አዲስ ራዕይ በየሁለት ወሩ በአማርኛ
ቋንቋ እየተዘጋጀች በኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ዓለም ዓቀፋዊና ፤ ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራያና ትንታኔ
ይዛ የምትቀርብ የኢህአዴግ የትንታኔ መጽሄት ነች፡፡ የዚች መጽሄት አዘጋጅ “የኢህአዴግ ህዝብ ግንኙነት ክፍል” ሲሆን አሳታሚው
ደግሞ “ኢህአዴግ” መሆኑን የመጽሄቷ የፊት ገጽ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ይናገራል ፡፡
እንደ መረጃዎች ይች መጽሄት በጠቅላይ ሚኒስትሩ
በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ታጠነጥናለች አንዳንዴም ጸሀፊው እርሳቸው ናቸው የሚባልም ወሬ አለ፤ አቶ መለስም ጻፉት ሌሎች አባላት ታትሞ
ከወጣ የድርጅታቸው አቋም ነው አመለካከታቸው እሳቤያቸውንና ተግባራቸውን
ከሞላ ጎደል የምታዩባት ክፍል ነች ፤ ይህች መጽሄት ተደናሽነቷ
ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ፤ መንግስት በሹመት ያስቀመጣቸው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ኃላፊዎች ፤ ከህዋስ ደረጃ ከፍ ያሉ አባላት
ብቻ በመሆኑ እንዲህው በቀላሉ በማንም እጅ ላይ የመታየት እድሏ
እጅጉን አናሳ ነው ፤ እዚች መጽሄት ላይ የሰፈረው ሀሳብን መሰረት
በማድረግ የኢህአዴግ ከወረዳ አንስቶ እስከ ሚኒስትርነት ያስቀመጣቸው ሰዎች በድርጅታዊ ጉባኤ እንደሚነጋገሩበትና ይዘቷን የሚፈትሹበት
፤ ጽሁፉን ላነበቡትም ሆነ ላላነበቡትም አባላት የመንስትን አቋም የሚያውቁበት መድረክ በየጊዜው እንዳላቸው ውስጥ አዋቂዎች ተንፍሰውልናል፡፡
አዲስ ራእይ በ2ኛ ዓመት ቅጽ 3 ግንቦት-ሰኔ 2004 ዓ.ም ለመዳሰስ የተፈለገው ዋናው ጉዳይ በፖለቲካ አምዷ በአሁኑ ሰዓት
ሀገሪቱ የእግር እሳት የሆነባትን የሀይማኖት ጉዳይ ነው ፤ ኢህአዴግ በዚች 70 ገጽ በማትሞላ መጽሄት በአሁኑ ሰዓት ያለውን
የሀይማኖት ችግር መሰረት በማድረግ 41 ገጹን በሚሸፍን መልኩ መተንፈስ ችሏል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ከሰጡት የሰዓታት
ትንታኔ ጠለቅ ባለ መልኩ ነገሮችን በስፋትና በጥልቀት በደፈረሰ አይኑ ተመልክቶ ሀሳቡን ማቀመጥ ችሏል ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተ
ተዋህዶ ቤተክርስትያን “አንዳንድ አማኞች” በማለት በግልጽ ያለውን እና የያዘውን አቋም ሲያንጸባርቅ አስተውለናል ፤
አክራሪነትን ከህገ መንግስቱ
አንጻር የተመለከተ መስሎት የማይመለከተን እኛንም በደንብ አድርጎ ወርፎናል ፤ በየቢሮ የሚለጠፉ የቅዱሳን ስዕላትንና የመጽሀፍ
ቅዱስን ጥቅስን እንዲህ በማለት ገልጾታል “የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ጠረጴዛዎችና ኮምፒዩተሮችና ግድግዳዎች ላይ ህዝብ
እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ…” በማለት አስቀምጦታል ፡፡ይህ ሁኔታ
በመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢታይም የሰውን የእምነት ነጻነት ከማክበር አኳያ ይህን የመሰለ የማቋሸሽና የማጥላላት ጽሁፍ መንግስትን
ወክሎ ወጥቶ መመልት መቻል እንደ አንድ ዜጋ ያሳፍራል፡፡ እዚህ ላይ የማህበረ ቅዱሳንን ስም በማይገባው ቦታ ከውሀቢያ እና ከአመለካከቱ
ጎን አስቀምጦት ማየት ችለናል ፤ ለምሳሌ በገጽ 33 ላይ “በአንዳንድ
የኦርቶዶክስ አማኝ ነኝ ባዮች ከማህበረ ቅዱሳንም የተለየ ሚና ያለው ኮር ሃይል የሚያስተጋባው አንድ ሀገር አንድ
እምነት የሚለው ቅዥት ጸረ ህገ መንግስታዊ ነው ፡፡ ወሀብያ ይሁን
የሌላ እምነት ተከታይ ጸረ ህገ መንግስት አቋሞቹንና ተግባሮችን አውግዞ እንደማኛውም ዜጋ ወይም ቡድን የራሱ መብት እንዲከበርለት
የሚፈልገው ሁሉ የሌላውንም መብት አክብሮ እስካልተንቀሳቀሰ ድረስ ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጋጭትና የእምነቱን አስተምህሮ የሆኑት
ጉዳዮች ላይ መንግስት የመምረጥም የመተቸትም ፍላጎት የለውም ፤ ይህንም አድርጎት አያውቅም” በማለት ያትታል ፤ አሁን እንደ
ነጥብ የማህበሩን ስምና የጽሁፉ ይዘት አብሮ የሚሄዱ ሆነው አያገኟቸውም ፤ “ሊበሏት ያሰቧትን …..” የሚባል ተረት ትዝ ያሰኞታል
፤ እኛ በርካታ የጥምቀት በዓላት ላይ ስንመለከት “አንድ ሀገር አንድ እምነት” የሚል ተጽፎ ለመመልከት አልቻልንም ፤ እነሱ
ካዩ ከተመለከቱና መረጃው ካላቸው ቢያሳዩን መልካም ነው ፤ መጽሀፉ ደግሞ
“አንድ
ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ነው የሚለው “አንዲት
ሀገር” የሚል የለበትም ፤ ይህ ጥቅስ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ ቢመስላቸውም እኛ ምን ማድረግ እንችላለን ? ከህገመንግስታችሁ
ጋር እናጣጥምላችሁ ? ምን እንበለው ? ምንስ ብለን ቲሸርታችን ላይ ጽፈን እንልበሰው ? እኛ ቃሉ የመፈጸም እንጂ
የማስተካከል የመለወጥ መብቱ የለንም ፤ ቃሉ ደግሞ እንደማይለወጥ በግልጽ መጽሀፉ ይነግረናል ፤ እኛ የተጻፈልንን ማመን ብቻ
ነው ፤ ደግመን እንበለው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት”
ስለ ሀገሩ ተውትና “አንድ ሃይማኖት” የተባለችው ቀጥተኛዋ በደም የቆየችልን አሁን እኛ ያለንባት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት
ብለን እናምናለን ፡፡
በሌላ በኩል በገጽ 37 ላይ
ይህን ሰፍሮ ያገኙታል “በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ
የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ እና በመሰረቱ ጸረ-ህገመንግስት መገለጫ ያላቸው አቋሞች የተላበሱበትና አንዳንድ የእኛ
አባላትና አመራሮችም ኢህአዴግነትንም ጸረ ኢህአዴጋዊ አቋሞችን የያዙ ይዘቶችንም የሚያንቀሳቅሱበት ሁኔታ በገሀድ የሚታይ
ነው፡፡ አባላችን ወደ ሃይማኖት ሲሄድ ኢህአዴግነቱን ትቶ ፤ ወደ ኢህአዴግ ሲመጣ ደግሞ ሀይማኖቱን ትቶ ሊሆን አይችልም ፡፡
