Saturday, August 27, 2011

መምህር ግርማ ታገዱ

 • ድቁና እንጂ ቅስና የለኝም በማለታቸው ታግደዋል - ሊቀጳጳስ አባ ቆውስጦስ
 • ማስረጃ በማቅረቤ እግዱ ተነስቶልኛል - መምህር ግርማ
 • በድቁና የሚያገለግል ሰው ይላላካል እንጂ አያጠምቅም
 • እኔ ቅስናዬን ደብቄ ነው

ከስርዓት ውጭ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በርካታ ሰዎችን ፀበል አጠምቃለሁ እያሉ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ቤት ገዝተዋል የሚል ቅሬታ የቀረበባቸው መምህር ግርማ ወንድሙ፤ የ1.5 ሚ. ብር መኖሪያ ቤትና ፒክአፕ መኪና ያገኘሁት በስጦታ ተገዝቶልኝ ነው ብለዋል - መምህር ግርማ”

ቪሲዲ፣ ጋዜጣና መጽሔት ምር የመምህር ግርማ ነው እየተባለ በየቤተክርስትያኑ ሲሸጥ አይተናል የሚሉ ቅሬታ አቅራቢዎች፤ በቤተክርስትያን ብቻ ሳይሆን በቤታቸውም ፀበል አጠምቃለሁ እያሉ ከምዕመናን ብር ይሰበስባሉ በማለት ይተቻሉ፡፡ ከስርዓት ውጭ በሆነ መንገድ በሚሰበስቡት ብር፤ የ1.5 ሚ.ብር ቤት፤ ፒክአፕ መኪና፤ ሚኒባሶችና ሌሎች ንብረቶችን አካብተዋል ይላሉ - ቅሬታ አቅራቢዎች፡፡

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት 12 የሰንበት ት/ቤቶች ባቀረቡት ቅሬታ፣ መምህር ግርማ የሚያካሂዱት የማጥመቅ ስራ ስርዓት የጣሰ ስለሆነ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ቆውስጦስ፤ መምህር ግርማ ላይ እገዳ የተጣለው ቅስና የሌለው ሰው ማጥመቅ ስለማይችል ነው ብለዋል፡፡ በድቁና የሚያገለግል ሰው ይላላካል እንጂ አያጠምቅም የሚሉት አባ ቆውስጦስ፤ በአቶ ግርማ ላይ ቅሬታ ስለቀረበ ጠርተን ስናናግራቸው፤ ድቁና እንጂ ቅስና የለኝም በማለታቸው ሊታገዱ ችለዋል ብለዋል፡፡

መምህር ግርማ በበኩላቸው እኔ ቅስናዬን ደብቄ ነው እንደዚያ ያልኩት ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ጥያቄ የቀረበልኝ በቁጣ በመሆኑ ቅስና የለኝም ብዬ ተናግሬያለሁ የሚሉት መምህር ግርማ፤ አሁን ማስረጃ በማቅረቤ እግዱ ተነስቶልኛል ይላሉ፡፡ አቡነ ቆውስጦስ ግን እግዱ አልተነሳም ብለዋል፡፡ አቶ ግርማ እግዱ ከተወሰነባቸው በኋላ ቅስና ስላለኝ እግዴ ይነሳልኝ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር የሚሉት አቡነ ቀውስጦስ፤ እኛ ሀሜትና ወሬን በመከተል ሳይሆን፤ በህጋዊ መንገድ ጠይቀን የደረስንበት ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡

 በመምህር ግርማ ንብረት ላይ ስለሚሰነዘረው ቅሬታ ተጠይቀው፤ ስለሌላው ጉዳያቸው እኛ አያገባንም ብለዋል አቡነ ቀውስጦስ፡፡ መምህር ግርማ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊትም መተተኛ ነው፣ አስማተኛ ነው የሚል አሉባልታ እየተወራብኝ ነበር፤ ያ አልሳካ ሲላቸው ቅስና የለውም ተብያለሁ ይላሉ፡፡ አሁንም በሥራ ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ ማንም በአሉባልታ ከምወደው ምዕመን አይለየኝም የሚሉት መምህር ግርማ፤ንብረታቸውን በተመለከተ በሰጡት መልስ የውጪ ተመራማሪና የጆርጅ ቡሽ አማካሪ የነበሩ ግለሰብ ሲፈወሱ በ1.5 ሚሊዮን ብር ቤትና ፒካፕ መኪና ተገዛልኝ፤ ይሔ ስጦታዬ ነው፤ ወሬኞች ግን ካቻማሊና ሚኒባስ አለው ብለው ያስወራሉ ብለዋል፡፡

