- የታሰሩ ክርስትያኖች ፍርድ ቤት ቀርበው 11 ቀን የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸዋል
- የዋስ መብታቸው ተነፍጓቸዋል ፤ የማህበረ ቅዱሳን ታፔላ ተለጥፎባቸው የታሰሩት ይበዛሉ (አባል መሆን ያሳስራል እንዴ?)
- እስረኛ መጠየቅም ያሳስራል ፤ ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ ነገሮች እየሄዱ ይገኛሉ
በጊዜው በፖሊስነት የተመደቡት የፖሊስ አባላት ፕሮቴስታንቶች እና ሙስሊሞች ሲሆኑ ቤተመቅደስ ውስጥ ከነጫማቸው በመግባት ቀሳውስቱን እና ዲያቆናቱን በዱላ እየወገሩ ሲያስወጧቸው እንደነበር ለማወቅ ችለናል ፤ አብዛኛው ክርስትያን እስር ቤት የገባው የማህበረ ቅዱሳን አባል ናችሁ ተብለው የማህበሩ ታፔላ ተለጥፎባቸው ነው ፡፡ የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆን የሚያስጠይቅበት ቦታ ሆኗል ፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ ይህ ሁኔታ እንደሚፈጠር ያወቁት ተሀድሶያውያን ከማረሚያ ቤት ፖሊሶች ጋር ቅዳሜ እና እሁድ ሻይ ቡና ሲሉ ከርመዋል ፤ መቼስ ሻይ ቡና እያሉ ስለ ጤንነታቸው እንደማያወሩ እርግጠኞች ነን ፤ እኛ የምንፈልገው ጉዳዩ በአግባቡ ገለልተኛ በሆኑ ፤ ጉዳዩ ላይ እጃቸውን ባላገቡ አካላት እንዲጣራልን ብቻ ነው፡፡ ቤተክህነቱም ጉዳዩን ጉዳዬ ብሎ ይያዘው የሚል መልዕክት አለን ፤ የአካባቢው ክርስትያን በሁኔታው ክፉኛ ልቡ ደምቷል ፤ ህግ አለመኖሩን በአካባቢው ፖሊስ መመልከት ችለዋል ፤ የሚጠቡ የልጆች እናት እህቶቻችንም በእስር ላይ ይገኛሉ ፤ እውነት እኛ ጋር ነው ምንም አንሆንም ፤
ጉዳዩ እዚህ ደረጃ ደረሰበት መንገድ………..
አቡነ ሳዊሮሰ የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት ጳጳስ ሆነው እንደተሾሙ በጊዜው ነገሮች ሁሉ በጎ ይመስሉ ነበር ነገር ግን ቆየት ብሎ እነ አቶ በጋሻውንና መሰል የተሀድሶ አቀንቃኝ ባልደረቦቻቸውን በማስመጣት በእግዚአብሔር ስም የሚጠራበት ፤ ታቦቱ ወጥቶ ምዕመኑን የሚባርክበት ቦታ ላይ አባቶችን፤ ህዝቡንና ቤተክርሰቲያኒቱን ማሰደብና ማስዘለፍ ጀመሩ፡፡ ህዝቡም በአብዛኛው ቅር ሲሰኝ ጥቂቶቹም የሳቸው ተባባሪ መሆን ቀጠሉ፡፡ በተለይ አዲስ በመገንባት ላይ ያለው የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲን ህንጻ አሰሪና ሰበካ ጉባኤ ኮሚቴ (ሁለቱንም ስራ ከህግ ውጭ ለሰባት አመት እየሰሩ የቆዩ)፣ የርሳቸው ጭፍን ደጋፊ ሆነው ተገኙ፡፡ ህዝቡም ሁኔታውን አይቶ እንዳላየ ባለማለፍ ማጉረምረሙን ቀጠለ፡፡ ይህ ሆኖ እያል ሳዊሮስ በግንቦቱ ሲኖዶስ ዝውውር ጠይቀው ወደ ወሊሶ ተመደቡ ፤ (አሁንም እዚያም እያመሱት ነው ፡፡)
