Monday, February 20, 2012

የአባቶች እርቀ ሰላምና እንቅፋቶች

ESAT ጊዜውን ያላገናዘበ እና ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ


(አንድ አድርገን ፤ የካቲት 12 2004ዓ.ም)፡- ይህ ዘገባ አሁን እየተካሄደ ያለውን እርቀ ሰላም መፍትሄ አልባ እንዲሆን ሆን ተብሎ የተሰራ ስራ ይመስለናል፡፡ እኛ አቡነ ጳውሎስ ቤተክርስትያናችን ላይ ምንም ያላደረጉ ፃድቅ አባት ናቸው እያልን አይደለም ፡፡ ነገር ግን ካለሁ ሁኔታ አኳያ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት የአንድነታችን ጉዳይ ነው ፡፡ አንድነታችን መስመር ካስያዝን በኋላ ሌላው ውስጣዊ ጉዳይ ይሆናል ፡፡ የዛሬ 20 ዓመት የተሰራ ስህተት አለ ፤ የዛሬ 10 ዓመት ገደማም የተሰራ ስህተት አለ ፤ በ1998 ዓ.ም ጭምር እምነቱን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ ህዝቡ ያሰማው ተቃውሞ አለ ፤ በቅርብም አባቶቻችን ላይ የተቃጣ ጥቃት ሁላ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ቢከናወንም መሰረታዊው ነገር ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ መምጣታቸው ይመስለናል ፤አክንባሎ ላይ የተቀመጠችውን አይጥ ለመግደል ብለን ትልቁን አክንባሎ ላይ አደጋ በሚያደርስ መልኩ መሰንዘር የለብንም ፡፡ይህን ያለፈውን ነገር ወደ ኋላ እየሄዱ ነገሩን እየቆሰቆሱ ከ20 ዓመት በኋላ ማቅረብ ግን ምዕመኑንም ሆነ ለሰላም መስፈን ፤ ለእርቀ ሰላም ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ የተንቀሳቀሱት አባቶች ላይ ተፅህኖ ያሳድራል፡፡ ያወራችሁትን ወሬ(ዜና እንበለው?ESAT : ዜና ትንታኔ - News Analysis 17 February 2012 )  በኢንተርኔት 5ሺህ ሰው አየውና መረጃውን በአለም ላይ የሰዎች ቀልብ የሳበ በመሆኑ ሰዎች እየተከታተሉት መሆኑን አስረግጣችሁ መናገርም አትችሉም ፤ የፖለቲካ ዜና አድማጩም ፤ የገባውም ፤ ያልገባውም ፤ ግራ የገባውም ሰው ዩቱብ ላይ ከፍቶ ስላየ በአለም ዙሪያ ያለ ሰው እየተከታተለ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ለምሳሌ የእኛን ብሎግ በቀን ከ4ሺህ እስከ 6ሺህ ሰው በአማካይ ይመለከተዋል የሚል ማስረጃ የመረጃ ቋታችን ይነግረናል ፤ ይህ ማለት ብዙ ሰው ይመለከተዋል ብለን መደምደም የሚያስችል ቁጥር ግን አይደለም ፤ በአለም ላይ 5ሚሊየን ሰዎች በቀን የሚጎበኙት ብሎግ እንዳለም ማወቅ አለባችሁ ፡፡ እነሱ እንኳን አፋቸውን ሞልተው መናገር አልቻሉም፡፡ ነገሮችን ሁላ አንፃራዊነታቸውን ሳታዛቡ  ብትዘግቡ ጥሩ ነው እንላለን፡፡

የእኛ ችግራችን የእኛው ስለሆነ ለቀቅ አድርጋችሁን እናንተም የፖለቲካ ስራችሁን ብታጣድፉ የሚሻል ይመስለናል ፤ አሁን ላለንበት ችግር ተጠያቂዎች ላይ እጃችን መጠቆም የመፍትሄ አካል ነው የሚል እምነት የለንም ፤ እንደ እናንተ ያለው ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ ፤ ህዝብ አባቶቻችን ላይ የተለየ አቋም እንዲኖረው ፤ ክብራቸውን በአደባባይ ዝቅ ሲያደርግ የሚያሳይ ዘገባ ለእኛ እና ለያዝነው የአንድነት እርቅ ላይ ጥቁር ነጥብ የሚያሳርፍ ቢሆንም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለሆነ የሚያመጣው ከፍተኛ የሆነ ተፅህኖ ፤ ሰላሙን የሚያስተጓጉል ነገር አይታየንም፡፡ ጊዜ ሊወስድ ይችላል አንድ መሆናችን ግን የማይቀር ነገር ነው፡፡

