Thursday, March 7, 2013

“ተሀድሶን” ጠርገን ሳናስወጣ “ተዋህዶ” የሚሉ ደግሞ ብቅ ብለዋል


(አንድ አድርገን የካቲት 28 2005 ዓ.ም )፡- ከአመት በፊት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጀርባ  ኤልያስ ወደ ምድር ወርዷል ትክክለኛ ሰንበት ቅዳሜ እንጂ እሁድ አይደለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች” መባል አንፈልግም እኛ የኢትዮጵያ ተዋህዶ አማኞች” ነን “ኦርቶዶክስ” የሚለው ስም ተለጥፎብን ነው እንጂ እኛን የሚገልጽ አይደለም ፤  የአሁኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ስርዓተ ቤተክርስቲያን አንዳድን ቦታ ላይ ትክክል አይደለችም ስለ አማላጅነትና መሰል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ጋር የሚጣረስ ሃሳብ ያላቸው ቡድኖች በአሁኑ ሰዓት በመሀል አዲስ አበባ “ማኅበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሃቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ ለእግዚነ ወእመፍጥረት ወላዲተ አምላክ” በሚል ስም ምእመኑን ግራ እያጋቡት ይገኛሉ፡፡

 እነዚህ ቡድኖች  ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።ትንቢተ ሚልክያስ  45 ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናልየማርቆስ ወንጌል 9 12 የሚሉትን የመጽፍ ቅዱስ ቃል መሰረት በማድረግ ነብዩ ኤልያስ ወደ ምድር ጳግሜ 5 2003 . እንደመጣ አብዝተው ይሰብካሉ ፡፡ ቦታው መሃል አራት ኪሎ ሲሆን በርካቶችን በተለያዩ በራሪ ወረቀቶች በመሳብ ላይ ይገኛሉ ፡፡  ቦታው ድረስ ሄደን እንደተመለከትነው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞንን የመሰሉ አርቲስቶች ቆብ ያጠለቁ መነኮሳትና ለማገልገል የሚፋጠኑ ወጣቶች በቦታው ላይ መመልከት ችለናል ፡፡ ተሀድሶያውያንም ሆኑ አሁን ላይ “ተዋሕዶ” ብለው ራሳቸውን ከእኛ ጋር እጅጉን በማመሳሰል የተነሱት ሰዎች መጨረሻቸው መንጋውን ከበረቱ ማስወጣት ነው፡፡ አሁን ላይ “ተዋሕዶ” የሚለውን ትርጉም ከአባቶች እንዳገኝነው በማለት የራሳቸውን ፍልስፍና ምዕመኑን እየጋቱት ይገኛሉ ፤ ጥቂቶች እስከ አሁን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መባል አልነበረብንም በማለት የጉባኤያቸው ተካፋይ መሆን ጀምረዋል ፡፡ እያየን ያለነው ነገር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን አንገታቸው ላይ የሚያስሩት ክር ትክክል አይደለም ፤ “ከሰማይ የተሰጠው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ክር ነው” በማለት ምዕመኑን የበፊቱን እያስወለቁ አዲሱን የራሳቸውን ክር እያጠለቁለት ይገኛሉ… ይሄ ነገር ዛሬ ዝም ከተባለ ነገ በዝተው የባሰ ቀውስ እንዳያመጡም ስጋት አለን …ለማንኛውም በዚህ አመለካከት  የተጠመቀችው ለምስክርነትም በቃው የምትለው አርቲስት ጀማነሽ ምን እንደምትል ከየካቲት ወር እትም ከሚሺሪያ መጽሄት ጋር ያደረገችው ሙሉ ቃለ መጠይቅ ብሎጋችን ላይ ለጥፈንልዎታል ያንብቡት….