እርሳቸው ከመነሳታቸው አንዳንድ መረጃዎች መውጣት ጀመሩ፡፡ ከሀገረማርያም ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለካህናት ማሰልጠኛ ብለው በርካታ ብር ወስደው በባንክ ቁጥራቸው ማስገባታቸው ተነገረ፡፡የገቢ ወጪ የባንክ ደረሰኝም ተገኘ፡፡ በተመሳሳይ ከሻኪሶ ወረዳም በሰማቸውና በሾፌራቸው ስም ገንዝብ መውሰዳቸው ታወቀ፡፡ አስቡት ራሳቸው የበሉት አልበቃ ብሏቸው በሹፌራቸው ስም የባንክ ቡክ በመክፈት ወደፊት የሚመጣውን ጥያቄ ለመሸሽ የቤተክርስትያን ብር የደረሰበትን ደብዛውን ለማጥፋት ይህን የመሰለ ሴራ ሰሩ ፤ ያን ጊዜ ይህ መረጃ የደረሰው ህዝብ ሆ ብሎ ተነሳና የቤተክርስትያንን ገንዘብ እንዲመለስ ጠየቀ ፤ ገንዘባችንን ይመልሱ ብሎ ደወለ አስደወለ ፤ ውጤቱ ግን ምንም ነበር፡፡ በወቅቱ ስራ አስኪያጅ የነበረው መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተክለማርያም (ዲ/ን) የስላሴ ኮሌጅ ተመራቂ ህዝቡን ወክሎ ጥያቄውን ለጠቅላይ ቤተክህነት አቀረበ፡፡ የማይነካ ነገርም ነካ፡፡ ወዲያው ከሃላፊነቱ ተነሳና ወደ አዲስ አበባ ተዛውሮ በሆነ ማተሚያ ቤት ውስጥ እንዲሰራ ደብዳቤ ደረሰው፡፡ ሌላ ስራ አስኪያጅም መመደቡ ተነጋረ፡፡ ፤ ለዝርፊያ የሚመች ሌላ ሰው ከወደ ወላይታ አካባቢ ብቅ አለ (አቶ ተሾመ ሓይለማርያም) የሚባል፡፡ ይህ ሰው ለኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን ንግስ እንዳይኖር ፤ ቅዳሴ እንዳይቀደስ ከ40 በላይ ሰዎች እንዲታሰሩ ፤ ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡
ሕዝቡም የጉዳዩ አመጣጥ ስለገባው (የአቡነ ሳዊሮስ ሴራ እንደሆነ ተረዳ ፤ ሳዊሮስና አባ ጳውሎስ በጣም ወዳጅ ናቸው)፡፡ በዚህ ወቅት አባ ሳዊሮስ ሲዛወሩ የቦረና ሃገረ ስብከት በአዋሳ ላይ እንዲደረብ ተደርጎ ነበር እናም ይህ ጉዳይ ሲነሳ፤ ወዲያው ሐገረ ስብከታችሁ ከባሌ ጋር ተዳምረዋል ተባለ፡፡ በዚህ ጊዜ ባሌ ራሱ ጳጳስ አልነበረውም አቡነ ዮሴፍ ከአውሮፓ አልመጡም ነበር፡፡ ስለዚህ ሆን ተብሎ የሚናገር አባት እንዳይኖረ የተደረገ ስልት ነበር፡፡
