Saturday, February 25, 2012

ባዕታ ለማርያም ሄጄ ይህን ተዓምር አይቼ መጣሁ


(የካቲት ኪዳነምህረት 2004 ዓ.ም)፡- ቀኑ እለተ አርብ የካቲት 16  ፤ ከስራ አምሽቼ  ብወጣም ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ሳልደርስ ወደ ቤቴ መሄድ አልፈቀድኩም ፤ በቦረና ጉርጂ ሊበን ዞን የተፈጠረውን ነገር እያወጣሁና አያወረድኩ ከ6ኪሎ ቁልቁል ወረድኩኝ ፤ ‹‹ምነው የእግዚአብሔር ዝምታው በዛ››  ‹‹ለምን በቃችሁ አይለንም›› እያልኩኝ መልስ የሌላቸው ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ለራሴው እየጠየኩ የቤተመንግስቱን አጥር አስታክኬ የአራት ኪሎ ቤተመንግስትን ዋርድያ በአይኔ ገረፍ ገረፍ እያደረኩ በጀርባ በር በኩል ባዕታ ለማርያም ግቢ ውስጥ ስደርስ አልታወቀኝም ነበር፤ በርካታ ምዕመን ግቢው ውስጥ ይታያል ፤ ግቢ ውስጥ የሚገኝው ምዕመን መሬት ላይ ቁጭ ብሎ የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማ አስተውሎ ለተመለከተው ውስጥን በሀሴት ይሞላል ፤ አኔም ከቦርሳዬ አንድ ወረቀት አወጣሁና መሬት ላይ አስቀምጬ ቁጭ አልኩኝ ፤ መርሀ ግብሩን የሚመሩት ልጀ እግር ካህን ‹‹ዛሬ የሚገርም የእመቤታችንን ተዓምር ትሰማላችሁ ፤ አንዱን ቀደም ብሎ የሰማችሁት ነው አሁን ደግሞ ሁለተኛው ተዓምር የተደረገላቸው እናትና ልጅ እዚህ አጠገቤ ይገኛሉ ›› ብለው የእመቤታችንን ተዓምር መናገር ጀመሩ ፤

ይህች የምትታያችሁ ልጅ የዘጠኝ ዓመት ህፃን  ነች ከጊዜ በኋላ በመጣ በሽታ ሩጣ ሳትጨርስ ቦርቃ ሳትጠግብ የአልጋ ቁራኛ ከሆነች ወራት ተቆጥረዋል ፤ እጇም ሆነ እግሯ ፓራላይዝ ሆኖ ከአልጋ ከተጣበቀጭ ሰንበትበት ብላለች ፤ 
ይህን ነገር አይደለም የራስ ልጅ ላይ ለመመልከት ይቅርና ለማሰብ የሚከብድ ሁኔታ ለቤተሰቦቿ ከባድና መሪር ሀዘን ነበር ፤ ከሁሉም አስበልጦ 9 ወር ከ 5 ቀናት በማህጸን ተሸክማ ላሳደገች እናት ደግሞ ይህን ሁኔታ መመልከት የከባድም ከባድ ነበር ፤ እናት ልጅቷን ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይዘዋት በመሄድ የበሽታውን ምንነት ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ ተስፋ አስቆራጭ ነበር ፤ ‹‹የዚች የ9 ዓመት ልጅ በሽታ የነርቭ ስለሆነ ድንገት በ21 ዓመቷ ሊሻላት ይችል ይሆናል›› ብለው የተለያዩ ምክንያቶችን ዶክተሮች አስቀምጠው አሁን ግን ተስፋዋ የተሟጠጠ መሆኑን ነገሯት ፤ መከረኛ እናት ልጅቷን ይዘው የነርቭ ሀኪም የተባለ ቦታ አንዳች ሳይቀራቸው ያላቸውን ገንዘብ ከመሀረብ በመፍታት ሊያሳክሟት እና ከበሽታው ሊያድኗት ሞክረው ነበር፡፡  ከመካከለኛ ክሊኒክ እስከ ሆስፒታል ድረስ መመላለሳቸው ገንዘባቸውን ከማሟጠጥ ውጪ ምንም የተረፋቸው ፤ ምንም ያገኙበት መፍትሄ አልነበረም ፤ 

