በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
‹‹በስራችን ቋሚ የምስክር ሐውልት ጥለን እንለፍ››
(አንድ አድርገን ግንቦት 10 ፤ 2004ዓ.ም)፡-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተክርስትያን በጅማ ሐገረ ስብከት ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ አገልግሎት ማህበር ሁለተኛው ዙር ታላቅ እና ታሪካዊ
መንፈሳዊ ጉባኤ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሀኒአለም ፤ መጥምቁ ዮሃንስና አቡነ አረጋዊ ካቴድራል ሰኔ 3፤ 2004 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል ፤ እስዎም በዚህ
ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ ‹‹ተነሱ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ›› ኤር 3፤16
እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይቀበል ፤ በስራችንም ቋሚ የምስክር ሐውልት
ጥለን እንለፍ፡፡ በዚህ በሁለተኛው ዙር ምዕራፍ ራስን የማስቻል ጉዞአችን ዛሬም ለጌጠኛ ቤታችን የልማት መንፈሳዊ አገልግሎት በመልካሙ
እግሮቻችን ፈጥነን እንውጣ፡፡
ዛሬ የገጠሪቷ ቤተክርስትያን ችግር እንቅልፍ የነሳን ሁሉ ፤ እንደ ቅዱስ
ጳውሎስ ‹‹የቀረውን ነገር ሳልቆጥር እለት እለት የሚያሳስበኝ የአብያተክርስትያናት ጉዳይ ነው፡፡›› 2ተኛ ቆሮ 11፤28 በማለት
ለዚች ለገጠር ቤተክርስትያን ‹‹በአንድነት እንቁም›› ኢሳ 50፤8 ፤ በጉባኤው ላይ ሲገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይባረካሉና ፤
ከመምህራንና ዘማሪያን ጋር እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ ፤ እንዲሁም ልዩ በሆነ ዘጋቢ ፊልም አብያተክርስትያናቱ ያሉበትን ሁኔታ እና
የልማት ስራ ይመለከታሉ፡፡
‹‹ጉባኤውን
በመካፈል ለገጠሪቱ ቤተክርስትያናት ለምናደርገው አገልግሎት ከጎናችን ቁሙ›› በማለት ማህበሩ መልዕክቱን ያስተላልፋል፤ በተጨማሪ
በየገጠሩ ተመልካች ያጡ አብያተ ክርስትያናት በምን አይነት ሁኔታ እንደሚገኙ የሚያውቁበት መንገድ ተመቻችቷልና ጉባኤውን አይቅሩ
፤ የዛሬ የእርስዎ የአንድ ምዕመን እርዳታ ነገ በርካታ አብያተክርስትያናት እንዳይዘጉ በተጨማሪም የተዘጉት እንዲከፈቱ ፤ ያሉትም
በልማት ስራ ራሳቸውን እንዲችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ፤ ‹‹ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ›› እንዲሉ የቻልነውን
እና አቅማችንን የፈቀደውን በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን በመወጣት ከአባቶቻንን የተረከብናትን አንዲት ቤተክርስትያን እና አንዲት
እምነትን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ያስችለን ዘንድ ዛሬ በብርታት እንስራ ይላችኋል፡፡
የቤተክርስትያን ደጆች በሃይማኖት እና በምህረት እንዲከፈቱ እናድርግ ፤