ጠንካራ አማኝም ጠንካራ ኢህአዴግም በመሆን መካከል ግጭት የለም ፡፡ ግጭት የሚፈጠረው ድንበሮችን ስናደበላልቅ ነው ፡፡
ስለዚህም በዚሁ አግባብ ግልጽነት ተፈጥሮ አባላችንን አመራራችን ሰልፉን ያስተካክል ፤ ለማስተካከል የሚቸገር ደግሞ በሰበባ
ሰበብ ሳይሸፋፈን ከድርጅቱ መጽዳት አለበት በማለት ያስቀምጣል” ይህን ያህል አትኩሮት ሰጥቶት ማስቀመጥ ከቻለ መንግስት
ጊዜው ራስ ምታት እንደሆነበት ያሳያል ፤ በብሎጋችን ላይ ከወራት በፊት የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ በተመለከተ በአዲስ አበባ
ውስጥ ከሚገኙ አንዱ ፍርድ ቤቶች ውስጥ 13 የሚደርሱ ሙስሊም ጠበቃዎች እና ዳኛዎች በእለተ ቅዳሜ በአሳቻ ሰዓት ተሰብስበው
መገኝታቸውን ጽፈን ነበር ፤ ይህን ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ
“በሀይማኖት ላይ የለዘበ አቋም እንዳታሳዩ ፤ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጋችሁ ብቻ ስራችሁን ስሩ” በማለት ቀጭን ትዕዛዝ
ማስላለፉን ገልጸን ነበር ፤ አሁንም መናገር የፈለገውን ነገር ግልጽ ባለ መልኩ መናገር ባይችልም ኢህአዴግ አቋሙን ግን
ሲያስቀምጥ ይመለከታሉ፡፡ ይህን የሚያገኙት ለአመራራቹ “ቀጣይ የትግል ግባችን ምን ይሁን” በሚለው ውስጥ ነው፡፡
በገጽ 17 ላይ አክራሪነት እና
የመንግስት አመለካከት እንዲህ በሚል ሲያስቀምጥ እናያለን “..የሀይማኖት አክራሪነት የሚለው አገላለፅ የተለያዩ ሰዎች
ከተለያዩ መመዘኛ በመነሳት ይተረጉሙታል ፡፡ የሃይማኖት መሪዎች አክራሪነትን ከሚመሩት ሃይማኖት መጻህፍት በመነሳት የቅዱሳን
መጻህፍቱን መሰረታዊ መርህዎች የሚጻረር እንደሆነ በዝርዝር
ያስረዳሉ ፤ ከዚህ በመነሳት ያወግዙታል ፡፡ የሀይማኖቱ እምነት ምን እንደሆነ ከሀይማኖት መሪዎቹ በላይ የሚያውቅ የለምና
እነዚህ መሪዎች ከሚያውቁት ነገር ተነስተው አክራነትን ቢተነትኑትና ቢያወግዙት መብታቸው ነው ፡፡ ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ
ድርጅታችንና መንግስታችን ግን በሃይማኖት ሊቃውንት የተገነቡ ስላልደሉ አንድን ወይም ሌላ ሃይማኖትን ለማራመድ ሳይሆን
ሁሉንም ዜጎች ለልማትና ዴሞክራሲ ዙሪያ ለማንቀሳቀስ የተደራጁ በመሆናቸው አክራሪነትን የሚመለከቱት ለልማትና ዴሞክራሲ
አጀንዳ ካለው ተጽህኖ በመነሳት ብቻ ነው፡፡ ከዚህም አኳያ ሲታይ የሃይማት አክራሪነት ጸረ ልማትና ጸረ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ
ሆኖ ይገኛል ፡፡
የዴሞክራሲ ስርአታችን ሁሉም
ዜጎች የእምነት ነጻነት እንዳለው ያስቀምጣል ዜጎች የራሳቸውን እምነት ነጻነት ማስከበር ይችሉ ዘንድ የሌላውን የእምነት
ነጻነት ማክበር እንዳለባቸው ያስቀምጣሉ ፡፡ አክራሪነት የምንለው ይህ መሰረታዊ የዴሞክራሲ መርህ በሃይማኖት ሽፋን መቃወም
ነው፡፡ ይህን የአክራሪነት አመለካከት ለሁሉም ሃይማኖቶች ሊታይ የሚችልና አልፎ አልፎም በተግባር የሚከሰት ነው፡፡ በዚሁ
መሰረት አንዳንድ ሙስሊሞች ሌላውን ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሙስሊሞች እንኳን ሳይቀሩ ሀቀኛ ሙስሊሞች አይደሉም
ብለው በመፈረጅ የእምነት ተቋሞቻቸውን ለማፍረስ ፤ የሃይማኖት አባቶችን መቃብሮች ቆፍረው ለማውደም ይከጅላቸዋል፡፡ በተግባር
ሲፈጽሙት ታይተዋል ፡፡ የራሳቸውን የእምነት ነጻነት ለማስከበር የሚሞክሩት የሌላን ነጻነት በማክበር ሳይሆን የሌላውን
ነጻነት በመድፈቅና በማፈን ነው፡፡ በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው
ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ ተለየ አመለካከት ያላቸው
ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡” በማለት ያስቀምጣል ፤ ከላይ እንደመነሻ
የተንደረደረበት ሀሳብ አክራሪነት ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ አክራሪ ሙስሊሞችን ስራዎቻቸውን ያስቀምጣል ፤ በስተመጨረሻ “አንዳንድ
ኦርቶዶክሶች” በማለት በእኛ ላይ አክራሪነትን ቋጭቶ ይደመድማል ፤
እኛ ተሀድሶያውያንን ተከታትለን ከቤተክርስትያኒቱ
አስተምህሮ ውጪ የሆነውን ምንፍቅናቸውን ለህዝብ ስላሳየን አክራሪ ተብለናል ፤ በመሰረቱ ቤተመንግስትን በወታደር መጠበቅ
ይቻላል እምነትን ግን እንደ እነርሱ በወታደር መጠበቅ አይቻልም ፤ አባቶቻችን ይችን እምነት ከመናፍቃን ጠብቀው ያቆዩልን
ክፉ ትምህርታቸውን በማውጣት መክረው አልመለሱ ሲሉ በጉባኤ በማውገዝ መሆኑን እኛ እንጂ እነርሱ ሊያውቁልን አይችሉም ፤
ተሀድሶያውያንን የእምነት ነጻነታቸውን አልተጋፋንም ፤ የፈለጉትን እምነተ ማመን መብታቸው ነው ነገር ግን “ቤተክርስትያናችን
የእነሱ አመለካከት ማራመጃ መድረክ አትሆንም” በማለታችን “አንዳንድ ኦርቶዶክሶች” ተብለን ስም ተሰጠን ፤ አሁን ብቻ
አይደለም ወደፊትም እነዚህን መሰል የቤተክርስትያን የእግር ውስጥ እሳቶችን ስራቸውን ከመቃወም ፤ መግባርና ተግባራቸውን
ከማጋለጥ ወደ ኋላ አንልም ፤ ጽሁፉ ጉደኛ ነው ብዙ ነገር አለበት እንቀጥል፡፡
“የዲሞክራሲ ስርአታችን
መንግስትንና ሃይማኖት መለያየት እንዳለባቸውና አንዱ በሌላው ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት እንደማይገባው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ዲሞክራሲ ብሎ ነገር በፍጹም የማይታሰብ ነገር መሆኑን ያረጋግጣል ፡፡ የሃማኖት አክራሪነት የምንለው
ይህንኑ መሰረታዊ የዲሞክራሲ መርህ በሀይማኖት ሽፋን መናድ
ነው ፤ ይህው አመለካከት በተለያየ መልኮች ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሰፊ ቁጥር ባይኖራቸውም ጥቂት ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች እንደ
ድሮ ሁሉ ኦርቶዶክስ ክርስትና የመንግስት ሃይማኖት እንዲሆን ፤ ኢትዮጵያ የክርስትያነ ደሴት ናት ከሚል ቅዥት ባለፈ አንድ “ሀገር
አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ፡፡