እናት ተስፋ ቆርጠው ሳለ አንድ አባት መጥተው ‹‹ይህች ልጅ በፋኑኤል ጸበል ነው የምትድነው›› ብለው ነገሯት እናትም ምንም ጊዜ ሳይወስዱ እዛው ታእካ ነገስት ባእታ ለማርያም ግቢ ውስጥ የሚገኝውን ጸበል አንድ ብለው ማስጠመቅ ይጀምራሉ ፤ ዘወትር አባቶች ለሊት 10 ሰዓት ከኪዳን ሰዓት በፊት ጸሎት ያደርጉላት ነበር ፤ የእመቤታችንንም ታእምር ከተነበበ በኋላ ‹‹ፍቃድ ከሆነ ይችን ልጅ ማርልን›› እያሉ ሙሉ ሰውነቷን ይዳስሱላት ነበር ፤ ተስፋ ባለመቁረጥ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ሲያስጠምቋት የነበረችው ልጅ  በአንድ ወሯ በ16ተኛው ቀን  በኪዳነምህረት እለት ተጠምቃ ስትወጣ ወደ ሙሉ ጤንነቷ ልትመለስ ችላለች ፤ አናትየው ይህን ስትናገር እምባዋን እያፈሰሰች ነበር ፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ ከጓደኞቿ የለያት ይህ በሽታ ጊዜው ሲደርስ ድና ወደ ትምህርት ገበታዋ ልትመለስ ችላለች ፤ እናትየዋም እንዲህ ብላለች ‹‹ይህው እዚህው ግቢ በእመቤታችን አማካኝነት ነው የዳነችው ስለዚህ እሷን ታገልግል ብዬ ሰንበት ተማሪ አድርጌ አስመዝግቤአታለሁ ›› ብላ አነባች ፤   በቦታው የነበረው ምዕመን ‹‹አንድ ጊዜ እግዚአብሔርን አመስግኑ›› ሲባል ግቢው ታቦት የወጣ በሚመስል መልኩ በጭብጨባ በእልልታ ሶስት ጊዜ ግቢውን ድብልቅ አደረገው ፤ በመጨረሻም እናትና ልጅ ተያይዘው ወደ ማረፊያቸው አመሩ::

እኔ በበኩል በጣም ነው ደስ ያለኝ ፤ ለልጅቷ የተደረገላትም ምህረት ሳስበው ግርም አለኝ ፤ እኔንም ቦታው ላይ ሆኜ ይህን ተዓምር ለመስማት ስላበቃህኝ አምላኬን አመሰገንኩኝ ፤ አዎን ሲደረግልን ብቻ ሳይሆን የተደረገለትንም ማየት እርሱ ሲፈቀድ ብቻ ነው ፤ ይህን የመሰለ ተዓምር ከእምነቱ ውጪ ያለን ሰው ይስባል፤ በእምነቱ ውስጥ ያለውን ደግሞ ያበረታል ፤ 38 ዓመት ሙሉ በአልጋ ቁራኛ የነበረውን ሰው  ‹‹አንተን እልሃለሁ፥ ነተሣ፥ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ አለው።›› የሉቃስ ወንጌል524 ያለው ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ከእናቱ ጋር ከእኛ ጋር ስለመኖሩ ምንም ጥርጥር የለንም ፤ የዛሬ 2000 ዓ.ም የተደረገው ተዓምር አሁንም በቤተክርስትያናችን ፤ በጸበሉና በእምነቱ ምክንያት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

እኔ አሁንስ እመቤታችን ቃልኪዳን የተቀበለችበት ቀን ምንኛ የተመረጠች እንደሆነች ሳስብ እየገረመኝ እየመጣ ነው የዛሬ 2 ዓመት በዓለ ንግስ ላይ ታቦት ከመቅደሱ ሲወጣ የቀስተ ደመና ምልክት በሰማይ ላይ ክብ ሰርቶ ታቦቱ እስኪገባ ድረስ የነበረበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል ፡፡ አንገታችንን ወደ ኋላ ሰበር አድርገን ወደ ሰማይ ስንመለከት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ክብ ቀስተ ደመና፤ ወደ ፊት ስናይ ደግሞ የእግዚአብሔር መክበሪያ ታቦት ፤ ከዚህ በላይ ምን ምስክርነት አለ ? ዛሬ ደግሞ ሙሉ ሰውነቷ ፓራላይዝ የሆነች ህጻን ሙሉ በሙሉ ድና ለመመስከር በቃች ……..ነገስ? የነገ ሰው ይበለን………. እኔም ታሪኩን እንዳላዛባ በወረቀት አስፍሬ ለናንተው እንዲህ ባለህ ሁኔታ ለመጻፍ በቅቻለሁ (ይህም ምስክርነት ነው)..

