Monday, August 15, 2011

የላይ ቤት ጥሪ ወይስ ሌላ ሤራ?

"በእንተ ቢጽ ሐሳውን ወበእንተ ዜና ዕረፍቶሙ ለአበዊነ":- የአባቶቻችን በ2 ዓመታት ውስጥ ተደጋጋሚና ድንገተኛ ዕረፍት የላይ ቤት ጥሪ ብቻ ወይስ ሌላ ሤራ ያለበት?

  • አቡነ አረጋዊ የቅድስት ሥላሴ ካቴዴራል የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ በጠና ታመዋል፡፡




   1. "ስሞን መሠርዮች" :-

የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች በጌታ አነጋገር ‘ጸራዊ” በሐዋርያት አነጋገር ‘ቢጽ ሐሳውያን” በሊቃውንት አነጋገር መናፍቃን ይባላሉ:: የቤተክርስቲያን ሰዎች ሳይሆኑ የቤተክርስቲያን ሰዎች መስለው ወይም ከቤተክርስቲያን ትምህርት ግማሹን ይዘው ግማሹን ያልያዙ ጎዶሎዎች ናቸው:: እነዚህ ሰዎች እንክርዳድ ስንዴ መስሎ እንደሚያድግ በክርስቶስ ዐጸደ ወይን በቤተክርስቲያን ውስጥ የበቀሉ አሳሳቾች ናቸው::
ሲሞን መሰርይ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው መናፍቅ ነው::[ ሐዋ 8 :13 -24 ] ሲሞን መሰርይ የፊልፖስን የቃሉን ትምህርት ሰምቶ ይህን ታአምራት አይቶ እሱም አመንሁ ብሎ ተጠመቀ: ነገር ግን ተከታታይ ሁኔታው እንደሚያመለክተው ሲሞን ከልቡ አምኖ ሳይሆን ፊልፖስ የሚያደርገውን ታአምራት ስላዩ እሱም ይህን የዚህ ሃይማኖት አባል የሆነ እንደ ሆነ ተመሳሳይ ታአምራት ማድረግ የሚችል መስሎት ታአምራት በማድረግ መወደስ አቦ አቦ ለመባል አስቦ ነው::

ይሀው ሊታወቅ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ሚለው ሐዋርያት ሰማርያ ወርደው በተጠመቁበት ምእመናን ላይ እጃቸውን እየጫኑ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሲያሳድሩባቸው አይቶ ሲሞን እሱም ይህችን ሰልጣን በእጁ አድርጎ እንደ ሐዋርያት ለመሆን ከጀለ ::በጥንቆላው የሰበሰባውን ገንዘብ አምጥቶ ይህን ስልጣንህን ብታካፍለኝ ይህን ገንዘብ እሰጥሃለሁ ብሎ ለቅዱስ ፔጥሮስ ሹክ አለው የሲሞን ቅሌት እዚህ ላይ ነው::

ፔጥሮስም ይህን በሰማ ጊዜ በመገሰጽ ቃል ‘ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ የእግዚአብሔርን መንፈስ በተጣመመ መንገድ ሽተሀዋልና አታገኛውም” ሲል ተቆጣው ::ከዚህ በኁዋላ ሲሞን የራሱን ተከታዮች በማፍራት ቅዱስ ፔጥሮስን መቃወም ጀመረ [የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀ ፓፓስ]

ይህ ነው ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቅስ አይቀርም ይሉዋል::እግዚአብሔርን ባልወደዱት መጠን ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው እንዲል::
ዛሬ ጉባዔ ሳይውሉ ምሥጢር ሳያደላድሉ የማይገባቸውን ክብር ለራሳቸው ለማድረግ የተሽቀዳደሙ ሳያስመሰክሩ መጋቤ ሐዲስ ላዕከ ወንጌል ሊቀ መዘምር የሚለውን ማዕረግ እንደ መርካቶ ሸቀጥ በገንዘብ የደረቡ ‘ሲሞን መሰርዮች” ከምዕመናን ተቀባይነት አግኝቶ ቤተክርስቲያንን ለመክፈል በሸረቡት ሴራ ተከታይ አፍርተናል ባሉት ጊዜ እኛ ያልነው ሁሉ ምእመኑ ትክክል ይመስለዋል ባሉት ሰዓት የግብር አባሮቻቸው መናፍቃን በየመጽሔቶቻቸውና በየጋዜጦቻቸው ድምጻቸውን በሚያስተጋቡበት ሰዓት ሐውልት ትውፊት ነው ብሉ ጾምን ቢያቃልሉ ምን የሚደንቅ ነገር አለ ?

