Friday, May 11, 2012

የባቦጋያ መድኃኒዓለም የመሬት ጉዳይ ፍርድ ቤት ለባለሀብቱ ወሰን


(አንድ አድርገን ግንቦት 4 ፤ 2004ዓ.ም)፡- በባቦጋያ መድኃኒዓለም የቦታ ጉዳይ ለተከታታይ ጊዜያት ቦታው ያለበትን በቅርበት በመከታተል ሁኔታውን መዘገባችን ይታወቃል ፤ ከቀናት በፊት አቶ ጌታቸው ዶኒ ቤተክርስትያኑን ዘግቶ ከአካባቢው ለመሰወርና ቤተክርስትያኒቱ እንዳይቀደስባትና አገልግሎት እንዳይሰጥባት ለማድረግ የቤተክርስትያኒቱን እቃ ቤት ሀላፊ ቁልፍ በጉልበት ሊቀበላቸው እንደነበረ ነገር ግን ሳይሳካለት እንደቀረ በጊዜው ዘግበን ነበር ፤ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር የእቃ ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አባት በጊዜው አካባቢው ላይ ለሚገኙ ክርስትያኖች ስልክ በመደወል አቶ ጌታቸው ዶኒ እየሰራ ያለውን ነገር ከተናገሩ በኋላ በርካታ ምዕመኖች ሁኔታውን በመቃወም በቤተክርስትያኒቱ መሰብሰብ ችለው ነበር ፤ እነዚህ ክርስትያኖች ተግባሩን ለመቃወም ቢወጡም ፤ ቤተክርስትያኒቱ አትዘጋም ቢሉም በወቅቱ የሰማቸው ህጋዊ አካል አልነበረም ፤ ይህ በእንዲህ እያለ አቶ ጌታቸው ሰው መሰብሰቡን በመመልከት ለፖሊስ ኃይል ስልክ በመደወል ለአመጻ የመጡ ሰዎች በማስመሰል 16 የሚያህሉ ክርስትያኖችን ለቀናት ማሳሰር ችሎ ነበር ፤ ከቀናት በኋላ በዋስ ቢፈቱም አንዱን ታሳሪ ግን ፖሊሶች ክፉኛ ዱላ ስላሳረፉበት ጉዳት ደርሶበት ነበር ከእስር የወጣው፡፡


ይህ የባቦጋያ መድሀኒአለም ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ለቤተክርስትያኒቱ የማይጠቅም ውሳኔ ከፍርድ ቤቱ ተሰምቷል ፤ በህገወጥ መንገድ የተወሰደውን ከ10ሺህ በላይ ካሬ ቦታ ‹‹ቤተክርስትያኒቱ ትጠይቅ እናንተ የእሷ ህጋዊ ተወካዮች አይደላችሁም ፤ እናንተ አትወክሏትም ፤ ይዞታው የባለሀብቱ ነው›› የሚል መልስ ከፍርድ ቤቱ ተሰምቷል ፤ ይህ ጉዳይ ደግሞ ነገሩን አጥብቀው ለያዙት ምእመናን መልካም ወሬ አይደለም ፤ በዚህ ሁኔታ አቶ  ጌታቸው ዶኒ እና የሪዞርቱ ባለቤት እስከ ወድያኛው የማያዛልቅ ደስታ አግኝተዋል ፡፡ ቤተክርስትያን ማለት የቤተክህነቱ ማለት አይደለችም ፤ ቤተክርስትያኒቱ የእምነቱ ተከታዮች ሁላ ናት ፤ ቤተክህነቱ ቦታውን እንዲሸጥ ሲደረግ እያየ እንዳላየ ቢያልፍ እንዴት ምዕመኑ ጥያቄ እንዳያቀርብ በሩ ዝግ ይሆናል ?  እንደ እነ ጌታቸው ያለ ሰው ቤታችንን በገንዘብ እየቀየሩ እየተመለከትን እንዴት ዝም በሉ እንባላለን ? ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ የሚናገረው ነገር ምዕመኑ ጥያቄ መጠየቅ እንደማይችሉና ከጠቅላይ ሚኒስሩ ጀምሮ እስከ ታችኛው የስልጣን ተዋረድ በሀላፊነት ላይ የሚገኙት ሰዎች ነገሩን ለሪዞርቱ ባለቤት ለአቶ ታዲዎስ እንደወሰኑለት ዲስኩሩን እየነፋ ይገኛል ፡፡