ጥቂት ከቃለ መጠይቁ የተወሰደ
  • ኦርቶዶክስ ሽፋን ነው፡፡ ቅባት ፤ ጸጋ ፤ ዘጠኝ መለኮት እያሉ በግድ አብረው ኦርቶዶክስ በሚል ሰንሰለት ከተዋሕዶ ጋር ጠፍረው አስረው አንድ ላይ ያስቀመጧቸው እምነቶች መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡
  • ኦርቶዶክስ ማለት ጸጋን ቅባትንም ዘጠኝ መለኮትንም የሚጠቀልል ከሆነ እኔ ኦርቶዶክስ አይደለሁም ፡፡ አልፈልገውም ፤ አልቀበል፤ እኔ ተዋህዶ ብቻ ነኝ፡፡
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲባል ቀጥተኛዋ ተዋሕዶ  የሚሉ ስለሚመስለኝ እኔም በዚያ ስም ራሴን ስጠራ ነው የኖርኩትኝ፡፡ በቅዱስ ኤልያስ አዋጅ ላይ ነው ያየሁት ፡፡ የቅዱስ ኤልያስ አዋጅም “እነዚህ እምነቶች የክርስትና እምነት ስላሆኑ ከተዋህዶ ጋር አንድነት ስለሌላቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሱ ንስጥሮስን እንዳወገዙ ፤ አርዮስን እንዳወገዙ በእምነትም በዶግማም ስለማይመሳሰል አውግዛችሁ ልትለዩ ይገባል” የሚል ታላቅ አዋጅ ነው ያየሁት ፡፡ ይህን ግን ሲኖዶሱ አልተቀበለውም፡፡
  • ከአሁን ወዲያ ደግሞ እውነተኛውን ነገር እስካወቅን ድረስ  አንደ አባቶቻችን “የለም ፤ አይሆንም ፤ አንድ አይደለንም” ብሎ መቆም ደግሞ የኛ ፋንታ ነው፡፡
  • ተዋሕዶ ነን ብላችሁ ልዩነት ስትፈጥሩ ተሃድሶ እንደሚባለው ሊፈረጅ ይችላል የሚል ስጋት የለሽም? (ከጋዜጠኛ የቀረበላት ጥያቄ)
  • ቅባት ጸጋ የሚባሉት እኛን ተዋህዶ በመሆናችን የከሰሱን እና ወንጀለኛ የደረጉን ናቸው ፤ በሙሉ ገዳም ውስጠ ያሉት በዚህ ተይዘዋል ፤ ጥቂት ተዋህዶ አማኞች  በስቃይ የሚኖሩ አሉ፡፡
  • በአሁን ጊዜ ብዙ ሃይማኖቶች አሉ ፤ እውነት ግን ያለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው ፤ አሷም ተዋህዶ ናት፡፡
  • ስንት ገዳም ገብቼ የስንት አባቶችን መስቀል ተሳልሜአለሁ ፡፡ ሳስበው ይዘገንነኛል ፡፡ ዋልድባን የሚያህል ቅዱስ ገዳም ነው በእንደዚህ አይነቶች ተሞልቶ ያገኝሁት፡፡ ዋልድባን የሚያህል የቅዱሳን አባቶች መቀመጫ ገዳም “ዘጠኝ መለኮት” የሚሉ መናፍቃን ግማሹን ይዘው እንዳሉበት አላውቅም ነበር፡፡
  • ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ይመልስ ዘንድ  ቅዱስ ኤልያስን እልክላችኋለሁ” ይላል አሁን ኤልያስ የመጣው ይህን ሊገልጥ ነው፡፡
  • እግዚአብሔር ከዚህ መስመር (ተዋሕዶ) ከሚያስወጣኝ ቢገለኝ እመርጣለሁ፡፡
  • ሶሪያ ትንቢተ ኢሳያስ ላይ እንደሚላት እየወደመች ነው ፤ አሜሪካ እንደምትጠፋ ራዕይ ላይ ተጽፏል
TO READ IN PDF CLICK HERE


ወደ ኮምፒዩተርዎ ሴቭ በማድረግ ያንቡት


37 comments:

  1. ቃለ መጠይቁ ግልጽ ይሁን

    ReplyDelete
    Replies
    1. we are sleep to eradicate Qebat,Tsega,Nine Melekos in Waldeba,there fore God tells us via Jemanesh who makes a very interesting interview.Please Ande adregen,don't divide us.She says the real teaching of our Church.Don't exaggerate some mistakes of her.Elias came down means for me some teachers who don't fear church ansd state leaders teach the real teaching of our Church.They are elias or Elsa who go in the spirit of Elias.Merule Maryam is my village,I know,like Jemanesh said,there are many monks and priests as well as peoples who believe in Qebat.Don't cover up these heretics.If you cover these problems of the Church,in what way that you are better than Qebats,Tsega,Zettegn melekot?leave Jemanesh anf fight these basic heretics in our churches.

