Tuesday, November 29, 2011

ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው

  • ‹‹The African Men for Sexual Health and Rights (AMSHeR)›› ብሎ የሚጠራ የዚህ ቡድን/ድርጅት ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ግብረሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወትና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ 
  • የውይይቱ መሪ ቃል ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነት›  (Claim, Scale-Up and Sustain) በሚል መሪ ቃል ኅዳር 23 ቀን 2004 .ከጧቱ 2 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል ድረስ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሔዳል
  • በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል ነው
  • ግብረሰዶማዊው የኬንያው ተቋም ኢሽታር ካነገበው ዓለማዎች መካከል በግብረሰዶም ዙርያ የአቻ ለአቻ ትምህርት የኬንያን አምሳያ በኢትዮጵያ ማዳረስ እንደሆነ አመልክቷል
  • ስብሰባው 15 አገሮች ላይ በጤናና በግብረሰዶማዊያን መብቶች ዙርያ የተዘጋጁ ተሞክሮዎች ይቀርብበታል

የአለቃ አያሌው ታምሩ መፃህፍት እንዲቃጠሉ ተጠየቀ


  • የሚገርመው መፅሀፉ እንዲቃጠል የተጠየቀው በልጆቻቸው አማካኝነት ነው፡፡

(አንድ አድርገን ፤ ህዳር 18 2004 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ እና በርቱዕ አንደበታቸው እጅግ ተደማጭና ተወዳጅ የነበሩት የታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው መፃህፍት እንዲቃጠሉ ተጠየቀ፡፡ ለሐገርና ለወገን የሚጠቅሙ አያሌ መፅሀፍትን የተረጎሙ እና ያሳተሙ ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ከሶስት ሺህ ዘመናት በላይ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ልዕልና ከፍተኛ ስተዋፅኦ ባበረከተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያ ውስጥ ዛሬ የሚታየውን የአስተዳደርና ሀይማኖታዊ ችግር ከማንም በፊት አስቀድሞ በግልፅ ሲቃወሙና ሲያወግዙ የኖሩ ናቸው፡፡

Monday, November 28, 2011

ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን


  • በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በአካባቢው ሙስሊሞችና ፖሊሶች የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አፈረሱ 
 (አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤2004 ዓ.ም  November 29 2011 ) በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አርብ በ15 /03/04 በሙስሊም ፖሊስ አባላትና እነርሱን ከሚመስሏቸው ማህበረሰብ አካላት ጋር ሆነው ቤተክርስትያኗን ያፈረሷት ሲሆን ፤ በአካባቢው የሚገኝ ታማኝ ምንጭ ለማወቅ እንደቻልነው የቤተክርስትያኒቷ ጉልላት በፖሊስ አዛዡ ግቢ ውስጥ መገኘቱን በዓየይናቸው ተመልክተዋለል ፤ በዞኑ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ አማኞች የሚደርስባቸው ግፍ አስመክቶ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ትናንት በ18/03/2004 ዓ.ም ማለዳ በደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅ/ቤት ክርስቲያኖች ለአቤቱታ በአምስት መኪና የሄዱ ሲሆን :: አቤቱታ አቅራቢዎች የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ቃል አቀባይ የሆኑት እስከ 10 ሠዓት ድረስ ሲሳለቁባቸው ውለው ያለ ምንም መፍትሄ ሸኝተዋችዋል:: አቤቱታ አቅራቢዎቹ ተመልሠው ወደመጡበት አካባቢ ቢመለሱ የመኖር ህልውናቸውናቸው አስጊ በመሆኑ በመጀመሪያ የደቡብ ክልል ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ከዞኑ ፖሊስ ለሚደርስባቸው ጫና ገለልተኛ በሆኑ ፖሊስ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቀጥሎም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ በባዶ ሆዳቸው መሪር እንባ እያነቡ ሲናገሩ ላያቸው ያስለቅሱ ነበር፡፡›› በማለት ዘግቦልናል ፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የሀገረሥብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀሌምጦሰም ለሚመለከታቸው ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ከደሴ ደብረ ቤቴል ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምረቃ የቀሩት አቡነ ጳውሎስ የጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መረቁ


