Wednesday, February 29, 2012

የእሳት ቃጠሎ በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም

በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የአከባቢው ምንጮች ገለጹ፡፡ እንደ ደረሰን መረጃ ከሆነ የእሳት ቃጠሎው ሊከሰት የቻለው በአከባቢው የሚኖሩ የኢሳ ጎሳዎች የገዳሙ ሀብት የሆኑትን እንስሳት ለመዝረፍ ባደረጉት ሙከራ መነኮሳቱ ለመከላከል ሲሞክሩ በኢሳዎቹ በተከፈተ ተኩስ ነው፡፡


ትላንት የካቲት 20 ቀን 2004 . ከጠቃቱ 400 ሰዓት አካባቢ የኢሳ ጎሳ አባላት ወደ ገዳሙ ክልል በመዝለቅ የገዳሙን እንስሳት ለመዝረፍ ይሞክራሉ፡፡ የገዳሙ መነኮሳትም ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ኢሳዎቹ በከፈቱት ተኩስ እሳቱ ሊቀሰቀስ ችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ ገዳሙ ላይ በአራቱም አቅጣጫ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ ተግዳሮቶች የተዳከሙት እና ቁጥራቸው እየተመናመነ የመጡት መነኮሳት የድረሱልን ጥሪ ማቅረብ ተስኗቸዋል፡፡ እስካሁን እሳቱን ለማስቆም አንድም አካል ወደ ገዳሙ አልተንቀሳቀሰም፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ አስራ አንድ ሄክታር የሚሆን የገዳሙ ደን እንዲሁም ልዩ ልዩ እንስሳት መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን!!!

ከገብር ኄር የተወሰደ