መንግስትን መቃወም ሌላ አጀንዳ ነው ፤ ነገር ግን መንግስትን ለመቃወም ሲባል ቤተክርስትያናችን ላይ ያለውን ብልሹ አሰራር ፤ ሙስና ፤ አድልዎ ፤ በደል አንስቶ ሀሳብን ለራስ በሚያመች መልኩ እየጠመዘዙ ነገሩን ወደ ሌላ አቅጣጫ መውሰድ ሌላ ነገር ነው፡፡ አቡነ ጳውሎስ ምንም ያህል አንዲት ቤተክርስትያን ላይ በደል ቢሰሩም እንኳን ለሰሩት ስራ ተጸጽተው ንስሀ ቢገቡ እግዚአብሔር መሀሪ አምላክ ነው እና ንስሀቸውን እንደሚቀበላቸው አንጠራጠርም ፤ እግዚአብሔር ልቦናቸውን ወደ መልካም ነገር እንዲመልስ ለሀገርም ሆነ ለቤተክርስትያናችን መልካም ስራ ሰርተው እንዲያላፉ ፤ ለሰሩት ስራ የንስሀ እድሜ እዲጨምርላቸው በጸሎት አምላካችንን መጠየቅ እያለ ሰዎች ልባቸውን እዲያደነድኑ ፤ የይቅርታ ልብ እንዳይኖራቸው ለማድረግ የሚሰራውን መጪውን ያላገናዘበ ስራ እንደ  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ  እምነቱ ተከታይ አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉ አባቶች ከአዲስ አበባ ይህን በጎ ሀሳብ አንስተው እርቀ ሰላም ለማምጣት ማሰባቸው ብቻ የሚያስመሰግናቸው ስራ ሆኖ ሳለ ከስብሰባው በፊት ፤ የሚወያዩበት አጀንዳ ሳይታወቅ አይሆንም አይደረግም ፤ በፍፁም አይሳካም ብሎ ማሰብ ከቅን ሰው የሚጠበቅ አካሄድ አይደለም፡፡ ስብሰባው በአንድ ለሊት ታስቦ እና ታቅዶ የተከናወነ አለመሆኑን እኛ ከማስረጃ ጋር ልናቀርብልዎት እንችላለን ፤ ይህ ስብሰባ ከመታሰቡ በፊት ለረዥም ወራት ያህል ቅድሚያ የተሰሩ ስራዎች በሁለቱም ሲኖዶሶች በኩል ነበሩ ፤ ለምሳሌ ያህል በጥቅምት 2004 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አባቶች በጉባኤ አንስተው የተነጋገሩበት አጀንዳ አንዱ ይህ እርቀ ሰላም ነበር ፤ ከአዲስ አበባ ወደ አሪዞና ያቀኑት አባቶች የተመረጡትም በቀደምት የቅዱስ ሲኖዶስ  ጉባኤ ላይ ነበር፡፡ ይህ የሚሄዱበት ቀንም የተቆረጠው ቀድሞ ከወራት በፊት ነበር ፡፡ አሁን ላይ ደርሶ የመጣ ዱብዳ ነገር አይደለም፡፡ እናንተ ይህን ጉዳይ ቀድሞ አለማወቃችሁ ጉዳዬን አዲስ ያደርገዋል የሚል እምነት የለንም፡፡