ሕዝቡም ነገሩ በገባው ቁጥር ይበልጥ አመረረ፡፡ አንድ ስራ አስኪያጅ የሃገረ ስብከቱ ጰጰስ ለሲኖዶስ ሳያቀርብ አይሻርም አይሾምም፡፡ ስለዚሀ ውሳኔው የቤተክርስቲኒያቱን ስርዓት የጠበቀ ስላልሆን አንቀበልም አለ ፤ ህገ ቤተክርስትያን ሲጣስ እያየን እጅ እና እግራችን አጣጥፈን የምንቀመጥበት ቦታ የለንም ፤ ይህች ቤተክርስትያን የሁላችን ናት ፤ እኛም እንደ ምዕመን ያገባናል ይመለከተናል አለ፡፡ ነገሮች እየከረሩ ሲሄዱ ነገሩን ረጋ ለማድረግ ሽማግሌዎች በህዝቡ መራጭ አማካኝነት ተመረጡ ፤ አዲስ አበባ ከአቡነ ጳውሎስ ዘንዳ ፤ ከጠቅላይ ቤተክህነት ነገሩን አስረድተው መልስ ይዞ ለህዝቡ ለማምጣት ቃል ገብተው ወደ አዲስ አበባ አቀኑ ፤ ከአዲስ አበባ ሲመለሱ ግን ምንም መፍትሄ አላመጡም ነበር ፡፡ የቀድሞው ስራ አስኪያጅም እንዳያስረክብ ህዝቡ አዘዘ፤ ከዚህ በኋላ አቡነ ፊሊጶስ ጠበቃ ቀጥረው ስራ አስኪያጁ በህግ ተከሶ ንብረት እንዲያስረክብ ፍርድ ቤት አቆሙት ፤ ፍርድ ቤትም ሚዛናዊ ያልሆነ ፤ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ውሳኔ ወሰነ ፤ የአካባቢውም ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ በምጣት ውሳኔውን በይፋ ተቃወመ ፤ ከአቅም በላይ በሆን ምክንያት (ሽማግሌዎቹ ከመንግስት ከፍተኛ ግፊት ነበረባቸው) ንብረት ርክክብ ተደረገ፡፡ በኋላ ግን አንድ ጥሩ ነጥብ ተገኘ፡፡ ፍርድ ቤት ንብረት እንጂ ስልጣን አረካክብ አልተባልኩም አለ ፤ ንብረቱም ተመልሶ ለሃገረ ስብከቱ ንብረት ክፍል እንዲገባ ውሳኔ ተሰጠ ፤ አዲሱ ስራ አስኪያጅ ግን ቢሮ እንዳይገባ ህዝቡ አገደ፡፡ የሃገረ ስብከቱ ሰራተኞች ደመወዝ ግን ታገደ፡፡
በዚህ መካከል አቡነ ዮሴፍ ከአውሮፓ መጥተው ባሌንና ቦረናን ደርበው ማስተዳደር ጀመሩ ፤ ህዝቡም ዘንድ ቀርበው ቀድሞ የነበረውን ችግሩን ተረዱ፡፡ ለጠቅላይ ቤተክህነት ደብዳቤ ጻፉ ፤ የቀድሞው ስራ አስኪያጅን መርጫለሁ አሉ ፤ የነበረውን ደመወዝም ውዝፍ ከፈሉ፡፡ ህዝቡ እልል አለ፡፡ እልልታው ግን ብዙም አልቆየ ነገሮች ተለወጡ፡፡ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሆነና ቦረና ሐገረ ስብከት ሌላ ጳጳስ ተመደበለት ከአሜሪካ (አቡነ እዎስጣቴዎስ) እርሳቸውም ሳይመጡ ቀሩ፤ ሃገረ ስብከቱም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ አባት ቀረ፡፡ እኛ ግራ የሚገባን ነገር አባቶች ከሀገረ ስብከት ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ሲመደቡ ቶሎ ስራ የማይጀምሩበት ሁኔታ ነው ፤ ለምን ይሆን? በጊዜው የተመደቡበት ቦታ ላይ ደርሰው ስራ ካልጀመሩ መጀመሪያውኑ መመደቡ ለምን አስፈለገ ?
