በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ ከሃይማኖቷ አስተምህሮ እና ቀኖና ውጪ የሆኑ ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ይህንን ድርጊት በሚመለከት መምህር ተስፋዬ ሸዋዬን እንደ አንድ የእምነቱ ተከታይ ግለሰብ ያላቸውን ሐይማኖታዊ አስተያየት ሰጥተውናል፡፡
To read in Pdf .....click http://www.4shared.com/document/4L5K8CVd/memehir.html
To read in Pdf .....click http://www.4shared.com/document/4L5K8CVd/memehir.html
- ብዙዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ እምነት ጥንታዊ እና ባህላዊ እና ልማዳዊ አስተሳሰብ ያጠቃታል ይላሉ ፡፡ ይህ አባባል በእርስዎ አመለካከት ምን ያህል እውተኛ ነው ?
- በድርሳን በገድል በተዓምር ላይ የተገለፁ ታሪኮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተለይም ከወንጌል ጋር ይጋጫሉ ?
- የተዋህዶ እምነት አስተምህሮ ከዘመን እና ከስልጣኔ ጋር አብሮ መጓዝ አቅቶታል የሚል አስተያየት ይሰነዘራል፡፡ በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
- የተዋህዶ እምነት አስተምህሮ የተመሰረተው በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን በአዋልድ መፃህፍት ላይ ነው የሚሉስ ምን መልስ ይኖሮታል ?
click read more...
- የሚነቅፏቸው ከርዕይ ያልደረሱ ጣዕመ ፀጋ ያልቀመሱ ዐይኑ ግንባር ሆኖ እንደተፈጠረው የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ ግንባር የሆነው ዐይነ ነፍሳቸው በክርስቶሰ ጣት ያልተዳሰሰ በመለኮት ምራቅ ያልራሰ ሰዎች ናቸው፡፡
- በቁስጥንጥንያ ከሐድያን እና ሐሳውያን ጳጳሳት በየጊዜው እየተነሱ በዘሩት የሐሰት ትምህርት ታሽተው ሐይማኖታቸውን በየፈረንጁ አገር ጥለው ፈረጅያቸውን አንጠልጥለው የመጡ መነኮሳትና አጫፋሪዎቻቸው ይህች ቃል ስጋ መሆኑን የምታምንና የምታስተምር መንፈስ ቅዱስ ምስክሯ የሆነን ሃይማኖት አፍነው ፍጥረታዊ ተረታ ተረት እንዲላማ ቢያደርጉም ትጥላችዋለች እንጂ አትወድቅላቸውም፡፡
- የተቀደሰችው ደጅ (ቤተክርስትያን) ከዚህ በላይ መርከስ ማስተናገድ አትችልም:: ይህን የምናገረው ውጭ ስላሉ አፅራረ ቤተክርስትያን አይደለም ፡፡ በውስጥ ሆነው በውጭ ያሉትን ወደ ውስጥ ለማስገባት በር የሚከፍቱትን ፤ እያጎሳቆሏት ያሉትን ሰው እንዲነቃባቸው እንዳይስትላቸው ስለማስጠንቀቅ ነው እንጂ፣…
- ኢትዮጵያ ከነበራ የቀድሞ ስፋትዋ ቢያንስ አሁን ባለችበት ቅርፅና ይዘት እንድትቆይ በማድረግ ቤተክርስትያን ባለውለታ ናት እንጂ ሐገር ያደህየች አይደለችም፡፡ ከአድዋ ድል ወዲህ ብዙዎች ቂም ይዘውባታል::
I would like to thank you the bloger for your just in time information provision and your efforts to actualise it.
ReplyDeleteThis above post is not easy to be zoomed properly. would you mind to correct it please?
Thank you in advance!
Ortodox tewahdo is the sign(ID)of Ethiopia, she give everything for her,calendar,history, boundary,artitacrure ,medicine ,why say that?....ask the white people,what Ehthiopia is ? she is owner of different culture and heritage Ex: Lalibela,Axum...etc...these gift is:
ReplyDeleteTo Ethiopia
from :tewahdo
please ask your father , for who claim our church!!!
menew yehen sewye ande yemilew tefa? Ato Tesfaye erasu mane honena! eweket kaleserubet ende ariyose mehone new!