ይህችን ቤተክርስትያን ከአባቶቻችን የተቀበልናት አንድ ሆና ነበር ፤ አሁን በእኛ ዘመን ሶስት ቦታ ተከፋፍላ ትገኛለች ፤ ታዲያ ከአባቶች የተቀበልነውን ቀኖና ፤ ዶግማ ወደ መጀመሪያው እንመልሰው ፤ ቀኖና ተሸሯል ፤ ማን እደሻረ እንነጋገር እና መተማመን ላይ እንድረስ ፤ ለወደፊትም የመፍትሄ አቅጣጫ እናስቀምጥ ፤ የአቡነ ጳውሎስም ሆነ ከእሳቸው በፊት ያለ አግባብ ስለተነሱት ፓትርያርክ ጉባኤ ሰርተን እንወያይ ማለት የቱ ጋር ነው ክፋቱ ? ሰው ስለመታረቅ ሲያስብ እኛ ልናግዘው ሀሳቡን ልንደግፈው ይገባናል እንጂ ፤ ልዬነታቸውን ልናጠብ መስራት ሲገባን መረጃ ስላለ ብቻ መረጃው ይሄ ነው መታረቅ የለብህም ማለት ተገቢ መስሎ አይታየንም፡፡ ይህች ቤተክርስትያን ዛሬ እኛ በእድሜአችን ካየነው የባሰ ችግር ውስጥ የነበረችባቸው ጊዜያት ያላለፉ መስሎ የሚታየን ሰዎች አለን ፤ እውነታው ግን በጣም በርካታ ጊዜያት ፈተናዎች አጋጥመዋት በአሸናፊነት ተወጥታችዋለች ፤ የግራኝ አህመድ ወረራ ፤ የዮዲት ጉዲት ዘመን ፤ 8000 ኦርቶዶክሳውያን በአንድ ቀን ሀይማኖታችንን አንቀይርም ብለው በሰማእትነት ያለፉበት ጊዜያት ከዋና ዋናዎቹ የፈተና ዘመናት በዋነኝነት የሚጠቀሱት ናቸው፡፡ ይህም ለእኛ ፈተናችን ነው እግዚአብሄር የፈተና መውጫ ቀዳዳ እንደሚያዘጋጅልንም እናውቃለን፡፡ አሁን ላይ ያለውን መለያየት ወደ አንድነት ማምጣት ብንችል ፤ ለአንድነታቸው የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማከናወን ብንችል ከታሪክ ተጠያቂነት እና ከህሊና ተወቃሽነት የምንድነው እኛው ነን ፤ ይህን ሀላፊነት ሳንወጣ ብንቀር የታሪክ ተወቃሽ ፤ የህሊናም ሰላም የምናጣው እኛው እራሳችን ነን፡፡ ቤተክርስትያን ግን ቃል እስከተገባላት ፤ እንክርዳዱ ከስንዴው የሚለይበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ሳትናወፅ ፀንታ ትቆያለች፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ያለ ሁለ ሀገሩን ይወዳል ማለት አይደለም ፤ አቡነ ጳውሎስን ሌባ ሌባ ያለ ሁላ እሱ ንፁህ ሰው አይደለም ፤ እንደ ኢሳት ያለ ተቃዋሚ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሁላ ደግሞ እውነተኛ ነው ማለትም አይደለም ፤ የመንግስት ተቃዋሚ ሁላ  ይችን ሀገር ወደ ተሻለ የእድገት አቅጣጫ ይወስዳታል ማለትም አይደለም ፤ ስለዚህ በቤተክርስትያን ውስጥ ተገኝተው አቡነ ጳውሎስ ሲሰድቡ ብታሳዩን እኛ እሳቸውን እናንተ እንዳላችኋቸው አንላቸውም ፤ መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል

‹‹ እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን። ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።›› የማቴዎስ ወንጌል 7፤ 1-5 

ስለዚህ የእናንተን አዛኝ ቂቤ አንጓች ዘገባችሁን አንሰማም ፤ ስለ አንዲት ቤተክርስትያናችን ብለን ችግሮችን በብልሀት እንፈታቸዋለን ፤ አይጧን ለመግደል አክንባሎውን አንሰብርም ፤ የስድስት ኪሎ ሀውልት በጣሊያን ወረራ ጊዜ በግፍ ለተገደሉ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን እናት አባቶቻችን የቆመ መታሰቢያ ሀውልት ነው ፤ እናንተ ደግሞ ከሀውልቱ ባልተናነሰ መልኩ ይህች ቤተክርስትያን አንድ እንዳትሆን እንደ ሀውልቱ ቆማችሁባታል ፤ ስለዚህ ዘወር በሉላት ፤ ወሬ መፍትሄ ሲሆን አይተን አናውቅም፡፡