በዚያን ጊዜ ህዝቡም ከኪሱ ገንዘብ እየከፈለ ለሃገረ ስብከቱ ሰራተኞች ደመወዝ እየሰጠ መስራትን መረጠ፡፡ ለ7 ዓመት ህንጻ አሰሪና ሰበካ ጉባዔ ሆነው ሲበሉና ሲያበሉ የነበሩትን በተመረጡት ሽማግሎዎች አሳሳቢነት አውርዶ ሌላ መረጠ (በቃለ አዋዲው መሰረት ህንጻ አሰሪና ሰበካን በመለያየት)... ትግሉ ግን እየቀጠለ ነው፡፡( የቀድሞው የቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ገባኤ ባንክ ሂሳብ በአቡነ ዮሴፍ ተዘግትዋል፡፡ አዲሱ ስራ አስኪያጅ በአቡነ ፊሊጶስ በኩል ከብሄራዊ ባንክ ደብዳቤ አጽፎ ቢመጣም ህዝቡ ፊርማ በማሰባሰብ ለነጌሌ ቦረና ንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ በማስገባት የብሄራዊ ባንክ ደብዳቤን ማሳገድ ችሎ ነበር)፡፡ አሁን አዲሱ “ስራ አስኪያጅ” ከመንበረ ጵጵስና ውጭ በመሄድ ሌላ ወረዳ ላይ ጽህፈት ቤት ከፍቻለሁ ብሎ ስራ ጀምርዋል፡፡ የራሱን ማህተምም በኪሱ ይዞ እየዞረ ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ ህዝቡ አሁን በዚህ ጉዳይ ባለው መረጃ መሰረት ይህን ህገወጥ ግለሰብ ለመክሰስ እየተዘጋጀ ነው፡፡
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከመጀመርያ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ያሉትን ዋና ዋና የደብዳቤ ልውውጦች ስካን አድርገን ለተሟላ መረጃ ለእርስዎ እናቀርብሎታለን፡፡
በሌላ በኩል የእኛን ስም ካላነሱ መጻፍ ያቃታቸው ይመስል አንዳንድ ድህረ ገፆች ከማህበረ ቅዱሳን ጋር የሚደባልቁን ወንድሞቻችን አሉ፤ የእነሱን ስራ መስራት መቻል በየትኛው እድላችን ነው ፤ ለበጎ ስራው አይደለም ማህበሩን እናንተም ጥሩ ስራ ብትሰሩ ረዳቶቻችሁ ነን ፤ ወንድማችሁ እንጂ ጠላቶቻችሁ አይደለንም ፤ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እኛ የማህበሩ አባል አይደለንም ፤ ማህበሩ ትልቅ ማህበር ነው ፤ እኛ ስለ ቤተክርስትያን ግድ የሚለን ጥቂት የቤተክርስትያን ልጆች ነን ፤ ማህበርም አይደለንም ፤ ማህበሩ ስለ ራሱ የሚናገርበት የራሱ ድህረ ገፅ አለው ፤በዮሐንስ ወንጌል 3፤11 ላይ ‹‹የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን›› ይላል ፤ ሐዋርያት ሥራ 4፤ 20 ላይ ደግሞ ‹‹እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም›› ይላል ፤ ስለዚህ እኛ ስለ ቤተክርሰትያን ዝም ማለት አንችልም ፤ እናንተ የምትሄዱበት መንገድ መጨረሻውን ስትደርሱ ታውቁታላችሁ፡፡ እኛን ማመስገንም ሆነ መስደብ ከፈለጋችሁ ‹‹አንድ አድረገን›› ብቻ ብላችሁ መጻፍ ትችላላችሁ ፤ ይህ እውነት ሆኖ ሳለ ባልሰሩት ስራ ፤ ግራ ክንፍ ፤ ቀኝ ክንፍ ፤ የማህበሩ ድህረ ገፅ ፤ ብሎግ እያላችሁ ስም አትስጡን ፡፡ምዕመኑ የተሻለ መረጃ እንዲኖረው ፍላጎታችነን ነው ፤ በሰሚ ሰሚ ሳይሆን የተጨበጠ ፤ ‹‹አንድ አድርገን›› ፈጣን ፤ ተዓማኒና ለማንም ሳይሆን ለቤተክርስትያን ወግና ትሰራለች ፤ ያልሆነ ስያሜ እየለጠፋችሁብን ሰዎች ዘንድ ድንግዝግዝ ያለ ነገር አትፍጠሩ ፤ እኛን ራሳችንን ውቀሱን ፤ እኛኑ ስደቡን ከሌሎች ጋር አንድ ላይ በማድረግ መደፍጠጡን ተዉ
Andadirgen....edmena tena yistachihu..biyans hizibu benante bekul enkiuan yitenfis