ReplyDeleteእባክህ ወዳጄ ስለማታውቀው ባታወራ ይበጅሃል.... ይልቁንም ለራስህ ስትል:: የተዋህዶ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑትን መምህር ተስፋዬን በዚህ ባልተገራ አንደበትህ ለማቃለል በመሞከርህ አንተው እራስህ እፈርበት::
Deleteእኔ የማውቀውን ስለማውቅ ያየሁትንም ስላየሁ ነው ይሄን የምለው :: ከእውነት ጋር መጋፋት እንዲህ ቀልድ እንዳይመስልህ.... የተጋፉትም ቢሆን እንደአመድ ቦነው ጠፍተዋል::እየጠፉም ነው:: የማወቅ ፍላጎት ካለህ ማወቅ እየቻልክ ስለማታውቀው ነገር ማውራት .............. እኔንጃ
አውነቱን ልንገር ስምህን ለመግለጽ ያፈርከው አስተያየት ሰጪ፡፡
Deleteበትረ ክህነት ያለው ሰው አይደለም መናገር ማርመሙ እራሱ የሚያስፈራ ነው፡፡ ምርመሙ እራሱ እራስን የሚያስት ነው፡፡ ቅዱስ አብርሃም ቅዱስ መልከ ጸዲቅን የእግዚያብሔር ሰው ሆይ፣ የእግዚያብሔር ሰው ሆይ፣ የእግዚያብሔር ሰው ሆይ፣ ብሎ ጠራው፡፡ ከዚያ በኋላ ጸጓር ሰው ወጣ፡፡ እንደ ቅዱስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰውነቱ በጸጉር የተመላ ሰው ወጣ፡፡ የዚህ ግዜ ደነገጠ፡፡ እሚሆነውን አጣ፡፡ እንደ ሞተም ሰው ሆነ፡፡ ክህነት በሐዋሪያትም ዘመን እንደዛ ነበረች፡፡ ቅዱስ መልከ ጸዲቅ በታየበትም ግዜ እንደዛ ነበረች፡፡ ክርስቶስም እራሱ ማንን ልትፈልጉ መታችኋል ብሎ በጠየቀ ግዜ ዧ ብለው ወድቀዋል፡፡ ወደ ገደል አፋፍ ላይ ወስደው ለመወርወር ሞክረው ነበር፡፡ ከዛ በኋላ እነሱ የሆኑትን አላወቁትም ክረስቶስ ግን በመካከላቸው ተመልሶ ወደ ነበረበት ሄደ፡፡
ከዚህ የተነሳ ክህነት አካሄዷና አሰራሯ እንዲህ ነው፡፡ ጉልበተኛ ናት፡፡ ባለስልጣን ናት፡፡ ጸጉርንም ጥፍርንም ሁለንተናን ጨምዳ የምትገዛ ናት፡፡ ስንብቷም አንዴ ለዘላለም ወደ ገነት ወደ ጽድቅ ፡፡ አንዴ ወደ ሲኦል ወደ ዘላለም ሃሳር ነው፡፡ ወደ ክብር ወደ ገነት ወደ ገነት ወደ ክብር፡፡ ወደ ሲኦል ወደ ሃሳር ነው፡፡
ከዚህ የተነሳ ክህነት የምትፈራ ናት፡፡ በዙፋኑ ላይ ያለ ንጉስ ቢሆን በካህን ፊት ከመመርመር የሚያመልጥበት የሚሸሽበት ምንም ነገር የለም፡፡ ሰራዊትም ሊያድነው አይችልም፡፡ የጦር መሳሪያም ሊያድነው አይችልም፡፡ በቅዱስ ኤልያስ ፊት የነበሩ ነገስታት የደረሰባቸው ይታወቃል፡፡ ቅዱስ ሙሴም ቢሆን ያደረገው ይታወቃል፡፡ የእግዚያብሔር ስልጣኑ አርፎባቸው የነበሩ ሰዎች ያደረጉት ይታወቃል፡፡
አባታችን መምህር ተስፋዬም ያቺ ትክክለኛዋ የቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ ስልጣነ ክህነት ከእግዚያብሔር የተሰጠችው ካህን ነው፡፡ እሱም ይክችን የክህነት ሹመቱን በልዑል እግዚያብሔር በግርማዊነቱ ችሎት በእግዚያብሔርነቱ ብርታት፣ በሥላሴ ቸርነትና በቅድስት ማርያም ተራዳኢነት አማላጅነት እስከመጨረሻው ህቅታው የጠበቀ ታላቅ አባት ነው፡፡ ልዑል እግዚያብሔር ምስክሬ ነው ብሎ ሲጠራው እግዚያብሔር በታየ በጎላና በተረዳ የመሰከረለት መምህር ነው፡፡
