽ ከወጣ በኋላ ከ9ሺህ በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል ፤ በተለያዩ መጽሄቶች ታትሞ ሰዎች ዘንድ ደርሶ መነበቡን ለማወቅ ችለናል፡፡ በጊዜው አባ ሰረቀ አንድ መጽሄት ላይ በሰጡት አስተያየት ‹‹ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ልብ ነው›› ማለታቸው የሚታወቅ ሲሆን ፤ ሙሉ ቃለ ምልለሱ እጃችን ላይ ይገኛል  ፤ መረጃውን ለሚፈልግ ሰው ለመስጠት ፍቃደኛ ነን ፤ በዚህ የሲኖዶስ ጉባኤ በዚህ ነገር ላይ ይነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መጽሀፉን በፒዲፌ ያንብቡ(To Read click here)

4. የተሃድሶ መናፍቃንን ስውር ሴራ:በማኅበረቅዱሳንና በስንበት /ቤቶች አማካኝነት የተሃድሶ መናፍቃንን ስውር ሴራ አስመልክቶ የቀረበው መረጃ ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ያሉበት ሚቴ አጣርቶ ስለጨረሰ በተሃድሶ መናፍቃንና በግብረ አበሮቻቸው ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

5. የሰሜን አሜሪካ አህጉረስብከት ያለውን ውዝግብ፡- አቡነ ፋኑኤል የሄዱበትን አፍራሽ አካሄድንና የምእመናን አቤቱታ ለቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ  ከአኅጉረ ስብከቱ ሰራ አስፈጻሚና ከምእመናን ተወካዩች ከአሜሪካ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ይህንን ጥያቄ ለማደባበስ ቅድመ ጉባኤው በኃ/ጊዮርጊስና በአቡነ ፋኑኤል አማካኝነት የተደረገው ደባ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ለዚህም ሲኖዶሱ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡

6. የገዳማት ጉዳይ፡-የተቃጠሉት የአሰቦትና የዝቋላ ገዳም፣ የወልቃይት የስኳር ልማት ፕሮጀክትና የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አጀንዳ እንደሚሆኑ ይገመታል፡፡ ዋልድባን ገዳም አስመልክቶ የማኅበረቅዱሳን አጥኝ ቡድን ሪፖርት ሰሞኑን በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ለፓትሪያሪኩና ለሊቃነጳጳሳት ካለመድረሱ ጋር ተያይዞ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ውይይት ሳይደረግበት ሊቀር እንደሚችል እየተፈራ ነው፡፡

ከአነዚህ በተጨማሪ ፓትሪያሪኩ የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደተለመደው እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡የጨለማው ቡድን ባቀነባበራቸውና ወደ ፊት በሚያቀነባብራቸው ሴራዎች የስብሰባ ጊዜ እንዳይባክንና የቤተክርስቲያኗን ክፉኛ እየጎዷት ያሉት የውስጥ አርበኞች ተጨማሪ ጊዜ እንዳያገኙ ተሰግቷል፡፡ ለዚህም አጀንዳዎችን ለማጽደቅና በቀጣይ ቀናት አጽራረ ቤተክርስቲያንን ለማስታገስና ህገ ቤተክርስቲያን ለማስከበር ለሚወሰኑ ውሳኔዎች የፓኩትሪያሪኩ እምቢተኝነት ብጹዓን ሊቃነጳጳሳትን እንዳያሰላች ይፈራል፡፡ ይህን ለመከላከል ፓትሪያሪኩን ራሳቸውን አጀንዳ በማድረግና ውሳኔ በማሰተላለፍ ስጋቱን መቀነስ ይቻል ይሆናል፡

እኛ እናንተ መረጃ እንድታገኙ ለማስቻል የቻልነውን ያህል መረጃ ከእናንተው ዘንድ ለማድረስ እንሰራለን ፤ እኛም ከመጻፍ አንቦዝንም እናንተም ከማንበብ አትቦዝኑ መልእክታችን ነው፡፡

12 comments:

  1. እግዚአብሔር ቸር ወሬ ያሰማን!!!!

    ReplyDelete
  2. ቸር ወሬ ያሰማን!!!

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር ቸር ወሬ ያሰማን!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. እግዚአብሔር ቸር ወሬ ያሰማን!!!

      Delete
  4. ብዕሩ ዘ-አትላንታMay 9, 2012 at 6:17 AM

    በርቱ ቸር ወሬ ያሰማን። ኃይል የእግዚአብሔር ነዉ። እግዚአብሔር ታሪክ ይለዉጣል።

    ReplyDelete
  5. እግዚአብሄር ሆይ እኛ እኮ ሀጢያተኛ ነን፣ አንተው ግን መሀሪ ነህና እባክህን ስለድንግል እናትህ ብለህ ይቅር በለን፡፡ ምንም ሀጢአተኛ ብንሆንም ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ነገር ሰላም ነስቶናል፤ አምላክ ሆይ እባክህ በአባቶቻችን ጉባኤ ላይ ተገኝተህ ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተክርስቲያን የማያዳግም ውሳኔ እንዲወስን እርዳው፡፡ እንክርዳዱ ስንዴ ነኝ እያለ ነው አምላክ ሆይ እባክህን ስንዴውንም ስንዴ እንክርዳዱን እንክርዳድ በልልን፡፡ እንክርዳዱንም በምህረትህ ስንዴ እንዲሆን ቸርነትህ አይለየው፡፡

    ReplyDelete
  6. መጀመሪያ እንክርዳዱን ከስንዴ መለየት ከዚያ ለስንዴው አስፈላጊውን መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማድረግ ይቻላል::

    ReplyDelete
  7. Yeselam Amelak yemihonewin lebetekerstian yemitekimewin sira endiseru yadirgachew!!!!

    ReplyDelete
  8. Cher werea' yaseman!

    ReplyDelete
  9. Egziabher le hulum gize silalew=hulunim be tiegist entebik.enkirdadun ke sindew yemileyibet gize yederese yimeslal.Weladite Amlak tiradan...Enantem bertu...Amen Amen Amen!!!!

    ReplyDelete