  • መኖሪያ ቤቱ ብር 1.5 ሚልዮን ያህል እንደወጣበት ተነግሯል 
  •  አቡነ ጳውሎስ ያለጥንቃቄ ባደረጉት ጉዞ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል 
  •  “አይ ቅዱስነትዎ፣ ተዋረዱ!! አሁን ይህ ለእርስዎ ክብር ነውን? የመቂ ሕዝብ እርሱን [ጌታቸው ዶኒን] ከእኛ የተሻለ ጠንቅቆ ነው የሚያውቀው፤ እንግዲህ የጌታቸው ዶኒ ጓደኛ ነው የሚልዎ!” /አቡነ ጎርጎርዮስ በድርጊቱ ማዘናቸውን ለአቡነ ጳውሎስ የገለጹበት መንገድ/
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 15/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 25/2011/ )ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ኅዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት መቂ ከተማ ተገኝተው የሊቀ ካህናትጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መርቀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ 98 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው መቂ ከተማ ከድልድይ በላይ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በ400 ሜትር ካሬ ስፋት ያረፈውና በ‹ሀ› ቅርጽ የተገነባው የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቪላ 1.5 ሚዮን ብር ማውጣቱን ግለሰቡ በምረቃው ዕለት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ባቀረበው አጭር ሪፖርት ገልጧል፡፡ በምረቃው ላይ በግለሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው 200 ያህል እንግዶች የታደሙ ሲሆን ድግሱም ሞቅ ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

Thursday, November 24, 2011

አስደናቂው የ666 ዓርማ

ታዲዎስ ግርማ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ  ባችለር ድግሪ ተመራቂ እና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የመልቲካልቸራል 2ኛ ዓመት ማስተርስ ተማሪ ሲሆን ስለ ‹‹አስደናቂው የ666 ዓርማ›› የፃፈውን ከእንቁ መፅኄጽ ላይ እንድታነቡት አቅርበንላችዋል::

ከፅሁፉ ተወሰደ.....
.......በዚህው በስደተኛ ካምፕ ውስጥ ሰውነቱን እያሻሸ እና በሰውነቱ እየገለጠ  የ666ን ተአምር የሚያሳየው ዮሴፍ የማነ ብርሀን ይባላል፡፡ የተወለደው በኤርትራ ሲሆን ለ41 ዓመታት የ666 መንፈስ አባል የነበረ ነው፡፡ ገና በእናቱ ማህጸን እያለ ርኩስ መንፈስ እንደተጸናወተው የሚናገረው ዮሴፍ ምግቡም እሳት እና አመድ ነበር፡፡ የግብረሰዶምን ምግባር በምስራቅ አፍሪካ አስፋፍቷል፡፡ ኤልዛቤል የምትባል መንፈስ እንደተቆራኝችው እና በዓለም ላይ አለች የተባለች ቆንጆ ብትመጣ ለዮሴፍ ሴት ሆና አትታየውም ፤ ሊነካትም አይፈልግም፡፡ እርሱ ዝሙት የሚፈፅመው ከ……………                            
click read more to continue

እኛስ ከእህታችን ምን እንማራለን ?

(by Wubishet Tekle) ቢመሻሽም ጻድቁ አባታችን ተክለሀይማኖትን ተሳልሜ ልምጣ ብዬ ወደ ደብረ አሚንተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ፤ ወርሃዊ በዓላቸው እንደመሆኑ መጠን መግቢያው በር ላይ ግርግር አለ፤ አንዲት ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ጧፍ የምትሸጥ ነጋዴ ጋር አንዲት ነጠላ የተከናነበች ወጣት ጧፍ ለመግዛት ቆማለች፤ እኔም አጠገባቸው ነኝ “ወንድም ይቅርታ አለችኝ’’ ወጣቷ፤ “አቤት” አልኳት “እኔ ስለማልገባ ነው ይህንን ጧፍ ስጥልኝ” አለችኝ፤ “እኔም ተሳልሜ ነው የምመለሰው ለሚገባ ሰው ስጪው” አልኳት፤ እሺ ለሚገባ ሰው አንተ ስጥልኝ አለችኝ፤