ReplyDeletebetam enamesegnalen yeh guday bedebub kilel addis ayedelem bealefut 2 ametat hawassa lay men endeneber bekreb yenebern enawkewalen .hawassa lay aschegari fetena behonm yemaheberu abalat huket setfetru sayehon hizbun setatenanu tenelketenal enam zarem bezih bota yetefeterew huket botawn keyere enji addis ayedelem enam zarem yetelemedewn behariachuhen bemantebarek yechin betechristian tadeguat.cheru egzihabher tinatun yesten
ReplyDeleteእናመሰግናለን ሌላ ቢዙ ማለት እንችላለን ነገር ግን ለእግዚአብሄር ህዝብ ይህን ያህል በቂው ነው፡፡ ለመጨመር ያህል ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ማመልከቻ ይዘው የሀዱት ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ 10 (አስር) ሲሆኑ የሄዱትም ከ 5 ወረዳዎች ማለትም ከነጌሌ፣ ከሻኪሶ፣ ከሀገረማርያም፣ ከአዶላ (ክብረመንግስት)፣ እና ከ ያቤሎ ነው፡፡ መለከቱትም ጭብጥ ነገር በአጭሩ 1) ሀግ ስብከታችን የሚባርክ አባት ይመደብለት 2)አቡነ ሳዊሮስ ያለአግባብ ከሀገረ ስብከቱ የዘረፉት ገንዘብ እንዲመልሱ ይደረግ (ከሀገረ ማርያም ከሀያ ሺህ (›20000) ብር በላይ፣ ከሻኪሶ አርባ ሺህ ብር (›40000)፣ ከሞያሌ አስር ሺህ ብር (10000) እንዲሁም ሌሎች በድምሩ ከሰባ ሺህ 70000 ብር በላይ እና 3)ያለ አግባብ ከስራው የተነሳው ሥራ አስኪያጅ አግባብነት ባለው መልኩ መጣራት ይደረግበት፡፡ የሚሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን አቡነ ጳውሎስ ይህንን የተውጣጣ ኮሚቴ በታላቅ ትህትና ካናገሩ በኋላ ለኔ ተውት ና ወደ ሀገራችሁ ሂዱ እኔ አጣርቼ መፍትሄ አደረጋለሁ በማለት ኮሚቴውን በሚያሰገርም እና የኮሚቴውን አባላት በሚያስደምም ሁኔታ ሸኝተውታል. ነገር ግን ያለምንም መፍትሄ ጉዳዩ ሲዘገይ ይሄው ስብስብ በድጋሚ መፍትሄ ይሰጠን የሚል ማመልከቻ ይዞ ወደደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቢመጣም ብጹህ አባታችንን ማግኘት ሳይችል በመቅረት ለመመለስ ተገዷል፡፡
ReplyDeleteበዚህ መሀል ነው እንግዲህ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ብተክነት ስራ አስኪያጅ ተደጋጋሚ ደብዳቤ በመጻፍ የሀገረ ስብከቱ መታወክ ላይ እሳት የማቀጣጠል ስራ እየሰሩ የሚገኙት፡፡ይህንን የምለው ማንኛውም ጉዳይ ላይ የሳጨው እጅ (ፊርማቸው) ያረፈብት ደብዳቤ ነበርና ነው፡፡
ዛሬስ፡፡ ነጌሌ እና ሻኪሶ በህዘቡ እና ለዚህ ጉዳይ በተመረጡ ሰዎች በአንድነት መንቀሳቀስ የተረጋጉ ይመስላሉ ውስጥ ውስጡን እሳቱ እንዳለ ቢሆንም፡፡ ሀገረ ማሪያም ምን ላይ እንዳለ ምንም ዐይታወቅም፡፡ ያቤሎ ጸጥ ያለ ነው፡፡ ሌሎች ወረዳዎች ከበፊት ጀምሮ ምንም ውስጥ እንደሌሉ ጉዳዩን በአርምሞ እየተከታተሉ ያሉ ይመስላል፡፡ ነገር ግን አዶላ (ክብረ መንግስት) የቡድን በሚመስል እንቅስቃሴ በእነ ተስፋዬ መቖያ (ከአሜሪካ ሆኖ የሚጫወተው እና በዛሬው ጉዳይ ላይም እጁ ሙሉ በሙሉ ያለበት የተሀድሶአውያን አቀንቃኝ) መሪነት በጊዜው ተመደበው የነበሩትን ሊቀ ጳጳስ (አቡነ ዮሴፍ የናቀ ማለትም ያለሳቸው ፍቃድ) ጉባዔ ከማዘጋጀት ጀምሮ ከ ቄስ ዝናቡ (የሚካኤል አስተዳዳሪ) እና ከ ቄስ ሰለሞን (የጉዳዩ ዋና አቀንቃኝ) ጋር በማበር ህዝቡን የማተራመስ ስራ በመስራት ልይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም በወረዳው ያሉ አንዳንድ ባለስልጣናት በሚያደርጉላቸው ጉርሻ በመታለል ትብብር እያደረጉላቸው ያሉ ይመስላል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆን በዛሬው ዕለት በቄስ ዝናቡና በተስፋዬ መቆያ (ከአሜሪ) መሀክል የስልክ ንግግር ከተደረገ በኋላ ለአንድ ተባበሪ ግለሰብ ምናልባትም በጊዜው የተደረገውን ስራ ያስተባበረ ስልጣን አለኝ ባይ ደካማ የተሰጠውን የታሸገ ስጦታ ለማየት ችለናል፡፡