ከሌሎች የተለየ መብትና ጥቅም እንዲኖረው ይመኛሉ፡፡ ይህ አመለካከት ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው የከሰመ ቢሆንም
አክራሪነት የሚገለጽበት አንዱ ገጽታ መሆኑ አልቀረም ፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ሙስሊሞች የሀይማኖት ብዙሀነት
ባለበት ሀገር እስልምና ነው ብለው ያመኑበት መመሪያ በመንግስትና በመንግስት ተቋች አማካኝነት እንዲፈጸሙ እስልምና መንግስት
ሃይማት እንዲሆን ሲከጅሉ ይታያሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሁለቱም እዚህው ሀገር የተፈጠሩ ይመስል የኦርቶዶክስም ሆነ
የእስልምና አንዳንድ ተከታዮች ዘንድ የሚስተዋለው የተዛነፈ አስተሳሰብ ሁለቱም ነባር እንደሆኑና ሌላው መጤ በመሆኑ የሁለቱን
ያህል ስፍራ እንደማይገባቸው አድርጎ የማሰብ ነው፡፡ ሌሎችም ሀይማኖቶች ደረጃው ቢለያይም ተመሳሳይ አክራሪነት ዝንባሌ
የተጠናወታቸው አባላት አሏቸው፡፡ እነዚህ የተዛነፉ አስተሳሰቦች በአደባባይ የሚነገሩ ጭምር ናቸው ፡፡ እዚህ ላይ
መዋቅራችንም ለችግሩ የራሱን ድርሻ መውሰድ አለበት ፡፡ የሁሉም ዜጎች የጋራ ንብረት የሆኑ አደባባዮችና መንገዶች በየበአሉ
ከኃይማት ጋር በቀጥታ ባልተያያዙ ጸያፍ መፈክሮች ሲጥለቀለቁ መዋቅራችን ጭምር አይቶ እንዳላየ የሚያልፍበት ሁኔታም
ይታያል፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ጠረጴዛዎችና ኮምፒዩተሮችና ግድግዳዎች ላይ ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና
ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር
በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡፡ በአንድም በሌላ መንገድ ይህንኑ አደገኛ መንገድ መከተል መደገፍ ነውና፡፡” በማለት
ያስቀምጣል፡፡
ይህ ጽሁፍ በጣም ገራሚ ከመሆኑ
የተነሳ ሰዳቢዎቹ ሲሳደቡ ጠያቄ እንደማይመጣ እርግጠኛ ሆነው ነው ፤ እውን ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት አይደለችምን ? በቁጥር
የምናውቃቸው በቁጥር የማናውቃቸው ከ20ሺህ በላይ አብያተክርስትያኖቻችን ቋሚ ምስክሮቻችን ናቸው ፤ ይህ ለናንተ ቅዥት ነው የማይፈታላችሁ
ነገር ነው ፤ እንደ “ማኔ ቴቄል ፋሬስ” ፈቺ የሚያስፈልጋችሁ ይመስለናል ፤ ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት መሆኗ እኛ ዝም ብንል
ምድሪቷ አፍ አውጥታ ትናገራለች ፤ትላንትና በእርዳታ ስም የመጡትን እምነቶች የተከፈቱትን አዳራሾች አትመልከቱ ፤ ይች ሀገር እንደ ሀገር እዚህ የደረሰችው በዚችው ቤተክርስትያን አስተዋጽኦ
ነው ፤ የመጣችሁበትን መንገድ ብትረሱ ፤ የተነሳችሁበትን ማህበረሰብ ብትዘነጉ ፤ የበላችሁበትን ወጭት ብትሰብሩም ነፍስ ከስጋችሁ
ስትለይ ፤ ነፍስም ፈጣሪዋን ሽታ ስትኮበልል በሞታችሁ ወቅት ግን ከ10 ሺህ ብር በላይ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ቀብራችሁ
እንዲያምር የምትፈልጉ ሰዎች ይህን ክዳችሁ ሰው እንዲክድ ብታደርጉ ይህ ታሪክ ስለሆነ መፋቅም መቀየርም መደለዝም አትችሉም ፤
ሌላው ደግሞ “ነባር አይደላችሁም” መባላችን አስገርሞናል ፤ ታሪክ ይናገራል ሙስሊም ወንድሞቻችን ወደዚች ሀገር የመጡት ከ5ኛው
ክፍለ ዘመን አካባቢ መሆኑን ተጽፎ የተቀመጠ እነርሱም የማይክዱት ሀቅ ነው ፤ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ34 ዓ.ም ክርስትናን
የተቀበለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሆኑን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ሰፍሮ እናገኝዋለን ፤ ታዲያ ማነው የነበረው ? ማንስ ነው በሂደት
የመጣው ? ፤ ማንስ ነው መጤ ? እናንተም እኮ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለአዲስ አበባ መጤዎች ናችሁ ዘነጋችሁት እንዴ ? ፤ ስለዚህ
የኦሪት መስእዋት ስታቀርብ የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስጠጊ እንጂ ተጠጊ አለመሆኗ እወቁ ፤ በሌላ
በኩል ኦርቶዶክሳውን ሆንን የመጽሀፍ ቅዱስን ጥቅስ በቲሸርቶቻችን ላይ አድርገን ስንሄድ ሀፍረት እንዴት እንደማይሰማን ጸሀፊው
ሀሳቡን ያስቀምጣል ፤ “ነገሩ እንዴት ነው” አለች አይጥ የድመት ጓደኝነት ያላማራት ፤ ሌሎች በእምነታቸው ሊያፍሩ ይችሉ ይሆናል
፤ ሳያውቁ ገብተውበት መውጫው ጉድጓድ ጠቦባቸው ያሉበት እምነት ያሳፍራቸው ይሆናል ፤ እኛ ግን አንዳች የምናፍርበት የምንሳቀቅበት
አንገት የምንደፋበት ነገር የለንም ፤ ለምንስ እናፍራለን ፤ በጣም ደስ ብሎን እንደምናደርገው በዚህ አጋጣሚ እወቁልን ፤ ለኛ
ስብከት ነው ፤ ካስተዋላችሁ 4ኪሎ አካባቢ አንድ አይምሮው ትንሽ የሚያመው ወንድም ከፊት ለፊቱ ላይ የእመቤታችንን ነገር ለመንገር “ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል” የሚል ጽሁፍ
ሲለጥፍ በጀርባው ደግሞ አሁን የማላስታሰውን አንድ በጣም ደስ የሚል ጥቅስ በጀርባው ላይ ለጥፎ ሲዞር ተመልክቻለሁ ፤ አደራችሁን
አሸባሪ እንዳትሉት ፤ እሱ ኑሮ ያሸበረው ይበቃዋል…….
“…እዚህ አገር የተፈጠሩ ይመስል..” ማለትስ ምን ማለት ነው ?፤ ዛሬ ጠያቂ ባይኖራችሁ ነገ ግን ይኖራችኋል
፤ ቀን የራሱን ነገር ይዞ ይመጣል ፤ ጊዜ በራሱ መፍትሄ የሚሆንበትም ወቅት ሩቅ ላይሆን ይችላል ፡፡ በምድር የማይሻር ስልጣን
የማይነቀል መንግስት የለም፡፡
በተለያዩ የመንግስት ፤ የግል
እና መንግስታዊ ያልሆነ ቢሮዎች የሚሰሩ ሰዎች የመስሪያቤታቸው ደንብና መመሪያ ባይፈቅድም የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስና ቅዱሳን ስእላትን
በግድግዳ ላይ ለጥፈው ይታያሉ ፤ ነገር ግን ይህ ነገር አግባብ
አለመሆኑን በመንገር የሚያወርዱበትን መንገድ ከማመላከት ውጪ “በምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ” በማለት ድርጅታዊ አቋምን
በሚያንጸባርቅ መጽሄት ላይ ሰፍሮ መመልከት ያሳዝናል ያሳፍራልም፡፡ እንቀጥል..
