Wednesday, June 13, 2012

የአቶ የጌታቸው ዶኒ ክስና የፍርድ ሂደት

(አንድ አድርገን ሰኔ 06/2004ዓ.ም)፡- በጌታቸው ዶኒ አቀነባባሪነት የባቦጋያ ምስራቀ ፀሀይ መድሃኒአለምን ቦታ አስመላሽ ጥቂት ኮሚቴዎች ላይ “የማስፈራራት ዛቻ አድርሰውብናል ፤ ሙዳይ ምጽዋት ገልብጠዋል” በማለት አቶ ጌታቸው ዶኒ እና የቤተክርስትያቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸው ይታወቃል  ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ በሀሰት ምስክርነት ያቀረባቸው ሰዎች በብር የተገዙ እና እሱ የፈለገውን እንዲመሰክሩለት ያሰበ ሲሆን ነገሮች እርሱ እንዳሰበው ሊሄዱለት አልቻሉም  ፤ ፤ አንድ ሰባኪ ወንጌል በፍርድ ቤት ለምስክርነት ቀርቦ በሀሰት እንደመሰከረና ቀሲስ መስፍን የምስክሮችን ቃል እየሰሙ ውጭ  ላለ ሌላ የሀሰት ምስክር ሲናገሩ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው ለአንድ ቀን መታሰራቸውንና በ2000 ብር ዋስ መለቀቃቸውን ጠቅሰን መጻፋን ይታወቃል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ በምስክርነት በቀረበበት ወቅት ሲመሰክር ከአቃቢ ህግ የቀረበለትን መስቀለኛ ጥያቄ ላይ አንደበቱ ሲያያዝ ተመልክቷል ፤ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል ሰምቶ ከጨረሰ በኋላ በ27/09/2004ዓ.ም ተከሳሾች የመከላከያ ምስክራቸውን እንዲያሰሙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር ፤ በጊዜውም የሁሉም ተከሳሽ ምስክሮች ሙዳይ ምጽዋት ተሰበረ በተባለበት እለት ተከሳሾች ከተማ ውስጥ እንዳልነበሩና  አንዱ ተከሳሽ በዓል ለማክበት ሳማ ሰንበት እንደነበረ ለፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ፤


በ04/10/2004ዓ.ም በዋለው ችሎት የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፖሊስ የምስክሮችን ቃል ለሌላ ምስክር በማስተላለፋቸው አቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርትና ፖሊስ በጊዜው አደረጉ ስለተባለው ተግባር የእምነት ክህደት ቃላቻውን እንዲቀበልና ለቀጣይ ችሎት እንዲያቀርብ ትእዛዝ ተላፏል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ ራሱ በጻፈውና የቤተክህነቱን ማህተብ ያለበትን “ቦታው የመድሀኒዓለም አይደለም” የሚል ሀሳብ ያለውን መልዕክት ከሳምንታት በፊት የአካባቢውን ምዕመን ሰብስቦ በአውደ ምህረት ላይ በፖሊስ እየተጠበቀ አንብቦ ነበር ፤ መልዕክቱ ሲጨመቅ “ይህ ቦታ በሽያጭ ለባቦጋያ ሪዞርት ባለቤት ተስጥቷል ፤ አሁን እኔ የመጣሁት ከጠቅላይ ቤተክህነት በዚህ ጉዳይ ተወክዬ ነው ፤ ሲኖዶስ የወሰነውን ብጹአን አባቶች የተስማሙበትን ጉዳይ እናንተ መቃወም አትችሉም ፤ ሲኖዶስ የቤተክርስትያኒቱ የበላይ አካል ስለሆነ ውሳኔው መቀበል አለባችሁ ፤ ቤተክርስትያኒቱ ቦታውን መጠየቅ አትችልም ፤ ቦታው የአቶ ታዲዎስ ነው ፤ እናንተ በዚህ ጉዳይ ላይ ብትቃወሙና ፍርድ ቤት ክስ ብታቀርቡ ምንም የምታመጡት ነገር የለም ፤ ቦታውን ለማስረከብ እና ለአፈጻጸሙ ተግባራዊነት ብትተባበሩ ይሻላል ፤”   የሚል መልዕክት ነበረው ፤ አቃቢ ህግ “ህዝብን ለአመጽ  የሚቀሰቅስ ሁኔታ አቶ ጌታቸው ዶኒ በቤተክርስትያኒቱ አውደ ምህረት ላይ ያነበበው በጽሁፍ እና በቪዲዮ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትለት`` ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ዛሬ ቪዲዮውንና  ጽሁፉን ለማየት ቀጠሮ ይዟል ፡፡ ይህም ቪዲዮ እኛ እጅ የሚገኝ ሲሆን የፍርድ ቤቱን የፍርድ ሂደት እንዳያስተጓጉል በመስጋት ብሎጋችን ላይ አላወጣነውም፡፡