      Delete
    2. What are you talking about wedaje. If she said she doesn't want to be called Orthodox Tewahedo, if they say the real Senbet is Saturday(like adventist 7 day), if she has issues about our Maeteb color, if she said Eleyas werede, if their meeting is outside our church, ...., there is a problems. Can't you see this? Why she was not able to learn from our fathers in church? I don't even know who she is calling "fathers", the one who is teaching her outside the church. Tehadiso did the same thing. If you said she is right. Then Tehadiso is right too. They didn't say anything bad. they just want to renew our church teaching. I don't think anything outside the church is right. Our church fathers need to pay attention to the fathers who are teaching her and have problem with the name Orthodox Tewahedo.

      Delete
    3. ሰው ኣምኖ እንዳይድን በማይሆን እምነ ኣታስቸግሩን እግዚኣብሔር ይቅር ይበለን !

      Delete
  2. ይህ እኮ ግልፅ ነው የተናገረችው(ቅባት ፣ፀጋ ፣ዘጠኝ መለኮት)ያለችው ምንም መናፈቅነት የለውም ፣ነገር ግን ያሳሰበኝ ይችህ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የምትለውን ስም መጥላቷ የጤና አይመስለኝም።ተዋሕዶ የምትለውን ተጠቅመው ምዕመኑን ለመበተን የሚጠቀሙበት ዘዴ ይመስለኛል(ቅባት ፣ፀጋ ፣ዘጠኝ መለኮት ለማድረግ የታለመ ሊሆን ይችላል) ምክንያቱም ከንግግሯ እንደተረዳሁት
    ሀ)መታብይዋ
    ለ)ነብዩ ኤልያስ መጥቷል ማለቷ
    ሐ)ከቤተክርስትያን ውጭ መሰብሰባቸው (ከተሃድሶያውያኑ ተለይቶ አይታይም)
    አላማው ሌላ እንደሆነ ያሳብቃል

    ReplyDelete
  3. She is talking about the issue of Ethiopian Orthodox Tewahido. If she started learning now it is good. Nothing new for EOTC.Who is the 'father' that teaches her as a special.....I hope she needs more clarification.......She didn't yet learn when the name of Orthodox was added by our earlier Fathers......Otherwise it may have some mission behind....Thanks Andadregen for sharing.If you can, you have to make interview her and clarify her view and with whom she is......

    ReplyDelete
  4. we know that God does not mentionday regarding His second coming.However,He has
    the indications of His coming.No one is able to give meanings to Gods word.
    unless he is taught by Holy spirit.Knowledge of theworld never help us get the meaning of the chapters and verses of the Bible.Orthdox and Tewahido are terms
    that contain deep spiritual meanings.These maenings can be crystal clear to
    our spiritual fathers, monks nuns,and saints.Hence itis advisable to learn from
    them before one dares to say a word.May God bless us all.

    ReplyDelete
  5. የሰጠሀው አርእስት እና የፅሁፉ ፍሬ ሃሳብ አይገናኝም።
    በርግጥም እንደዚህ አይነት ነገር በቤተክርስቲያናችን ካለ ሊወገዝ ይገባል።
    እባካችሁ በብሎጋችሁ ላይ ስድብ እና አሽሙር ትታችሁ ስለዚህ ነገር አባቶችን ጠይቃችሁ እንረዳው።
    ያልገባኝ ነገር በየብሎጉ ሽሙጥ እና ዘለፋ ከሌለው ሰው አያነብም የተባላችሁ ትመስላላችሁ
    ትህትና ተናግራችሁ ትህትና ስበኩን እንጂ ወንድሞቼ የነፍስ ነገር እኮ ነው ለስድብ እማ እነ ኢሳት እና መሰሎቹ አሉልን ።

    ReplyDelete
  6. Ataganu Enezih sewoch meseretawi yehaymanot astemiro yalebachew almeselegnim. EOTC is for tewahido not for others like tsega,qibat etc; Jemanesh and her colligues should understand that.