ከወራት በፊት በተሀድሶያውያን ማር ላይ የተቀመጠ መርዝ ቤታችን ውስጥ ይዘው በመግባት ምዕመኑን ግራ አጋብተውት ነበር ፤ ብዙ ደጋፊ እንጂ ያመነ ክርስትያን ባላፈሩበት ሁኔታ እሾህ ሆነውብን ነበር ፤ ይህም ፈተናዋ ነበር ፤ ነገር ግን ጊዜ እውነትን ለያዘ ሰው ፈራጅ ነውና በአሁኑ ሰዓት ከበፊቱ ጋር ስናወዳድረው አንፃራዊ ሰላም በቤተክርስያናች ላይ ሰፍኖ ይገኛል ፤ እነዚህ ሰዎች ተገለሉ ማለት አበቃላቸው ተመልሰው አይነሱም ማለት አይደለም ፤ እንደ ክርስትያን እግዚአብሔር ወደ ልቦናቸው እንዲመልሳቸው የምዕመኑ ፀሎት ሊሆን ይገባል ፤ ነገር ግን ከፀሎት ጋርም ቢሆን ነቅተን ቤተክርስትያናችንን ከመጠበቅ ለአፍታ ያህል መዘናጋት የለብንም ፤ ‹‹ ‹‹እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ ››ነው የሚለን መፅሀፉ፡፡ የአባቶቻችንንም ጉባኤ መሳካት እንደ ክርስትያን እንጂ እንደ ፖለቲከኛ ማሰብ የለብንም ፤ ኢሳት አለን ከምትሉት መረጃ በላይ እኛ ደግሞ አስር እጥፍ በላይ አለን ፤ የጽሁፍ ፤ የድምፅ ፤ የቪዲዮ ሌላም ፤ መረጃው ፍርድ ቤት ይዞ መሄድም አቅቶን አይደለም ፤ ነገር ግን እሳቱን ለማጥፋት እንደ ውሀ የተጠቀምንበት መንገድ ውሀው ቤንዚል ስለሚሆን ለማውጣት አልወደድንም ፤ ይህን መንገድ ብንከተል ሌላ ችግር እንፈጥራለን እንጂ ለቤተክርስትያንም ሆነ ለሀገር ሰላም እንፈጥራለን ብለን አናስብም ፤ መረጃ ቢኖርም አጠቃቀሙን ካላወቁበት ጉዳቱ ስለሚያመዝን አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ይመስለናል፡፡ የ1998 ዓ.ም የመስቀል አደባባይ ችግር ሰፊ እና ብዙ መነሻ ሀሳቦች ስላሉት እዚህ ላይ ምንም ማለት አንፈልግም፡፡



እኔ አንድ የምለው ነገር አለኝ እንደ ኢቲቪ ሚዛናዊ ያልሆነ የዜና ማሰራጫ የለም ፤ በአይናችን ያየነውን ፤ በቦታው ተገኝተን የተሳተፍነውን ስብሰባ ኢቲቪ ላይ መልኩን ቀይሮ ሲመጣ በጣም ይገርመኛል ፤ እነሱም የሚዋሹበት አላማ አላቸው ፤ 21 ኢንች ቴሌቪዥን በእነሱ ውሸት ተሸማቆ 14 ኢንች መሆኑን በቀልድ መልክ ሰምተን ልንስቅበት እንችላልን ፤ ይህ የሚያሳየው ማህበረሰቡ  በኤሌክትሮኒክ ሚዴያዎች ላይ ምን ያህል እምነት እንዳጣ እና ለማመንም እንደሚቸገር ጭምር ነው፡፡ አሁን እናንተም ከጀርባችሁ እንደ ኢቲቪ አላማ አስቀምጣችሁ ማህበረሰቡን ሚዛናዊ ባልሆነ ዘገባ ፤ መፍትሄ የማይሆንን አሳብ ዘወትር እያመጣችሁ አታደንቁሩት ፤ ቤተክርስትያናችን ለምታካሂደው አንድነት ጉባኤ እንቅፋት አትሁኑብን ፤ ካቀረባችሁ ሚዛናዊ የሆነ ሁለቱንም ወገን ያማከለ ፤ መፍትሄ ሊሆን የሚችል ፤ ተዓማኒነት ያለው ዘገባ ብታቀርቡ መልካም ነው ፤ ያለበለዚያ ለአላማችሁ ማሳሄጃ የቤተክርስትያንን ጉዳይ እንደ ጥይት አትጠቀሙበት፡፡

