Thursday, February 28, 2013

ግልጽ ደብዳቤ ፡- ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፮ኛ ፓትርያርክ ወርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ   አምላክ አሜን!

ከሁሉ አስቀድሜ ቅዱስነትዎ እግዚአብሔር ባወቀ ተመርጠው እንዲጠብቁ የተሾሙበት መንጋ አካልና ታናሽ የምሆን የመንፈስ ቅዱስ ልጅዎ ለምሆን ለኔ ቡራኬዎ ይድረሰኝ እላለሁ፡፡
በመቀጠልም የአገልገሎት ዘመንዎን ልዑል እግዚአብሔር የተቃና እንዲያደርግልዎ ልባዊ ምኞቴን እየገለጽኩ፣ ይህችን አጭር ደብዳቤ መጻፌ ድፍረት ተደርጎ እንዳይቆጠርብኝ እጅግ ከፍ ባለ ትህትና እጠይቃለሁ፡፡

 
ስለ ራሴ ቀደም ሲል እንደገለጽኩት የመንጋው አካል የሆንኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ስሆን፣ የቤተ ክርስቲያናችን ፭ተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዕረፍትን ተከትሎ ቀደም ሲል በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ተከስቶ ለሁለት አሥርት ዓመታት ያህል ጎራ በማስለየት የቤተክርስቲያናችን የበላይ አካል የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስ ያለያየና ያወጋገዘ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እልባት አግኝቶ፣ ቤተ ክርስቲያናችን እንደ ቀደመ ታሪኳ ወደ አንድነት እንድትመጣና የተጠራችለትን ሐዋርያዊ ተልዕኮ በፍቅርና በአንድነት ለመወጣት እንድትችል በእጅጉ ከተመኙትና ይፈልጉ ከነበሩት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን ልጆችዎ መካከል አንዱ ነኝ፡፡

ብጹዕ አቡነ ማቲያስ 6ተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆኑ


Wednesday, February 27, 2013

ለቤተክርስቲያን አስተዳራዊና መንፈሳዊ ትንሣኤ ነቀፌታ የሌለባቸውን አቡነ ዩሴፍ መምረጥ እንደ አማራጭ

      • “ለመሆኑ ከፈቃደ እግዚአብሔር ለምን ትሸሻላችሁ? እናንተንስ እንዴት እንመናችሁ?” አቡነ ዩሴፍ የተናገሩት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ምርጫው በእጣ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ በማግስቱ ላስቀለበሱት አባቶች
      • አቡነ ዩሴፍ በቤተክህነቱ ካለው ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ ፍቅረ ንዋይ፣ ስሜታዊነት(ግብታዊነት) ተለይተው ፥አርአያ ክህነትን ጠብቀው ፥ ሥጋ እንዳየ አሞራ በቤተክርስቲየኒቱ ላንዣበቡ ተሐድሶ መናፍቃን መዶሻ የሆኑ ጥሩ አባት ለናፈቀን የቀረቡልን ሲሳይ ናቸው፡ 
       
        (አንድ አድርገን የካቲት 20 2005 ዓ.ም)፡- የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ይጠበቅ ዘንድ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ አባቶች ልዩነት ጠፍቶ በፍቅር በአንድነት መንበረ ፓትርያርኩን ተረክቦ በአባትነት የሚመራን መልካም እረኛ ከሐሜትና ተንኮል በጸዳ ልቡና ምእመናንም ሆኑ ካህናት እንደልጅነት፤  ፓትርያርኩ እንደ አባት በመሆን በፍቅር እንኖር ዘንድ ያልተመኘና ያልጣረ ቢኖር የቤተክርስቲያንን ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲሁም ሰላምና ፍቅርን የማይወድ የክፋት አበጋዝ ብቻ ነው፡፡ሆኖም ግን የዚህች ርትዕት ቤተ ክርስቲያን ፈተናዋ ሊቋጭለት አልቻለምና  ይህ ምኞታችን በእውነተኞቹ አባቶችና ምእመናን ጥረት ፈርጀ ብዙ በሆኑ መንገዶች ቢሞከርም ለጊዜው አልሆነም፡፡የፓርትያርክ ምርጫ ጉዳይ ከተወሰነ በኋላ ግን ከድጡ ወደማጡ እንዳንሔድና ለመናፍቃንና እለከርሶሙ አምላኮሙ /ሆዳቸው አምላካቸው/ ለተባሉት እየበሉ ለሚርባቸው ጭራቆች አሳልፎ ከመስጠት፣ መንጋውን ከመበተንና የለቅሶውን ዘመን ከማራዘም ያለፈ ረብ ያለው ለውጥ ማምጣት አይቻል ይሆናል የሚል ስጋት ብዙዎቹ የሚጋሩት ሆኖ ቆይቷል፡፡