ይህ ጽሁፍ ጽንፈኞችን በአንድ
አንቀጽ አንዲህ ብሎ ይገልጻቸዋል “ሁል ጊዜም ጽንፈኞች ማንኛውም ሰው በሚከተለው እምነት የግል መብት የለውም ብለው ያምናሉ
፡፡ ውይይትና መግባባት ፤ ሰላማዊ ውይይትን በማውገዝ በአመጽ ተደግፈው የራሳቸውን አተያይ ይጭናሉ ፡፡ ከፍቅር ጥላቻን ፤ ከርህራሄ
ጭካኔን ፤ ከመቻቻል መናቆርን ፤ ከእውቀት ድንቁርናን ፤ ከውይይት ጉልበትን ይመርጣሉ ፤ ያበረታታሉ ፡፡ ጽንፈኞች የመንግስትና
የሃይማኖት መለያየትን አይቀበሉም ፤ ይልቅ እነሱ እምነት የተለየ የበላይነት እንዲኖረውና መንግስታዊ ድጋፍ ጡንቻ እንዲኖረው
ይፈልጋሉ፡፡ ይህ አመለካከት በተለያዩ የእስልምና እና ክርስትና ሃይማኖቶች ውስጥ በመሸጉ የተወሰኑ ቡድኖች የሚስተዋልና በተለያየ
መልክና ደረጃ የሚንጸባረቅ ነው፡፡” በማለት ይገልጻቸዋል ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ነገር ግን አክራሪ ኦርቶዶክስ
ግን ሊኖር አይችልም ፤ ሁለታችንንም በአንድ ሚዛን አስቀምጦ በአንድ መነጽር እየተመለከቱ መጻፍ አግባብ አይደለም ፤ ባይሆን
ባሳለፍናቸው ጥቂት አመታት በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በጅማ እና እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አክራሪ በሆኑ ሰዎች መከራን ተቀብለዋል
በመቀበልም ላይ ይገኛሉ ፤ በተለይ በጅማ የበርካቶች ደም ሲፈስ መመልከት ችለናል ፤ ነገር ግን መንግስት ይህ ነው የሚባል ርምጃ
ሲወስድ መመልከት አልቻልንም ፤ የተጎዳነው በደልና ግፍ የደረሰብን እኛው ሆነን ሳለን ከአድራሽ ሃይሎች ጋር ደምሮ ሂሳብ ማወራረት
ተገቢ አይደለም ፤ የዛሬ ዓመት አካባቢ በጅማ አውራጃዎች ከ35 በላይ የሌሎች የእምነት ተቋማት አዳራሾቻቸው በእሳት ሲጋዩ ፤
ሰውም ሲፈናቀል በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ጆሯችን ሰምቷም ፤ ከጋዜጦች ላይም አይኖቻችን አንብበዋል ፤ የሚገርመው ነገር ግን ይህን
አደረሱ የተባሉት ሰዎች ማንነታቸው ስናውቅ የመንግስን እርምጃ አለመጣጠሙ ነበር ፤ እነዚህ ሰዎች በመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙ
፤ የአካባቢው ባለሀብቶች ፤ የመስጂድ ኢማሞች ፤ የውጭ ገንዘብ ፈሰስ የሚደረግላቸው ቡድኖች እና የኢህአዴግ አባላት ሆነው መገኝታቸው
አስደምሞናል ፤ እስኪ የደረሰውን የሞት ፤ የአካል ፤ የንብረት ፤ የሳይኮሎጂ ጉዳት አስቦ የተወሰደውን እርምጃ ተገቢ ነው የሚል
ሰው ማነው ? ፤ እኛስ እውነትን እንናገራለን ጥሩውን እናበረታታለን የማይጠቅሙ አካሄዶችን እንነቅፋለን ፤ እነዚህን የመሰሉ
የወረደ አመለካከት ያላቸውን ለራስ ለቤተሰብ ለእምነት ፤ ለድርጅታችሁ
ኢህአዴግ እና ለሀገር የማይጠቅሙትን ማጥራት ከውስጡም የማጽዳት ስራ መስራት ሲገባው ፤ እጁን ወደ ሌሎች ላይ መጠቆሙ የሚያዋጣ
አካሄድ አይመስለንም ፡፡
ጽሁፉ ይቀጥላል…
“ በሀገራችን ዜጎች በሚከተሉት
እምነት ምክንያት በሚገፉባቸው ተገደው የሌላውን ሃይማት ካልተከተሉ ከቀያቸው የሚፈናቀሉበት ፤በሚከተሉት እምነት ምክንያት በተወሰኑ
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ሀገራቸውን የማገልገል ፤ ከተቀጠሩም ከመሰላሉ ስር ፈቀቅ እዳይሉ ይደረግባቸው የነበሩት በነዚያ
ህገ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ጥበቃ በነበራቸው ግፎች በነገሱባቸው የጨለማ ዘመናት እንኳን ጠንክሮ የዘለቀው የሃይማኖት መቻቻል
፤ ይህ ህዝቦች አብሮ የመኖር እና መደጋገፍ ትስስር ለመበጣጠስ በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጽንፈኛ አክራሪ ኃይሎች የተፈጸሙ ይጥፋት ድግሶች ማስተዋል ጥሩ ነው፡፡ ጥፋቶቹ ማተራመስ
የጀመሩት በቅድሚያ የወጡባቸውን የሃይማኖት ተከታዮች ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የተቃጠሉ እና የፈረሱ መስጅዶች ፤ የታዋቂ የእስልምና የመቃብር ስፍራዎች በሙሉ ጥፋት የተፈጸመባቸው እስልምናን እንከተላለን
በሚሉ ጥቂት ጽንፈኞች ነበር፡፡ የሙስሊሙን ተቋማት ከማፈራረስ ሳይቦዝኑ ቤተክርስትያናት አውድመዋል፤ በክርስትና በኩል ሌላውን የሚያንቋሽሹ ፤ የተለያዩ የክርስትና ተከታዮችን
ጨምሮ መናፍቃን ፤ ኢ-አማንያን በማለት የሚተነኮሱ ኃይሎች አሉ፡፡ ከሁሉም ሃይማኖቶች አንጻር ያሉት እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና
አንዱ በሌላው ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ
የሚሰሩ ናቸው፡፡ በእርግጥ ከበርካቶች በስተጀርባ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስፖንሰሮች ያሉአቸው የፖለቲካ አጀንዳ የተላበሱ
ጽንፈኞች ናቸው ፡፡ ብዙሀኑ ግን ለእምነታቸው ዘብ የቆሙ እየመሰላቸው በቀላሉ ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ …. ወሃቢያን ወይም ሌላው
የመከተል የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው ፡፡ መንግስት ሊመርጥላቸው አይችልም፡፡” በማለት
ይቀጥላል ፤ የበፊቱን የመንግስ አገዛዝ ማስቀመጣቸው ተገቢ ነው ፤ ቤተክርስትያችንም ከመሀመድ ግራኝና ከዮዲት ጉዲት በኋላ ከፍተኛ
ጉዳት የደረሰባት ወቅት ነው ፤ በጊዜው ከአሁኑ የተሻለ የሀይማኖት መቻቻል እንደነበረ ጊዜው ያሳለፉ ሰዎች ምስክሮች ናቸው ፤
ነገር ግን ያሳለፍነው ጊዜ ምንኛ ጨለማ ቢሆንም ይህን ወቅት ብርሀን ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ ግን የለም ፤ ሚዛኑ የመድሀኒአለም ነውና እኛ ዝም እንላለን ፤