ለማህበረሰብ ግን ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ ማቅረብ በህግም የሚያስጠይቅ ተግባር ነው ፤ ኢሳት በመሰረቱ የመንግስት ተቃዋሚ ጣቢያ ነው ይህን እናውቃለን ፤ ብዙም ሰው በውጩ አለም እንደሚከታተለው እናውቃለን ፤ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ገዥ ፓርቲውን ለመቃወም ሲባል የቤተክርስትያናችንን ስም በሆነውም ባልሆነውም ቦታ ከቶ የወሬ ማጣፈጫ ማድረግ ተገቢ ነው አንልም፡፡ ይህች ቤተክርሰትያን አንድ ብትሆን የመጀመሪያ ተጠቃሚ ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ናት ፤ የቤተክርስትያን አንድነት ለሀገር አንድነት ጥቅም እንዳለው ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ የአድዋ ጦርነት ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ ብትመለከቱ ጥሩ መረጃ ይሰጣችኋል ብለን እናምናለን ፤ በጊዜው ሰው ለሀገሩ እና ለቤተክርስትያኑ ብሉ ሲዘምት በሊቃነ ጳጳሳት እና አባቶቻንን ከጦርነት ካልተመለሰ ተብሎ የቁም ፍትሀት ተደርጎ ነበር ሀገርን ለማስከበር ፤ ህዝብ ላይ የሚመጣውን አደጋ ቀድሞ በመመልከት ፤ ለሰማዕትነት ወደ ጦር ሜዳ ሲጎርፍ የነበረው ፤ እግዚአብሔርም ሀገሪቱን ሳያሳፍራት ጠላትን ከእግራቸው በታች እንዲንበረከክ አድርጎላቸዋል፤ የአድዋ ጦርነት ጊዜ የቤተክርስትያናችን አስተዋፅኦ እንዲህው በቀላሉ ፅፈን የምንጨርሰው ጉዳይ አይደለም ፤ ለድሉ መበርከት የአንበሳውን ድርሻ የምትወስደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ናት ፤ ይህ ድል የመጣው በጊዜው የነበረው አንድነታችን ነው ፡፡ አሁንም ለቤተክርስትያን ትንሳኤ አንድነታችንን ለእኛም ለሀገርም እንናፍቀዋለን ፤ ታዲያ አሁን ላይ አንድ እንዳንሆን የምትፈልጉ እናንተ ማን ናችሁ ? ለሚመጣው ትውልድስ ምን ልታስረክቡት ነው አንድነታችን ላይ ጣት የምጠቁሙት ? እኛ ለልጆቻችን በሰው ሀገር ተቀምጠው የመንግስት ተቃዋሚ ሆነው እንዲያድጉ ፍላጎታችን አይደለም ፤ ሀገር አለን ፤ ህዝብ አለን፤ እምነት አለን ፤ አንድ የሆነችን እምነት የቤተክርስትያንን ትምህርት ተምረው ለራሳቸው ፤ ለቤተሰባቸው ፤ ለአካባቢያቸው ፤ ለሀገራቸው ጥሩ ዜጋ ሆነው እንዲያድጉ ነው የምንፈልገው ፡፡ የእኛን ጥፋታችንን ከነ በጎ ስራችን መማሪያ ይሆናቸው ዘንድ መንገር ነው የምንፈልገው ፤ ከእኛ ስህተት ተምረው እነርሱም አደራ ተቀብለው የቤታችን ቀኖና እና ዶግማ ለመጪው ትውልድ እንዲያስተላልፉ እንፈልጋለን ፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ አንድ መሆናችን ግድ ነው፡፡

በሌላ በኩል አዲስ አበባ ውስጥ በየ15 ቀኑ የሚታተሙ መፅሄቶች አንዱ የሆነው ‹‹ላይፍ›› መፅሄት መረጃዎችን በትክክል ሳይቀበል ግራቀኙን ሳይመለከት ‹‹ የሁለቱ ሲኖዶሶች ጉባኤ ያለ ስምምነት ተበተነ›› የሚል ዘገባ አውጥቷል::