ከዚህኛው ተዓምር በፊት ሌላ አንድ ነበር ፤ እኔ በእግሬ ስሄድ እሱ አምልጦኛል ፤ እሱ ደግሞ ከዚህም ይበልጥ ነበር ፤ ባላረፍድ አያመልጠኝም ነበር ፤ ይህችንም ላሰማህኝ ተመስገን ነው፤ 

መልካም ሰንበት ፤ቸር ሰንብቱ

27 comments:

  1. ይደንቃል:: ሳነበው የልጅቷን እናት እምባ አስብኩት:: ኪዳነምህረት ከልጇ ከወዳጇ ለኛም ምህረትን ትለምንልን::

    ReplyDelete
  2. ይደንቃል:: ሳነበው የልጅቷን እናት እምባ አስብኩት:: ኪዳነምህረት ከልጇ ከወዳጇ ለኛም ምህረትን ትለምንልን::

    ReplyDelete
  3. EGZIABHERE AMLAKE KIDUSE SEMU LE ZELALEM YIKEBERE YEMESGEN, YEMEBETACHEN AMALAJENET KEHULACHEN GAR YEHUN.

    ReplyDelete
  4. Egziabhere yrtemesegene yehun, Dingile yetewahedo enat.
    Kale Hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  5. እልል ብዬ ብጮህ ደስ ባለኝ! ሳነበው እንባዬን መግታት አቃተኝ "እግዚአብሄርን ስራህ ግሩም ነው በሉት" ምን ይሰጠው ለዚህ ቸርነት? ምግባር ባይኖረን መች ተወን? ወላዲተ ቃል ምን ብዬ ላመስግንሽ? ቃል ኪዳንሽ ፍጹም አንገት አያስደፋ ተመስገኚልኝ እማዬ ! ምህረትህን ያበዛህልን ቅዱስ እግዚአብሄር ስምህ ይባረክ! አሜን

    ReplyDelete
    Replies
    1. EGZIABHER AMLAK YETEMESEGENE YIHUN. YELIJITUA MEFEWES BETAM DES YILAL. ENEM AYNENE LE 4 AMET AMOGN YETEFEWESKUBET BOTA NEW BIZU TAMIRAT YEMISERABET BOTA NEW AMEN.

      Delete
  6. Betam new des yemilew,ke desta bizatm yasleksal,bebotaw tewat enem neberku betam bzu teamratochi neberu,yehonechi setm anid aynua bednget tefto emebete meskot lay tedegfa aynuan ashashita bertolatal,lersu min ysanewal.

    ReplyDelete
  7. እኔም በቦታው ነበርኩ እመሰክራለሁ አይቻለሁ ሰምቻለሁ….. በቀጣይም ሌላ ምስክርነት ነበር ከቻላችሁ እሱንም እንዲሰማ አድርጉ፡፡ ምህረት የምታሰጥ እናታችን፤ እመቤታችን !!!!!!!!

    ReplyDelete
  8. tamiruni le alemi nigeru diniki sirawini mesikiru yilalina antemi bezih wagani tagegnalehina desi yibelihi kale hiwotinim yasemalini!!! neger gini kezemenu atimaki neni bay atalayochi gar yeminiber sewoch eninika ladelew ina lamene bebeatu bizu mihiret alena lezemenu atimaki, berekeke tibebachew ena besiri bitesa lehayni 5birr lerasi mitati 10birr ... eyalu kibakidusi eyechebechebu kehosipitali yalitenanese keminegidubini enitenikeki(kidisiti afomiya,melaku kidusi mikahel negni yezarea ameti emetabishalehu bilo kezatebish seytani ladinish metahu bilo liyatalilat simokir yetali deme matebih bila dili bitinesawi bekuta liyatefati sinesa newi kidusi mikaheal yedereselati(yezareawochumi bilitochi teneka witu sibalu kegibiri abatachewi betemaruti mesereti begilitsi sayhoni besiwiri yasidebedibalu) kegna yemitebekewini enisira kerisu yemitebekewini yseral) yemiyabilechelichi hulu weriki adelemi ena wegenea nika fetari ema bezich 4 ameti enikuwani lijochuni beye sifirawi eyadane menafikuni ena ahizabuni leyito kesemay bemiweridi esati ketito alehu kemaleti mini yisiteni " SEYTANI ERASUNI YEBIRIHANI MELAKI ESIKEMIMESIL YILEWITALI TEKETAYOCHUMI ..." newi yetebalini wesibihati... yikoyeni!!!