በተጨማሪ በጥቅምት
11 ላይ ተሀድሶያውያንን በመቃወም ፤ ቤተክርስትያን አትታደስም በማለት ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንደ ንብ በመትመም
የተቃወሙትን ወጣቶች ሁኔታ ሌሎች የፖለቲካ አላማ ያላቸው ሰዎች ያነሳሷቸው ናቸው ብሎ ጽሁፉ ያትታል ፤ ይህ ስለ ቤተክርስትያናቸው
ብለው ያደረጉት እንጂ የፖለቲካ ጥማት ያለባቸው ሰዎች ገፋፍተው ያስወጧው አይደሉም ፤ በጊዜውም ተቃውሟቸውን የገለጹት ፍጹም
ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መንገድ መዝሙር በመዘመር እና እነዚህ ሰዎች ላይ አለን የሚሉትን የቤተክርስትያኒቷ አስተምህሮ ያልሆኑትን
መረጃዎች ለብጹአን አባቶቻችን በማቅረብ እንጂ ከውጭ ሀገር የገንዘብ እርዳታ ተደርጎላቸው የፖለቲካ ማራመጃ ሆነው አይደለም ፤
ተቃውሞው የተደረገው በቤተክርስትያን ግቢ እንጂ በቤተመንግስት አለመሆኑን እናተም የምታውቁት ይመስለናል ፤ በጊዜው የነበሩት
የሰንበት ተማሪዎች ለእምነታቸው ዘብ ቆመዋል ፤ የአባቶቻቸው እምነት እንዳይሸረሸር ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋ ፤ ፍጹም አልተሳሳቱም
፤ ለእምነት መቆርቆርን ያሳዩን ያስተማሩን አይከኖቻችን ናቸው ፤ በሌላ በኩል “መናፍቃን” የሚለውን ስም ባለቤቶቹ ሳይከብዳቸው
መንግስት የገደል ማሚቱ ሆኖ ያስተጋባላቸዋል ፤ እናንተ አባል
ያልሆነን አሸባሪ በማለት ታፔላ ስትለጥፉ ምንም ያልመሰላችሁ እኛ ግን ውስጣችንን እንደ ነቀዝ ቦርቡረው ሊጨርሱን ጥቂት የቀራቸውን
ሰዎች የሚመለከተው አካል ስራቸውን መዝኖ ሲያወግዛቸው እኛም መናፍቃ ነበሩ ስንል ለምን ትሉናላችሁ ፤ ህገ መንግስቱን ይጋፋል
ትላላችሁ ፤ ይህ ህገ መንግስት እኮ ለሁሉም ነው የሚሰራው ፤ መፎከሪያ ማስፈራሪያም ሆኖ መቀመጥ የለበትም፤ ለማንኛውም በመጽሀፉ
ላይ ከሰፈሩት 41 ገጾች ውስጥ 30 ያህሉ ሙስሊሞችን የሚመለከት ሲሆን 10 ደግሞ ቀስቱ ወደኛ ሆኖ አግኝተነዋል ፤ ዋና ሀሳብ
ያልናቸውን በጣም በጥቂቱ ለማሳየት ሞክረናል ፤ መጽሀፉን የምታገኙ ሰዎች አንብቡትና የራሳችሁን ፍርድ ስጡ ፤ በቅርብ ለማታገኙት
በሀገር እና ከሀገር ውጪ ላላችሁት ደግሞ መለስ ብለው ብሎጋችንን ይጎብኙ እንደወረደ በፒዲፌ አዘጋጅተን ብሎጋችን ላይ እናስቀምጥሎታለን
…….
አንብባችሁ ሀሳባችሁን ላኩልን…..
“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት
አንዲት ጥምቀት፤” ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤5
|
የመጣችሁበትን መንገድ ብትረሱ ፤ የተነሳችሁበትን ማህበረሰብ ብትዘነጉ ፤ የበላችሁበትን ወጭት ብትሰብሩም ነፍስ ከስጋችሁ ስትለይ ፤ ነፍስም ፈጣሪዋን ሽታ ስትኮበልል በሞታችሁ ወቅት ግን ከ10 ሺህ ብር በላይ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ቀብራችሁ እንዲያምር የምትፈልጉ ሰዎች ይህን ክዳችሁ ሰው እንዲክድ ብታደርጉ ይህ ታሪክ ስለሆነ መፋቅም መቀየርም መደለዝም አትችሉም
ReplyDeleteእኔ ሳስበው መንግስት የውጭዎቹ ሰሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ አያደረጉ ያሉትን በከፍተኛ ገንዘብ የታገዘ እንቅስቃሴ አያውቀውም ለማለት እልችልም፡፡ ነገር ግን ለምን በዙ ነገር ሰያወሩ ይሄን አደገኛ አካሄድ ዝም አሉ
ReplyDeleteወገን
ReplyDeleteራሳችሁን ነጣ ለማውጣት ዲፌንድ ስታደርጉ ሙስሊሞችን በመንካት መሆን የለበትም።ኦርቶዶክስ አክራሪ የለውም ሙስሊሞች ግን አላቸው የሚባለው አያስኬድም፡፤እኛ አክራሪ አይደለንም ማለት ትችላላችሁ።የሃይማኖት መቻቻል እውን ይሆን ዘንድ መከባበሩ እንጅ በነገር መጎነታተሉ ትርጉም የለውም።መንግስት ሰድቦን እናንተም ተጨምራችሁ እኛ በመካከል ሳንድዊች መሆን አለብን?አይገባም!ነውርም ነው!
ስትቃወሙ ለይታችሁ ተቃወሙ ።ሌላው ኢትዮጵያ የክርትስያን ደሴት ናት የሚለውን አባባል ለጊዜው ተውት ።ይሁንላችሁ ችግር የለውም።ግን ማለቱ ለምን አስፈለገ?እውነት ከሆነም እውነታውን ታውቁታላችሁ !እኛም አዎ የክርስቲያን ደሴት የሙስሊሞች ግን ባህር ወይም ውቅያኖስ ናት ብንል ያስኬዳል?ያስማማል?እናም እየትስተዋለ ቢሆን ይመረጣል።መንግስት ስልጣኑን ለማራዘም እኛን እያባላ፡ቤተክርስቲያን አባላቶቹ አቃጥለው ሙስሊም አክራሪዎች ናቸው በማለቱ እናንተም ካመናችሁ ያሳዝናል!ቤተክርስቲያን በመቃጠሉ ደስተኛ ሙስሊም የለም።የሰው ደም በመፍሰሱ ደስተኛ ሙስሊም የለም።ከመጋረጃ በስተጀርባ ግን ስውር እጆች አሉ!አንድ ቀን ሃያሉ አላህ ይቆርጣቸዋል።
I wish every Muslim thinks like you which is your fathers believe. Make sure all your friends have thinking like you. We have nothing against our Muslim or anyone. we just don't wont anyone touch our church that is all. It is nice to read your positive comment.
DeleteThank you
This is a great message! I like it. Wondime you thought is so matured...I wish every Muslim think and believe like you!! Wish you all the best1
Deleteyaa i like it please andadirgen also consider this idea on your post
Deleteበጽሁፉ ላይ በተቀመጡት በብዙ ነገሮች ልስማማ እችላለሁ፡፡ ቢያንስ ግን በሚከተሉት ነገሮች ላይ በፍጹም አልስማማም!
