Friday, November 29, 2013

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰ



 
(አንድ አድርገን ጥቅምት 19 2006 ዓ.ም)፡- ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ላይ ከሰሜ ሆቴል ወደ ጊዮርጊስ ቁልቁል ሲሄድ የነበረ አንድ ከባድ የጭነት ማመላለሻ(SINO TRUCK)  መኪና ባጋጠመው የፍሬን ችግር ምክንያት ሹፌሩ መኪናውን መቆጣጠር አቅቶት ቀጥታ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጽርን ደርምሶ በመግባት ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፡፡  በወቅቱ በቦታው ላይ በእቅልፍ ላይ የነበሩ ሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የሆነ አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ከፍተኛ አደጋ የደረሰባቸው ሶስቱ ሰዎች ወዲያውኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና አካባቢው ላይ ባሉ ሰዎች ጥረት ራስ ደስታ ሆስፒታል ተልከው ጊዜያዊ እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል ፡፡ በአደጋው የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር እና ግንብ ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሲሆን በተጨማሪ ሰው በፍርስራሽ ውስጥ ይኖራል ተብሎ በመገመቱ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሹን የማንሳት ስራ ሲያከናውኑ ተስተውሏል፡፡ የደረሰው አደጋ አሰቃቂ መሆኑን በቦታው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡

ከአደጋው በኋላ የመኪናው ሹፌር በሰጠው ቃል መሰረት የመኪናው ንፋስ እምቢ በማለቱ አደጋው የደረሰ መሆኑን ተናግሯል፤ በአሁኑ ሰዓት  ፖሊስ የመኪናው ሹፌር ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

Friday, November 22, 2013

የእነ በጋሻው ጉዳይ ወደ እርቅ እያመራ መሆኑ ተገለጸ

(አንድ አድርገን ህዳር 12 2006 ዓ.ም )፡- ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ በሃዋሳ ፤ ዲላ እና ሌሎች አካባቢዎች ሁከት በማስነሳትና በሃይማኖት ህጸጽ በህዝቡ በተነሳባቸው ጥያቄ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ ደርሶ የነበረው የእነ በጋሻው ደሳለኝ ጉዳይ በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመጨረሻ እልባት እንዲሰጠው በተወሰነው መሰረት ሶስት ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን ሲያጠና ከቆየ በኋላ በእርቅ ለመቋጨት የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረሱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
 
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን አጣርተው የመጨረሻ እልባት እንዲያበጁለት የተመረጡት  ብፁዕ አቡነ  እስጢፋኖስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘካናዳ እና  ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለዚህ እርቅ መነሻ የሆነው 21/2/06 በቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በጋሻው ደሳለኝና ያሬድ አደም በብፁዕ አቡነ ገብርኤል እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቃቸውና አቡነ ገብርኤልም ‹‹ይቅር ማለት የአባት ስርአት ነው›› ብለው ቅርታውን መቀበላቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በእለቱ እርቁን መጠየቅ እንደሚፈልጉና ይቅርታውንም ለመጠየቅ ሶስት በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ከአዋሳ እንዲጠሩላቸው ስም ጠቅስው በጠየቁት መሰረት የተባሉት ሶስቱ የሀገር ሽማግሌዎች ተጠርተው 27/02/06 .  ይቅርታ የጠየቋቸው ሲሆን ሽማግሌዎችም እንደ ግለሰብ ይቅርታውን ለመቀበል እንደማይቸገሩ ጠቅሰው፤ ነገር ግን አሁን በሕዝብ ተወክለን ስላልመጣን በሕዝብ ስም ይቅርታውን መቀበል እንደማይችሉ በጊዜው ገልጠውላቸው ነበር፡፡

Thursday, November 21, 2013

ዐረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።


ከኃይለሚካኤል፥ ኅዳር ፱ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም.

ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት ዐረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ፣ መዲና ወዘተ ተብለው ይጠሩ በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። ዐረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት  ወይም የእደ ጥበብ ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ አስተዳደር  የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር።[1] ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር።[2] ጣዖት አምላኪዎችም ነበሩ።  ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር። እስከ አራት መቶ ዓ.ም. አካባቢ ዐረቦች ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር ግጥም መፎካከር   የዐረቦች ባህል ነበር።[3] እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። ዐረቦች ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።

Wednesday, November 20, 2013

እነ በጋሻውን በእርቅ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ ይገኛል



(አንድ አድርገን ህዳር 11 2006 ዓ.ም)፡-
  • ግራ ቀኙን ያማከለ ውይይት በሀዋሳ ተካሂዷል ተብሏል
  • የእርቅ ጉባኤውን ሶስት ሊቃነ ጳጳሳት መርተውታል፡፡
  • ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ከሲኖዶስ የተወከሉ ናቸው፡፡
  • ‹‹ከእውቀት ማነስ አስተማሩ እንጂ የሃይኖት ህጸጽ ተገኝቶባቸዋል የሚያስብል ስራ አልተገኝባቸውም›› አባቶች የተናገሩት
  • ይዘው የወጡትን ሰዎች ይዘው እንዲመለሱ ጉባኤው ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡
  • የዕርቅ ስራው እየተሰራ የሚገኝው በፌደራል ጉዳዮች ተጽህኖ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ ፡፡
  • ‹‹ወይ በእርቀ ሰላም ቀላቅሏቸው ወይም የእምነት ፍቃድ እንስጣቸው›› የፌደራል ጉዳዮች አቋም
  • በቤተክርስቲያኒቱ ከሰበካ ጉባኤ ውጪ በሰንበት ትምህርት ቤት ፤ በልማት ጉባኤ ሁለት ሁለት ሰዎች እንዲመድቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
  • በዚህ መልኩ ዕርቁ እንዲከናወን ለ28/03/2006 ዓ.ም ጊዜያዊ ቀጠሮ ተይዟል፡፡
እስኪ ይጠብቁን

Saturday, November 16, 2013

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው

  • ‹‹ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ›› መዝሙረ ዳዊት 82 ፤ 3


(አንድ አድርገን ህዳር 08 2006 ዓ.ም)፡- መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ከ300 በላይ በየጎዳናው ወድቀው የነበሩና የተረሱ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያንን በተለይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን አረጋውያንን ከወደቁበት ጎዳና ፤ ከተረሱበት ቦታ በማንሳት በአዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት አጠገብ  መጠለያ አዘጋጅቶ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ለመንከባከብ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

Friday, November 15, 2013

የ2005 ዓ.ም የቤተክርስቲያኒቱ ሀገራዊ ገቢ አንድ ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ተጠጋ




(አንድ አድርገን ህዳር 6 2006 ዓ.ም )፡- ዐዋጅ ነጋሪ ተብሎ ጥቅምት 2006 ዓ.ም በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ  የተዘጋጀው መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር በሀገር ውስጥ ብቻ  የሚተዳደሩ 50 የሀገረ ስብከቶች ጠቅላላ ገቢ የሚያሳይ መረጃ ይዞ ወጥቷል፡፡ በሰባካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የወጣው ስታስቲክሳዊ መረጃ   የእያንዳንዱን አህጉረ ስብከት የ2005 ዓ.ም የዘመኑን ገቢ ያሳያል፡፡ እንደ መረጃው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በገቢ መጠን ከሁሉም በከፍተኛ ሁኔታ ልቆ ይታያል ፡፡ ጠቅላላ ገቢውም 322,739,515 ( ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ አስራ አምስት) ሲሆን  ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀጥለው  
1.     አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት               322,739,515.29
2.    ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት                  46,330,546.99
3.    የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት              32,843,596.64
4.    ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት              29,805,415.24
5.    ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት                25,853,270.26
6.    ምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት            21,894,699.00
7.    ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት                20,456,331.63
8.    አርሲ ሀገረ ስብከት                      19,297,272.45
9.    መቀሌ ሀገረ ስብከት                     18,352,795.05
10.  ምስቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት               17,522,762.00
11.    ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት              16,896,645.44