    ReplyDelete
  7. we don't know about these kibat,tsega and nine melekot....please andadrgen it is not about jemanesh or others.. would you tell us their teaching.....i think it is important to know about.

    ReplyDelete
  8. ብላቴናዋ ከጀርመንMarch 8, 2013 at 3:12 AM

    ድና ተመለሰችእንዴ ካሜሪካን በገመና ድራማ ላይ ለመጨረሻ ግዜ ያየሁዋት በጠና ታማ ለህክምና ወደአሜሪካን ስትሄድ ነው ምናልባትም የድራማው የሚቀጥለው ፓርት ይሆናል ይሄኛው ! ለማንኛውም ስለሰጣችሁን መረጃ እናመሰግናለን ገና ከዚህም የባሱ ሊመጡ ስለሚችሉ መርበትበት ሳይሆን የሚጠቅመን ባለንበት ጸንተን ስለመገኘታችን ሁላችንም ስለራሳችን መጸለይና የትንቢት መፈጸሚያ ከመሆን ያድነን ዘንድ አብዝተን አቤቱ አቤቱ ማለት ሳያዋጣን የሚቀር አይመስለኝም እኛ ስንባላ አጅሬው ተመችቶት ስራውን እየሰራ ስለሆነ እራሳችንንና ቤተሰባችንን ነቅተን እንጠብቅ የቆመያለ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ነውያለው መጽሀፉ!

    ReplyDelete
    Replies
    1. kkkkkkkkkkk belatenawa good humor

      Delete
  9. Hey jemanesh u need to understand that kibat and likes are not orthodox and our EOTC do not include the name or the teaching. But still I believe that the EOTC should denounce them.

    ReplyDelete
  10. Bewinetu ye beteChristian andu ena wanaw sirawa masitemar edehonew,yelijochuam sira hule memar ena dimstsuan mesmat new,enam qeribo memar,aqirbo mastemar yigebal ; diyablisosin asafiro Nefsin lemadan ena lemedan be andinet le andinet beFiqir ena Betiegist be Ewiqetim hulun madregim senay new ; be andim belelam yeneberubinin chigiroch,yemifeterutinimim endih bale huneta mayet ena lemefitat metar yenefis adin,yechristina,meleyayetin yemetagel gidetachin yimesilegnal; hulum neger sile NEFS ena sile NEFS newina.

    ReplyDelete
  11. ጀማነሽ ታዋቂ እንጂ አዋቂ አይደለችም:: በታዋቂነቷም አድናቂ እንጂ መካሪ ማፍራት አልቻለችም:: ታሳዝናለች! የምታውቋት አልቅሱላት:: የቅዱሳን አምላክ ይታደጋት:: ወዮ ለዚህ ዘመን አገልጋዮች ወዮ በኃላፊነት ወንበር ላይ ላላችሁ ወዮ ለመንጋው ለማትራሩ እረኞች. . . ዘመነ መሳፍንት ራሱን ሊደግም እያቆበቆበ ነው::

    ReplyDelete
    Replies
    1. absolutely U R right

      Delete
    2. Agree with you my friend. You are absolutely right.

      Delete
    3. You are absolutely right my friend God bless u!

      Delete
    4. you are absolutely right my friend God bless u!

      Delete
  12. I read this article and most of what she has said falls under the teachings of our church. The major issues are this fixation towards Tewahedo and Elias and what Jemanesh and the likes need is more education about our Orthodox church.

    Yes, there are theological debates in our church, which has nothing to do with the name Orthodox. The issue of Kibat vs Tsega and immaculate conception are major issues that have been debated by theologicians for years. If these kinds of teachings are rampant, as she claims them to be, then they can be referred to the Holy Synod, but you cannot abandon the name Orthodox because there are people in some monastries debating about the nature of Christ or immaculate conception.