ReplyDelete• ማህበረቅዱሳናዊ የሚባል አመለካከት ወይም እምነት የለም፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የአባቶቹ እምነት እንዳይሸረሸር ተግቶ እንዲሰራ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ታላቅ አደራ ተቀብሎ እየሰራ ነው፡፡ ይህም ሲራ እጅግ ፍሬ እየፈራ መሆኑ የግንቦቱ ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በቂ ምስክር ነው፡፡ ባይሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁለት አመለካከት ተሰጥሯል፡፡ ያባቶቻችን ስርአት አይለወጥም ኦርቶዶክስ እምነቷ ሊታደስ አይችልም የሚልና ሌላው ደግሞ በተጻራሪው የቆመው በአባ ጳውሎስ የሚመራው ቡድን ነው!
• ማነፍቅ እያሉ የእምነት ነጻነታቸውን እስከመጋፋት ደርሰዋል የተባለው ጉዳይ.... ወራጅ አለ! እንዲህ ብሎ ያወገዛቸው የቤተክርስቲያኒቱ ባለ ሉአላዊ ስልጣን... ቅዱስ ሲኖዶስ ነው! በኢህአዴጋዊ ቋንቋ ለማሳጠርና ለማስረዳት ደግሞ፤ አንድ ፖለቲከኛ ኢህአዴግ ውስጥ ሆኖ ጸረ-ኢህአዴጋዊ አካሄድ ሊያራምድ አይችልም! ከኢህአዴግ ራሱን ለይቶ ግን ሰላማዊ በሆነ መንገድ የራሱን አጀንዳ ሊያራምድ ይችላል.. በተነጻጻሪ መልኩ አንድ ግለሰብ ረቶዶክስ ውስጥ ሆኖ ጸረ-ኦርቶዶክስ ትምህርት ሊያስተምር አይችልም ከቤተክርስጢኒቱ ራሱን ለይቶ ግን የፈለገውን እምነት ማራመድ ይችላል!አሁን ለመጽሄቱ አዘጋጅ ግልጽ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ! በራሳቸው ቋንቋ ስለ አስረዳኋቸው! መናፍቅ መናፍቅ ነው! ሌሎችም ብዙ ነገሮች ይኖሩኛል ወደፊት እመለስበታለሁኝ፡፡
'ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ1934 ዓ.ም ክርስትናን የተቀበለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ' ይሄ ስህተት ነው፡፡ በ34ዓ.ም. ተብሎ ይስተካከል፡፡ ወቅታዊ ነገርን ማቅረባችሁ ጥሩ ሆኖ አንዳንዴ ብስለት የጎደላቸው ዓረፍተ ነገሮችና መልዕክቶችን ታስተላልፋላችሁ፡፡ ሌላው ሆሄያትንንም ተጠንቅቃችሁ ብትጽፉ መልካም ነው፡፡ ስትጽፉም እኛ ብሎ መላው ክርስቲያንንም ወይም የደገፋችሁትን ወገን ለመወከል ከመሞከር እንደ ባለ ብሎግ ባለቤትነት በራሳችሁ ብታቀርቡት መልካም ይመስለኛል፡፡በተረፈ በርታ /በርቱ፡፡
ReplyDelete1934 tebelo yetu gar new yetsafew kemawerat befit matearte teru nw
DeleteAntem kemetsafih befit atara. It is now corrected but it was like the quoted one when they first posted it. Kefelegih bale blogun teyiq.
DeleteGood comment and please keep on going.
ReplyDelete“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤5
ReplyDeleteኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት መሆኗ እኛ ዝም ብንል ምድሪቷ አፍ አውጥታ ትናገራለች
ReplyDeleteThe book helped me to know that the government even doesn't have a good writter. Very poor. I really am sad to know we are governed by illiterate people. I feel like it is written by some "dureye".
ReplyDeleteDear Government,
If you have the chance to read this, Please know that wisdom is what you are missing. you don't know who cares about the country's growth and who don't. who cares about the peace and who don't. It really is a shame to know that you know nothing and you are a leader of so many smart people. You don't even know how to use Amharic properly. I have no word to write more. Because we are talking to a dummies.
May God give you the mind to notice what is going on.
From Dc
አገር ድንኳን ትሁን ጠቅልዬ የማዝላት
ReplyDeleteስገፋ እንድነቅላት ስረጋ እንድተክላት
“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤5
ReplyDeleteውድ ኢህአዴግ
ReplyDeleteለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ አፈርኩብህ!!!
ሲበዛ ደፋሮች ናችሁ፣ ሙስሊሙን ለመውቀስ ክርስቲያኑን መጨፍለቅ ምን ይሉታል? አፋችሁ ቢክድም ልባችሁ ያውቀዋል ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት! ደግሞ ማፈሪያ ሃሳባችሁ እንዴት የምናምነውን በቲሸርት ላይ ለብሰን በመሄድ እናፍራለን? ቲሸርቱ ከገረማችሁ ግንባራችን ላይ ጽፈን መሄድ እንጀምራለን። የተዋህዶ በመሆናችን ተባርከናል::
ወሃቢያን እና ማህበረ ቅዱሳንን የምታዩበት አይን የተለያየ ቢሆን መልካም ነው! እኛ መናፍቅም ሆነ ሌላው ሃገራችንን ይልቀቅ አላልንም ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ግን አዎን!!! ሳይወዱ በግድ! ከላይ ወንድሜ እንደጠቀሰው የኢህአዴግን ማልያ ለብሶ ለቅንጅት መጫወት እንደማይቻል ሁሉ የተዋህዶ መስሎ ምንፍቅና መስበክ ግን እእእእእእ እዛው!!! ደግሞስ መናፍቁ መናፍቅ ቢባል መንግስት ምን አገባው ወይስ ከመናፍቅ ጋር ተደርቦ አብያተ ክርስቲያናችንን ማፈራረስ አላማው ነው? አላርፍ ያለች ምን አሉ ከግንብ ጋር ራስህን እያጋጨህ መጥፊያህን ባታቃርብ ጥሩ ነው "እግዚአብሄር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሄር ነው"
Thank Dear Andadirgen God and His Mother St.Virgin Marry bless you!
ReplyDeleteThe dogs are strangling spread the serpent poison and snare to the innocent for spoil. We Ethiopians Orthodox and Muslim are much responsible to this poor land than "the WEYANE GOV". Always when this "gov" becomes tensioned on the fear of political hotness of the nation and the region, they try to divert the attention with very silly and stupid issues.Practically, I observed it gave them some relief but they are like a man who sleep on the tree!
History and time will punish you severely like Mubarek (ugly death). We know you WEYENEs' are the most foolish and fearful people but we have stone strength and refuge to save Ethiopia!
I advise you ABUNE POULOS teach you Amharic and AMHARIC writing. The most ugly paper ever I read in my life including even in the future! You waste my time for useless!
For the last 38 years everything bad and wrong which have happened to the country and the nation due to WEYALE for instance famine and War more than 4 million took-out with weeping death for a number of our people from Tigray, Wolo, and Eritrea and all over the country. At last we left loss in the family, loss as a nation no peace still and no gain, no democracy even though you said "you fought for good"
I wish God will down you and to live in peace together with real love and development! We are not like you, we love you and we pray for you the to see the mercy of God and his way be fore you die!
God Bless Ethiopia!
From HINITICHO, TIGRAY!
All eotc have united together to save our church which including to in side and out side enemy, on myunderstanding the key enemy of our church is TEHADESO AND ABA PAULOS for my reason they have floop side of coin. Aba Paulos shame on him he did not say one word to save Waldiba and to stop tehadeso web that acuused our father on shame language.