"ማለዳም። ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?"- ማቴ 16:3 

‹‹ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም››
From Addis Admas

26 comments:

 1. for every one who want to know the truth come & see at ST.ESYEHPANOS EVERY Saturday &Sunday.
  THE PROGRAM HAD NEVER STOOPED & IS & WILL CONTINUE.
  Reade at
  www.ireport.cnn.com/docs/doc-627906
  thou send Ethiopians & foreigners .....
  AND W ACHE ON Y TUBE ALL 14 VCD.

  ReplyDelete
 2. ሁሉም እኮ ከፍሬው ያስታውቃል:: እሳቸውንም ስታዩ ሁሉም ግልጽ ነው:: ባሉባልታ ሰውን ከመክሰስ እውነቱን ሄዶ ለራስ ማጣራት ይሻላል:: እሳቸውን የሰጠን አምላክ አሁንም ፀጋውን ያብዛላቸው ለኛም ምህረቱን ያድለን::

  ReplyDelete
 3. የቀድሞ አባቶቻችን ጵጵስና እንኩዋን ቢኖራቸው እኔ አልችልም ብለው በጾም በጸሎት ለመትጋት ገዳም ይገቡ ነበር:: ይህ ዘመን ገና ብዙ ያሳየናል:: እግዚአብሔር ምእመኑን ይጠብቅልን::

  ReplyDelete
 4. የቀድሞ አባቶቻችን ጵጵስና እንኩዋን ቢኖራቸው እኔ አልችልም ብለው በጾም በጸሎት ለመትጋት ገዳም ይገቡ ነበር:: ይህ ዘመን ገና ብዙ ያሳየናል:: እግዚአብሔር ምእመኑን ይጠብቅልን::

  ReplyDelete
 5. አሜን አንድ ያድርገን
  ኪዳነማርያም

  ReplyDelete
 6. እኔ በበኩሌ ሁልጊዜ በጣም ነበር የሚገርመኝ እውነት እኚህ ሰው ጸጋው ካላቸው ለምንድ ነው በቤታቸው የሚያጠምቁት? የሚል ጥያቄ ሁልጊዜ ይፈጥርብኝ ነበር፥ አንድ የብዙ ጊዜ ስህተት አለብን እኛ አንድ ሰው (ካህን፣ መነኩስ፣ ወይም ሊቀ ጳጳስም) ቢሆን ሲያጠምቀን የአጥማቂው ሃይል ነው ብለን ካመንን በጣም ስህተት ነው፣ ፈውሱ ሁልጊዜ የሚገኘው በፀበሉ እንጂ በአጥማቂው ሰው ሃይል ሊሆን አይችልም፣ ይሄ ደግሞ በመፀሐፍ ቅዱስም በዓይን ያየነውም እውነት የተለየ ያደርገዋል፣ በመፅሃፈ ሳሙኤል ነብዩ ኤልሳዕ የሶሪያውን ንጉስ በዮርዳኖስ ባሕር ሄደህ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብለህ ተጠመቅ ነው ያለው፥ ያ ማለት የዮርዳኖስ ወንዝ ድህነት ሆኖት እንደሄደ እንመለከታለን፣
  በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ያሉ ፀበሎች አጥማቂ የላቸውም፣ ምን ለማለት ነው "መምህር ግርማ" የተለየ ሃይል የላቸውም ፀጋም ቢኖር በዛው በቅድስናው ሥፍራ እንጂ እኝህ ሰው በቤቴ ውስጥ እንዲህ አይነት ሥራ እሰራለሁ ቢሉ፣ ሰው ልብ ሊለው የምገባው አጥማቂውን እያመልክነው ነው ማለት ነው፣ ያደግሞ ትልቅ ስህተት ላይ ይጥለናል፣ መጥምቁ ዮሐንስ እኮ አንተ የእግዚአንሔር ልጅ ነህ ሲሉት ስንቱን ሽባ ሲተረትር፣ ጎባጣውን ሲያቀና፣ እውሮችን ሲያበራ፣ ብዙ ልዩልዩ ገቢረ ታምራትን ሢሰራ፣ እኔን አምልኩ አላለም "እኔ መንገድ ጠራጊው ነኝ" እኔ በውሃ አጠምቃችኃለው እርሱ ግን በእሳት ያጠምቃችኃል፣ እኔ የእግሩንም ትቢያ ልሆን አይገባኝም ነው ያለው።
  አጥማቂው መምህር ግን እኔ ብዚ ሥራ እሰራለሁ በእኔ ሃይል ካሉ፣ ይህ የጣዖት አምልኮ ሊባል ይችላልና ጠንቀቅ ማለቱ ይገባል ባይ ነኝ፡ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የወሰዱት እርምጃ ይበል የሚያስብል ነው። ቤተክርስቲያንን እንደ መዥገር ተጣብተው የግል ጥቅምን የሚያግበሰብሱ ብዙ ተዋሲያን ስላሉ ይህ የመጀመሪያው ሥራ ነው እና ይበል ቀጥሉበት የሚያስብል ሥራ ነው፣ የቤተክርስቲያኗ ብፁአን አባቶች በተለያየ ሃገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ተመሣሳይ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ምዕመኑን ከነዚህ አስመሳይ መዥገሮች ሊታደጉት ይገባል።
  ቸር ወሬ ያሰማን እንላለን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wendme atsasat kemawrat be botaw megegnet mayet mamen new .Esachew andim ken ene adankachu silu semiche alawkim sintun kehaymanotu wich beteleyaye eminet yetbetenew hizb anid adergu enji alatefum. Degimo bezich midir kahin be melkam bet melkam mekina ayinurow teblo ytedenegege hig yelm mekina , bet min chigr alew befekadegninet sew le kisachew yefelgewin yahil sitota liyaberkilachew yichilal, manim ymiyadergew new minew lesachew sihon tenchachachu hulgez egele bet alew mekina alew slezih lemin adege diha hono mnor le ethiopiawiyan tyetesete gidaj aydelem.yih yepintewoch were new mistrachew slwetabachew , diyablos siraw siltegalete min yawra Abatachin Egziabiher edmena tsega abzito yistiwot.

