- ‹‹ጳጳሱ ፈሪ ናቸው አስፈራሯቸው››…..አቶ በጋሻው ደሳለኝ
- ‹‹ወንጌል እና ቅዳሴ አንድ ነው ››………ብጹዕ አቡነ ያሬድ
- በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ላይ ጫማዋን የወረወረች ቀንደኛ ሴትን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ተሐድሶዎች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል
‹‹ እኛ ምርጦቹ የሪያል ማድሪድ ቡድን ነን››
አቶ በጋሻው ደሳለኝ ከሮያል መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ
የምስራቅ ሐረርጌ እና የሱማሌ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንድሁም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በሐረር እየተካሔደ ያለውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ በመገምገም ጠንከር ያለ የማስተካከያ ውሳኔ በማስተላለፋቸው መስከረም 5 ቀን 2004 ዓ.ም ቁጥራቸው ከሃያ የማይበልጡ የቀድሞ የተሐድሶ አባላት(ዕጓለ ፀራዊ) ሊቀ ጳጳሱ ድረስ በማምራት ክርስቲያዊ ትውፊቱን ያልጠበቀ የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር ያልጠበቀ የተቃዎሞ ድምጽ አሰምተዋል፡፡
ሀገረ ስብከቱ ለየአጥቢያው ያስተላለፈውን መመሪያ በተመለከተ በከተማው ከተውጣጡ የተሐዲሶ መናፍቃን አቀንቃኞች የቀረበ የጽሁፍ እና የቃል አቤቱታ
1. መመሪያው እንዲነሳልን በቅዱስ ፓትርያርኩ የተጻፈው ደብዳቤ እንዲተገበር
2. መመሪው መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ ጉዳይ ነው፡፡
መናፍቃን በበዙበት ወቅት እኛም በዝተን መገኘት ሲገባን ይህ መመሪያ በመውጣቱ እናዝናለን፡፡በመቀጠልም የነበረውን ችግር ተረድተው በመልዓከ ሰላም ጴጥሮስ የተሰጠው የደሞዝ ማስተካከያ መልስ በቂ ነው ፡፡ የቀድሞውን (1987 ዓ ም) በማንሳት አባቶችን እየገፉ በድንች ማኅተም በማሳሳት ወኅኒ ቤት ሊያወርዱአቸው ነበር፡፡ አሁንም አባታችን ሆን ብለው ሕዝቡን ለመበተን የሚሮጡ አሉ፡፡
አዋሳ የተፈጠረው ችግር ከዚህ ሄደው ነውና ምንም መጣ ምን ሐረር ከተማ ላይ ወንጌል አይቁዋረጥም፡፡ሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉትን የስራ ኃላፊዎች እስከ ሞት ድረስ እንፋለማለን ፤የደፈረሰው አሁን መጥሪያው ጊዜ ደርሶአል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ቢሞቱም አሁንም በክፉ ስራቸው ይነሳሉ፡፡አቡነ ይስሐቅ እሾህ ተክለው ሄደው እስከ አሁን ድረስ እንፋለማለን፡፡ ስለ ወንጌል እና ስለ ኢየሱስ መስዋእት እንከፍላለን፡፡
በሐረር ደብረ ሳህል ቅ/ሚካኤል መድረከ ላይ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ተፋልሷል፡፡
የበፊቱን ማለትም በ1987 ዓም የነበረውን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በማስተወስ ብዙ ገንዘብ የተገኘው ቤ/ክ የተሰራው ሕንጻ የሚሰራውም በሕዝብ ነው ፡፡ የወጣው መመሪያ ስብከተ ወንጌልን የሚያጠናክር ሆኖ አላገኘነውም ፡፡