ReplyDeleteYou don't know that Aba Pauwlos supports the construction of the sugar factory instead against it. We Ethiopian Orthodox Christians Just have to pray deeply from our heart to protect our mother church. And for all of us who has the money and time to go to Waldiba we have to go there. I think we don't have to expect someone to organize pilgrimage to Waldiba so we have to take every action we could do by ourselves(personally).
Deleteየመጣችሁበትን መንገድ ብትረሱ ፤ የተነሳችሁበትን ማህበረሰብ ብትዘነጉ ፤ የበላችሁበትን ወጭት ብትሰብሩም ነፍስ ከስጋችሁ ስትለይ ፤ ነፍስም ፈጣሪዋን ሽታ ስትኮበልል በሞታችሁ ወቅት ግን ከ10 ሺህ ብር በላይ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ቀብራችሁ እንዲያምር የምትፈልጉ ሰዎች ይህን ክዳችሁ ሰው እንዲክድ ብታደርጉ ይህ ታሪክ ስለሆነ መፋቅም መቀየርም መደለዝም አትችሉም
ReplyDeleteየመጣችሁበትን መንገድ ብትረሱ ፤ የተነሳችሁበትን ማህበረሰብ ብትዘነጉ ፤ የበላችሁበትን ወጭት ብትሰብሩም ነፍስ ከስጋችሁ ስትለይ ፤ ነፍስም ፈጣሪዋን ሽታ ስትኮበልል በሞታችሁ ወቅት ግን ከ10 ሺህ ብር በላይ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ቀብራችሁ እንዲያምር የምትፈልጉ ሰዎች ይህን ክዳችሁ ሰው እንዲክድ ብታደርጉ ይህ ታሪክ ስለሆነ መፋቅም መቀየርም መደለዝም አትችሉም
ReplyDeletethat is not the way we belive weyana!!!!!! but as long as we belive our ethiopia ortodox church is our life i don't know about you(weyana) or (melas and his Jeale.
ReplyDeleteThanks
7ኛ ላይ June 19, 2012 በ12:41 AM ሰዓት Anonymous ብለው አስተያየትዎን የጻፉ ሰው ስለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አንዳርን ብሎግ ላይ በ1934 ተብሎ በስተት እንደተጻፈ አድርገው የጻፉት የእርምት አስተያየት ምን ላይ እንዳዩት በጣም ግራ የሚያጋባ ነው 1934 የሚል ጽሑፍ አንድም ቦታ ላይ የለም ምናልባት አልታይ ብሎኝ ከሆነ ብዬ ጽሑፉን በሙሉ በword እና excel ላይ ፔስት አድርጌ search/ፈልግ/ብዬ እስከመፈለግ ብደርስም 1934 የሚል ነገር አላየሁም ባይሆን ያገኘሁት የሚከተለውን ነው "ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ34 ዓ.ም ክርስትናን የተቀበለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሆኑን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ሰፍሮ እናገኝዋለን ፤ ታዲያ ማነው የነበረው ? ማንስ ነው በሂደት የመጣው ? ፤ ማንስ ነው መጤ ? እናንተም እኮ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለአዲስ አበባ መጤዎች ናችሁ ዘነጋችሁት እንዴ ? ፤ ስለዚህ የኦሪት መስእዋት ስታቀርብ የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስጠጊ እንጂ ተጠጊ አለመሆኗ እወቁ ፤" እናም አራሚው እርስዎ ራስዎ እርማት ያስፈልግዎታል አንባብያን ሁላችሁ አስተያየት ስታነቡ የተጻፈውን እያሰተዋላችሁ እንድታነቡ ጥቆማዬን አቀርባለሁ። በነገራችን ላይ እኔ ተራ አንባቢ ነኝ ከታዘብኩት ተነስቼ ነው የጻፍኩት። ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
ReplyDeleteI am sure that good time will come for us.
ReplyDeleteአንድአድርገኖች መረጃችሁ ደርሶናል፤በርቱ፡፡ ስለጃንደረባዉ መጠመቅ በተመለከተ መጀመሪያ ላይ ያወጣችሁት ጽሁፍ ላይ በ1934 ዓ.ም ይል እንደነበር እኔም አንብቢያለሁኝ፡፡ይህ ሳይሆን አሁን ሊያወያየን የሚገባዉ ከመጋረጃዉ በስተጀርባ ያለዉ ጉዳይ መሆን አለበት ማለትም መንግስት ለምን ማህበረ ቅዱሳንን ልክ ከዉሃቢያ ጎን ሊፈርጀዉ ቻለ በሚለዉ ዙሪያ፡፡
ReplyDeleteከፖለቲካ ህጸጾች አንዱ እና ዋነኛዉ ጅምላ ፍረጃዉ ነዉ፡፡በአገራችን የተካሄዱትን ክስተቶች በየጊዜዉ ብናያቸዉ በወቅቱ ተጠቅመዋል፤ተጎድተዋል፤ተቸግረዋል-----የሚባሉት አካባቢዎች፤የህብረተሰብ ክፍሎች፤የፖለቲካ አመራሮች፤-ጥናት ቢደረግባቸዉ በአብዘሃኛዉ በጅምላ የተፈረጁ ነዉ የሚሆኑት፡፡በተለይ እኛ አገር የመፈረጅ አባዜ አለ፡፡ከፖለቲከኞች ጋር ሲዋል የፖለቲከኞች አባል፤ከሃይማኖት ሰዎች ጋር አንድ ሰዉ ሲታይ ለሃይማኖቱ ብቻ የሚሰራ ለአገር ግን ምንም የማያስብ ተደርጎ የሚቆጠርበት፤በሁለት ጣቱ ቭ ቅርጽ ሰርቶ ወደ ላይ ካሳየ ቅንጅት አባል ነዉ የሚባልበት(ለነገሩ 1997 ዓ.ም ላይ ነበር)፤በጥረቱ እና በላቡ ያገኘዉ ሃብት ካለ በሙስና የተገኘ ነዉ ብለን የምንፈርጅ ብዙዎች ነን፡፡እረ ስንቱን ፈረጅንዉ፡፡ስንቱ አግባብነት በሌለዉ ፍረጃ ከዉድድር ዉጭ ሆነ?ለነገሩ የዚህ አባዜ ከ1966 አብዮት ጀምሮ በአገሪቱ የተስፋፋ እንደሆነ አንዳንዶች ይጠቁማሉ፡፡
መንግስት ከጅምላ ፍረጃዉ ይዉጣ፤ከመንግስት ያልተናነሰ እረ እንደዉም በአንዳንድ የስራ መስኮች ከመንግስት የበለጠ ስራ የሚሰሩ አካላትን ከጥፋተኞች ጋር አብሮ መደመሩ ከኑግ ጋር የተገኘሽ ሰሊጥ አብረሽ ተወቀጭ አባዜ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡እዉነታን መካድ አያስፈልግም፤ክርስትና እና ኢትዮጲያ የማይለያዩ ጉዳይ ናቸዉ፡፡ኢትዮጲያ ስትል ክርስትና ቀድሞ ይመጣል፡፡ያ ሲባል ግን ሌሎቹ ሃይማኖቶች ለአገራችን ማንነት ምንም አስተዋጽኦ የላቸዉም ማለት አይደለም፡፡በመቻቻል አገራችን እነድትታወቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት እኮ የተለያዩ እምነት ተከታይ ምዕመናን መኖራቸዉ ነዉ፡፡
መንግስት የእምነት ተቋማትን ስስ ብልት እየለየ በዉስጣቸዉ ነገር እንዲዘራ ባያደርግ መልካም ነዉ፡፡የክርስቲያን ደሴት እያሉ ነዉ ብሎ ነገሮችን ማራገብ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ለመንግስት ራስ ምታቱ የትኛዉ ነዉ?የሃይማኖተኞች አንድነት ወይስ መከፋፈል፡፡እኔ የራሴን ሃሳብ ላስቀምጥ መንግስት ሆደ ሰፊ እና እሩቅ አሳቢ ከሆነ የኢትዮጲያን የአማኞች ነባራዊ ሁኔታ ማወቅ አለበት፡፡ለእምነቱ አይደለም ለበሬዉ እየሳሳ ድርቅ ሲያጋጥመዉ በሬዉን አርዶ ከመብላት ይልቅ ሞቱን ያስቀደመ ዜጋ አገራችን ዉስጥ እንደነበር ማስታወሱ ቀሊል ነዉ፡፡ሃይማትማ እዚህች አገር ይጠጌ አይነኬ/asymptote/ነዉ፡፡ፖለቲከኞቹ ወደ እምነት ቤቶቹ ለአምልኮ ሊጠጉ ይችላሉ ግን የፖለቲካ ፍላጻቸዉን ለማሳረፍ መሞከሩ ተገቢ አይደለም፡፡ፖለቲከኞቹ የሚያምኑት እምነት ሊኖራቸዉ ይችላል፤ተገቢም ነዉ፤ነገር ግን ለፖለቲካ ትኩሳታቸዉ ማስፈጸሚያ እንደመሳሪያ ሃይማኖትን ለመጠቀም በማሰብ በአማኙ ዉስጥ እርሾ ይዞ በቂም እና በበቀል እንዲከፋፈል የሚታሰብ ከሆነ ግቡ ሃሳቡን ለሚያስቡት ፖለቲከኞች ዉድቀት ነዉ፡፡
