Friday, August 5, 2011

እሹሩሩ... ለ"ተሐድሶ" ያስፈልጋልን?

በብስራት ገብሬ


        በመጀመሪያ የኢ....መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው::እግዚአብሔር ያውቃል...እኛ ምንም አንሆንም እያልን ስንት ወገኖቻችን ሄደዋል:: እኛ ግን በግራና በሞቀ ቤታችን ሆነን 'ይህን ካላየሁ አላምንም' ይህን ካልሰማሁ.... እንላለን:: ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ወቅት እንዲህ አይነት ፋታ የሚሠጥ ነገር ሣይሆን መሠረቷን በብዙ አቅጣጫዎች እንድታጣ ሆና በአራቱም አቅጣጫ ተወጥራለች:: የምትጠብቀው "..በሉ አሁን ጀምሩ የሚለውን.." እግዚአብሔር ፊሽካ ሳይሆን በሚቆረቆሩላት በሚኖሩባት በሚያዝኑላት ልጆቿ ታግዛ አይምሬ ቅጣት ሊቀጧት ከተዘጋጁ ጠላቶቿ ጋር ፊት ፊት እንድንዋጋላት...እንድንጋፈጥላት ነው::እግዚአብሔር ከእሱ ስርዓት ውጭ ካልሆንን ከጎኗ ይሆናል::        እይታዬ:- ሁላችንም እምነታችንን እንወዳለን ነገርግን እምነታችንን የሚነካ የሚበርዝ የሚያጠፋ ነገር ሲነሳ ከውጪ ሆኖ "አይይ... ልቦና እግዚአብሔር ይስጣቸው..." ብሎ ከንፈር ከመምጠጥ ውጭ አንዳችም ነገር ስናደርግ አንታይም ይህም ነው ቤታችንን ጠላቶቿ እንዲዳፈሯት የሚያደርገው ጠላትን ለማጥፋት ማን ነው ሽጉጥና ጠመንጃ ብቻ መፍትዔ ያደረገው?? ለጠላት ሽጉጥም...ጠመንጃም... 'የበዛ' ትህትናም አያስፈልግም:: በቤተክርስቲያናችን ስርዓትና ወግ መሠረት አንድም እንዲማሩ ማድረግ ካልሆነም አርፈው እንዲቀመጡ ማድረግ/ማፅዳት እንጂ::ለዚህም ይረዳን ዘንድ 


1.  የጠላትን ውስጠ-መሠረት እና ማንነት ማወቅ 
2.  ዝም ብንል የሚያስከትለውን ጥፋትና እልቂት መገንዘብ
3.  እኛ ያለንበትንና ጠላቶቻችን ያሉበትን ሁኔታና ደረጃ ለማወቅ መቻል እና እንዴት መከላከል 
      እንዳለብን ማወቅ(በግልም  በህብረትም)
4 ከተቻለ ዳግመኛ እንዳይመለሡ ለማድረግ መጣር::

እነዚህን ማድረግ ከቻልን ቤታችንን መጠበቅ የሚቻል ይሆናል በእኔ እይታ አሁን የኢ.... የምትፈልገው ሁሉን ለማወቅና ተገቢውን እርምጃ ለመውሠድ ብቃቱም ኃይሉም ኖሮት ውስጡ ግን ተነሳሽነት የጎደለውን 'ፈሪ' አይደለም ! ፈሪ ማለት ለኔ ይሄ ነው! ሌላው ሲሞት የሚደራደረውን::ሃይማኖት... እምነት ሲጠፋ ቆሞ የሚያየውን::
         በአንድ ወቅት አንዱ የተሐድሶ አቀንቃኝ 'ስላሴ' አትበሉ'እየሱስ' በሉ ብሏል ብዬ በመፃፌ "...ለምን ሙሉ ሲዲውን(CD) እንዲሁም ሙሉ ስብከቱን አንሠማም..." እህህ..."ነገርን ማባባስ ለምን?" ያስፈልጋል ተብያለሁ:: አውቃለሁ ምን ያህል የኢ.... ልጆች ትህትና እንዳለን:: ልንኮራበትም ይገባል:: ይህም ቢሆን ትህትናው በሌሎች ፍርሃት መሠለ:: ዋጋም አስከፈለን:: ትህትናችን ከመብዛቱ የተነሣ በቤታችን... በጓዳችን... በካፌ ውስጥ ቁጭ ብሎ ከማውራት ከመቆዘም ዝም ከማለት የተሻለ/የዘለለ ምንም አላደረግንም:: 

ዋናው ቁምነገር ግን እምነታችንን... ውበታችንን ሳናጣ ስለጠላቶቻችን ድርጊትና እንቅስቃሴ በግልፅ ማውራት ያለብን ይመስለኛል በግልፅም ወደመፍትዔ መሄድ አለብን::

....ነገር ማባባስ ነው ተብሎ ዝም ከማለት የሚመጣውን መቀበል በብዙ ይበልጣል::


  • እየተባለ ያለው ቤታችንን ስለመጠበቅ ነው!
  • እየተባለ ያለው እምነታችንን ስለመጠበቅ ነው!
  • እየተባለ ያለው እውነትን ስለመጠበቅ ነው!
ሁላችንም የሚሆነውንና እየተካሄደ ያለውን ነገር በትኩረትና በአንክሮ የመከታተል የመረዳት ግዴታ አለብን:: ማንም ጊዜ ኖሮት ስለጠላት ለማውራትና ጭቅጭቅ ለመፍጠር የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም:: ችግር ከሌለበት በስተቀር::ማንም ለኔ ስለለኔ መረጃም ሆነ ማስረጃ ማቅረብ የለበትም:: እንደ ዕድል ይሁን እንዳጋጣሚ ብዙዎቻችን አስተያየት ሠጪና የሩቅ ተመልካች ሆነን ተፈጥረናል:: የሚያስቀው'ለማመን' እንኳን ጠላቶች ያደረጉትን ነገር ሁሉ/ሙሉውን መረጃ እቤታችን..ቢሯችን ድረስ እንዲመጣን እንፈልጋለን:: ለምን? የሚገርመው የመጣንን መረጃ እንኳን ግራና ቀኝ አይቶ መወሠን ካለመቻላችንም በላይ ለማጥላላት ስንሞክር እንታያለን:: በዚህ መሐል ደግሞ ለኢ.... የተቆረቆሩ የሚመስሉ የበግ ለምድ የለበሱ የኛን ትንሿን ድክመት ጨምረው የተገኘውን መረጃ የማንቋሸሽ ስራ በስፋት ይሠራሉ:: የውስጣችንንም ኃይልና ብርታት ይገሉታል:ያዳክሙታል:: የተፈለገውም እንዳይሆን ይጥራሉ::

      በመጨረሻ ወዳጆቼ እርስ በራስ ከመተቻቸት ከመሸሽ አንድ ሆነን እግዚአብሔር እንዲረዳን ብርታቱን እንዲሠጠን እየለመንን በአንድ ድምፅ በመጮህ ጠላቶቻችንን ይብቃችሁ እንበላቸው ፊት አንስጣቸው::

እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

አሜን

ይቀጥላል....

2 comments:

  1. እግዚአብሄር ሀገራችንን ይባርክ፡፡ አሜን፡፡

    ReplyDelete
  2. Thanks a lot for sharing this with all folks you really understand what you are speaking approximately!

    Bookmarked. Kindly additionally talk over with my web site =).
    We will have a hyperlink trade contract between us
    Also see my web page > GFI Norte

    ReplyDelete