ባለፈው ዓመት ገብርኤል ላይ በተደረገው አውደ ጥናት (የአውደ ጥናቱ ርዕስ” በሐረር ከተማ የሚደረጉ ታላላቅ ጉባዔያት ምዕመናንን ከማነጽ አንጻር ያላቸው ፋይዳ እና ድክመቶቻቸው” የሚል ነበር ) ጥሩ ያልሆነ መልዕክት ሰምተናል አሁንም ያንን ነው እየሰማን ያለነው፡፡ ቁልቁል እንድወርድ ተደረጓል፡፡ መድኃኔዓለም በ2002 ዓ.ም የነበረው የምዕመናን ቁጥር 4000 ነበር፡፡በአንድ ዓመተ ልዩነት 2000 ደርሷል፡፡ በብዙ የቆሰለ ምዕመን እንክብካቤ ያስፈልገዋል እንደ በፊቱ ሸሽተን ሳይሆን ሞተን እናስከብረዋለን፡፡
የሀገረ ስብከቱ ፀሐፊ በአቡነ ዜና ማርቆስ ጊዜ ያቀረቡት መወድስ ጦርነትን ባርኩልን የሚል ነበር፤ ንስሐ ገብተዋል ወይ? በብዙ ነገር አድምተውናል ፤አሁን ግን ሲያደሙን መኖር አይችሉም፡፡
ብፁዕነታቸውንም በመተቸት ‹‹በታላቅ ጉባኤ ላይ መጥተው ሲባርኩን አላየንም ይህንን ያስተካክሉ›› ሲሉ ድፍረት በተሞላበት አንደበት ሲናገሩ ተሰምተዋል ፡፡ መድኃኔዓለም በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ 400,000 ብር በመገኘቱ የደነገጡ አሉ፡፡ ከመዋጮውም ያለተሳተፉ ማኅበራት አሉ፡፡ ይህም ጥያቄ ውስጥ አስገብቶናል፡፡
‹‹የሀረርም ሆነ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሰባክያነ ወንጌል አይመጥኑንም፡፡በዓመት ሁለት ጊዜ ለሚደረገው ጉባዔ የሚደግሰው ሰበካ ጉባኤው ነው፡፡ የስብከተ ወንጌሉን ኮሚቴ መበተን ነው ምን ያደርጋልም›› ብለዋል፡፡
የአመጽ ድምጹ በመሰማት ሂደት ላይ እያለ በመሐልም በሀረር ምዕመናን ዘንድ ሄሮድያዳ በሚል የተሰየመችው እና ገንዘብ በመሰብሰብ የእነበጋሻውን የebs ፕሮግራም እስፖንሰር በማድረግ ብቻ የሚታወቀው የማኅበረ እስጢፋኖስ አባልና አቡነ ዜና ማርቆስ ላይ ጫማዋን አውልቃ በመወርወር የምትታወቀው ባልቴት ‹‹በጌ›› ደወለ ብላ በመውጣት መመሪያዎችን ደጋግማ ስትቀበል ተስተውላለች፡፡ በዚህም ወቅት ምስጢር መቋጠር የማይሆንለት የቻይና የተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎ በጋሻው ‹‹ጳጳሱ ፈሪ ናቸው ስደቧቸው አንድ አራት ሆናችሁ አዲስ አበባ ኑ ስትመጡም ማኅበረ ቅዱሳን አሳደደን ማለት አለባችሁ›› የሚለውን የወቅቱን ፈሊጣቸውን አስጠንቶ ሲለቃት አሰምቷል፡፡
ሁሉንም በአጽንኦት ያዳመጡት ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች እና ማብራሪያዎች
በ2004 ዓም የተጻፈው ደብዳቤ ስህተታችንን የምናርምበት ነው፡፡ እናንተ ግን አቆላልፋችሁታል፡፡ ከላይ ወደ ታች ከዚህ ወደ ላይ ተጠላልፎአል፡፡ የሁላችንም እጅ አለበት፡፡የእናንተም እጅ ይኖርበታል፡፡ በዚያው በደብራችሁ ብትጠይቁ መልስ ታገኙ ነበር፡፡
በየዓመቱ የድግሪ እና የድፕሎማ መምህራን ለሀገረ ስብከቱ ይላካሉ፡፡ ያሉን ኮሌጆች ሦስት ናቸው፡፡ እነዚህ አልዋጥ ካሉአችሁ ሌላ ከየት ልታመጡ ነው?
በየሀገረ ስብከቱ የሦስት ወር ኮርስ እየተሰጠ ነው፡፡ ይህም ወደ ፊት ወደ ኮሌጅ ያድጋል፡፡ እነዚህንም አንቀበልም ካላችሁ ከየት ልታመጡ ነው? ሙሉ ጉባኤ ያለበት ሀገረ ስብከት ሀረር ነው፡፡ እነዚህን ያልተቀበላችሁ ማንን ልትቀበሉ ነው?