የመጀመሪያውን የ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› ጉባኤ የተካፈላችሁ ምዕመናን በዚህኛው ጉባኤ እንደማትቀሩ እርግጠኞች ነን ፤ በጊዜው ከ25 ሺህ ምዕመናን በላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ጉባኤው ላይ መገኝት ችሎ ነበር ፤ በጊዜው ለተመልካች የቀረበው የተዘጉ አብያተክርስትያናት በምን ሁኔታ ከምዕመኖቻቸው ጋር እንደሚገኙ ባቀረቡት የደቂቃዎች ዘጋቢ ፊልም የበርካቶች ፊት ስለተዘጉት አብያተክርስትያኖቻን በእምባ ሲታጠብ ለመመልከት ችያለሁ ፤ ከዚያ ጉባኤ ቀን በኋላ ሰው ስለ ቤተክርስትያን ስላለችበት ሁኔታ ተመልክቶ ሲያለቅስ ተመልክቼ አላውቅም ፤ ከ2 ዓመት በፊት የተካሄደው ጉባኤ ላይ በጅማ አካባቢ የሚገኙ የተዘጉ በርካታ አብያተክርስትያናት እንዲከፈቱ በማድግ ማህበሩ ክርስትያኒያዊ ግዴታውን ተወጥቷል ፤ ወደፊትም እግዚአብሔር እንደፈቀደ ከሰሩትና ካሰቡትም በላይ አምላክ እያከናወነላቸው ይሰራሉ ብለን እናምናለም፡፡ ዝቋላ እሳት ሲነሳ መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በማምጣት በርካቶች ወደ ስፍራው እንዲሄዱና አደጋውን የመቀነስ ስራ እንዲሰሩም ማህበሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል ፡፡ የዚህ በራሪ ወረቀት መጨረሻው ላይ ‹‹አባክዎን አንብበው ሲጨርሱ ለሌላ ምዕመን ያሳተላልፉ›› የሚል መልዕክት ተቀምጦበታል ፤ እኛም መልዕክቱን አንብበን ስንጨርስ ብሎጋችን ላይ ሺዎች እንዲያነቡትና ጉባኤውን እንዲካፈሉ ለማድረግ ልናወጣው ችለናል፡፡ ጉባኤው ላይ መገኝት የማትችሉ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ ምዕመናን ፤ ለአብያተ ክርስትያናቶቹ እጃችሁን መዘርጋት የምትፈልጉ ሰዎች ካላችሁ በተቀመጠው የስልክ አድራሻ ተጠቅማችሁ አስተባባሪዎቹን ማግኝት እንደምትችሉ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
የመግቢያ ዋጋ 10 ብር
የመግቢያው ቲኬት የሚገኝባቸው ቦታዎች
1. ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ዑራኤል መዝሙር ቤት
2. ቅድስት ልደታ ኤፍራታ መዝሙር ቤት
3. ቅድስት ማርያም መጥቅዕ መዝሙር ቤት
4. ቦሌ መድሐኒዓለም መጥምቁ ዮሐንስ መዝሙር ቤት
5. ቅዱስ ራጉኤል ሴፓራ መዝሙር ቤት
6. ቀጨኔ መድሐኒዓለም ግርማ ህንፃ መሳሪያ
7. ሳሪስ አቦ መቅደላዊት መዝሙር ቤት
8. ገርጂ ጊዮርጊስ ተመስገን ብርና ጌጣጌጥ መሸጫ
9. ተክለሐይማኖት መባዕ መዝሙር ቤት
10. የካ ሚካኤል ደሳለኝ መዝሙር ቤት
11. አፍሪካ አንድነት ሚካኤል የጽዮን መዓዛ መዝሙር ቤት
12. ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ዮሐንስ መዝሙር ቤት
13. ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል ሚካኤል መዝሙር ቤት
14. ጎፋ ገብርኤል የአብ ፍሬ መዝሙር ቤት
15. መካኒሳ ሚካኤል አደባባያ ሶሊያና ካፌ
16. ፈረንሳይ ለጋሲዮን ኬላ ሮኖቦት መዝሙር ቤት
17. ገርጂ ማርያም ራማ መዝሙር ቤት
18. አዲሱ ሚካኤል ሰላም ምግብ ቤት
19. ቅዱስ ያሬድ ሐረገወይን መዝሙር ቤት
20. ቅዱስ እስጢፋኖስ እዝራ መዝሙር ቤት
21. ቦሌ ሚካኤል ፍቅረ መድሀኒዓለም መዝሙር ቤት
22. ቀራንዮ መድሐኒዓለም ትንሳኤ መዝሙር ቤት
23. አማኑኤል ቤተል መዝሙር ቤት
24. ምክካየ ኀዙናን ኤማሁስ መዝሙር ቤት
25. ብስራተ ገብርኤል ታቦር መዝሙር ቤት
ለበለጠ መረጃ 0911-201649 ፤ 0911-216440 ፤ 0913-255249 ፤ 0911-015623 ፤ 0924-373474
‹‹ደጆችሽ አይዘጉ››
…………
አዎን ‹‹ቤተክርስትያን
ሆይ ደጆችሽ አይዘጉ››
No comments:
Post a Comment