Wednesday, November 23, 2011

አባ ሰረቀብርሃን በሎስ አንጀለስ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

  • ታቦት ሰርቀዋል ፤ ተይዘዋል፡፡
  • ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን ፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
አባ ሰረቀ ማን ናቸው? ከዚህ በፊት ያልተሰሙ ወሬዎች ያንብቡት
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ ለማለት ቢያስቸግርም የቤተክርስቲያናችን ሥርዓት፣ የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ አንቱ በማለቱ እቀጥላላልሁ ። አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበት ሎሳንጀለስ ከተማ) ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈዋቸው ስለሄዱ አባ ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል ። አንዲ የቤተክርስቲያናችን አዛውንትማ ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው ነው የሚያንገሸግሻቸው። 

ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ በሎሳንጀለስ እንዴት ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦ 

የቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹ ሰብኣዊ ገጽ ››


ከዕንቁ መፅሄት 4ተኛ ዓመት ቁጥር 54 ላይ ያገኝነውን እናካፍላችሁ
  • ምዕመኑ ለሚቀጥለው ትውልድና ስለነገይቱ ቤተክርስትያን ህልውና ሲጨነቅ አንዳንዶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዛሬ ሊያገኙት ስለሚጓጉት ተጨማሪ ሹመት ፤ ቤት ፤መኪና ፤ እንቅልፍ አጥተው ይጨነቃሉ ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰብአዊ ገፃቸው ወደ ማህበራዊ ትህምክተኝነት እንዲዘቅጡ አድርጓችዋል ፡፡ ምጣኔ ሀብታዊ ቅርምት ውስጥም ከቷችዋል፡፡
  • በቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ልዕልና ቀጣይነትና ተከታታይነት ባጣበት ፤ አይናችንን አበው ረሀብ በሚሰቃይበት በዚህ ዘመን ሁሉ አቀፍ ታሪኮች ያስፈልጉናል፡፡ አለበለዚያ ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሰብአዊ ገፅ እያየለ ሄዶ ሲኖዶሳዊ ይዘቱን እና ቅርፁን እንዳያሳጣን እንሰጋለን ፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ይህው ነው፡፡ በዚህ ዘመንም ቤተክርስትያኒቱ የሚሞቱላትን ብፁአን አበው አጥታ እንደማታቅ ሁሉ የሚያዋርዱአትንም ተቸግራ አታውቅም ፡፡

ጥቅምት 11 በቅድስተ ማርያም

Tuesday, November 22, 2011

ጾም

እንኳን ለፆመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ

(ከአለቃ አያሌው ታምሩ በ1953 ዓ.ም ታትሞ ከወጣ መፅሀፍ የተወሰደ)ሙሉውን በ PDF ያንብቡ
ጾም በብሉ ኪዳን በተወሰነ ባልተወሰነ ጊዜም  ይፈፀም ነበር፡፡ በሀዲስ ኪዳን የዘወትር እና የተወሰነ ፆም አለ፡፡ የፆም መሰረቱ ‹‹ቀድሱ ጾመ ወሰብኩ ምህላ››  ‹‹ፆም ለዩ ፤ ምህላ ያዙ›› የሚለው ነው ፡፡ ኢዩ 2፤16 ፆም በብዙ ወገን ስለሆነ ክፉ ከማየት ዓይንን ፤ ክፉ ከመስማት ጆሮን ፤ ክፉ ከመስራት እጅን ፤ ወደ ሀጥያት ከመሄድ እግርን ፤ ክፉ ከመናገር ምላስን ፤ ክፉ ከማሰብ ልብን መከልከል ታላቅ ፆም ነው ፡፡ ስራውም ከፍፁምነት በላይ ነው፡፡