        Tuesday, February 26, 2013

        ቆይታ ከ6ተኛው እጩ ፓትርያርክ ጋር

        (አንድ አድርገን የካቲት 20 2005 ዓ.ም)፡- ህዳር 19 1993 ዓ.ም ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ከምኒሊክ መጽሄት ጋር ረዘም ያለ ቆይታ አድርገው ነበር ፤ ለአንድ አድርገን ብሎግ አንባቢዎች ትንሽ መረጃ ቢሆን ዘንድ በማለት መጽሄቱ ላይ የሰፈረውን እንዲህ አድርገን ለናንተ አቅርበነዋል፡፡ትላንት “ቆይታ ከ6ተኛው ፓትርያርክ ጋር ተብሎ የተጻፈው ቆይታ ከ6ተኛው እጩ ፓትርያርክ ጋር” ተብሎ ይስተካከል (ብዙ ቦታ ቀናቶቹ እ.ኤ.አ የተቀመጡ ናቸው)

        •    አሁን ያለውን መንግሥት በመቃወም አንደግፍም  የሚሉት የፖለቲካ ድርጅቶች  ከቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው ያንን የፖለቲካ ተግባራቸውን ስላካሄዱ ነው ቤተክርስቲያን የተከፋፈለችው፡
        •  አንድ ፓትርያርክ ሊቀ ጳጳስም ይሁን ቄስ ፤ ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ አባት የሆነ ሁሉ መመዘን ያለበት በመንፈሳዊ ህይወቱ እና በመንፈሳዊ አቋሙ ነው፡፡
        •  “ቤተክርስቲያኒቱ በእውነት የፓለቲካ ፤ የዘር ፤ የቋንቋ መድረክ መሆን የለባትም፡፡
        •  እግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ  ሆኖ ወደ ህብረትና አንድነታችን አንደምንመለስ ትልቅ ተስፋ ነው ያለኝ፡
        • የአሁኑን ፓትርያርክ በምን ልግለጻቸው? አሁን ለማለት የምችለው በሁለት አይነት መክፈል ይቻላል፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ አለ፡፡ የዘር ጉዳይ አለ፡፡
        •  በጎሳና በቋንቋ ተለያይተን  ምንም የምናስወግደው ችግር አይኖርም
        •  አቡነ መርቆርዮስ ችግር ቢያጋጥም እዛው መንበራቸው ላይ ሆነው መቀበል ነበረባቸው፡፡
        • ከጥንት ጀምሮ ቤተክርስቲያን  የአንድነታችን ምልክት ናት፡፡
        • የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ስርዓት መያዝ አለበት፡፡ ሲኖዶስ ጠንካራ ጉልበት እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡ የጳጳሳቱ ክብር መጠበቅ አለበት ፤ የቤተክርስቲያኗ ክብር መጠበቅ አለበት፡፡

        መግቢያ፡-
        “አቡነ ማቲያስ እባላለሁ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነኝ ፤ በመጀመሪያ ከኢትዮጵያ የወጣሁት እ.ኤ.አ 1979 ዓ.ም ወይም በእኛ አቆጣጠር 1971 ዓ.ም ነው፡፡ በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ለ3 ዓመት ያህል ኖርኩኝ በኋላ ደርግ መንግስት እየተከታተለ ችግር ሲፈጥርብኝ ወደ አሜሪካ ሀገር ተሰደድኩኝ፡፡ ከዛም አሜሪካ ያሉትን ኢትዮጵያውያን በሃይማኖት ሳሰባስብ ኖርኩኝ፡፡ አሁን ያለው መንግስት እስከተተካ ድረስ  በዋሽንግተን ዲሲ  በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉትን ኢትዮጵያውያንን ስለ ሃይማኖት ሳስተምር ፤ ስመክር ፤ ሳሰባስብ ሳስተባብር ኖርኩኝ፡፡ በ1992 እ.ኤ.አ በሲኖዶስ ስብሰባ ተጠርቼ ወደዚህ ሀገር ተመልሼ ስመጣ በነበርኩበት ሀገር የሀገሩ ሊቀጳጳስ ሆነህ ስራ  ተብዬ ወደ አሜሪካን ሀገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ተላኩኝ፡፡ አሁን አዛው እኖራለሁ ማለት ነው፡፡”