   Delete
 7. መጀመሪያ ኮመንት የፃፍከው ይሔን ሁሉ ከማለት በፊት ስለምትናገረው ማጣራት ይቀድማል:: ሰው ስላለ ብቻ ባሉባልታ ለመዝለፍ አትቸኩል:: ብታጣራ ኖሮ እኚህ ሰው አንዼም እኔ አድናለሁ ሃይል አለኝ እንደማይሉ በተረዳህ ነበር:: ሃይል የእግዚአብሔር ነው ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን ሲሉ በጆሮህ በሰማህ ነበር:: እራሳቸውን አንዼም ከፍ ሳያረጉ በእግዚአብሔር ቃል ጀምረው ሰዉ በእግዚአብሔር ሃይል ሲፈወስም ባየህ ነበር:: እራሳቸው እኔ አድናለሁ አሉ ያልከው ካንተ የተፃፈ እንጂ ከሳቸው የወጣ አይደለም:: በቤታቸው አጠመቁ ላልከውም እከሌ እንድህ አለ እንዲህ ሲባል ተሰማ የሚሉት የእውነት መረጃዎች አይደሉም:: የተለየ ሃይል የላቸውም ላልከውም የተለየ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት እኛ ሳይገባን ምህረቱን ሊያሳየን በዚህ በሃጢያት ዘመን ሰለፍቅሩ በሳቸው ላይ አድሮ የሚያሳየን ሃይል ነው:: እናም መዥገር ብሎ ከመሳደብ አጣርቶ በስነስርዓት ሃሳብን መግለጽ ብልህነት ነው:: ምክኒያቱም ያልከው ትክክል ቢሆን እንኩዋን በሳቸው እድሜ ያለን አባት መሳደብ ሃጢያት እንጂ ጽድቅ አይደለም!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም ያንተን ሃሳብ እጋራለሁ፡፡ ከማውራት መዝኖ መፍረድ ይገባል፡፡ እኚህ አባት የእግዚአብሔርን የማዳን ሃይል ቢገልፁልን ምኑ ይሆን ሃጢያቱ፡፡ ለነገሩ ለክርስቶስ ያልበጁት ሰዎች ዘር በዚህ ዘመን ይጠፋል ብለን ከጠበቅን ተሳስተናል፡፡ የሚገርመኝ እኚህ አባት እኔ አዳንኩ ቢሉ እንኳን ሃጢያቱ ለራሳቸው እንጂ ለሌላ አይተርፍም፡፡ ሙሴ በፈተና ሲወድቅ ውሃውን እኔ አፈለኩላች ጠጡ ባላቸው ግዜ ማርና ወተት የምታፈሰውን ሃገር ውሃውን የጠጣው ህዝብ ገብቷልና እኛ ዛሬ ማሠብ ስለሚገባን ስለመዳን ብቻ እናስብ ሌላውን ነገር ለሱ እንተው እናመ እኛ ማነን ብለን መጀመሪያ ራሳችንን እንመርምር የሰውን ጉድፍ ለማውጣት ከምንንቀጠቀጥ፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጠን፡፡ አሜን