ቅኔ በቤተክርስትያን

‹‹ቅኔ በቤተ ክርስቲያናችን የሚስጢራት ማብራሪያ መተንተኛ ሲሆን ይህን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሀብት እንዳይጠፋ ታላቅ መሰዋእትነት የከፈሉ አባቶቸን አምላክ የባርክልን እያልን አያንዳንዳችንም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የምትጠብቅብንን ኃላፊነት እንድንወጣ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን አሜን፡፡››
በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
click read more to continue

Monday, November 21, 2011

ቤተክርስቲያኑ አሁንም የእኔ ነው ወደፊትም የራሴው ነው ( አቡነ ፋኑኤል)

የደብረ ምሕረት የትላንትናው ትዕይንት ይሄን ይመስል ነበር
  • እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው:: 
  • 14 ዓመት ደክሜ ከሰራሁት ቤቴ የትም አልወጣም ::
  • ወደዳችሁም ጠላችሁም ከዚህ የትም አልሄድም:: 
  • አዎ አዲስ አበባ ላይ ቪላዎች ቤቶች አሉኝ፣ ያንን ትቼ ይህንን ህዝብ ላገለግል መጣሁ::
  • ከዋሺንግተን ዲሲ እስከ ካሊፎርኒያ የኔ ግዛት ነው::
  • ከዚህ በኃላ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ መፃተኛ የሚባል ቤተ ክርስቲያን የለም

    በትላንትናው እለት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ላይ የተገኙት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ላይ  እንዳደረጉት ‹‹ምንም የምታመጡት ነገር የለም ፤ እኔን የላከኝ ቀበሌ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስ ነው›› በማለት ለበዓል የታደመውን ምዕመን አስገርመውት ውለዋል። 

200,000 ብር ፡- የአቡነ ሺኖዳን ሲመተ በዓል ለማክበር


አቡነ ጳውሎስ ከሌሎች ስድስት ሊቃለ ጳጳሳት (ብፁእ አቡነ እዝቅኤል ፤ አቡነ ገሪማ ፤ አቡነ ቆውስጦስ ፤ አቡነ ጎርጎርዮስ ፤ ብፁእ አቡነ ያዕቆብ) ጋር በመሆን በተማረ እና በአግባቡ በተደራጀ የሰው ሃይል የምትመራው የኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብተክርስትያ አባት በሆኑት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 40ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ላይ ለመገኝት ባለፈው ቅዳሜ ከቀትር በኋላ ወደ ግብፅ ካይሮ አምርተው ነበር፡፡ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ጉዞውን እንዲቀላቀሉ በፓትርያርኩ ቢጋበዙም ግብዣውን እንዳልተቀበሉት ታቋል፡፡ ለጉዞ ክብር ከ200,000 ብር በላይ ወጪ መደረጉን የታወቀ ሲሆን አቡነ ጳውሎስ በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የሚከበረው 20ኛ በዓለ ሲመታቸው ላይ እንዲገኙ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን ይጋብዛሉ ተብሎ ይጠበቃለል፡፡


እኔ እግዚአብሔር ፈቅዶ ብዙ የገጠር አብያተክርስትያኖችን ለማየት ችያለሁ ፤ ሁሉም ጋር ስመለከት ስር የሰደደ ችግር እንዳለባቸው ጧፍ ፤ እጣን ማግኝት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መድረሳቸውን ለመገንዘብ ችያለሁ ፡፡ ቤተክህነቱም ለእነዚህ ቤተክርስትያናት ምንም አይነት እርዳታ ለመስጠት ፍቃደኝነት ይጎለዋል ፤ ነገር ግን ይህው በሆነው ባልሆነው ነገር የቤታችን ብር እየተመዠረጠ ይገኛል፡፡ ምንም ማለት አልፈልግም ‹‹ለሁሉም ግን ልብ ይስጣቸው›› ብያለሁ፡፡