‹‹ጊዜ ሊወስድ ይችላል እግዚአብሔር አንድ እደሚያደርገን አንጠራጠርም››  
አንድ አድርገን 

አንዲት ፡ ቅድስት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያንን ፡ በሚመለከት ፡ ዕለት ፡ በዕለት ፡ የሚታየዉ፦ - የውስጥና ፡ የውጭ ፡ ችግር ፡ - አደጋና ፡ የወደ ፡ ፊት ፡ ስጋት ፡ ምን ፡ እንደኾነ ፡ ኹሉም ፡ የእናት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ልጆች ፡ እንዲያውቁት ፡ የበኩላቸውንም ፡ መፍትሔ ፡ እንዲፈልጉ ፡ ሐሳብ፡ እንዲሰጡ ፡ በክርስትናቸው ፡ የሚጠበቅባቸውን ፡ ሓላፊነት ፡ እንዲወጡ ፡ የክርስቶስን ፡ መስቀል ፡ ለመሸከም ፡ የማይሰቀቅ ፡ ክሣደ ፡ ኅሊና ፡ ኖሯቸው ፡ ለስብከተ ፡ ወንጌልና ፡ ሐዋርያዊ ፡ ተልእኮዋ ፡ መሳካት ፡ ለህልውናዋ ፡ መጠበቅና ፡ ለፍጹም ፡ አንድነቷ ፡ እንዲነሡ ፡ የምታተጋ ፡ ዐውደ ፡ ምጽሓፍ ፡ ወመስተሳትፍ ፡ ናት ።


18 comments:

  1. egziabeher yebarekachehu bezihu qetelubete

    ReplyDelete
  2. Thanks! Mot LE ETHSAT ena cifn gazeTegnochu!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  3. እባካችሁ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ፖለቲካን የምታራምዱ አካላት ተቆጠቡ ዘወርም በሉልን፡፡ እግዚአብሔር አንድ ያድርግልገን ያደርገናልም!!!!!
    አንድ አድርገኖች በርቱ
    Esu Becherenetu Ethiopian yitebikat!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  4. ቀሲስ ገብረ ኢየሱስFebruary 20, 2012 at 5:56 AM

    አንድ አድርገኖች ፦ ላመሰግን የምችልበት ቃላት የለኝም:: እግዚአብሔር ይስጣችሁ:: አገራችን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ አስተዳደር እንድትመጣ ከፍተኛ ሥራ ይሰራል ብለን ተስፋ የጣልንበት የኢሳት ቴሌቪዥን ቤተ ክርስቲያናችን አንድ እንዳትሆን የሚያደርገውን ሙከራ ስመለከት አገሪቱንም አንድ የሚያደርግ ሥራ መስራቱን እንድጠራጠር አድርጎኛል::ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት በአንድም በሌላም መንገድ የአገር አንድነት ነውና :: እባካችሁ አባ ጳውሎስን ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኗን ተመልከቱ በማታውቁት ገብታችሁ ከእግዚአሔርም ከሰውም ጋር አትጣሉ:: እናንተ ፖለቲከኞች ናችሁ :ምናልባት እርቅ ከመጣ በስደት የሚገኙ አባቶችና ቤተ ክርስቲያኗ ወደ ኢትዮጵያ ከተቀላቀሉ መንግሥትን የመቃወሚያ መድረክ እና ደጋፊ እናጣለን ብላችሁ ከሆነ የዜጎችን ድምጽ በትክክል ማሰማት እስከ ቻላችሁ ድረስ እንኳንስ በስደት አገር ቤት ያለው ዜጋ ከእናንተ ጋር ይሆናል;:ብቻ እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያኗ ላይ አንሱ !!:: አንድ አድርገኖች በድጋሜ እግዚአብሔር ሥራችሁን ይባርካችሁ::

    ReplyDelete
  5. Bepoletikaw yemitakerbuten netasa asteyayet alfo alfo binadenkewem ahun gin linetelachehu new. Bela minim yezachehu atimtu anifeligim. It is shame on you ESAT.