Monday, November 11, 2013

በሳውዲ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥት ኃፊነቱን ይወጣ


(አንድ አድርገን ህዳር 3 2006 ዓ.ም)፡- ከወራት በፊት የሳውዲ መንግሥት በህገወጥነት ስራ የተሰማሩ የማንኛውም ሃገር ሰዎች አንድም ህጋዊ እንዲሆኑ ያለበለዚያ ከሀገር እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር ፤ ብዙ የፊሊፒንስ ፤ የኢንዲኒዥያ ፤ የህንድ እና የፓኪስታን ዜጎን መንግሥታቸው ጊዜ ገደቡ ሳይጠናቀቅ በኢምባሲዎቻቸው አማካኝነት አንድም ሕጋዊ የማድረግ ሥራ ሲሰሩ ነበር ያልሆኑትም በርካቶችን ወደ ሃገራቸው ሲመልሱ ነበር ፡፡ የኛ ሃገር መንግሥት ግን ተኝቶ ሲያበቃ የቤት ለቤት አፈሳው ሲጀመር ፤ የሰዎች ደም እንደ ከንቱ ሲፈስ ፤ የኢትዮጵያውያን ሞት ከውሾች እኩል ሲታይ ፤ አፈናው ፤ ዱላው ፤ ግድያው ፤ አስገድዶ መድፈሩ ሲባባስ አቤት እንኳን ማለት አለመቻሉ እጅጉን ያሳዝናል ፡፡ በተለያዩ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን በግልጽ የኢዮጵያኖችን መከራ ሲያስተላፉ  የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ በኤፍ ኤም 97.1 ላይ ቀርበው ‹‹ኢትዮጵያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር እንደሚወራው አይደለም ፤ ኢትዮጵያውያ ሳውዲ ውስጥ በቁጥር እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም›› ብለው አስተያየታቸው ሲሰጡ መስማት ውስጥን ያደማል፡፡ እስኪ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ፤ ከዚህም የባሰ ጉዳት ሳይደርስ መንግሥት አቤት ይበላቸው ፡፡ ወደ ሀገራቸው ለመምጣት ያሰቡትን በእስር ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ከሰዓታት እድሜ ውስጥ ይድረስላቸው ፡፡ ከዚህ የባሰ ሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳይካሄድባቸው ሁሉም በያለበት ድምጹን ያሰማላቸው፡፡  

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በስደት ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሌም ታስታውሳለች ታስባለችም። ይልቁንም በአሁኑ ሰዓት በአረማውያኑ ሃገር የሚሰቃዩትንና ሕይወታቸውም ያለፈውን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም ከይሳቅ ወገን እንዲያሳርፍና ለወገኖቻቸውም መጽናናትን ይህንንም አስከፊ ግፍ ለሚፈጽሙባቸውም ልቦናን ይሰጥ ዘንድ ዘውትር ትጸልያለች። እግዚአብሔር በስደት ያሉትን ወገኖቻችንን ያስብልን፡፡ መድኃኒዓለም ይድረስላቸው፡፡


እስኪ ስለነዚህ ወገኖች ሁላችን እንጸልይ

‹‹የቅዱስ ያሬድ ዜማን ማጣጣም ያልቻልነው ሥጋዊ ጆሮ ስላለን ነው ፤ መንፈሳዊ ጆሮ ቢኖረን መንፈሳዊው ባልሆነው ዜማ ምንኛ ባዘንበት ነበር›› ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

  • በዚህ ዘመንም ከአባታችሁ ከቅዱስ ያሬድ የተቀበላችሁትን ዜማ ትታችሁ ሌላ ያሬዳዊ ያልሆነዜማን እናሰማችሁ ባዩ በዝቷል፡፡
  • ከአባቶች ባልተሰጠ ሥርዓት ዓይንን ጨፍኖ እጅን እያወራጩ እስከመዝለልም ተደርሷል፡፡
  • “ያሬዳዊ ዜማ ለገበያ_አይመችም” በሚል መፈክር ብዙዎች ገንዘብን ፍለጋ የዜማ ርስታቸውንጥለዋል፡፡
  •  ያሬዳዊ ዜማን እንከተል እያሉ የናቡቴን ድምጽ የሚያሰሙ ምዕመናንና ካህናትም በቃልምበየመዝሙሮችም ላይ ሜልኮሎችወግ አጥባቂዎችኋላ ቀሮችትምክህተኞች› እየተባሉ ሲወረፉ እንመለከታለን፡፡

(አንድ አድርገን ህዳር 03 2006 ዓ.ም)፡- አባቶቻችን ብዙ መስዋዕትነትን የከፈሉትና ደማቸውን ያፈሰሱት ሥጋቸውን የቆረሱት አጥንታቸውንም የከሰከሱት ግዑዟን ምድር ለማውረስ ብቻ አልነበረም፡፡ ከብዙ መስዋዕትነት ጋር ወደዚህ ትውልድ ያሻገሩት ሌላ ትልቅ ርስት አለ፡፡ይህም ሃይማኖትና ትውፊት ቋንቀዋና ፊደል ዜማና ሥርዓት ነው፡፡