ጊዜው ወርሀ ክረምት ነው :: የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፆመ ፍልሰታ ወቅት ሲሆን በቤተክርስትያናችን ህግና ስርዓት መሰረት ይህ ጊዜ ዲያቆናት ፤ ካህናት መነኮሳት ፤ ጳጳሳት እና ምእመናን ለሐዋርያት የተገለፅሽላቸው እናታችን ለእኛም በምህረት አትለይን እያሉ በፆም ፤ በፀሎት ፤ በስግደት የሚለምኑበት ጊዜ ነው፡፡
ቦታው በሐረር መንገድ አዋሽ ሰባትን አልፈው ካለው የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያ ትንሽ ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ከአሰቦት ገዳም መገንጠያ ሳይደርስ ከዋናው አስፋልት አንድ ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ሲሆን የቦታው ስም ቦርደዴ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቤተክርስትያን የሚገኝበት ቦታ ላይ ከ30 የማይበልጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሲገኙ በቁጥር ከ40 እና ከ50 እጥፍ ልቀው የሚገኙት ግን ሙስሊም ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ ይህ ቦታ ለአንድ አፍታም ቢሆን ከነገር እና ከትንኮሳ እፎይ ያለበት ጊዜ የለም፡፡ ቦታው ድረስ ሄጄ በተመለከትኩበት ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ያለው የሙቀት መጠን ክረምት ሳይል በጋ ከ40 ድግሪ በላይ ስለሆነ ቆሞ ማስቀደስ እንደ እግዚሐብሔር መልካም ፍቃድ ፤ ምህረት ፤ ቸርነት እንጂ እንደ እኛ ብርታትና ጥንካሬ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡
ቤተክርስትያኒቷ አካባቢ ያሉት ምዕመና ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብ እና ንዋየ ቅዱሳትን ማሟላት አቅሙ ስለሌላቸው ይህ ችግር የቀን ተቀን የውስጥ ችግር ችግራቸው ሆኖ አሁንም አሉ ፡፡ የባሰ አታምጣ ነውና አንድ ጊዜ ቅዳሴ ላይ ወንጌል ለማንበብ ጧፍ አልቆ በኩራዝ የተጠቀሙበት ጊዜም ነበር ፡፡
በአካባቢው የሚገኙ ከአክራሪ ወገን የሚመደቡት የእስልምና ተከታዮች በአካባቢው ላይ ለ24 ሰዓት ያህል ከ4 በሚበልጡ መስኪዶቻቸውን ድምፅ ማውጫ Speaker ወደ ቤተክርስትያን አዙረው ‹‹አላህ ዋክበር›› በሚሉበት ሁኔታ ላይ ምንም ጥያቄ ያላቀረቡት በአካባቢው የሚገኙ ክርስትያኖች በዓመት አንድ ጊዜ ለ16 ቀናት ብቻ ያለውን የሱባኤ ጊዜ ለሊት ሰዓታት እና ኪዳኑ ፤ ጠዋት ትርጓሜው እና ስብከቱ ፤ ከሰዓት ቅዳሴው ረበሸን ብለው ቤተክርስትያኒቷ እንድትዘጋላቸው ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸውን አረጋግጠናል፡፡ ይህን ጥያቄ የመስተዳድሩ ሃላፊ ከሰማ በኋላ ለሚቀጥለው ቀን የቀጠራቸው ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ሲመጡ ምንም ምላሽ ስላላገኙ ሓላፊውን በኃይል ከቢሮ ያባረሩት ሲሆን ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው የክልሉ መንግስ ጋር እንደደረሰ ፤ አካባቢው ላይ የሚገኙ ክርስትያኖች ጉዳዩን ወደ ፊደራል መንግስት የወሰዱት ሲሆን መንግስት የዛኑ ቀን ማታ አካባቢው ላይ የሚገኙ ፌደራል ፖሊሶች ማታ 3፡00 አካባቢ ወደ አካባቢው በፓትሮል በመምጣት ይህን ጥያቄ የጠየቁትን ሰዎች ግማሽ ያህሉን ለቅመው ወስደው ወደ እስር ቤት የከተቷቸው ሲሆን የተቀሩትን ግን ሸሽተው አምልጠዋል፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ ሁኔታውን በጥቂቱ ያረጋጋ ሲሆን ፡፡ በአሁኑ ወቅት አካባቢው በፊደራል ፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል::