ታሪክ የማታውቅ ከሆነ ለትችት ምላስህን ከማውለብለብህ በፊት ገድል አንብብ፡፡ የቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ደቀመዝሙር የሆነው በኋላም ሶስተኛው የደብረሊባኖስ ገዳም አባ ምኔት ተደርጎ የተሸመው ቅዱስ አቡነ እጨጌ ፊሊጶስ በዘመኑ እውነትን አፍረጥርጦ ለንጉስም ቢሆን ተግሳጽን መስጠት ስለመረጠ የንጉስ ዳቦ ፍርፋሪ ለቃሚ አሽከሮች በሰነፈ አንደበታቸው፣ በስጋዊ ደማዊ አንደበታቸው ሲያጥላሉት ኖረዋል፡፡ እሱ ግን እንደ የቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ ስልጣነ ክህነትን ከልዑል እግዚያብሔር የተቀበለ ስለነበር በሰነፎች ምላስ አልተጎዳም፡፡ በስልጣነ ክህነቱ ተግቶ በሰራው ትሩፋት ትውልድ ዛሬም ወደ ፊትም ከልዑል እግዚያብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን ሲያውቀው ይኖራል፡፡
መምህር ተስፋዬም እውነቱን አፍረጥርጦ ስለነተናገረ ሁሌም ስለሱ ባሰባችሁ ቃሉን በሰማችሁ ግዜ እሳት እንዳየ ገለባ ትርበደበዳላችሁ፡፡ ደግሞም እወቁት የአብርሃም የይስሃቅ የያቆብ አምላክ ምን ግዜም ከመምህር ተስፋዬ ጋር አብሮት ነው፡፡ የሚናገረው አካላዊ እውነት ስለሆነ ቀጣፊዎችን ያስጨንቃል፣ የጸጸት ልቦና ያላቸውን ንስሃ እንዲገቡ ያደርጋል፣ እውነተኞችን በተግባር በትሩፋት ጸንተው እንዲጓዙ ያደርጋል፡፡
እና ወንድም አወኩኝ ብለህ ምላስህን ከላንቃህ ጋር ስታማታ ነብስህንም ስጋህንም መርገምት ውስጥ እንዳትከት!
መምህር ተስፋዬ እግዚአብሄር ይስጥልን::
ReplyDeleteአሜን
Deleteመምህር ተስፋዬ እግዚአብሄር ይስጥልን::አባታችን መምህር ተስፋዬ ቃለ ሕይዎትን ያሰማልን
ReplyDeleteእግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመኖዎን ይባርክሎት።
እግዚአብሔር ያክብርልን.!
Amen
Deleteመምህር ተስፋዬ እግዚአብሄር ይስጥልን::አባታችን መምህር ተስፋዬ ቃለ ሕይዎትን ያሰማልን
ReplyDeleteእግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመኖዎን ይባርክሎት።
እግዚአብሔር ያክብርልን.!
አባታችን መምህር መምህር ተስፋዬ እግዚአብሄር ይስጥልን::ቃለ ሕይዎትን ያሰማልን
ReplyDeleteእግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመኖዎን ይባርክሎት።
እግዚአብሔር ያክብርልን.!
መምህር ተስፋዬ እግዚአብሄር ይስጥልን::አባታችን መምህር ተስፋዬ ቃለ ሕይዎትን ያሰማልን
ReplyDeleteእግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመኖዎን ይባርክሎት።
እግዚአብሔር ያክብርልን.!