    ReplyDelete
  13. I read this article and most of what she has said falls under the teachings of our church. The major issues are this fixation towards Tewahedo and Elias and what Jemanesh and the likes need is more education about our Orthodox church.

    Yes, there are theological debates in our church, which has nothing to do with the name Orthodox. The issue of Kibat vs Tsega and immaculate conception are major issues that have been debated by theologicians for years. If these kinds of teachings are rampant, as she claims them to be, then they can be referred to the Holy Synod, but you cannot abandon the name Orthodox because there are people in some monastries debating about the nature of Christ or immaculate conception.

    ReplyDelete
  14. የGG ፖለቲካ ተጀመረ ጎጄዎች መንበር ሲያጡ ያሴሯት የጅል ቀልድ ናት:: የሞተን ትምህርት ከመቃብር መጎተትን ምን አመጣው? ሁከት መፍጠሪያ በመሆን ያገለግል እንደሆነ እንጅ ቤተ ክርስቲያንማ በች ይህ ብርቋ ነው? የኖረችበት ነው:: ጉባኤ ያዘጋጁና ሊቃውንቱን ይግጠሙ እንጂ እኛ ምን እናድርግ?
    እስኪ ደግሞ የአጥማቂዎች ነን ባዮቹን ነገር በነካ እጃቹ ዳሱልን:: ከመብዛታቸው የመመሳሰላቸው ነገር አሳሳቢ ነው:: የመከሩ ጊዜ እስኪደርስ እንግዲህ መታገስ ነው:: እኛንም አያናውጸን!

    ReplyDelete
    Replies
    1. መልዓከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተቀቡ ቅዱስ አባታችን ናቸው፡፡ ሰውን ከፍሬው ማወቅ ይቻላል፡፡ ከሰይጣን ቁራኝነት በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ነጻ ባስወጡ፣ በዲያቢሎስ ሰንሰለት የታሰሩተን በኃይለ እግዚአብሔር ባስፈቱ፣ ድውያንን በወላዲተ አምላክ ስም፣ በቅዱሳን ስም በፈወሱ፣ በስም ክርስትና ሲዋልሉ የነበሩትን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የመዳንን ትክክለኛ ጐዳና ባሳዩ ነው "አጥማቂ ነን ባዮች" የሚባል ቅጥያ የሚሰጣቸው? መድኃኔያለም ለ'ኔና ለእርስዎ አስተማሪ አድርጎ የሾመለን የዘመናችን ታላቅ አባት ናቸውና አይንዎትን ይግለጡ፡፡ ወዳጄ ግድየለም ይመኑ፣ ባይምኑ ግን በጭፍን ቅናት አልያም "አውቃለሁ" ባይነት በረከቱ እንዳያልፍዎት እመክርዎታሉ፡፡ ታናሽ ታናሽ ወንድምዎ፡፡

      Delete
    2. መልዓከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተቀቡ ቅዱስ አባታችን ናቸው፡፡ ሰውን ከፍሬው ማወቅ ይቻላል፡፡ ከሰይጣን ቁራኝነት በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ነጻ ባስወጡ፣ በዲያቢሎስ ሰንሰለት የታሰሩተን በኃይለ እግዚአብሔር ባስፈቱ፣ ድውያንን በወላዲተ አምላክ ስም፣ በቅዱሳን ስም በፈወሱ፣ በስም ክርስትና ሲዋልሉ የነበሩትን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የመዳንን ትክክለኛ ጐዳና ባሳዩ ነው "አጥማቂ ነን ባዮች" የሚባል ቅጥያ የሚሰጣቸው? መድኃኔያለም ለ'ኔና ለእርስዎ አስተማሪ አድርጎ የሾመለን የዘመናችን ታላቅ አባት ናቸውና አይንዎትን ይግለጡ፡፡ ወዳጄ ግድየለም ይመኑ፣ ባይምኑ ግን በጭፍን ቅናት አልያም "አውቃለሁ" ባይነት በረከቱ እንዳያልፍዎት እመክርዎታሉ፡፡ ታናሽ ታናሽ ወንድምዎ፡፡

