Friday, September 23, 2011


ለሃይማኖት ሰባኪያን ፈቃድ ሊሰጥ ነው!!!!


  • በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በኩል ፈቃድ የሚያገኙ ሰባኪያን በአብነት ትምህርት ቤት የተማሩ ወይም ከመንፈሳዊ ኮሌጆች በዲፕሎማ ወይም በዲግሪ የተመረቁ ብቻ ይሆናሉ፡፡
  • በተሰጠው ፈቃድ በአግባቡ የማያገለግል ሰባኪ ፈቃዱን እስከ መቀማት የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡
ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም ታትሞ የወጣው ነጋድራስ ጋዜጣ ቅጽ 08 ቁጥር 297 የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የሠላም እና የምክክር ጉባኤ መስከረም 9 እና 10 በሒልተን ሆቴል ‹‹ፈቃድ በሌላቸው የሃይማኖት ሰባኪያን›› ላይ መምከሩን ዘግቧል፡፡

የየሃይማኖት ተቋማቱ ተወካዮች በሃይማኖት ሰባኪያን ዙርያ ያለውን አሰራር ለማስተካከል በሚቻልብት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሰባኪያነ ወንጌል የአገልግሎት ምስክር ወረቀት እንደምትሰጥና ይህንንም የምስክር ወረቀት የሚያገኙት የአብነት ትምህርትና የትውፊት ትምህርት ያላቸው በሥነ መለኮት በዲፕሎማ ወይም በዲግሪ የተመረቁ መሆን እንደሚኖርባቸው ተገልጧል፡፡
‹‹በየቤተ ሃይማኖቱ ለሃይማኖት ትምህርት ወጥቶ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ሰባኪ ወይም በዳይ ጥፋቱ በተጨባጭ ከተረጋገጠ ፈቃዱን በሰጠው የሃይማኖት ተቋም ከጥፋቱ እንዲታረም ይደረጋል፡፡የማይመለስ ከሆነ ፈቃዱ እንዲሰረዝ ተስማምተናል፡፡›› ያሉት የጉባኤው ተሳታፊዎች ‹‹የሚሰጠው ፈቃድ በተወሰነ ጊዜ መታደስ እንዳለበት አስገንዝበዋል ››ሲል ነጋድራስ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በሜቲ ኤጄታ (memettiej1@gmail.com)


1 comment:

  1. This is the good one. I love it. Otherwise those illegal sebakiyan will play like something in the church.
    me from 4 kilo

    ReplyDelete