አካባቢው ላይ ያለው ክርስትያንም ተስፋ ሳይቆርጥ ጥያቄው መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን መጠየቅ ያለበትንና መሄድ ያለበትን ርቀት ለመሄድ በጽናት ቆሞ ይገኛል :: ይህን ጉዳይ ጉዳያችን ብለው ከአጽራረ ቤተክርስትያን ጋር የሚያደርጉት ትግል እንደ ቀላል የምናየው አይደለም ፤ ለነገ ለልጅ ልጆቻቸው ቤተክርስትያቱን ከስርዓቷ እና ከትውፊቷ ጋር አንድ ላይ ለማስረከብ ዛሬ ላይ የተበላሸውን ነገር ለማስተካከል በአላማ ቆመዋል ፡፡

እነዚህ ክርስትያኖች እንዴት በእምነትና በጽናት መቆም እንዳለብን ያስተምሩናል ፤ እኛ ትክክሎች እና እውነት እኛ ጋር እስካለ ድረስ ማንኛውም የቤተክርስትያን ጉዳይ ላይ ተስፋ መቁረጥ የለብንም ፤ እውነትን መቅበር እና እስከ ወዲያኛው ቀብሮ የሚያስቀር ምንም ነገር የለም ፤ ጥያቄዎቻችን መልስ እስኪሰጣቸው ድረስ በጽናት ልንቆም ይገባናል ፤ ሰዎች መልስ ባይሰጡን ጊዜ መልስ ይሰጠናል ፤ ጊዜ መልስ ባይሰጠን አንድ አምላክ መልስ እንደሚሰጠን ማመን መቻል አለብን ፡፡

እንደ ጌታቸው ዶኒ ያለን መሰሪ ሰውን እንደ አመጣጡ ለመጋፈጥ ለምናውቀው ሰዎች ከበድ ያለ ይመስለናል  ፤ ጌታው ዶኒ ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው እንደዚህ በየቦታው እየሄደ የሚያምሰው ? የሚል ሰውየውን ከማያውቁት ሰዎች ጥያቄ ይነሳል ፤ ይህን ሰው በህግ መጠየቅ አይቻል ሆይ ? የሚሉም አልጠፉም ፤ የኛ መልስ ‹‹ይቻላል›› ነው ፤ ነገር ግን  ጥያቄዎቻችንን መሰረት በማድረግ እርስ በእርስ በመማከር ፤ ባለሙያን በማማከር ልንታገለው ይገባል ፤ መነሻውንና መድረሻውን ሳያውቁ ውጊያውን ቢጀምሩት ትግሉ በርካታ ዋጋዎችን ያስከፍላል ፤ ሰውየው ህጋዊም ሆነ ህገወጥ ሆኖ መስራትን ተክኖታል ፤ እሱን ለማስረዳት ጥሩ ምሳሌ ሆኖ ያገኝሁት ቢኖር ፤ ዘወትር ረቡዕ በኢቲቪ የሚተላለፈው ‹‹ሰው ለሰው›› ተከታታይ ሳምንታዊ ድራማ ላይ ‹‹አቶ አስናቀን›› ሆኖ የሚሰራው አበበ ባልቻ የተላበሰውን የድራማው ገጸ ባህሪ በትክክል ጌታቸው ዶኒን ይመስለዋል ብለን እናምናለን ፤ ከእንዲህ አይነቱ ሰው ጋር ነው በጽናት የበረቱት ሰዎች ገትረው እየተሟገቱት ያሉት ፡፡ በሚፈልግበት ሰዓት ከቤተክህነቱ አቡነ ጳውሎስ የፈረሙበትን ማህተብ ያረፈበትን ህጋዊ ደብዳቤ ይዞ አውደ ምህረት ላይ በማንበብ እመኑኝ የሚያስብል ፤ ሰዎች በሌሉበት ሰዓት በጉልበት ተጠቅሞ ቁልፍ ለመቀማት የሚሞክር ሰው ፤ ቀን ቀን ጉዳዩን ለማስፈጸም ከክልሉ ባለስልጣናትና ከኦህዲድ ቢሮ የማይጠፋ ፤ በቀጣይ ቀናት ስለሚሰሩት ህጋዊ መሳይ ህገወጥ ስራዎች ከሪዞርቱ ባለቤት ጋር ማታ ማታ እያገኝው የሚወያየው ሰው ፤ ምዕመናን ያለቀለት እና ይግባኝ የማያስብል ጉዳይ መሆኑን እንዲያውቁት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የመንግስት ደህንነት ሰዎች ስም በመጥራት ሰው ላይ ሳይኮሎጂካል ጫና ለመፍጠር የሚጥር ፤ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች  በማስገደድና ጫና በማድረግ ያላነበቡትንና ያልተስማሙበትን ቃለ ጉባኤ ለማስፈረም ቀና ደፋ የሚል ሰው ነው አቶ ጌታቸው ዶኒ ማለት ፡፡ ይህ በድራማ ከምታቁት ሰው ቢብስ እንጂ የሚያንስ ባህሪ የለውም ፤ ጌታቸው ዶኒ ማለት ሰይጣን ስጋ ለብሶ ማለት ነው ፡፡