      Delete
    3. ከላይ ማሳሰቢያቸውን የሰጡት ሰው የማንንም ስም አላነሱም:: "ባልታዛር" የሚል ስያሜ የያዙት አስተያየት ሰጪ ግን ያልተገባ አስተያየት የሰጡ ይመስለኛል:: "ጭፍን ቅናት" "አውቃለሁ ባይነት" እያሉ የጠቀሱትን ከየት አምጥተውት ነው? ገና ሳይነሳ እንደዚህ ካሉ በጉዳዩ ላይ መረጃ ቢቀርብ ምን ይሉ ይሆን? የቀረበውን በመረጃ ይሞግታሉ ወይስ በደጋፊነት ብቻ ይቃወማሉ? ቤተ ክርስቲያናችን የሁላችን ናት:: የመናገር መብት ቢኖረንም በመከባበር ሲሆን ለመግባባትና ነፍሳዊ ድህነት ለማግኘት ይረዳናል:: እርሶ እንዳሉት መምህሩ ትክክል ለመሆናቸው ማስረጃ አቅርበው ይከራከሩ እንጂ የሌሎችን መልእክት በመሳደብ በማንጓጠጥ አይሁን::

      እስኪ ይመልከቱ ጌታችንን ባጋንንት አለቃ ጋኔን ያወጣል ተብሏል:: ይህንን ግን በመሳደብ ሳይሆን በማስተማር እውነተኛ ማንነቱን እንዲያምኑ ነው ያደረገው:: ሊገድሉት የመጡትንም እንግደላቸው ብለው ደቀ መዛሙርቱ ሰይፍ ቢያነሱም የጌታችን ምላሽ "ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ" የሚል ነው::ታዲያ ወንድማችን የአንደበትም ሆነ የብእር ሰይፍ ማንሳትም ተመሳሳይ ነው:: በመሆኑም እባኮ ለራሳችን የምንናገረውን ከማረም ከጀመርን ሌሎች እንዳይሳሳቱ እድል እንፈጥራለን:: ከዚያም በላይ "ንግግራችሁ በጨው እንደተቀመመ ይሁን" የሚለውን ትእዛዝ በማሰብ ጥንቃቄ ያድርጉ::

      የከበረ ማንነት እንዳላቸው የተረጋገጠላቸው ቅዱሳን እንኳ ዛሬ ይታማሉ ያለ ስማቸው ስም እየተሰጠ ይነገርባቸዋል:: ይህንን ግን ማስቀረት የምንችለው ትክክለኛውን ማንነታቸውን ለይተን በማስረጃ በማቅረብ እንጂ በመሳደብ አይደለም:: ለአገልጋይ መታማትን የሚያህል የከበሬታ ወንበር ከየት ይገኛል:: ይታሙ ይሰደቡ ይተቹ ይጠየቁ ምክንያቱም አንደኛ ትክክለኛውን ምላሽ ይሰጡበታል ብዙዎችንም ይታደጉበታል:: ሲቀጥል የሚታረሙባቸውንም ምክር ያገኙባቸዋል ከዚያም ሲያልፍ ማስቀረት በማንችላቸው ጉዳዮች ላይ በክርክር ጊዜ መፍጀት አላስፈላጊ መሆኑን እንማርበታለ:: እስልምና እምነት ተከታዮች ጌታችን ከነቢያት አንዱ ነው:: ይህንን ማስቀረት አይቻልም ሳንደክም ግን ጌትነቱን መመስከራችን ማስረዳታችን ከስድባችን በላይ አንዳንድ ነፍሳትን እየነጠቅን ለማምጣት ያግዘንም ትላላችሁ? በመከባበር እንመካከር እንጂ በመጠላላት አንደናቆር የሚል ሀሳብ ባቀርብ ይጠቅም ይሆን? /ቄስ በልይነህ/

      Delete
    4. Egziabher yistot abate, I don't know why but most of us can't have a healthy argument to one another.