ባሳለፍነው እሁድ የባቦጋያ አካባቢ ምዕመናን ከአስተዳዳሪው ጋር በመሰብሰብ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በጊዜው በርካታ ምዕመናን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከቦታው እና ከፍርድ ቤት ጉዳዩ ጋር በማያያዝ አቅርበውላቸዋል ፤ በጊዜው ችግር እንዳይፈጠር በመፍራት ስብሰባው ላይ 30 ፖሊሶች ተገኝተው ነበር ፤ የመጀመሪያው ጥያቄ “ለምን ከአቶ ጌታቸው ዶኒ ጋር በመሆን የመድሀኒዓለምን ታቦት ማረፊያ ቦታ ሬክላም እንዲነቀል አደረጉ ? የተነቀለው መስቀል በእጅዎ ከያዙት መስቀል በምን ይለያል ? ሰውየው ቤተክርስትያኖች ላይ ብዙ ችግር ያደረሰ ሰው ነው ፤ በግሉ የእምነት ተቋም ያቋቋመ ሰው ነው ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ የ2004 ዓ.ም የግንቦት ጉባኤ ላይ ስለ ሰውየው ምንፍቅና የተነጋገሩበት ግለሰብ ነው ፤ ስራው በቪዲዮ ከማስረጃ ጋር የተጋለጠበት ፤ ምዕመኑ ሁሉ ስራውን የሚያውቀው ቤተክርስትያኒቱን ለማፍረስ የተነሳ ግለሰብ ነው ፤ ታዲያ ይህን ሁሉ እያወቁ እንዴት ከዚህ ሰው ጋር በመሆን ከዚህ ሰው ጋር ያብራሉ ?  ፤ …… እና መሰል በርካታ ጥያቄዎችን የተጠየቁ ሲሆን … ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንዲህ በማለት አቅርበዋል “የጠየቃችሁኝ ጥያቄዎች ሁሉ ጠንከር ጠንከር ያሉ ናቸው ፤ እኔም ውስጤ እንደናንተው ጥቂት እምነት አለኝ ፤ እንድመልስ አታስገድዱኝ ፤ ፊልሙን በተመለከተ እኔም አይቸዋለሁ አቶ ጌታቸውን ስጠይቀዉም ፊልሙን ማን እንዳሳተመዉ ንገረኝ ነዉ ያለኝ እንጅ ልክ ነዉ ስህተት ነዉ አላለኝም ፤ ሰውየው አደረሰ ስለተባለው ነገር የማውቀው ነገር የለም ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መግለጫውንም አላነበብኩም ፤ የሲኖዶስ መግለጫውን አምጡልኝና እኔም ከናንተ ጎን ነው የምቆመው ” ብለዋል፡፡ ይህን እንዳሉ ያልመለሱትን ጥያቄ “ሬክላሙ ለምን እንደተነቀለ አታውቁም ወይስ…. ? በማለት ሌላ ጥያቄ ተከትሏል ፤

ሌላ ምዕመንም  “በቦታ ላይ የተተከለው መስቀል በሊቀጳጳሱ ተባርኮ ነው የተተከለው ፤ እርስዎ እጅ ላይ የያዙትን መስቀልም ተባርኮ ነው የተሰጠዎት ፤ መስቀሉ ይነቀል ቢባል እንኳን መነቀል ያለበት በአግባቡ መሆን ሲገባው ከአቶ ጌታቸው ዲኒ  ጋር በማበር ይህን ማድረግ አልነበረቦትም” በማለት ገስጸዋቸዋል፡፡ በጊዜው በጥበቃ ላይ የነበሩ ፖሊሶች ከዚህ በፊት በአቶ ጌታቸው አማካኝነት የተነገራቸውና አሁን ደግሞ ቦታው ላይ እየተደረገ ያለው ነገር ተመልክተው ግራ እንደገባቸው ሲወያዩ ተስምተዋል፡፡