መናፍቃን ‘በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያሰማራነው የውስጥ ኃይል የሕንድን ታሪክ ልደግምልን ነው” እያሉ በሚፈነጩበት ሁኔታ ‘ተሐዲሶ የለም ‘ማለት ምን የሚሉት ነው? ካለወቁ ጠይቆ መረዳት እንጂ::"...ምን ሳይል አይሸትም "ይባል የለ::

ይሁን እንጂ የሕንድን ቤተክርስቲያን በተሐዲሶ ስም የመናጡ እንቅስቃሴ የአንግልካን አስተምህሮ የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያንን ገንጥሎ የፕሮቴስታንት ቸርች በመመስረት ብቻ አልተጠናቀቀም :: እነዚህ አካላት በተቁዋቁዋመው የቲዎሎጂ ሴምናሪ እያገለገለ የነበረውን አብርሃም ማልፓን የተባለውን ሰው በመጠቀም በተሐዲሶ ስም ሌላ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ሌላ ጥረት ማድረግ ጀመሩ::

አብርሃም በጊዜው አንደበተ ርቱዕ ስለነበረ በቲዎሎጂ ሴምናሪ የነበረው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ የምዕመናኑን ልብ ለማገኘት የቲዎሎጂ ደቀመዛሙርትንም ልብ ለመግዛት ሁነኛ ሰው ነው በሚል ለይተው የመረጡት ሰው ነበር” [ሐመረ ተዋሕዶ ነሐሴ 2002 ገጽ66]::ታዲያ ዛሬ በኛ ቤተክርስቲያን ልክ ይህን የሚመስል ሁኔታ የለም ወይ?
  
ቢያንስ”ምን ሳይሆን አይሸትም” እንደሚባለው መጠርጠርም ብልህነት ነው::
ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ 16: 18 ‘ወአናቅጸ ሲኦልን ኢይሄይልዋ [ የገሃነም ደጆች አይችሉአትም]” ያለውን ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይህን በተረጎመበት ‘ ሰውን ብትታገል ታሸንፋለህ ወይ ትሸነፋለህ ቤተክርስቲያን ግን ከቶ አትሸነፍም” እንዳለ ቤተክርስቲያን ከቶ አትሸነፍም : ነገር ግን ፈተና ከቤተክርስቲያን እንደ ማይጠፋም የጠቆመበትም ነው'::

ከቤተክርስቲያን ታሪክ የሚንረዳውም ይሄንን ነው::

ሲሞን መሰርዮች ‘ፎቶየን ሲያይ ሳይጣን መጮህ ጀምሮአል” በማለት : አንድ ሕንጻ ለማሰራት በተዘጋጀ ጉባዔ ከጉባዔው ልገኝ ከሚችለው ገንዘብ በላይ እየጠየቁ በማስጨነቅና በማጭበርበር በሰበሰቡት ብር ተከታይ ለማፍራት ብጥሩ ኤፒስ ቆፖስነትን ለመሾም ብደራጁ ቤተክርስቲያንን ለመክፈል ከመናፍቃን የበሉትን ግብር ለመክፈል ብቁዋምጡ ምን ይገርማል?
የሚያሳዝነው እንደ ፔጥሮስ ገስጾ የሚለይ መጥፋቱ ነው ::

ነገር ግን ስለቤተክርስቲያናችን ህልውና ስንል ከዚህ በላይ መታገስ የሚንችል አይመስለኝም ::መንኛውም ዜጋ የፈለገውን እምነት የመከተል ነጻነት ቢኖረውም በማያምንበት በሌላ እምነት ውስጥ የራሱን አስተምህሮ እየነዛ ሁከት መፍጠር አይችልም::

ያለንን መረጃ ይዘን በሕግ አግባብ መጠየቅ አለብን::                                  

