Monday, February 18, 2013

“ምርጫ ውስጥ ስካተት አትርሱኝ” አቡነ ጎርጎርዮስ

(አንድ አድርገን ህዳር 11 ቀን 2005 ዓ.ም)፡-የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ፤ ክብር ፤ ባህል ፤ እምነት ፤ሥርዓት ፤ መንግሥትና ቋንቋ ያቋቋመች ፤ የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ፤ ከሔኖክ ፤ ከመልከ ጼዲቅ ፤ ከነቢያትና ከሐዋርያት የተላለፈውን ትምህርት ፤ ሥርዓት ፤ እምነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ የኖረች ፤ በማስተላለፍ ላይ ያለች ፍኖተ ሕይወት ናት፡፡ ቅዱሳን አበውን ፤ ኃያላን ነገሥታትን ፤ ልዑላን መሳፍንትን ፤ ክቡራን መኳንንትን ፤ ዐይናሞች ሊቃውንትን በሥጋ ፤ በነፍስ ወልዳ ያሳደገች የሌላ የማትፈልግ ፤ የራሷንም የማትለቅ ዕጥፍ እናት ፤ ስንዱ እመቤት ናት፡፡” በማለት ስለ ቤተክርስቲያን የተናገሩት ታላቁ ሊቅ የቀለም ቀንድ አለቃ አያሌው ታምሩ ነበሩ ፡፡ እንዲህ የተባለላት ቤተክርስቲያን  ዛሬ ከእርቀ ሰላም የተከደነ አጀንዳ በኋላ ስድስተኛ ብላ ፓትርያርክ ለመሾም ወሳኝ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ 

 
ቀድሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እረፍት ከተሰማ በኋላ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ቤተክርስቲያኒቱ የቆመችበትን ቦታ ባለማስተዋል ፤ የግልንና የቡድን ጥቅም በማስቀደምና ቀድሞ የነበረው የጥቅም ምንጭ እንዳይቋረጥባቸው የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች እርቀ ሰላሙ ቢፈጠር የሚመጣባቸውን ተጽህኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ ሲንቀሳቀሱ አስተውለናል ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥም አንዱ አቡነ ጎርጎርዮስ ናቸው ፤ አቡነ ጎርጎርዮስ  ከወራት በፊት በሚስጥርና ባመቻቸው መንገድ ሁሉ ከፍተኛ የምረጡኝ ቅስቀሳ በተለያዩ ከተሞች ሲያደርጉ እንደነበር በጊዜው ማወቅ ችለናል ፡፡ ቅስቀሳውን ካደረጉበት ቦታዎች ውስጥ ህዳር 9 ቀን 2005 ዓ.ም ደብረዘይት ///ሚካኤል ////ቤት አዳራሽ ፤ በተጨማሪ  የመልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን ንግስ በዓል አስታከው ለሶስት ቀናት ከህዳር 11 ቀን እስከ ህዳር 13 ቀን 2005 ዓ.ም  ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህዝቡን የማንቃትና “ምርጫ ውስጥ ስካተት አትርሱኝ” የሚል ቅስቀሳ ያደረጉ ሲሆን በጊዜው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሳይመለሱ በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ በማምራት ውስጥ ውስጡን የራሳቸውን የምረጡኝ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መሰንበታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እርቀ ሰላሙ በሂደት ላይ ሳለ መቋጫው ምን እንደሆነ ቀድመው የተገነዘቡት አቡነ ጎርጎርዮስ በጊዜው በተመደቡበት ሀገረ ስብከታቸው ሥራ ወደ ኋላ በማለት  ሃሳባቸውን ወደ ሌላ መዳረሻ ነጥብ አዙረው ሲወጡ ሲወርዱ አስተውለናል ፡፡ የዝዋይ ማሰልጠኛ ማዕከል እየተማሩ ያሉ ደቀመዛሙርትምንና  ምዕመኑን በገንዘብ ፣ በእውቀትና በተገኘው ሁሉ በልጣችሁ ተገኙ” የሚሉ  መልዕክቶችንም ከበህዳር ወር ሲያስተላልፉ ነበር፡፡(የድምጽ ቅጅዎቹ እጃችን ላይ ይገኛሉ)
በአሁኑ ሰዓትም የመጠቆም እድላቸው እንዳለ ሆኖ በአስመራጭ ኮሚቴው የመጀመሪያ ማጣሪያ ውስጥ የመግባት እድላቸው በመስፈርቱ መሰረት የተጣበበ ቢሆንም እሳቸው እዛ ውስጥ ባይገቡ እንኳን የሚፈልጉትን እጩ ፓትርያርክ በብዙ ድምጽ ወደ ላይ ለመግፋት በርከት ያሉ ወዳጆቻቸው ጋር በመደወል ድምጽ ሰጪው አካል እንዲደራጅና ድምጹን እሳቸው ጥቆማ ውስጥ ካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ለእሳቸው እንዲሰጥ ፤ ያለበለዚያ ሶስት ውስጥ የመግባት እድል ላላቸው እሳቸው ለሚፈልጉት አባት እንዲሰጡ እያሳሰቡና እየወተወቱ ይገኛሉ፡፡ ይህን አካሄድ በድብቅ ሌሎችም እጩ ፓትርያርኮች ሊያካሂዱት እንደሚችሉ ይገመታል፡፡
ይህ ድርታቸው  የኃይል ሚዛኑ ወደ ሚፈልጉት አባት እንዲደፋ በማድረግ  የሚፈልጉት ጳጳስ ፓትርያርክ እንዲሆን በማሰብ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሲሆን ፤ ይህን የመሰለ ስራ የሚሰሩ ድምጽ ሰጪዎች እንቅስቃሴ ነገን ከማሰብ ይልቅ ማሰሪያ ልጣቸውንና መድረሻ ቦታቸውን ብቻ በማሰብ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፡፡ ምርጫው ይህን በመሰለ ሂደት የሚወጠር ከሆነ የመጨረሻው ሂደት ወዳልሆነ መንገድ እንዳይሄድ ስጋት አለ፡፡ 
በምርጫ ጥቆማው መሰረት አስመራጭ ኮሚቴው አምስት አባቶችን ለቅዱስ ሲኖዶስ ሲያቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመጨረሻ ምርጫ ሶስቱን እንደሚያስቀር ይታወቃል፡፡  በተቀመጠው የመምረጫ መስፈርት መሰረት የኮሚቴውን ወንፊት ያልፋሉ ተብለው የሚገመቱት አባቶች መካከል አቡነ ሳሙኤል ፤ አቡነ ገብርኤል ፤ አቡነ ማቲያስ እና አቡነ ሉቃስ በግምት ውስጥ ሲገኙ ምርጫው ከዚህ ግምት ውጪም ሊሆን እንደሚችል ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት ሰዎች ይናገራሉ፡፡

No comments:

Post a Comment