        Monday, February 25, 2013

        የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የፓትርያርክ ምርጫ ላይ ድምጽ እንዳይኖራቸው ለማድረግ ዘመቻ ተጀምሯል



        • የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ከሀገረ ስብከት ተወክሎ ድምጽ እንዳይሰጥ ትዕዛዝ ተላፏል፡፡
        • የማኅበረ ቅዱሳን አባል የሆኑትን ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ለፓትርያርክ ምርጫው ሀገረ ስብከታችሁን ወክላችሁ እንዳትልኩ ይህ ሆኖ ቢገኝ ኃላፊነቱን ራሳችሁ ትወስዳላችሁ፡፡”  የተላለፈው ትዕዛዝ
        • ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ያለምንም ተቀናቃኝ የካቲት ሃያ አራት 6ተኛ ፓትርያርክ ሆነው ይሾማሉ፡፡


          (አንድ አድርገን የካቲት 19 2005 ዓ.ም)፡- የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ባቀረባቸው አምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ዙሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ እጩዎቹን በማጽደቅ ትላንት ጥር 18 2005 ዓ.ም ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ፤ ይህ ይፋዊ መግለጫ 2791 በላይ ጥቆማዎች እንደደረሱት ገልጿል ፡፡ ለእጩነት የተጠቆሙት አባቶች በጠቅላላ 36 ሲሆኑ 15ቱ በአግባቡ ባለመጠቆማቸው እነርሱን ጥሎ አስራ ዘጠኙ ላይ በተቀመጠው የመመዘኛ መስፈርት መሰረት አምስቱን አሳልፎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኮሚቴው ያከናወነውን ስራ አባ አስጢፋኖስ እንዲህ በማለት ገልጸዋል “የአስመራጭ ኮሚቴው ከአምስት ያልበለጡ ከሶስት ያላነሱ እጩ ፓትርያርኮችን የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለማቅረብ ሰፊ ውይይት አድርጓል ፤ በተደረገው ውይይትም አሁን በአገልግሎት ላይ ካሉ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል 19 ሊቃነ ጳጳሳትን በቀጣይነት ለማጣራት አሳልፏል ፤ እጩዎቹን ለመለየት የተከተለው መመዘኛም እድሜና ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡” በማለት ገልጸዋል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ባደረገው ማጣራትም አምስቱን እጩ ፓትርያርኮችን ለይቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቧል ተብሏል ፡፡ እነርሱም ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለፓትርያርክነት እጩ ሆነው መቅረባቸው ተገልጧል፡፡ የአምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ስም የቀረበለት ቅዱስ ሲኖዶስም ማጽደቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ “ለመንጋው የሚሆን እረኛ እግዚአብሔር እንዲሰጠን ምዕመናን ፋጣሪያቸው በጸሎት እንዲጠይቁ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል”ብለዋል፡፡ 

          ታሪክን የኋሊት “ፓትርያርኩን አትምጡ ስንላቸው መጥተው እኛንም በገማ እንቁላል አስደበደቡን” አቡነ ማቲያስ




          • አቡነ ማቲያስ አቀድሳለሁ ነው የምልዎት  እንዲህ አይነቱ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ምን ይጎዳል” አቡነ ጳውሎስ
          • እንደ ፖሊሶቹ ቁጥር ማነስና ጥንቃቄ ጉድለት የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎች  የፈለጉትን ዓይነት ወንጀል በላያችን ላይ ከመፈጸም የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም” አቡነ ማቲያስ በጊዜው የተነሳውን ተቃውሞ  ሲገልፁ
          • “ፓትርያርኩን አጅበን ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተን ቦልቲሞር ስንደርስ ፤ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረው ተቃዋሚው የፖለቲካ ቡድን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በድንገት ወጥቶ ወረረን ፤ በጣም ቀፋፊ የሆነ ስድብ ውርጅብኝ አወረደብን፡፡
          • አቡነ ጳውሎስ ይጎበኙታል የተባለው ሕንጻ ውስጥ ፈንጂ ተቀብሯል ስለተባለ እርሳቸውና ከእሳቸው ጋር ያሉት 9 ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