ሰዓቱስ የሰርኩ ጉባኤ ተራዘመ እንጅ ምኑ ነው የሚያዳክመው?
ብሔራዊ በዓል አለ፤ ቅዳሜ እና እሁድ አለ፤ ከ 10 ሰዓት ጀምሮ ትምህርት ቢሰጥ ሶስት ክፍለ ጊዜ አለ፡፡ ይህ አይበቃም ወይ? ይጨመር ካላችሁ እናየዋለን፡፡ ይህን ያደረግነው ከሩቅ የመጡ ሰዎች ችግር እንዳይደርስባቸው በማሰብ ነው፡፡
በክብረ በዓላት ዋዜማው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አልቆ የማህሌቱ ስርዓት ይጀምራል፡፡ ጠዋት በመድረክ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ሙሉ ቀን ማድረግ አይቻልም፡፡ ስለዚህ አስር ሰዓት ይጀምራል ይህ ያንሳልን? ቅሬጣችሁ ሦስት ቀን ይሁን ከሆነ በስፋት እናየዋለን፡፡
ወንጌል እና ቅዳሴ አንድ ነው፡፡ ወንጌል ሲነገር የምናለቅስበት የምንወቀስበት እንጂ እልልታ የምናቀልጥበት ጊዜ አይደለም፡፡ እልልታም ቦታ እና ጊዜ አለው፡፡
ለመሆኑ እግዚአብሔር እንደሰጣችሁ ሰርታችኋልን? ምን ሰርታችሁ ነው እንዲህ አደረግን እያላችሁ የምትመኩት?! ያደረጋችሁትን የሚመሰክርላችሁ አለ እናንተ አይደላችሁም፡፡ የመድኃኔዓለም ምዕመናን ቁጥር 4000 ነበር በአንድ ዓመት 2000 ቀነሰ ያላችሁትስ የዚያን ጊዜ ይህ መመሪያ ወጥቶ ነበር ወይ? በማለት ጥያቄ አዘል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ብጹዕነታቸው ማብራሪያውን ካጠቃለሉ በኋላ ‹‹አሁን ባለው የስራ መደራረብ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብሰባ እና የጥቅምት ሲኖዶስ ዐቢይ ጉባዔ ስላለብኝ ከጥቅምት ሲኖዶስ በኋላ መስተካከል ያለብት ጉዳይ ካለ እናስተካክለዋለን›› በማለት ማሳሰብ ሲጀምሩ አማጽያኑ ‹‹በ12 እና በ27 ጉባኤ አለ እንዴት ይሆናል?›› ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ‹‹እስከዚያው በወጣው መመሪያ መሰረት እንድካሄድ›› በማለት የተሰጣቸውን መልስ በመቃወም ‹‹እስከምንነጋገር ድረስ መምህራን እና ዘማርያን እናስመጣለን ያለበለዚያ የሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጉባኤውን ዘግተውት ሄዱ ይባላሉ›› በማለት ሊቀ ጳጳሱን በግብር አባታቸው በጋሻው አንደበት ለማስፈራራት ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡
በመጨረሻም ብጹዕነታቸው አስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ማብቂያ ድረስ ጉባዔያት በሀገረ ስብከቱ መምህራን አንዲሸፈኑ ወርሀዊ ጉባኤውም ለሦስት ቀናት እንዲሆንና መመሪያውም መከበር እንዳለበት በአጽንኦት ከአሳሰቡ በኋላ የስብሰባው ፍጻሜ ሆኗል፡፡
አጠቃላይ ሒደቱን የተከታተሉ ታዛቢዎች የአማጽያኑ ድምጽ በጋሻው በደቡብ ኢትዮጵያ ሞክሮ አልሳካ ያለውን የብጥብጥ ሴራ እንዲሁም በብጹዕ አቡነ ገብርኤል የቀመሰውን ውርደት ብጹዕ አቡነ ያሬድ እና ምሥራቅ ሐረርጌ ላይ ለማወራረድ እየጣረ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com)
yigermal
ReplyDeleteእግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ እኛም ነቅተን ቤታችንን እንድንጠብቅ እርሱ ይርዳን!!! አሜን::
ReplyDeletewey nitirik! by the way the gap and such raw could lead to infiltrators of enemies of Jesus. Please take care
ReplyDelete