   Delete
  2. @emneti am agree with you ወገኖቼ ሆይ አትገረሙ ይችምድር እኮ ክርስቶስን እንኳ በፊት ለፊት ስንት ተአምር እየሰራ ለማመን ተቸግራ ነበር እኝህን አባት እግዚያብሔር ለበጎቹ ሰጠ :: አሁንም የጸጋው ባለቤት እድሜና ጤና ይስጣቸው አሜን

   Delete
 8. @EMNET
  በጣም ደስ የሚል መልስ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው ያንተ ኮሚንት በዛ ኮሜንት በማብዛት እኮ ማሳመን አይቻልም የባሰ ጠበቃቸው ነው ያስብላል እንጂ

   Delete
 9. emnet
  yasadigih ! perfect answer !
  "ማንም በአሉባልታ ከምወደው ምዕመን አይለየኝም"
  መምህር ግርማ
  Long Live !
  bezih astseyafi zemen aannd abat egziabhear biseten maguremremu lemin new? ewinet ye egiziabhear kal kezih belay ayadergimin? minale rebashoch ..kemtrebishu hidachihu bitfewesu ..bewichi hukata bewisit hukata ..sew endayidin mekelkelachihu keman yihon ?
  አሁንም በሥራ ላይ ናቸዉ

  ReplyDelete
 10. እባካችሁ አባታችንን ለቀቅ አድርጉልን በዚህ ጉዳይ የተንጠለጠላችሁ ዉረዱ እስቲ የተማራችሁ እንደሳቸዉ አስተምሩ "ማንም ከላይ ካልተሰጠዉ በሰተቀር ምንም ሊያደርግ አይችልም" የሚለዉን የወንጌል ቃል እናገናዝብ መልካም ኦርቶድክሳዊ ስብከትና የፈዉስ አገልግሎት ለማገድ መከጀልና ሰብአዊ መብታቸዉን መጎነታትል ተገቢ አይደለም ...አሁንም ለቀቅ አድርጉልን... MB

  ReplyDelete
 11. እባካችሁ አባታችንን ለቀቅ አድርጉልን አሁንም ለቀቅ አድርጉልን

  ReplyDelete
 12. ere gud sew men neketotal ..ye egetheabeher cherenet megelese siaketen besew sega yehen yakel ...merebareb ye seytan new enji yemenfese kedus aydelem.....ken lebona medehanialem yeseten

  ReplyDelete
 13. @ emnet
  I like the polite way u answered.God is the one who is healing us using memeher Girma.So anyone can come and see the work of God at Estifanos church.Memher Girma never said I healed u.He always said that it is God who healed his people.So please note that jealousy and spreading false rumour is not the act anticipated from christians. May God enlighten our hearts!!!

  ReplyDelete
 14. rejem edeme yesetelen tsegawun yabezalen lememeher girma

  ReplyDelete
 15. This is purely from Devil ...

  ReplyDelete
 16. amen memeher germa tsegawen yabzaleowt ya alubalta were lemen ensemalen Egziabher besetachew tsega eyefewesu new zemenu zemenu belen gezeyachenen kemenakatel ye ewnet amnen wede Egziabher enemeles hulunem neger gelse argo yenegrenal eziw commentoche lay erasu sent bezu leunet ale ere wegen be denb enedemamet anekefafel ere bakachehu

  ReplyDelete
 17. i know that i dont know more but what if it is done by "degemt" can u explain that

  ReplyDelete
  Replies
  1. emen enji atefera selemn teterateraleh?

