Tuesday, May 31, 2016

በእንተ ልዕልና ሲኖዶስ


የሀገራችን ሕገ መንግሥት መሠረታዊ መርኾች ከሚባሉት መካከል አንዱ አንቀጽ ፲፩ ነው፡፡ መሠረታዊ መርሕ ማለት ሕገ መንግሥቱ ራሱን ያዋቀረበት አስኳል ፍሬ ነገር ማለት ነው፡፡ በዚህ አንቀጽ ላይ ሕገ መንግሥቱ የሃይማኖት እና የመንግሥትን መለያየት በተመለከተ የደነገገ ሲኾን በተለይም አንቀጹ ከያዛቸው ሦስት ንዑሳን አናቅጽ መካከል የመጀመሪያው እና ሦስተኛው እንዲህ ይነበበባሉ፡፡
  • መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፡፡
  • መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡

የመጀመሪያው ንዑስ አንቀጽ እንደሚያመለክተው መንግሥት ሃይማኖታዊ ቁመና ተላብሶ ወይም ሃይማኖት መንግሥታዊ ቁመና ተላብሶ የሚገኝበት ወይም የሚመሠረትበት አመክንዮ እንደሌለ ያሳያል፡፡ ስለኾነም እነዚህ ሁለት አካለት ተጠባብቀው እና ተናብበው እንዲሄዱ የሚያደርግ ሁኔታ እንዲመቻች ሕገ መንግሥቱ የሰጠው መፍትሔ የለም፡፡ ተገነዛዝበው መሥራት የሚኖርባቸው እጅግ በርካታ የጋራ አጀንዳዎች በመካከላቸው እንደሚኖሩ ስለሚገመት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሃይማኖታዊ ቅርስ እንዴት ሊተዳደር ይችላል? የሚለውን ብናነሣ የሁለቱን መገነዛዘብ ግድ የሚል ኾኖ እናገኘዋለን፡፡ በአንድ አቅጣጫ ቅርስ የሀገር ሀብት ነውና መንግሥት ያገባኛል ሊል ሲችል በሌላ በኩል ደግሞ የእምነት ተቋሙ ያፈራው ወይም ያካበተው ቅርስ በመኾኑ ይህኛውም ያገባኛል የማለት መብት አለው፡፡