ወደፊት እኛ በጽሁፍ ያሰፈርናትን በድምጽ የምናቀርብላችሁ መሆኑን ቃል እንገባለን ፤ እስከ አሁንም ያላቀረብነው የቦታው ጉዳይ ጫፍ ስላልደረሰ የምናወጣው መረጃ የባጋያ መድሀኒዓለምን ቦታ ማስመለስ ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽህኖ እንዳይፈጥር በመፍራት እንጂ ከአንባቢዎቻችን የምደብቀው መረጃ ኖሮን አይደለም፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ትላንት በደረሰን መረጃ መሰረት  መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ላይ የተመደቡት አዲስ አስተዳዳሪ እና አቶ ጌታቸው ዶኒ በመመካከር ክስ ፍርድ ቤት አቅርበዋል ፤ ለቤተክርስትያን ተቆርቋሪ ወንድምና እህቶቻችን የፍርድ ቤት መጥሪያ  አምጥተውላቸዋል ፤ የክሱ ጭብጥ‹‹አስፈራርተውናል›› የሚል ሲሆን ከሳሽ የባቦጋያ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ አንደኛ ምስክር ደግሞ አቶ ጌታቸው ዶኒ ሆኖ ቀርቧል ፤ ለተከሳሾች የክስ ቻርጅ የደረሳቸው አርብ 03/09/2004 ዓ.ም መሆኑን አውቀናል ፡፡ ወደ ፊት ምን እደሚፈጠር አብረን የምናየው ነገር ይሆናል፡፡ ሰው እንዴት እድሜ ልኩን ቤተክርስትያኒቱን ለማፍረስ ተግቶ ይሰራል ፤ ከዚህ በላይ ግልጽ ነገር የለም ፤ ይህን የእሱን ስራ  ከጠቅላይ ቤተክህነት አንስቶ እስከ  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ መረጃው እጃቸው ላይ እንዲገባ ተደርጓል ፤ ሁሉም የመፍትሄ አካል መሆን ቢያቅታቸው እንኳን ፡፡

አሁን ግን እዚህ ብሎግ ላይ የማይጻፍ ነገር ቦታውን አስመላሽ ኮሚቴ የተወሰደውን የመድሀኒዓለምን ቦታ ለማስመለስ አዲስ አካሄድ መርጠው  መንገዱን እየሄዱን እንደሆነ ሰምተናል ፤ መንገዱንም ውጤቱንም ወደፊት እንነግሮታለን፤ ለጊዜው አምላክ ቸር ወሬ ያሰማን፡፡

‹‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው በሁኔታዎች ተስፋ አንቆርጥም ፤ ቦታው እንደሚመለስም አንጠራጠርም ፤››

5 comments:

 1. KHY andaderegen...Egeziabeher Aserare betekerestiyanene yastageselen...

  fin ande hasabe alegn:-asmelashe komitewe lela akahede ayetetekemu mehonuneme ezihe laye banegeletse teru yemeselegnale

  ReplyDelete
 2. There are so much injustices being done up on us. Am one of those who get furious with the decision of the so called 'court". i Know the people of that 'atbia" very much. All they have been doing to reclaim back the land belonging to "Misraqe tsehay Medhanalem Church" in a calmy and peaceful means. The so called Getachew Doni and his commanders at the "bete kihnet" including all blood suckers both in the church and elsewhere shall soon be subdued and be brutally killed. No more tolerance, this is what the people shall do if the peaceful means is considered as fear. nothing shall come than seeing our Church kept intact hitherto getting overstaffed with shameless, arrogant persons claiming to be church fathers like paulos, gerima,marqos,sawiros, fanuel and their likes. Tolerance has its own limit. You damn guys guided by devil and wore devilish mantle shall be obliterated altogether with the satan on the saddle of power.

