Thursday, January 29, 2015

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዘወርት


 አንድ አድርገን ጥር 21 2007 ዓ.ም
በዲ/ ተረፈ ወርቁ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ የሆኑት / / መርሻ አለኸኝ ከጥቂት ወራት በፊት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና በማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ በተከታታይ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዘወርትበሚል ዐቢይ ርዕስ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ተከታትያለኹ። / መርሻ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓለም የክርስትና መድረክ የነበራትንና አሁንም ያላትን ልዩ ስፍራና ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን በተመለከተ ያቀረቡት ታሪክ የዳሰስ ጥናታዊ ጽሑፋቸው ለዚህ ጽሑፍ ዐቢይ ምክንያት ኾኖኛል።

/ መርሻ የኢትዮጵያ / የክርስትና እምብርት ከሆነችው ከእስራኤል ጋር ከዘመነ አበውና ከሕገ ኦሪት ጀምሮ እስከ ሐዲስ ኪዳን ዘመን ድረስ ስለነበራት ሦስት ሺህ ዘመናትን ስላስቆጠረው ረጅም ታሪኳ፣ ክርስትያናዊ ጉዞዋና ዓለም አቀፍ ግንኙነቷን አጠር ባለ መልኩ ለመግለጽ ሞክረዋል። ዲያቆን መርሻ በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸውም የኢትዮጵያ / በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአሜሪካና በካረቢያን ለረጅም ዓመታት የቆየውን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ተንትነዋል።

Saturday, January 24, 2015

‹‹ቤተ ክርስቲያኗ ውለታ ፈላጊ ባትሆንም ለሀገር ባህልና ለቅርስ ጥበቃ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከሚነገረው በላይ ነው፡፡›› ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል

አንድ አድርገን ጥር 17 2007 ዓ.ም
  • ከ80 እና ከ90 በላይ በሀገሪቱ የሚጎበኙ ቅርሶች ታሪካዊ ቦታዎች የቤተ ክርስቲያኒቷ ናቸው፡ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያኗ  ሃይማኖትን ከሀገር ፍቅር ጋር  አያይዛ ስትሰራ መቆየቷንና  አሁንም እየሰራች እንደሆነ ያመላክታል፡፡
  • አንድ ሰባኪ መጀመሪያ መስበክ ያለበት ራሱን ነው፡፡ እኛ ሱፍ ለብሰን ለምን የሀበሻ ልብስ አትለብስም ማለት ይህ ማደናገር እንጂ ማስተማር አይደለም፡፡ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ስናስተምር እኛ ራሳችን በዚያ ውስጥ ማለፍ መቻል አለብን፡፡ ራሱን ያልሰበከና ሕይወት የሌለው ሰባኪ አደናጋሪ ነው እንጂ ሰባኪ አይደለም፡፡
  • ሃይማኖታዊ በዓላትን ከሌላ ነገር ጋር ቀላቅሎ ማቅረቡ እና ከእምነቱ ጋር አብሮ የማይሄዱ ነገሮችን አጫፍሮና አገናኝቶ  ማቅረቡ ተገቢ አይደለም፡፡ አሁን ያለው አካሄድ ግን‹‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል›› ዓይነት ነው፡፡
  • ትውፊት ተጠብቂ የሚቆየው በሀገር ውስጥም በውጭም የሚከበሩ መንፈሳዊ በዓላት እንደ ጥንቱ አባቶቻችን ሥርዓቷ ሳይፋለስ ወጥ ሆነው እንዲቀጥሉ ማድረግ ሲቻል ነው፡፡
  •  የመስቀል በዓል ነው ካልን ሌላ ቅልቅል አያስፈልገውም፡፡የመስቀል በዓል የቤተ ክርስቲያናችን በዓል እንጂ የባህል በዓል አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የመስቀል በዓልን የምታከብረው በሃይማኖት በዓልነቱ ነው፡፡ ዩኔስኮም ሲመዘግበው የሃይማኖት በዓልነቱ እንጂ የባህል ብሎ አይደለም፡፡ ከነበረው ይዘት የሚለቅ ከሆነ ዩኔስኮም ከመዝገብ ይፍቀዋል፡፡
  • ማንኛውም የውጭ ሀገር ጎብኚ የሚመጣው  ጥምቀትን ለማየት ነው እንጂ የካርኒቫል በዓል አለ ብሎ አይመጣም፡፡ እነዚህ ፍልስፍናዎች የሴኩላሪዝ ተጽህኖዎች ናቸው፡፡ አላማው ሃይማኖትን ማዳከም ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን 2300 አዲስ ተጠማቂያን አገኝች