በጎሬ ደጀ ሰላም የቆመው የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሐውልት

 (በሔኖክ ያሬድ)
‹‹አርበኞች መሞትን ማን አስተማራቸው
አቡነ ጴጥሮስ ነው ባርኮ የሰጣቸው፤
ሚካኤል ቀድሞ መንገድ ቢመራቸው
በኦሜድላ በኩል ብርሃን ወጣላቸው፡፡››
ከሰማንያ ዓመት በፊት ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ሲወር፣ ‹‹ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት›› ተብሎ ፀረ ፋሺስት ተጋድሎ ሲጀመር ፋና ወጊ ከነበሩት መካከል ሁለቱ ጳጳሳት፣ ብፁዓን አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ይገኙባቸዋል፡፡ ከአምስት ዓመት የአገር ውስጥና ውጭ ተጋድሎ በኋላ ኢትዮጵያ ድልን መቀዳጀት የጀመረችው ጥር 12 ቀን 1933 .. በምዕራብ ኢትዮጵያ ድንበር ኦሜድላ ላይ ሰንደቅ ዓላማ በተውለበለበበት ጊዜ ነበር፡፡ ከሰባ አምስት ዓመት በፊት ሚያዝያ 27 ቀን 1933 .. ድሉ በመናገሻ ከተማው በንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ አማካይነት ዳግም ሰንደቅ ዓላማው በመውለብለብ ከተበሰረ በኋላ፣ በተከታታይ ዓመታት የድልና የሰማዕታት ሐውልቶች ተተክለዋል፡፡ አንዱ የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነው፡፡ ለዓመታት ትኩረት ተነፍገው የቆዩት የጎሬው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሰማዕት በሆኑ በሰባ ዘጠኝ ዓመት የቆመላቸው አዲስ ሐውልት፣ በግንቦት አጋማሽ ላይ ተመርቋል፡፡ ከአዲስ አበባ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ጋር ተመሳሳይነት ቢኖረውም፣ የቆመው ግን እንደ አቡነ ጴጥሮስ በከተማው አደባባይ ላይ ሳይሆን፣ በጎሬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ውስጥ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዐፀድ ውስጥ የቆመው ሐውልታቸው በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ግንቦት 14 ቀን 2008 .. ተመርቋል፡፡ የአዲስ አበባው የሰማዕቱ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዳግም ተከላ ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ሲከናወን፣ ፓትርያርኩ ለመንግሥትና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ሌላኛውን በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሰማዕት የሆኑትን የብፁዕ አቡነ ሚካኤልን ሐውልት ሰማዕትነትን በተቀበሉበት ቦታ በጎሬ ከተማ በክብር እንዲመለስና እንዲቆም፣ ለሚመለከተውና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፤›› ያሉትን በማስታወስ ሐውልታቸው፣ ድሮ ምስላቸው በነበረበት አደባባይ (ከቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት የሚገኝ) ላይ ለምን አልቆመም? በማለት የጠየቁም አሉ፡፡ ፋሺስቶች አዲስ አበባ በገቡ በሦስተኛው ወር (ሐምሌ 22 ቀን 1928 ..) ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስና አዲስ አበባ በጠላት በመያዟ ምክንያት ዋናው ከተማ ወደ ኢሉባቦር ጎሬ ሲዛወር፣ ጳጳስ የነበሩትና ፋሺስቶች ጎሬ ከተማን በኅዳር 1929 .. በያዙ በሳምንቱ (ኅዳር 24 ቀን 1929 ..) ሰማዕት የሆኑት አቡነ ሚካኤል ናቸው፡፡ አቡነ ሚካኤል እጃቸው ከተያዘ በኋላ ለሰባት ቀናት በእስር ላይ ቆይተው፣ ጠላት ኅዳር 24 ቀን 1929 .. ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወረድ ብሎ አሮጌ ቄራ መሄጃ ላይ፣ ከሁለቱ እውቅ አርበኞች ከግራዝማች ተክለሃይማኖትና ከቀኛዝማች ይነሱ ጋር በመትረየስ መግደሉ ይታወሳል፡፡ ከድል በኋላም 1936 .. አጽማቸው ተለቅሞ በመውጣትና በሳጥን ተደርጐ በክብር በመታጀብ በጐሬ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማረፉ፣ ደጃዝማች ጣሰው ዋለሉ የኢሉባቦር ጠቅላይ ገዥ በነበሩበት ዘመን፣ እዚያው ሰማዕት በሆኑበት ቦታ ላይ ሐውልት እንደቆመላቸውና 1980 .. መጠነኛ እድሳት እንደተደረገለት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ጎሬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ የሰማዕቱ የአቡነ ሚካኤል ፎቶ በትልቅ ፍሬም ተሠርቶ ተሰቅሎበት ቢኖርም፣ ደርግ ሥልጣኑን ሲያደላድል የሰማዕቱን ፎቶ አንስቶ የካርል ማርክስ፣ የፍሬድሪክ ኤንግልስና የቭላድሚር ኢሊዩች ሌኒንን ፎቶዎች በአንድነት መስቀሉ ይነገራል፡፡ ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ በቀድሞ መጠርያው በበጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት፣ ከደብረ ታቦር ከተማ በስተ ደቡብ አቅጣጫ በሚገኘው አፈረዋናት ምክትል ወረዳ፣ ልጫ መስቀለ ክርስቶስ በተባለ ሰበካ፣ ከአባታቸው ከቄስ ገብረ ክርስቶስና ከእናታቸው ከወ/ ትኩዬ 1874 .. መወለዳቸውን ገጸ ታሪካቸው ያመለክታል፡፡
from:-  http://www.ethiopianreporter.com/