    ReplyDelete
  9. emebeata lanchi men yesanshal? menem

    ReplyDelete
  10. Anchin yakebere Egziabher yikber yimesgen.1 kenem yenen lij Dingil be ekfsh endemitanorilgn mulu emnete new.yewsten tawkiyalesh'na.Lijen Enatenetshen atnefgytem Amnalehu

    ReplyDelete
  11. Anchin yakebere Egziabher yikber yimesgen.kentu yemihon baryashem 1 ken yenenem bilatena mireshilgn lijen be ekfsh endemitanorilgnena yale Enat endematiteyat amnalehu.Meche?zewoter kemenem belay yeminafkew ken new.DINGIL ADERA LIJEN MARILGN.Wogenoche Enem ye Enaten yemihret ken yeminafk hatyategna negn.betselotachihu lijen timrlign zend asbugn.

    ReplyDelete
  12. Yale woladit amlak amalajinet alem ayidinim yalutin abat astawosiku. Ergit new yale dingil MARYAM hiwot yelem. Dingilin enatu adirigo yemerete le egnam le dihinetachin meseret adirgo yeseten yabatochachin amlak kidus EGZIABHER ke enatu endihum ke kidusanu hulu gar yikber yimesgen Amen!

    ReplyDelete
  13. sanebew betam desblognel. mskrnetum legna bemedresu enamesgnalen

    ReplyDelete
  14. ለቅድስት ድንግል ማሪያም የሚሳን ነገር የለም

    ReplyDelete
  15. ወላዲተ ቃል ምን ብዬ ላመስግንሽ? ቃል ኪዳንሽ ፍጹም አንገት አያስደፋ ተመስገኚልኝ እማዬ ! ምህረትህን ያበዛህልን ቅዱስ እግዚአብሄር ስምህ ይባረክ! አሜን

    ReplyDelete
  16. meheretun ena chernetun kegna yalarake abat ....emebetachen zarem bemheretua tegobgnen

    ReplyDelete
  17. Dingel Mariam lehulachenim tamruan tadergelin

    ReplyDelete
  18. Tewodros N.
    ወላዲተ ቃል ምን ብዬ ላመስግንሽ? ቃል ኪዳንሽ ፍጹም አንገት አያስደፋ ተመስገኚልኝ እማዬ ! ምህረትህን ያበዛህልን ቅዱስ እግዚአብሄር ስምህ ይባረክ! አሜን

    ReplyDelete
  19. ክምር ይግባው አንችን ለሰጠን ለልጅሽ፤ ያዘኑትን የምታስደስት ቅድስት እናት።

    ReplyDelete
  20. Huliem Yikiber Yimesgen

    ReplyDelete
  21. ቢሮ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ነበር የማነበው እልልል ብዬ አመስግኛለሁ እመብርሃን እኛንም ትጎብኘን

    ReplyDelete
  22. ለቅድስት ድንግል ማሪያም የሚሳን ነገር የለም YIHIN BIBLE YIDEGIFAL WEY? LEMEBETACHIN YALEN FIKIR MINIM BIHON KE GOD KAL GAR MEGACHET YELEBETIM የሉቃስ ወንጌል 1፥37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ENGIDIH MANINI KEMAN GAR ENASITEKAKILALEN? ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። . . . ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች LUKAS 2 GOD YASIBEN

    ReplyDelete
  23. እግዚአብሔር ዝም አይልምምምምምምምም

    ReplyDelete
  24. Emebetachin medehanitachin....yelekisoachin adimach...yewunet enatachin hulem be hatsiyat bininor enkuwan tanuren

    ReplyDelete
  25. እመቤታችን የዋልድባንና ሌሎችን ገዳማት ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ አይታ መፍቴ እንድትሰጠንና በልዩ ተአምሯ በዙሪያችን ያለዉን ፈተና ታስወግድልን! አሜን!

    ReplyDelete
  26. "እግዚአብሄርን ስራህ ግሩም ነው በሉት" እመብርሃን እኛንም ትጎብኘን

    ReplyDelete