Tuesday, September 20, 2011

አለመታደል


ስለ ልጆቿ ችግር የሚያለቅስ አባት ያላት ቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት። በፈንታው ደግሞ ስለ እርሷ ማልቀስ ሳይሆን የሚያስለቅሷት፣ ስለ እርሷ የሚያዝኑ ሳይሆን የሚያሳዝኗት፣ ልጆቿን በእንባቸውና በትምህርታቸው አጥር መከታ ሆነው ከመጠበቅ ይልቅ ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሊለቀስላት ይገባል።
ስለ ልጆቻቸውና ስለ ቤተክርስትያን የሚያለቅሱ አባት

tears of Pope Shenouda

 http://www.youtube.com/watch?v=ESG-KO4QX88&feature=share

ቅዱስነታቸው ፖፕ ሽኖዳ 3ኛ 117ኛው የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው። እንደተለመደው ከምእመናን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሚመልሱበት የተለያየ ዝግጅት አላቸው። ከዝግጅቶቻቸው መካከል በየሳምንቱ በካይሮ በመንበረ ማርቆስ የሚያደርጉት አንዱ ነው። እነዚህን የምእመናን ጥያቄዎች So Many Years With The Problems Of People” በሚል ርዕስ እየታተሙ ለንባብ በቅተዋል። ጥያቄዎቹ ዶግማን፣ ሥርዓትን፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የተመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። መልሶቻቸው የማያወላዱ፣ በአጭር አባባል ብዙ መልስ የሚሰጡ ናቸው። አንድ ጥያቄ ግን በቃላት መልስ ከመስጠት ይልቅ በእንባና በዝምታ መመለስን መርጠዋል። ከንግግራቸው በአጭሩ እንመልከት።
“በቅርብ ቀናት ስለሆኑ ነገሮች ብዙ ጥያቄዎች (በጽሑፍ) መጥተውልኝ እየተመለከትኩ ነው” ሲሉ ጀመሩ ቅዱስነታቸው። በቅርብ ቀናት ሆነዋል ያሏቸው ነገሮች በአክራሪ ሙስሊሞች በተለያዩ የግብጽ አካባቢዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች እንዲሁም ወጣት ክርስቲያን ሴቶችን በግድ እያገቡ ማስለም እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን ማለታቸው መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ቀጥለውም እንዲህ አሉ..............
ስሙ ወንድሞቼ፤ ልናገረው የምሻው ብዙ ነገር በአእምሮዬ ነበረኝ። በልቤም ውስጥ ከዚያ የሚበልጥ ብዙ ነገር አለ። ይሁን እንጂ ዝም ማለትን እመርጣለሁ። እኔ ዝም ማለትን የመረጥኹት (በምትኩ) እግዚአብሔር እንዲናገር ስለምፈልግ ነው። እመኑ፤ ዝምታችን ከመናገር በላይ ገላጭ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ደግሞ ዝምታችንን እያዳመጠ ነው። እግዚአብሔር ዝምታችንን ይሰማል። የዝምታችንን ትርጉምና እየደረሰብን ያለውን መከራም ያውቃል። መከራ እየተቀበልንበት ስላለው ጉዳይ ነገራችንና ችግራችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን እንሰጣለን። በእጆቹም ላይ እንተወዋለን። እናም ‘ያንተ ፈቃድ ይሁን/ ወይኩን ፈቃድከ’ እንላለን። (ጌታ ሆይ) ‘ይህንን ችግር መፍታት ከፈለግኽ ፈቃድህ ይሁን፣ የመከራን መስቀል እንድንሸከም ከፈቀድክም… (ካሉ በኋላ እንባቸውን እያፈሰሱ አለቀሱ) “…ችግራችንን ለእግዚአብሔር እንስጥ/ እንተው ያልኩበት ምክንያት እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ/ የሚቆጣጠር ስለሆነ ነው። እርሱ ሁሉን ያያል። ሁሉንም ነገር ይሰማል። ሁሉንም ነገር ያውቃል።” 

ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? ስለ ቤተ ክርስቲያን ደኅንነት፣ ስለ ምእመኗ ጤንነት፣ ስለ ልጆቿ ችግር የሚያለቅስ አባት ያላት ቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት። በፈንታው ደግሞ ስለ እርሷ ማልቀስ ሳይሆን የሚያስለቅሷት፣ ስለ እርሷ የሚያዝኑ ሳይሆን የሚያሳዝኗት፣ ልጆቿን በእንባቸውና በትምህርታቸው አጥር መከታ ሆነው ከመጠበቅ ይልቅ ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሊለቀስላት ይገባል። 

ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪን የምትሰጥ” እንዲል ቅዳሴው ለቤተ ክርስቲያኑ የሚያለቅስ በርግጥም ቅን መሪ ነው።


ልጆቻቸውን እና ቤተክርስትያንን  ያስለቀሱ አባት
በአንድ ወቅት አባ ጳውልስ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል፡-
ክፍ መሪ ተሰጠን ብላችሁ አታጉረምርሙ።ክፍ መሪ ከሆነም የእናንተ ውጤት ነውThis is what you deserveደግ መሪ ለማግኘት መጀመሪያ ደግ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል‛፡፡ አቡነ ጳውሎስ 

እውነታቸውን ነው እሳቸውን የመሰለ ክፉ መሪ ፤ የልጆቻቸው እምባ የቤተክርስትያናችን በተሀድሶያውያን እና በመናፍቃን መከበብ ምንም ያልመሰላቸው  አባት የተሰጠን ከእኛ ክፋት ቢሆንስ ማን ያውቃል ? ክፉውንም ደጉንም የሚሾም አንድ አምላክ ይወቀው እንጂ፡፡
ከዚያም የሰቆቃው ኤርሚያስ ጸሎት ትዝ አለኝና የመጀመሪያዎቹን አራት ስንኞች እንዲህ እያልኩ አነበነብኩ፤
                        አቤቱ የሆነብንን አስብ፤
                        ተመልከት ስድባችንንም እይ፤                
                        ርስታችን ለእንግድች፤ 
                        ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።

ስል ሮሮዬን እግዜር ወዳለበት ወደ ሰማይ አሰማሁ።
                                                               በማይገለጥ የተከደነ የለም በሚባለው መጽሃፍ ውስጥ
                                                              (ከዲዊት አዘነ)

አቡነ ጳውሎስ ልጆቻቸውን ሲያስለቅሱ
                                   (የተሐድሶ ሴራ የሐዋሳ ምዕመናን ካዘጋጁት ላይ የተወሰደ.......ሙሉውን መልከቱ)
አቡነ ጳውሎስና የሐዋሳ ምዕመናንን በቅድስተ ማርያም ቤተክርስትያን.....
‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››

ምንጭ፡
  • ደጀ ሰላም
  • በማይገለጥ የተከደነ የለም በሚባለው መጽሃፍ ውስጥ

No comments:

Post a Comment