    ReplyDelete
  6. ሥንታየሁ ጌታቸው (italy)

    እንዴት ብዬ እንደምገልጸው ከብዶኛል ሚዛናዊ አቀራረባቹ ነገር ግን አንድ ነገር ልበላቻሁ ቃለ ህይወት ያሰማቹ ,,,, እግዚአብሔር ያክብራቹ::


    ,,,አሁንም ለቤተክርስትያን ትንሳኤ አንድነታችንን ለእኛም ለሀገርም እንናፍቀዋለን ፤ ታዲያ አሁን ላይ አንድ እንዳንሆን የምትፈልጉ እናንተ ማን ናችሁ ? ለሚመጣው ትውልድስ ምን ልታስረክቡት ነው አንድነታችን ላይ ጣት የምጠቁሙት ? እኛ ለልጆቻችን በሰው ሀገር ተቀምጠው የመንግስት ተቃዋሚ ሆነው እንዲያድጉ ፍላጎታችን አይደለም ፤ ሀገር አለን ፤ ህዝብ አለን፤ እምነት አለን ፤ አንድ የሆነችን እምነት የቤተክርስትያንን ትምህርት ተምረው ለራሳቸው ፤ ለቤተሰባቸው ፤ ለአካባቢያቸው ፤ ለሀገራቸው ጥሩ ዜጋ ሆነው እንዲያድጉ ነው የምንፈልገው ፡፡ የእኛን ጥፋታችንን ከነ በጎ ስራችን መማሪያ ይሆናቸው ዘንድ መንገር ነው የምንፈልገው ፤ ከእኛ ስህተት ተምረው እነርሱም አደራ ተቀብለው የቤታችን ቀኖና እና ዶግማ ለመጪው ትውልድ እንዲያስተላልፉ እንፈልጋለን ፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ አንድ መሆናችን ግድ ነው፡፡

    ReplyDelete
  7. Ene Ende EPRDF hageritun legud yetale Ende Aba Paulos Betekirstianin yawared be Ethiopia meriwoch tayito ayitawokim biye aminalehu.Neger gin Ende ESAT yale worada ena hizibin lemasawok min metekem endalebet yemayawuk gena enchich yehone degimo yale ayimesilegnim. Yemiadergutin yemayawuku nachew.

    Endihum ene dejeselam yemesaselutin andandie yemayastelulu honew aginichachewalehu. bezih zegeba layi huletum tifategnoch nachew.

    ReplyDelete
  8. it's a great article. God bless your service Andadirgen.
    BUT, ESAT, please don't interfere in church issues, you are politician, we need fathers to be united by any means, we know how much we are terribly in trouble because of their separation. The only means is to forgive each other according to God's word, not by politician word.
    Especially, Sisay, you are highly interfering without thinking the consequence that would come for future generation. please please just go with your politics ...if you need to be positive thinker for the church come with taking out your politics shoes.

    Cher Yaseman

    ReplyDelete
  9. Thanks for the critical and rational analysis of the scene. Dear brothers & sisters in Christ,let us take this fasting as an opportunity to pray for the oneness of our church. God is so kind that he will answer our question in the upcoming peace agreement. Let our Virgin Blessed Mary be with us in her prayer too!!! Amen!Amen! Amen!

    ReplyDelete
  10. ቀሲስ፡ገብረ፡ኢየሱስ፡እግዚአብሔር፡ይባርክህ፡ቁልጭ፡አድርገህ፡አስቀምጠህዋል፡፡ኢሳቶች፡ለኢትዮጵያ፡መቆርቆራችሁ፡ ስህተት፡አይደለም፡ግን፡መሰረቷ፡እኮ፡ተዋህዶ፡ሃይማኖቷ፡ነው፡፡መሰረት፡ፈርሶ፡ቤት፡እንደማይቆም፡ልትገነዘቡ፡ይገባል፡፡ አንድ፡አድርገን፡እግዚአብሔር፡ብርታቱን፡ይስጣችሁ፡ይባርካችሁ!!!

    ReplyDelete
  11. Dear Andeadregen

    What a response.... Good on you guys I am proud of you , You are the ever true sons and daughters of Ethipian Orthodox Tewahedo. Keep doing ur marvelous job may GOD bless u all.


