(አንድ አድርገን ግንቦት 25 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-የማህበረ ቅዱሳንን
20ኛ ዓመት በማስመልከት የእግር ጉዞ ለማድረግ አንድ ቀንና ጥቂት ሰዓት ቀርተውታል ፤ እኛም ቲኬቱን በ100 ብር ገዝተን ጉዞውን እንደ ባለፈው የሐዊረ ህይወት
ጉዞ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር ፤ በዚህ ጉዞ ከ 20 ሺህ በላይ ምዕመናን ይገኛሉ ተብሎ ታስቦ ነበር ፤ ድንገት በሞባይሌ የጉዞ ፕሮግራም ወደ ጉባኤነት እንደተቀየረ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በቤተክህነት አዳራሽ እንደሚካሄድ የሚያሳስብ የጽሁፍ
መልዕክት ደረሰኝ ፤መልዕክቱም አንዲህ ይል ነበር “Our Dear families ! sorry because of
Betekehenet our journey is changed to Gubae at betekehenet hall. Starting from
4:00 am morning’’ መልእክቱን አንብቤ ስጨርስ ለምን? ብዬ በመጠየቅ ወደ ማህበሩ ድህረ ገፅ ገብቼ
ስመለከት “ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን
20ኛ ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ሊካሔድ የነበረው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን
ደብደቤ ባለመጻፉ በታቀደለት መሠረት ሊከናወን አልቻለም፡፡” የሚል መልዕክት አነበብኩኝ ፤
ቀጥሎም የጉዞው አስተባባሪ
ዲ/ን ዋሲሁን በላይ እንዳስረዱት “ በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ
ጸሐፊ ፊርማ የወጣው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መዝገብ ቤት ገብቶ ወደሚመለከታቸው ክፍሎች እንዳይደርስ ´የመዝገብ ቤት ሰራተኞች ደብዳቤው
እንዳይወጣ ከበላይ ታዘናል በሚል ደብዳቤው አልወጣም፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ የያዘው ደብዳቤ የጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር
ሃላፊዎችም አልደረሰንም በሚል ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ደብዳቤ ለመጻፍ አልቻልንም፡፡” ይላል፡፡ ይህን ሳስብ ለጊዜው ውስጤን ጥሩ ነገር አልተሰማውም ፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር
ሊሆንና ሊከናወን የሚችለው እንደ እግዝአብሔር ፍቃድ መሆኑን እናውቃለን ፤ አሁንም ማህበሩን ላለማሰራትና እንቅፋት በመሆን ቤተክህነቱ
የሚወዳደረው አልተገኝም ፤ እስኪ አሁን ይህ ምን ይባላል ? እንደ
እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ 20 ዓመታትን በብዙ ፈተና ማህበረ ቅዱሳን እዚህ ደርሷል ፤ ከአሁን በኋላ የሚኖሩት ዓመታት አልጋ በአልጋ
ይሆናሉ ተብሎ ባይጠበቅም ፈተናውን ከእግዚአብሔር ጋር እያለፈ ቤተክርስትያኒቱን ለመጪው ትውልድ እንደሚያስተላልፍ ተስፋችን ነው ፤ መልካም ነገር የማይወድ ዲያቢሎስ ብቻ መስሎ ይታየን ነበር
፤ ለካ ሰውም ከእርሱ ብሶ ለክፋት መቆም ይችላል ፤
በመሰረቱ ከቤተክህነቱ ይህ
ደብዳቤው ወደ አዲስ አበባ መስተዳር ቢሄድም ያለ ጥያቄ ጉዞ ይፈቀዳል የሚል እምነት የለንም ፤ የቤተክህነቱን ያህል የማስተጓጎል
ስራ ባይሆንም እንኳን ፤ የእግር ጉዞውን ብናደርግ መልካም ነበር ፤ አሁንም ቢሆን በተሻለ ሁኔታ እና በአንድ መንፈስ የተሻለ ጉባኤ እንደሚሆን እናምናለን ፤
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን
ይባርክ
የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው
ReplyDeleteJust to make it simple what left is only walking and attending the anniversary on the dedicated churches. But I don't look it only in that way the actions tells more than words. We have to be alert in all aspects, we have to be the forefront to know the exact reality of the country;we are in a state of emergency to unite and live under the umbrella of our religion Orthodox Tewahedo so as to look over surviving alongside generations.
ReplyDeleteMay God shepherd our religion!
Just to make it simple what left is only walking and attending the anniversary on the dedicated churches. But I don't look it only in that way the actions tells more than words. We have to be alert in all aspects, we have to be the forefront to know the exact reality of the country;we are in a state of emergency to unite and live under the umbrella of our religion Orthodox Tewahedo so as to look over surviving alongside generations.
ReplyDeleteMay God shepherd our religion!
Reply
የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው .... egziabher ke'egna gare new ..telate yekoferale rasu yegebabetale... enebereta negeru hulu le'bego new
ReplyDeleteእውነት ብላችኃል እኛ ያገኘነውን በረከት እነዲያገኙ ፀሎታችን ነው።
ReplyDelete