በተጨማሪ የመድሀኒዓለም ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት ቀን የቤተክርስትያኒቱ ሰንበት ተማሪዎች እያሉ እንዴት ከሌላ ቦታ ሰንበት ተማሪ ያመጣሉ? ተብለው የተጠየቁ ሲሆን ለዚህም “ማን እንዳመጣቸው እንደማያውቁ” መልስ ሰጥተዋል ፤ በጊዜው የነበሩ ምዕመናን የቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ሆነው ሳለ እንዴት ከየት እንደመጡ አላውቅም ይላሉ? ሲሉ ተሰምተዋል ፤ እነዚህ ሰንበት ተማሪዎች የማምጣቱ ሂደት ላይ የአቶ ጌታቸው ዶኒ እጅ እንዳለበት ለማወቅ ተችሏል ፤ በቤተክርስትያኑ ውስጥ የሚገኙ ሰንበት ተማሪዎች የእነሱን አላማ የሚቃወሙና የቦታን ተላፎ መሰጠት የማይደግፉ በመሆናቸው በዝማሬ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በቀኑ አልተፈቀደላቸውም ፤ በጊዜው የመጡት ሰንበት ተማሪዎች በደብረብርሀን መንገድ በሰንዳፋ በኩል ጨፌ ከሚባል አካባቢ እንደመጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሰባኪ ወንጌል (ቀሲስ ሐይለ እየሱስ) በሀሰት ፍርድ ቤት በመመስከራቸው መጀመሪያ ራስዎ ይማሩ ፤ ከዛ እኛን ለመስበክ ይምጡ ፤ አሁን ግን እኛን መስበክ አይችሉም ፤ አውደ ምህረት ላይም አይቁሙብን ብለዋቸዋል ፤

ይህ የቤተክርስትያን የቦታ ጉዳይ እንደ ቤተል ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ጉዳይ የሰው ህይወት እንዳይጠይቅ ብርቱ ጥንቃቄ ቤተክህነቱ እና መንግስት ቢወስዱ መልካም ነው ፤ ጥያቄዎች በጊዜያቸው መልስ አለማግኝታቸው ችግሩን ወደ ባሰ አቅጣጫ ስለሚወስደው ቀድሞ ሊጤን ይገባል ፤ በህዝቡ ላይ ህገወጥ ሆነው ህጋዊ ስራ እንደሚሰሩ የሚያስመስሉትን ለቤተክርስትያን ለህዝብና ለሀገር ሰላም ጠንቅ የሆኑትን እንደ አቶ ጌታቸውን የመሰሉ ሰዎች መንግስት ሀይ ይበላቸው …… በአንድ ሰው ምክንያት ሺዎች መበጥበጥና መታወክ መቻል የለባቸውም፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ምዕመኑ መከራን መሸከም የለበትም ፤ ችግሮች ተጠንተው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል


የቦታውን ጉዳይ በጥልቀት ለማንበብ ይህን ይጫኑ

“እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን”

6 comments:

  1. የሪዞርቱ ባለቤት አቶ ታዴዎስ ጌታቸው የጌታቸው ዶኒ ልጅ ናቸው እንዴ ስማቸው ስለተመሳሰለብኝ ነው፡፡

    ReplyDelete
  2. Leka Kahinat Getachew Doni Belu Meshar Atichilum Yih Yesinodos Siltsan New Beterefe Leka Kahinat Getachew Doni Lemin Yemedihane Alemn Bota Melkek Akatachew Minale Biyarfu Yemidiru Fird Bet Bisetsachew Yesemayu Fird Bet Nege Ale Yihinn Yiweku

    ReplyDelete
  3. ፈጣሪ የዶኒን ልብ ይመልስ፡፡ገንዘብ እንደሆነ ስር የለዉም፤ስር ግን ያሳጣል፡፡የገንዘብ ጣጣን ከይሁዳ መማሩ በቂ ነዉ፡፡ቤተክርስቲያኒቱ ስር ለገንዘብ የተሰማሩ ሰዎች በሙሉ እጃቸዉ ሳያጥር ወደ ሌላ የገቢ ማስገኛ ስራ ይሰማሩ፡፡የጌታ ቤት መነገጃ አይሆንም፤ሆኖ አያዉቅምና፡፡

    ReplyDelete
  4. ፈጣሪ የዶኒን ልብ ይመልስ፡፡ገንዘብ እንደሆነ ስር የለዉም፤ስር ግን ያሳጣል፡፡የገንዘብ ጣጣን ከይሁዳ መማሩ በቂ ነዉ፡፡ቤተክርስቲያኒቱ ስር ለገንዘብ የተሰማሩ ሰዎች በሙሉ እጃቸዉ ሳያጥር ወደ ሌላ የገቢ ማስገኛ ስራ ይሰማሩ፡፡የጌታ ቤት መነገጃ አይሆንም፤ሆኖ አያዉቅምና፡፡

    ReplyDelete
  5. ፈጣሪ የዶኒን ልብ ይመልስ፡፡ገንዘብ እንደሆነ ስር የለዉም፤ስር ግን ያሳጣል፡፡የገንዘብ ጣጣን ከይሁዳ መማሩ በቂ ነዉ፡፡ቤተክርስቲያኒቱ ስር ለገንዘብ የተሰማሩ ሰዎች በሙሉ እጃቸዉ ሳያጥር ወደ ሌላ የገቢ ማስገኛ ስራ ይሰማሩ፡፡የጌታ ቤት መነገጃ አይሆንም፤ሆኖ አያዉቅምና፡፡

    ReplyDelete
  6. Egziabher lebetechristian sewoch lib yistilin. Amen!

    ReplyDelete