ሙታን እፎይ ማለት አልቻሉም


አሁን ባለንበት ሰዓት ብዙ ለጆሮ የሚከብዱ ፤ ለማመን የሚያስቸግሩ ፤ ሰዎች ያደርጓችዋል ብለን የማንገምተው ነገር ሁሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ማህበረሰባችን ምን አይነት ዝቅጠት ውስጥ እንደገባና ፈሪሀ እግዚአብሔር የሚባልመም ነገር የሌለበት ሆኗል፡፡ ሰው በምድር ላይ እግዚአብሔር ፈቀደለትን ዘመን ይኖራል፡፡ ‹‹አፈር ነህና ወደ አፈር›› ስለተባለ ከባለቤቱ ጥሪ ሲደርሰው ፤ መልአከ ሞት ከተፍ ሲል ፤ ይችን ምድር ተሰናብቶ ስጋው ከነፍሱ ተለይታ ይህችን ዓለም ይሰናበታል፡፡ ወዳጅ ዘመድ ይሰበሰባል ይለቅሳል ፤ ይታዘናል ግብአተ መሬት ይፈጸማል ፤ 

Saturday, November 19, 2011

የሴት ራስ - ወንድ


(by Birhanu Admass Anleye )እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለጊዜዉ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የሃይማኖት ዐምድ ‹‹ሃይማኖት እና ሴቶች›› በሚለዉ የመወያያ ርእሰ ጉዳይ ላይ ከእኛ እምነት አንጻር ያቀረብኳትን ትንሽ መጣጥፍ እነሆ ብያለሁ፡፡


ቤልጄየም ዉስጥ በምትገኘዉ የአንትወርፕ ከተማ አይሁድ ይበዙባታል፡፡ በዚሁ ምክንያት በዚያ ሀገር ሱቆች እንኳ ሳይቀር በብዛት የሚይዙት ለአይሁድ የሚሆኑትን ልብሶችና ሌሎች የእነርሱን ፍላጎት የሚያሟሉ ነገሮች ነዉ፡፡ ምክንያቱም በዚያ ለሁለት ሺሕ ዐመታት በተሰደዱባቸዉ ቦታዎችም ባሕላቸዉንንና ዕሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ የሚኖሩ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ የተማሩት ትምህርትና የደረሱበት ሥልጣኔና ዘመናዊነት ምንም ያህል ተጽእኖ እንዳያመጣ አድርገዉ መቛቛማቸዉም ሥልጣኔና ዕሴትን አንዴት አስታርቆ መሔድ እንደሚቻልም ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡

Thursday, November 17, 2011

አቡነ ፋኑኤል በአሜሪካ አጎዛ አንጥፉልኝ እያሉ ነው

  • አቶ በጋሻውን ይዘው ለመሄድ ብዙ ጥረቶችን ለማድረግ ቢሞክሩም የተሳካላቸው አይመስልም፣ ነገር ግን እርሱን ለማምጣት የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉም ቅዱስ ፓትሪያሪኩም ቃል እንደገቡላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
  • በቤተ ክርስቲያኑ አካባቢም ምዕመናኑ፣ አገልጋዮች ካህናት እንዲሁም ዲያቆናት ለሁለት ተከፍለዋል፡፡
  • ህዳር ፲ ቀን (Nov. 20, 2011) ማለትም የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግስ እለት ታላቅ የሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞ ይደረግባቸዋል፡፡
  • ሕዝቡ እንደተቀበላቸው አስመስለው "ሕዝቡ ተቀብሎናል ሃሳብ አይግባችሁ" ብለው ፕሮፓጋንዳቸውን ለመሥራት እና ወደ ኢትዮጵያም ለመላክ ቅድመ ዝግጅትም እያደረጉ ነው፡፡

 03/11/2011 ከቀትር በፊት አቡነ ፋኑኤል በድብቅ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ገብተው ማደራቸው ታውቋል፥ በገቡበት ዕለት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ተገምቶ ስለነበር ቀድመው ለሰዎች ሐሙስ ብለው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ አስነግረው  ነበር ነገር ግን እሳቸው ሰኞ ከእኩለ ቀን በፊት ማንም ሳይሰማ ወደ ከተማው ገብተው አድረዋል። በዚሁ እለት በቨርጂኒያው