      Delete
  15. የእግዚአብሔር ማሞገሻ የነበረውን የሙዚቃ መሳሪያ እኮ ነው ዲያቢሎስ ይዞት የወረደው ነው"

    ይች አባባል እልገባኝም?ምን ናለት ፈልጋ ነው? መልእክት ያላት ይመስላል እነዚህ አርቲስቶች ዝና ሊያልቅባቸው ሲል ሌላ መታያ መንገድ ይፈልጋሉ በእርግጥ የምትሰራው ድራም ለማን እንደሆነ አልገባትም እውነት ቢኖራትም የመለመሏት የቤተክርስትያን ጠለቶች እንደሆኑ ያወቀች አይመስልም ልትገራ ይገባል ጀማነሽ ቆም ብለች አስቢ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንግዜም እውነት ናት ተዋህዶ ብለሽ ለመክፋል መሳሪያ አትሁኝ

    ReplyDelete
    Replies
    1. እንቁላል:እያደር:በእግሯ:ትሄዳለች:አይደል:የሚባለው !!!የመጨረሻ:ተልዕኮዋን:እየነገረችን:መሰለኝ:እሱም:የሙዚቃ:ና:የዳንኪራ:መሣሪያዎቹን:ወደ:ቤተክርስቲያን:ማስገባት:ይህ:ደሞ:የረጅም:ግዜ:የተሃድሶ:ና:ቤተክርስትያኑዋን:የመናፈቃን:ወይም:የፕሮቴስታንት"ቤተክርስትያን":ማድረግ:ዕቅዳቸው:ወይም:ቅዥታቸው:እንደሆነ:ያሳያል።

      Delete
  16. I haven't seen anything wrong with Jemanesh except "Elias metual" she is absolutely right. It is very shame to see zetegn melekot in waldiba. It is very common to see qibat and tsega people in Misrak Gojjam.

    ReplyDelete
  17. To have better understanding we need to read the whole book. Just like one of the people wrote the head line and the content totally different. Before we judge we need to listen both side in clean heart. We can lean from this. God bless.

    ReplyDelete
  18. Egzio meharene Kiristos. Wey ajrew seytan betam yigermal ahun degmo be tewahdo sim metabin. Kehulu yegeremenge degmo emebetachinin " Eme fitret" bilew metratachew new meches seytan menafikanin siyasnesa mejemeria kekibir masanes yemifeligew Getachin medhanitachinen Eyesus kirstosin ena Enatun new. Emebetachinin eko kehulu belay yemiyadergat EME AMLAK mehonwa new enji eme fitret mehonua aydelem. Eme fitret maletachew getachinin (kibir yigbawina) fitur maletachew yihon weyes.....Fitret yemilew kal 22 tun sinefitretat yemigelis kal sihon seytanim erau kefitretat andu new. Silezih emebetachinin lik ende abatochacin Eme Amlak weladite Amlak bilen linterat yigebanal enji Eme fitret yemilew meteria ayhonatim.

    Kibain tsegan weyem zetenge melekotin mekawem ande neger new.Addis minfikina mejemer degmo lela erasun yechale neger new.lelawin mewkes bichawin gin hakenga ayadergenim. Silezih Jemayneshin ena meselochiwan Egziabhier Amlak Ayne libona Yistachihu Tetemdachihubet kalachihut yeseytan yematalel wetmede yawitachihu. Meches sihitetachihu hulu keyewahinet yemeta yimeslengal.

    ReplyDelete
    Replies
    1. thank you brother, the first thing I noticed was the word 'eme fitret'. I was askingt to myself why she didn't say Eme Amlak. As you said, there is a problem. You said it well and anyone can understand it. Yemiyasazinew she is fine yemilu bezih blog asteyayet yemisetu menorachew new.
      Jemayneshin ena meselochiwan Egziabhier Amlak Ayne libona Yistachihu Tetemdachihubet kalachihut yeseytan yematalel wetmede yawitachihu.

      Delete
  19. Is there anyone out there including -Dn Daniel Kibret who could answer the fundamental questions raised by Jemanesh.Where does the Orthodox Tewahedo church stands when it comes to the nature of Christ.That is what needs to be answered.Any one of you who are posting comments here don't even know the answer .Why does the church make this clear to the beleivers.WE WANT TO KNOW WHAT THE CHURCHS' STAND IS ON THE NATURE OF CHRIST.

    Don't expect everyone is ignorant!!We want answers not empty talks.

    ReplyDelete