እኛ በአሁኑ ሰዓት እንትና 18 ገፅ ወቀሳ ፃፈ ፤ ያኛው ሰባኪ አውደ ምህረት ላይ እንዳይቆም ተከለከለ ፤ በዚህ መፅሄት ላይ እንትና መልስ ሰጠ ፤ አንዱ ይቅርታ አለ ሌላኛው ይቅርታ ተቀበለ እያልን ስራ መስራት በሚገባን ወቅት ወሬ ስናራግብ ለቤተክርስትያን መሆን በሚገባን ሰዓት ጊዜያችንን እና አቅማችንን አልባሌ ቦታ ላይ በማዋልና ትርፍ የሌለው ስራ በመስት ላይ እንገኛለን፡፡
አሁንም ጊዜው አልረፈደም ስለ ጥቂት ሰዎች ማውራታችንን አቁመን ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ዘብ እንቁም ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ይህን የጠየቁ ሰዎች ነገ ምን ማድረግ እንደሚያስቡ ለማስረዳት መምህር ሊያሻን አይገባም፡፡
በዚች ምድር ላይ የምንቆየው እንደ ማቱሳላ 969 ዓመት አለመሆኑን አውቀን በኖርንበት፤በምንኖርበት ጊዜ ሁሉ ከቤተክርስትያን ጎን ለመቆም ያብቃል፡፡
(ከአንድ አድርገን)
ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም
‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ››
ende yemin were new bemichalew mengid sew , mehmnuem eysera new, keslam yalnsuten, yebtkirstyan teltoche, atkwmeu new yemtluit, gode eko new
ReplyDeleteሰላም እንደምን ከረማችሁ ያንድ አድርገን ጦማሪዋች በጣም ልቤን የሰበረ ዜና ነው ያስነበባችሁን እውነት ነው ወሬ አብዝተናል በሀገር ውስጥም ካገር ውጭም ያለነው ምእመናን በየፌስት ቡክላይ ከመጻፍ የዘለለ ነገር ማድረግ ተስኖናል እባካችሁን ለገዳሙ መርጅያ የሚሆን ገንዘብሆነ ቁሳቁስ ለማሰባሰብ የምንችልበትን መንገድ ብትነግሩን የበኩሌን ለመወጣት ዝግጁነኝ የቤተክርስቲያንአምላክ ተዋህዶን ይጠብቅልን! አሜን
ReplyDeleteእንደዚህ ለቤተክርስቲያናችን ስለሚገባን ክርስቲያናዊ ግዴታ የሚያሳስብና አስተማሪ የሆነ ጽሁፍ ስታወጣ በጣም ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን ፀብ ጫሪነትን የሚፈጥሩና የሰው ስም በማጥፋት ዘመቻ ላይ ትኩረት ያደረጉ ጽሁፎች ላይ ጊዜ ባታጠፉ ጥሩ ነው፡፡ እኛ በሚረባና በማይረባ ነገር እርስ በርሳችን ስንባላ ሌሎች የእኛን ውድቀት ለማፋጠን መሯሯጥ ጀመሩ፡፡ ስለዚህ የሁላችንንም ልቦና እግዚአብሔር ያብራልን፣ አስፈላጊውን በጎ ነገር ሁሉ በማድረግ ቤተክርስቲያናችንን እንጠብቃት፣ እባካችሁ አንዱ አንዱን ጠልፎ ለመጣል ከመሮጥ ይልቅ አሁን በቤተክርስቲያናችን ያለውን አንገብጋቢ የሆነ ሃይማታዊ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ሰላም ስለሚፈጠርበት ሁኔታ ሁላችንም እንረባረብ፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናና ይጠብቅ፣ ልቦና ይስጠን፡፡
ReplyDeleteyebetekrstiyan amlak yitebiken
ReplyDeleteahun gena tiru neger ametachihu, yemibejen sewen telife lemetal medekem sayihon be andinet honen ye wechi telatachinen memeket new
ReplyDelete