አወዛጋቢው ሲዲ

አነጋጋሪውን ሲዲ አግኝተነዋል ይመልከቱት




  • አሁን የደረሰን ወሬ ከዴላ የነትዝታው እና በጋሻው ደጋፊዎቻቸው ህዳር ሚካኤል ለ3 ቀን ጉባኤ ለማድረግ ይፈቀድልን ብለው አቡነ ጳውሎስ ጋር እንደመጡ ለማወቅ ችለናል..ይፈቅዱላቸው ይሆን? አብረን እናያለን:: 
  • በየዓመቱ ሲፈነጩበት የነበረው ህዳር 12 ጉባኤ የቅዱስ ሚካኤል ሳይሆን የትዝታው ጉባኤ በመባል ነው የሚታወቀው
ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያሳይ የ 20 ደቂቃ ቪሲዲ ለዛሬ አቅርበንላችኋል

Wednesday, November 16, 2011

ለሰባኪያን ፈቃድ ለመስጠት ጫፍ ተደርሷል



ከ2 ወር በፊት ለሃይማኖት ሰባኪያን ፈቃድ ሊሰጥ ነው በማለት መዘገባችን ይታወቃል ፡፡ በደረሰን መረጃ መሰረት በቅርብ ቀናት ውስጥ ፈቃዱን የመስጠት ሂደቱ እንደሚከናወን ለማወቅ ችለናል፡፡ የበፊት ዜናውን ለማንበብ



መስከረም 9 እና 10 የተለያዩ የእምነት የተቋማት አባቶች በሂልተን ሆቴል ተገናኝተው ስለ ሰባኪዎቻቸው በምን አይነት መንገድ የራሳቸውን እምነት ማራመድ እንደሚችሉና ፤ በመካከላቸው ያለውን ክፍተት እንዴት ወደ ወንድማማችነት መቀየር እንዳለባቸው፤ ያለውን ልዩነት ማጥበብ የሚችሉበትን መንገድ መንግስት ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ተወያይተው ውሳኔ ያሳለፉበት አንዱ ነጥብ ለሰባኪዎቻቸው ከመንግስት ጋር በመተባበር የሰባኪነት ፍቃድ እንደሚሰጧቸውና ይህን የፍቃድ መታወቂያ ያልያዘ ሰባኪ እምነቱን ወክሎ በየትኛውም አውደ ምህረት ላይ እንዳይሰብክ የመግባቢያ ሀሳብ ላይ ደርሰው ነበር፡፡

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ፤ ፊሊጶስ Vs የዘመኑ ሰባኪዎች

  • እነሆም እናንተ በአለማዊ እና በግል ጉዳይ ተጠምዳችሁ ያላችሁ ሰባኪያን ሆይ፡- መንፈሳዊ ግዴታችሁን ልትወጡ ይገባችኋል፡፡ ከቶስ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ አስተማሪ ለእኛ እንዴት ሊገለጥልን ይችላል? እናንተ ካላስተማራችሁን እንደ ፊልጶስ ካልተረተራችሁልን ቅዱስ ቃሉን እንዴት ልናስተውለው እንችላለን? 
(አንድ አድርገን ህዳር 6 2004 ዓ.ም) :- የጌታም መልአክ ፊልጶስን፡- ‹‹ተነስተህ በደቡብ በኩል ከእየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ›› አለው፡፡ ተነስቶም ሄደ፡፡ እነሆም ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግስት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሰለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳለም መጥቶ ነበር ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነብዩን የኢሳያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር፡፡ መንፈስም ፊሊጶስን፡- ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው፡፡ ፊልጶስም ሮጦ የነብዩን የኢሳያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና በእውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን? አለው፡፡ እርሱም፡- የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? አለው፡፡ ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው፡፡ ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፡-