2. "የአስቆሮቱ ይሁዳዎች":-

 የዛሬ 2 ወር መምህሬና የንስሀ አባቴ ከሆኑት አባት ጋር ስላለፈው የርክበ ካህናት የቅዱስ ስኖዶስ ጉባኤ ስንጫወት በተለይም የኤጲስ ቆጶሳት ስመት ስለመቅረቱ ስናወራ አባቴ አንድ ነገር አነሱ «እነዚህ ሹመት የቀረባቸው መነኮሳት ዻዻሳትን ሊያስደበድቡ ይችላሉ » ስሉኝ '«ዲያቆን» በጋሻው ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ሲያርፉ «እሴይ አንድ የኢየሱስ ጠላት ሞተ »ማለቱን ሳስታውስ አንድ ጥርጣሬ አድሮብኝ ነበር:: ልክ ከኣበቴ እንደተለያየሁ ወደ ቢሮየ አቅንቼ ደጀ ሰላም እንደከፈትኩ ብፁዕ አቡነ በርናባስ ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ዕረፍት ጋር በሚመሳሰል መልኩ ማረፋቸውን አነበብኩ::

 የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የመጋበ ብሉይ ሰይፈ ስላሴ ዛሬ ደግሞ የብፁዕ አቡነ በርናባስ ዕረፍታቸው ተመሳሳይና ድንገተኛ መሆኑን ለተከታተለ ጥርጣሬ ማሳደሩ አይቀርም:: እነኝህ አባቶች በትምህርታቸውና በኃላፍነታቸው የቤተክርስቲያን አምድ የሆኑ አባቶች ነበሩ::ዛሬ ደግሞ ብፁዕ አባታችን አቡነ ሚካኤል::

እንደ ሲሞን መሠርይ የመንፈስ ቅዱስን አሠራር በብር ለመግዛት እስከ ግማሽ ሚሊየን ብር የሚያወጡ ሰዎች ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለማስወገድ ጥረት አያደርጉም የሚል እምነት አይኖረኝም :: በተላይም "ተሐዲሶ "ከደቀነው ሴራ ጋር ስደመር ጥርጣሬያችንን ይጨምራል:: ለመሆኑ እነዚህ ሹመት ለማገኘት ግማሽ ሚሊየን ብር ያወጡ ሰዎች እንዴት ይህን ያህል ብር ሹመት ለማግኘት ሊያወጡ ቻሉ? እንደው በግላቸው ሹመት ስለፈለጉ ብቻ ይሆን?ወይ ከጀርባ ሌላ የተሰለፈ ኃይል አለ?

ከዛሬ 3 ዓመት በፊት ጀምሮ ቤተክርስቲያንን ለማዳከም በሚደረገው ሴራና የመንፈሳዊ ትምህርት ቤቶችዋን ለመበረዝ በሚደረገው ጥረት ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት እንደሆነ በአሜሪካን አገር በሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች ጭምር መውጣቱን ሳስታውስ ጥርጣሬየ ወደ ማመን ይጠጋል::

ምናልባት በሃይማኖት ሽፋን ለሉላዊነት(GLOBALIZATION) እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ሁኔታዎችን የማስወገድ ተልዕኮ አካል ይሆን? 

እውነተኞቹን አባቶች ጨርሶ ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር የሚደረገው ሴራ አካል ከሆነስ ?

እባካችሁ አባቶች እራሳቸውን እንዲጠነቀቁ ቢደረግ? የአስከሬን የሕክምና ምርመራ ውጤትም ለሚመለከተው አከል በትክክል መድረሱና ምርመራው በትክክል መደረጉ የሚረጋገጥበት ሁኔታ ቢኖር?

 ስለቤተክርስቲያን ሁላችንም ዘብ የሚንቆምበት ጊዜ አሁን ነው::
እግዚአብሔር አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን::

3 comments:

  1. ere yemisemawe hulu yemegerm new minew enedezih betekerestiyanachen fetenawa beza

    ReplyDelete
  2. Gimitu Tikikil Yimeselengal Beteley degimo Liphiphisina asefesefew Yemetebiku Yetehadiso akenekangoch Sera selemihon Bewinet abatochin Bekirebet Yemiketatel Bichal Yetena balamoya bihon Yemel hasab aleng

    ReplyDelete
  3. OMG i have no word.just save tewahdo....

    ReplyDelete