          (አንድ አድርገን የካቲት 18 2005 ዓ.ም)፡- “አንድ አድርገን” በየጊዜው ወደ ኋላ መለስ በማለት በበቤተክርስቲያናችን ላይ የሆነው እና የተደረገውን ነገር አሁን ያለው ትውልድ ያውቀው ዘንድ ፤ ከባለፈ ታሪክ ተምሮም የተሻለ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርግ ዘንድ ታሪካችንን መልካምም ይሁኑ መጥፎ ጥሬ ሀቃቸውን ታሪክን የኋሊት እያለች እንደምታቀርብ ይታወቃል፡፡   አቡነ ማቲያስ የዛሬ 14 ዓመት በርካታ ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል ያሏቸውን ታሪኮችን በስምንት የተለያዩ ጉዳዮች ከፋፍለው ከ20 ገጽ የማያንስ በጊዜው በህትመት ላይ ለነበረችው ለ”ኢትኦጵ” መጽሔት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለአቶ ተስፋዬ ተገኝ በአስቸኳይ የፖስታ አገልግሎት የላኩት ጽሁፍ ላይ ስለ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  የአሜሪካን አገር ጉብኝት ሁኔታዎቸ ያሰፈሩትን ጽሁፍ ለአንባቢያን ለማድረስ ወደድን ፡፡ አቡነ ማቲያስ ለ”ኢትኦጵ” መጽሔት በላኳት ደብዳቤያቸው ብዙ ነገር ያወጉናል፡፡

          ለስድስተኛ ፓትርያርክነት የሚወዳደሩት ዕጩዎች ሰኞ ይታወቃሉ


          (Reporter February 24 2013):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ለመሆን የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ በዕጩነት የሚቀርቡት ተወዳዳሪዎች ሰኞ የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ይፋ እንደሚሆኑ ታወቀ፡፡
          አስመራጭ ኮሚቴው ዕጩ ፓትርያርክ እንዲሆኑ ከካህናትና ምዕመናን በተሰጠው ጥቆማ ላይ ተመሥርቶ ባደረገው ውይይት የለያቸውን ዕጩዎች በይፋ ባይገለጽም፣ ለየካቲት 16ቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ማቅረቡ ታውቋል፡፡

          የካቲት 21 ቀን ለሚደረገው ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ዕጩ የሚሆኑ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የካቲት 18 ቀን እንደሚታወቁ፣ ከምርጫውም በኋላ በዓለ ሲመቱ የካቲት 24 ቀን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል፡፡

          Saturday, February 23, 2013

          ቅ/ሲኖዶስ በአምስቱ ዕጩ ፓትርያሪኮች ላይ ዛሬ መወያየት ይጀምራል



          *From Addis Admass :

          • ለፓትትሪያርክነትይታጫሉተብለውየተጠበቁሊቃነጳጳሳትአልተካተቱም

          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ÷ በፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ተለይተውና ተጣርተው በሚቀርቡለት አምስት ዕጩ ፓትርያሪኮች ላይ ዛሬ መወያየት ይጀምራል፡፡

          ለምልአተ ጉባኤው ስብሰባ በሀገር ውስጥና በውጭ የተመደቡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚገኙ ሲኾን አስመራጭ ኮሚቴው ባወጣው የምርጫ መሪ ዕቅድ መሠረት፣ ለዕጩ ፓትርያሪክነት ይኹንታ ያገኙ አምስት ዕጩ ፓትርያሪኮች የካቲት 18 ቀን 2005 . ለሕዝቡ ይፋ የሚደረጉበት ውሳኔ የሚተላለፍበት ይኾናል፡፡

          ምረጡኝ ብዬ አላልኹም፤ ምረጡኝ ብዬ አላውቅም



          • ፓትርያሪክ እንድሆን የመንግስት ባለሥልጣን አላግባባሁም 
          • ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ ይገባቸዋል›› - /ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል/


          From Addis Admass :

          አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሞተ ሥጋ ከተለዩ ስድስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ ከፓትርያርኩ ኅልፈት በኋላ በሕገ ቤተ ክርስቲያን በተደነገገው መሠረት ስድስተኛው ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክነት ተሠይመው ቤተ ክርስቲያኒቱን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