Wednesday, March 30, 2016

አንድ ካሬ 305 ሺህ ብር በሊዝ በሚሸጥበት ወቅት ፤ አንድ ካሬ በ5 ብር የምታከራይ ቤተክርስቲያን



(አንድ አድርገን መጋቢት 21 2008 ዓ.ም ፡- የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ይህ / 1986 . በአካባቢው ምዕመናን እንደተመሰረተ ይነነገራል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ይዞታ ወደ 80ሺ ካሬ የሚጠጋ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተሰሩ ወይም በመሰራት ላይ ከሚገኙ እጅግ ግዙፍ ከሚባሉ አብያተክርስቲያናት ውስጥ አንዱ ሊሆን የሚችል ሕንጻ ቤተክርስቲያን እያስገነባ ይገኛል፡፡

የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በተለያዩ ስራዎች ለተሰማሩ አስራ ሁለት ግለሰቦች  በወር 157,332 ወርሐዊ ኪራይ የሚያገኝ ሲሆን ከ7ሺህ ካሬ በላይ የሚገኝውን ቦታ ደግሞ  በካሬ ሜትር 5 ብር እስከ  8 ብር ከግለሰቦች እንዳከራየና   ወርሃዊ ኪራይ እንደሚሰበስብ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ 

Sunday, March 27, 2016

አፋን ኦሮሞ ከልሳነ ግእዝ ያገኘው በረከት


ከሪፖርተር ጋዜጣ ፡- ሔኖክ ያሬድ
የራሷ ፊደል ያላት ኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ታሪኳ የሚመዘዘው በተለይ በመጀመሪያው ምታመት በአክሱም አካባቢ ነው፡፡ ከብራና (ቆዳ) እና ከወረቀት በፊት በድንጋይ ላይ በሚጻፍ ጽሑፍ የወቅቱ ገጽታና የነገሥታቱ ዜና መዋዕል በግእዝ፣ በሳባና በግሪክ ቋንቋዎች ይዘገብበት ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ልዩ ክፍሎች መተርጐም በተጀመረበት ጊዜ ከድንጋይ ወደ ብራና ሽግግር ሲደረግ በርካታ የሃይማኖትና የሥርዓት መጻሕፍት ተጽፈዋል፡፡

Saturday, March 19, 2016

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሀፍ አስመረቀች




አዲስ አበባ መጋቢት 102008 (ኤፍ..) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሀፍን ዛሬ አስመረቀች። መጽሀፈ ቅዳሴው የቋንቋው ተናጋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች በቀላሉ እንዲረዱትና እንዲያስቀድሱ የተዘጋጀ ነው። 10 ዓመት ያህል በፈጀው በዚህ የትርጉም ስራ ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጻጻሳትና ሊቃውንት እንድሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተሳትፈውበታል። 516 ገጾች ያሉት መጽሀፈ ቅዳሴው 14ቱን የቅዳሴ ሂደቶች ያካተተ መሆኑም ተነግሯል።

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን አቀፍ ሆና በእኩልነት የምታገለግል መሆኑን ገልጸው፥ በቀጣይ በሌሎች ቋንቋዎች ይሀው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በምረቃው ላይ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችና የክልሉ ተወላጆች ተገኝተዋል።
 


አይን ያወጣ ዝርፊያ



source :- Addis Admass



  • ሥራ አስኪያጁ በልጃቸው ሕክምና ስም የሚያሰባስቡት ገንዘብ ተቃውሞ ገጠመው

      በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያበሚል ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ ከእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ግማሽ ሚሊዮን ብር በርዳታ እንዲሰጣቸው መወሰኑን የተቃወሙት የገዳሙ ሒሳብ ሹም ከሥራና ከደመወዝ መታገዳቸውን ገልጸዋል፡፡