እንግዲህ ም እንላለን; እግዚአብሄር ቤተክርስቲያንን እና በንጹህ ልቡና የሚያመልኩትን አይተውምና ምናልባትም የኛ ሀጥያት ለዚህ ዳርጎን ከሆነ በንጹህ ልቡና እና ከሀጥያት እስከመጨረሻው ርቀን እንቅረበውና ሁሉንም እንዲያስተካክልልን እንለምነው፡፡ እሱ ለቤቱ ከማንም በላይ ያስባልና ቤቱንም ዕኛንም ይጠብቅን፡፡ ለሁላችንም የንስሐ እድሜን ያድለን፡፡ ለወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ይህን መከራ ለበጎ ነው ብለው እንዲወስዱ ልቡናውንእና ጽናቱን ይስጥልን፡፡
አምላካችን ኢትዮጵያን እና ቤተክርስቲያናችንን ይባርክ!
may we know how to contribute to this blog, because i have all the letters and attachnents (soft and hard copy) submitted to the "teklay bete kihnet', 'sinid', and 'the patriarch office' at hand, so that you can see, edit and if you fill important post them. i am saying this for the sake of genuine christianity not to blackmail individuals. thanks
ReplyDeletemelekam new buden kelelachew,ewent sele meseqelu kehone edih yemetehonut,Amlak yeredachew
ReplyDeleteDear Andeadregen God bless u guys
ReplyDeleteAs this two big brothers are good friends what we expect from them just full stop, we what it followed just pray to Almighty GOD.
ሕዝቡም የጉዳዩ አመጣጥ ስለገባው (የአቡነ ሳዊሮስ ሴራ እንደሆነ ተረዳ ፤ ሳዊሮስና አባ ጳውሎስ በጣም ወዳጅ ናቸው)
ነገር ግን አዶላ (ክብረ መንግስት) የቡድን በሚመስል እንቅስቃሴ በእነ ተስፋዬ መቖያ (ከአሜሪካ ሆኖ የሚጫወተው እና በዛሬው ጉዳይ ላይም እጁ ሙሉ በሙሉ ያለበት የተሀድሶአውያን አቀንቃኝ)
GOD BLESS U ANDADRGEN KEEP DOING YOUR MARVELOUS JOB
እኛ ስለ ቤተክርስትያን ግድ የሚለን ጥቂት የቤተክርስትያን ልጆች ነን
እኔ ምንም አልልም ብቻ እግዚአብሔር አገግሎተችውን ይባርክ። እበካችው የማንንም ወሬ አትስሙ ስለ ቤተክርስቲያናችንም ለመናገር ወደ ኋላ አትበሉ። እግዚአብሔር አምላከችን ቤተ ክርስቲያናችንን ይጣብቅልን ከማለት ሌላ ምን እላሌው። ሁሉም የእጁን ያገኛልና።
ReplyDeleteውድ ክርስቲያኖች የዚይህ ጉዳይ ዋናው አነሳሽ አቶ ተስፋዬ መቆያ ነው:: እኔ ነገሩን በደንብ ሰምቻለሁ በቦታው ላይ ከነበሩት እህቶቼ ላይ:: ይህ የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ስለሆነ ስም ማጥፋት ተደርጎ እንደማይታይ ተስፋ አደርጋለሁ:: ከሁለት ወር አካባቢ በፊት አሁን ተሃድሶ የተባሉትን ዘማሪዎች ይዞ ጉባኤ በ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካሂዷል እኔ ይህንንም ያድርግ ወንጌል የጠማው ህብረተሰብ ስላለ ጥሩ ነው የዛን ጊዜም ጸብ ተነስቶ 4 ቀን እሱ እራሱ ታስሯል :: ግን ይሄ ሁሉ አልነበረም ለአሁኑ 40 ሰዎች መታሰር ምክንያቱ የአንድ ስላሴ ቤክ ሚያገለግል ግለሰብ ባለቤትና የ አቶ ተስፋዬ ባለቤት ግጭት ነው :: በዚህ ውስጥ ደግሞ አቶ ተስፋዬ ይገባል እናም ብዙ ነገር ተደራርሰው ነበር እሱን መዘረዘር አያስፈልግም በዚህ ምክንያት አቶ ተስፋዬ ሰራላቸዋለው እያለ እየዛተ ነበር ወደዚህ(ወደ አሜሪካ) የተመለሰው ያው ሀሳቡ ተሳካ ማለት ነው:: ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ እነዛም ግለሰቦች ከቤተክርስቲያን ስለማይጠፉ ተበቀላቸው ማለት ነው :: እውነቱን ልንገራችሁ አቶ ተስፋዬ መቆያ ይህ ግጭት እንደሚመጣ ስለሚያውቅ ለባለቤቱ ደውሎ ልጆቹን ይዛ ከቤት እንዳትወጣ አርጒል::
ReplyDeleteእነዛ ግለሰቦችም ጋር ጥፋት በደንብ አለ ለምን ብትሉ በግላቸው ቂም በቀል ለመወጣጣት ነገሩን ወደ ቤክ ይዘው ቤተክርስቲያንን ሽፋን አድርገው ቂም መወጣጫ ማድረጋቸው::
እኔ አሁን ዋናው ነገር መናገር ምፈልገው እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው የአስመሳዮች የበቀለኞች አምላክ አይደለም :: ቤተክርስቲያንም የዚህ ማስፉጻሚያ ቦታ አይደለችም::
እባክህን እባክህን እባክህን ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ሞገስ እግዚአብሔር እየተናገረህ ነው : እባክህን ድንግል ማርያም እየተናገረችህ ነው እስኪ ለመስበክ ከመነሳትክ በፊት እራስህን ለጥቂት ደቂቃ ቁጭ ብለህ መርምረው እውነት እኔ እራሴ የመድሀኒቴን ቃል ሰምቼዋለሁ በል ይህንን ስል ሌላም ብዙ ምሰማቸው ነገሮች ስላሉ ነው:: እመብርሃን ጣእሟን ታሳድርብህ ያሳደገህ ቅዱስ ሚካኤል ይርዳህ ሁሉም ነገር ሚሆነው እርሱ ሲረዳን ብቻ ነው ሰው በራሱ ደካማ ፍጡር ስለሆነ::
ለሁላችንም የንስሐ እድሜን ያድለን::
'ውድ ክርስቲያኖች የዚይህ ጉዳይ ዋናው አነሳሽ አቶ ተስፋዬ መቆያ ነው' can we take the person commenting this is orthodox Christian ? how a Christan talks without evidence ? how a an orthodox say one kesis ATO ? who gave you to degrade Gods servant ? If he made msitakes only the church can take the 'Kesis' status ? Lemangiawim yhe kante aytebekim
Deleteabet mewenejajel andim eko silegudayu kelibu yazene yelem binorima somina selot yaweji neber erasum betun zegto yiseliy neber .yehi hulu yehatyatachim mebzat new hulum wederasu biyay min ale?
ReplyDeleteAnde Adiregen,
ReplyDeleteI don't think you need to tell for your readers that you are not pro MK blog. What you should do is just show that you are not supporting any group by providing balanced and non hatred information. The bible also says 'you shall know them by their deeds'...so you better walk the walk than talk the talk.
Dear Andadiregen,
ReplyDeleteDo you think it is morally acceptable (forget about christian behavior ) to publish comments that are directly attacking individuals specially that are serving the church without any acceptable evidence ?