    አንድ አድርገኖች ፦ ላመሰግን የምችልበት ቃላት የለኝም:: እግዚአብሔር ይስጣችሁ:: አገራችን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ አስተዳደር እንድትመጣ ከፍተኛ ሥራ ይሰራል ብለን ተስፋ የጣልንበት የኢሳት ቴሌቪዥን ቤተ ክርስቲያናችን አንድ እንዳትሆን የሚያደርገውን ሙከራ ስመለከት አገሪቱንም አንድ የሚያደርግ ሥራ መስራቱን እንድጠራጠር አድርጎኛል::ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት በአንድም በሌላም መንገድ የአገር አንድነት ነውና :: እባካችሁ አባ ጳውሎስን ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኗን ተመልከቱ በማታውቁት ገብታችሁ ከእግዚአሔርም ከሰውም ጋር አትጣሉ:: እናንተ ፖለቲከኞች ናችሁ :ምናልባት እርቅ ከመጣ በስደት የሚገኙ አባቶችና ቤተ ክርስቲያኗ ወደ ኢትዮጵያ ከተቀላቀሉ መንግሥትን የመቃወሚያ መድረክ እና ደጋፊ እናጣለን ብላችሁ ከሆነ የዜጎችን ድምጽ በትክክል ማሰማት እስከ ቻላችሁ ድረስ እንኳንስ በስደት አገር ቤት ያለው ዜጋ ከእናንተ ጋር ይሆናል;:ብቻ እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያኗ ላይ አንሱ !!:: አንድ አድርገኖች በድጋሜ እግዚአብሔር ሥራችሁን ይባርካችሁ::

    ReplyDelete
  12. ኢሳቶች አሁን እኛ የምንፈልገው አንድነትን ነው እኛም ይህ አልጠፋንም ድግሞ አናንትም በተክርስቲያናቸንን መጠቀሚ አታድረጉ እንሰማቸሁም የፖለቲካውን በፖለቲካ አትቀላቀቅሉ እንደዚህ ከሆናቸሁ እናንተንም በጥርጣሬ ነው የምንመለክት ደግሞስ እንነት እነማንቸሁ..አኛ የአቡነ ጰውሎስ ስራ አልጠፋንም ግን ምፍተሄው ቅድሚያህ የምንፈልገው እነድነትን ..ከዛሌሎቸህ የሰተካክለሉ ብእግዚአበሔር ቸርነት ግን እናነተ ፖለቲካቹህን ወደ ቤተ ክርሰቲን ኣታምጡብን

    ReplyDelete
  13. Egiziabiher yibarikachihu andadirigenoch beritu amilak yiridachihu
    kalehiyiwet yasemalin bilenal!!!!!!

    ReplyDelete
  14. ሌላ የምላቸህው ነገር የለም ቁልጭ፡አድርጋቸሁ፡አስቀምጣቸህዋል አንድ፡አድርገን፡እግዚአብሔር፡ብርታቱን፡ይስጣችሁ፡ይባርካችሁ!!! በርቱ በርቱ
    from eth.jimma

    ReplyDelete
  15. "የእኛ ችግራችን የእኛው ስለሆነ ለቀቅ አድርጋችሁን እናንተም የፖለቲካ ስራችሁን ብታጣድፉ የሚሻል ይመስለናል"...የድንቁርናችሁን ልክ የሚያሳይ አባባል። ይገርማል በጣም። ደግሞ እኮ ያለማፈራችሁ አንድነትን የሚሰብክ ከኛ ወዲያ ማለታችሁ። የድንቁርና ጥግ....

    ReplyDelete
  16. ላመሰግን የምችልበት ቃላት የለኝም!!! Good job. Please keep on responding in a such manner (well articultated and unbaised).

    Zebra

    ReplyDelete
  17. ኢሳት የዘገበው እውነት ነው ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ምን አይነት የሰላም ውይይት ይደረጋል በራሳቸው ህግ የሚሄዱ እግዚአብሔርን ሳይሆን መንግስትን መከታ የሚያደርጉ ቤ/ክን ለማፍረስ ታጥቀው የቆሙ ደራጎን ናቸው ከደራጎን ጋር ደግሞ ምንም አይነት እርቅ አይሳካም፡፡

    ReplyDelete