እናም ፖለቲካ ሆይ
አስበህ ተንቀሳቀስ
እኛንም አትፈረካክስ
የረሀቡ ቁስል ሳይደርቅ
አታምጣብን ሌላ ዉጥንቅጥ
ይህ ሰልችቶናል እንደ ዜጋ
ስለተነሳን የድህነትን በር ልንዘጋ
wubshet(bd)
“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤" ይህ ትምህርት ቀድሞም ነበረ አሁንም አለ ለወደፊትም ይኖራል:: መንግስት ተብየው ግን እንዲሁ ዝም ብሎ ነገሮችን እያተራመሰ በማጋጨትና በማጣላት ወደመጥፎ ነገር ከመውሰድ ድክመቱን ተቀብሎ ህዝቡን ማስተዳደር አልቻልኩም በቃኝ ቢል ሳይሻለው አይቀርም ለጤንነቱም ይሻለዋል::
ReplyDeletePeacefully, I am ready to pay any thing to save my mother church. The key point is we all eotc children have time to organized to protect our curch with poltician, Tehadeso and corrupted leaders that directely supported by Aba Paulos. Tehadeso should be succeed if Aba Paulos on the position, it is time to act now to put more pressure on him that to change his wrong map of his leadership. Unless, he will be take 100% responsebilty all mismanagement.
ReplyDeleteThe peace of God stay on all of children of Eotc.
mengist hulunem aweko new yemibetebitew, melse setesetu mengist endemayak adergachihu lemen endemetitsefu aygebagnem
ReplyDeleteእኔምለው መንግሰታችን በእንትኑ ላይ ያለውን በሃይማኖት ጉዳይ ምንግስት ጣልቃ አይገባም በመንግስት ጉዳይ ሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ምናምን ምናምን የሚለውን ዘነጉት እንዴ ነው እነዚህ ሰዎች ጭው ብሎባቸዋል፡፡
ReplyDeleteመጽሀፉ ደግሞ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ነው የሚለው “አንዲት ሀገር” የሚል የለበትም ፤ ይህ ጥቅስ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ ቢመስላቸውም እኛ ምን ማድረግ እንችላለን ? ከህገመንግስታችሁ ጋር እናጣጥምላችሁ ? ምን እንበለው ? ምንስ ብለን ቲሸርታችን ላይ ጽፈን እንልበሰው ? እኛ ቃሉ የመፈጸም እንጂ የማስተካከል የመለወጥ መብቱ የለንም ፤ ቃሉ ደግሞ እንደማይለወጥ በግልጽ መጽሀፉ ይነግረናል ፤ እኛ የተጻፈልንን ማመን ብቻ ነው ፤ ደግመን እንበለው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ስለ ሀገሩ ተውትና “አንድ ሃይማኖት” የተባለችው ቀጥተኛዋ በደም የቆየችልን አሁን እኛ ያለንባት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት ብለን እናምናለን ፡፡
ReplyDeleteመጽሀፉ ደግሞ “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤” ነው የሚለው “አንዲት ሀገር” የሚል የለበትም ፤ ይህ ጥቅስ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ ቢመስላቸውም እኛ ምን ማድረግ እንችላለን ? ከህገመንግስታችሁ ጋር እናጣጥምላችሁ ? ምን እንበለው ? ምንስ ብለን ቲሸርታችን ላይ ጽፈን እንልበሰው ? እኛ ቃሉ የመፈጸም እንጂ የማስተካከል የመለወጥ መብቱ የለንም ፤ ቃሉ ደግሞ እንደማይለወጥ በግልጽ መጽሀፉ ይነግረናል ፤ እኛ የተጻፈልንን ማመን ብቻ ነው ፤ ደግመን እንበለው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ስለ ሀገሩ ተውትና “አንድ ሃይማኖት” የተባለችው ቀጥተኛዋ በደም የቆየችልን አሁን እኛ ያለንባት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናት ብለን እናምናለን ፡፡
ReplyDeleteበተለያዩ የመንግስት ፤ የግል እና መንግስታዊ ያልሆነ ቢሮዎች የሚሰሩ ሰዎች የመስሪያቤታቸው ደንብና መመሪያ ባይፈቅድም የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስና ቅዱሳን ስእላትን በግድግዳ ላይ ለጥፈው ይታያሉ ፤ ነገር ግን ይህ ነገር አግባብ አለመሆኑን በመንገር የሚያወርዱበትን መንገድ ከማመላከት ውጪ “በምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ” በማለት ድርጅታዊ አቋምን በሚያንጸባርቅ መጽሄት ላይ ሰፍሮ መመልከት ያሳዝናል ያሳፍራልም፡፡ መንግስት ተብየው ግን እንዲሁ ዝም ብሎ ነገሮችን እያተራመሰ በማጋጨትና በማጣላት ወደመጥፎ ነገር ከመውሰድ ድክመቱን ተቀብሎ ህዝቡን ማስተዳደር አልቻልኩም በቃኝ ቢል ሳይሻለው አይቀርም ለጤንነቱም ይሻለዋል::
ReplyDeleteEgziabher hoy! Ebakih Ethiopian kezih aynet fetena netsa awtat! Amen!
ReplyDeleteHulun Begizew Endemitserawim amnalehu! Siledink aterarih Egizihabher hoy amesegnihalehu!
Evil government. “በምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ”. Lets say even in developed nations people put their family picture on their desk. And we Ethiopian orthodox consider S.t Marry as our mother so this means if I put her painting on my desk is this mean that I am against the law. What an evil time.
ReplyDeleteAmuqe'awoch amuqu! Enanten belo b/k tebaqi. Be manem tezaz sayweta tezaz awchiwoch honachu b/k'nen yemetbetebetu enante aydelachehum? Ye emnet netsanet endinor kalfelegachu be emnetm hone be zemenawi temehrt awaqi nen maletachu men ley new? Yenante docterate le semayu amlak menum endalhone atawkum? Eski poletikawn tetacheh sele emnetachen bicha enawera.
ReplyDeleteHaving read this I thought it was rather informative. I appreciate you finding the time and energy to put this information together.
ReplyDeleteI once again find myself personally spending way too much
time both reading and posting comments. But so what, it was still worth
it!
Also see my web page: man utd transfer news today