  ReplyDelete
 3. ahune ezuwe negere ejige asazagne eyehone newe....seyetan sewe hono memetate jemerual!!!!synodosume yemayadageme wesanea biyasalefe yehea hula mekera balebeza ...

  pastor paulosem kebotachew binesu yehe hula neqete bebetekirstiyanachen lay balederese nebere ...

  zarem egiziabeher betekirstiyanene yitebeqelen

  ReplyDelete
 4. ይህ መልእክቴ ምክሬ ሐሳቤን የሚቀበሉ ከሆነ በገንዘብ ለከበሩ በገንዘባቸው ተመክተው የእግዚአብሔርን ንብረት ለወሰዱት ለአቶ ታዲዎስ ይሁን የመጀመርያ ምክሬ እግዚአብሔርን መበደልዎን አውቀው ንስሐ ገብተው የቤተ ክርስቲያንኑ ንብረት ይመልሱ ሁሉም ነገር ጊዛዊ ነው አሁን በእጆዎ ያለውን ሀብት ይበቃዎታል "አይ አይበቃኝም" ብለው በዚሁ በድፍረትዎ የሚቀጥሉ ከሆነ ከሰው ጋር ሳይሆን በሀብትም ማንም ከማይደርስበት ሰጥቶ ሰጥቶ የማያልቅበት ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር ጋር ነው እየተጋፉት ያሉት ይቅርብዎ ከእሱ ጋር ለመታገል ጉልበት የልዎትም የያዙት ይበቃል በኋላ እንዳይቆጭዎ ባላደረኩት ኖሮ እንዳይሉ ከእርስዎ ጋር አማካሪ ሆነው የቤተ ክርስቲያንን ልብስ ለብሰው ካሉ ሆዳሞች ሐይማኖት የሌላቸው... እንደ ጌታቸው ከመሰሉ ልቡሳነ ሥጋ አጋንት ይጠበቁ እንደዚህ አይነቶቹ ለእርስዎም ሆነ ለቤተ ሰብዎ ጥፋት የተላኩ መሆናቸውን ይወቁ

  ReplyDelete
 5. ይህ መልእክቴ ምክሬ ሐሳቤን የሚቀበሉ ከሆነ በገንዘብ ለከበሩ በገንዘባቸው ተመክተው የእግዚአብሔርን ንብረት ለወሰዱት ለአቶ ታዲዎስ ይሁን የመጀመርያ ምክሬ እግዚአብሔርን መበደልዎን አውቀው ንስሐ ገብተው የቤተ ክርስቲያንኑ ንብረት ይመልሱ ሁሉም ነገር ጊዛዊ ነው አሁን በእጆዎ ያለውን ሀብት ይበቃዎታል "አይ አይበቃኝም" ብለው በዚሁ በድፍረትዎ የሚቀጥሉ ከሆነ ከሰው ጋር ሳይሆን በሀብትም ማንም ከማይደርስበት ሰጥቶ ሰጥቶ የማያልቅበት ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር ጋር ነው እየተጋፉት ያሉት ይቅርብዎ ከእሱ ጋር ለመታገል ጉልበት የልዎትም የያዙት ይበቃል በኋላ እንዳይቆጭዎ ባላደረኩት ኖሮ እንዳይሉ ከእርስዎ ጋር አማካሪ ሆነው የቤተ ክርስቲያንን ልብስ ለብሰው ካሉ ሆዳሞች ሐይማኖት የሌላቸው... እንደ ጌታቸው ከመሰሉ ልቡሳነ ሥጋ አጋንት ይጠበቁ እንደዚህ አይነቶቹ ለእርስዎም ሆነ ለቤተ ሰብዎ ጥፋት የተላኩ መሆናቸውን ይወቁ

  ReplyDelete