በእለተ ቅዳሜ ጥር 9 2007 ዓ. ከሁለት ሺህ ሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ ጉምዝ ማሕበረሰብ አባላት ተጠምቀው  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  እምነት ተከታይ ሆኑ፡፡ 
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን 

Saturday, January 10, 2015

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የምትደግፋቸውና የምትቃወማቸው ሳይንሳዊ ጉዳዮች

  
ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ከ18 በላይ መጽሐፍትን በአማርኛና በእግሊዝኛ ጽፈዋል፡፡ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲም ‹‹ዲክሽነሪ ኦፍ ክርስቲያን ኢዲሽን›› የተሰኝውን መጽፍ አሳትሞላቸዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ የፀረ ውርጃ ፤ ጽንስ ማቋረጥ ፤ እና ግብረሰዶም እንቅስቃሴ ድምጻቸው ጎልቶ ከሚሰሙ አባቶች ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ የሜዲካል መጽሔት ዘጋቢ አጥናፉ አለማየሁ በዚህ እና  ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ አቡነ ሳሙኤል አወያይቷቸዋል፡፡


ሜዲካል፡-  ፅንስ ማቋረጥን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያላት አቋም ምንድነው?
አቡነ ሳሙኤል፡- ፅንስ ማቋረጥን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትቃወመዋለች ፤ አስተምህሮዋና ቀኖናዋም ይቃወማል፡፡ ምክንያቱም ፅንስ የሰው ዘር በምድር ላይ እንዲበዛ እግዚአብሔር ስለፈቀደ ‹‹ብዙ ተባዙ አላቸው ባረካቸውም›› ዘፍ 1፤28 ባለው አምላካዊ ቃል መሰረት  የሚገኝ በረከት ነው፡፡ ስለሆነም ፅንስ ገና ያልታየና ያልተወለደ ቢሆንም  ከእግዚአብሔር ሕይወት የተሰጠው ፍጡር ነው፡፡ ‹‹ከእናቴ ማሕፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ›› መዝ 21፤9  ‹‹ከማሕፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍኩ ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ መሸሸጊያዬ ነህ›› መዝ 70፤6 እንደተባለው ሁሉ ፅንስ የእግዚአብሔር ጥበቃና መግቦታ ያለው ነው፡፡

እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ለወደፊት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ተልዕኮ ያለው እንደሚሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ዕውቅና  የተሰጠውና የመኖር መብት ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ከዚህ በላይ በተገለጸው አምላካዊ ቃል መሠረት ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፅንስ ማቋረጥን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡(ዘጸ 20፤13)

Thursday, January 8, 2015

የቤተ ክርስቲያኒቱ የገቢ ማስገኛ ተቋማት ኪራይ የግለሰቦች መጠቀሚያ መኾናቸው ተጠቆመ

  • ሀብትና ጥቅሟን የሚያስጠብቅ የኪራይ ተመን ፖሊሲ የሚወጣበት ጥናት ተጀምሯል
  • የጥቂት አድባራት ሓላፊዎችና ጥቅመኞች እንቅስቃሴ ጥናቱን እንዳያኮላሸው ተሰግቷል
  • የአለቆች የመኪና ሽልማት የሙሰኞች ከለላና ለብልሹነት በር የሚከፍት ነው ተብሏል

 አንድ አድርገን ታኅሳስ 30 2007 ዓ.ም
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ ገዳማትና አድባራት፤ የገቢ ማስገኛ ምንጮችና የልማት ተቋማት የኪራይ አገልግሎት ከሰበካ ጉባኤያት ዕውቅናና የወሳኝነት ሥልጣን ውጭ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ጥቅም ለጥቅመኛ የአድባራት ሓላፊዎችና ግለሰቦች ተላልፎ የተሰጠበት መኾኑ ተጠቆመ።

የተሰጠው፣ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና አንዳንድ ገዳማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለማስገኘት የተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ ለፓትርያርኩ አቅርቦታል በተባለ የማስታወሻ ጽሑፍ ነው። የከተማው አስተዳደር ለሀ/ስብከቱ አድባራትና ገዳማት ለማምለኪያ፣ ለመካነ መቃብርና ለልማት መገልገያነት የሰጣቸው መሬቶች፣ ለገቢ ማስገኛ በሚል አብያተ ክርስቲያናቱን ተጠቃሚ በማያደርግ የዋጋ ተመንና ሀብቷን ለጥቅመኞች አሳልፎ በሚሰጥ የውል ዘመን ለግለሰቦች እየተከራዩ ስለመኾኑ በጽሑፉ ተመልክቷል።