   Delete
 18. I have watched 19 VCDs of Memher Girma, I have yet to hear him say "I healed you". Memher Girma always gives the glory to God. Before you judge this man, please listen to his teachings. If he was "Asmatena" he would not be sharing his healing methods (which are praying, worshiping and holly communion). Before I started listening to him on radio abyssinia, no other priest had ever shared or explained to me what I needed to do at home to worship God, but Memher Girma did. He thought us how to pray and worship. Watch his VCDs... listen to his teachings. If you can’t see this, may God open your eyes and ears.

  In this time and age when man has become sinful to a point of no return, God has found one man to show us his Glory… Let’s not throw stone at this man.

  Memher Girma,Egiziabher Tsegawn abzeto yechemrwate (for the sake of us).
  God Bless you all!
  AA

  ReplyDelete
 19. ስንት ጴንጤዎች ያወሩት ንግግር ለማጣራት ጊዜ የለንም

  ReplyDelete
 20. የመምህር ግመርማ ሥራ ስህተት ካለበት ለምን አያስቆሙልንም የሚመለከታቸው ሰዎች ወይንም አባቶች ፤ እኛንም ለስህተት ከምንዳረግ፤ ምን አለበት መጥፎ ስራ ከሆነ ማገድ ይቻል የለም እንዴ፡፡ የኛ ሰው እንደሆነ በሞኝነት ብዙ ስህተቶችን እናጠፋለን የቸገረው ደግሞ መፍትሄ ማግኘቱን ነው እንጂ የሚያየው እና አሁን ደግሞ ያው ወደ ጣሊያን ሄደዋል ለዚሁ ሥራ ነገር ግን ማናቸውንንም አስተማሪ ሄኖም ይሁን እንደሳቸው አገልግት በመስጠት ላይ የሚገኙትን የምናባልጋቸውና የምንሰቅላቸው እኛው ነን፡፡ ገንዘብ በመስጠት፤ ወደ ላይ በመካብ፤ ራሳቸውን እንዳይሆኑ ከሰው የተለዩ በማድረግ ልባቸው በሙገሳና በእውቅና እንዲሞላ፤ ከሰው በላይ የሆኑ እንዲመስላቸውና ቀጥሎም ገንዘብ ያልሰጠ ሰው ጋር አገልግሎት ላለመስጠት፤ ለምሳሌ መምህር ግርማ በስልክም እፈውሳለሁ እንደሚሉት የሀገር ውስጥ ስልክ ከሆነ ባለማንሳት የውጭ ሀገር ስልክ ከሆነ ግን መልስ እንደሚሰጡ፤ ይህንን ሁሉ የማን ሥራ ነው› ምእመናኑ ከሳቸው በፊትም በጋሻውን እንደዚህ በጣም ሲካብ ሲካብ ከአቅም በላይ በሆነ ሙገሳ ወደቀ፤ ወደ ተሳሳተ መንገድ ውስጥ ገባ ከኔ በላይ ማን አለ ወደሚል ሀሳብ ገባ ልጁ በፊትም ልቡ ትንሽ ናት ያለእውቀት የቆመች ስለነበረች ተሸርሽራ ወደቀች፡፡ በጣም መምህራን በነሱነታቸው በሚሰጡን ትምህርት ነው መመዘን ያለባቸው እንጂ እንደጭራ እየተከተሉ እነሱን ማምለክ ተገቢ አይደለም እኛው እያበላሸን ስለሆነ መለስ እንበል፤ አጉል የካብናቸው ሰዎችም መውደቂያቸውን ያቃርቡታል ራሳቸውን በመካብ፤ በመቆለል፤ የእግአብሄር ቃል እኮ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ አለ፤ ዝቅ ብለው ማስተማር በትክክለኛው አለባቸው እንደበጋሻው ኤናውጣ መሆንም አይገባም፤ መምህር ግርማም በተሳሳተ መንገድ የምህረት ሥራ የሚሰሩ ከሆነ አሳውቁን አንሳሳት፤ በእግዚአብሄር ሀይል የሳቸውን እርዳታ ፈልገን የምንሄድ ሁሉ ከስህተት እንዳንወድቅ እባካችሁን ትክክለኛነታቸውን አሳውቁን፤፤

  ReplyDelete