Thursday, March 21, 2013

አራት ኪሎ የመሸገው የኤልያሳውያን ቡድን አስተምህሮ



·   “ኦርቶዶክስ ተዋህዶ” ብሎ ከመሰየም ይልቅ “ካቶሊክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን” ብሎ መሰየም አስር እጥፍ የተሻለ ነው፡፡
·   የ “ተዋህዶ” ልጆች ሁሉ ልብሳችንን ጸአዳ ፤ የልብሳችንን ዘርፍ  ፤ የአንገታችንን ማህተብ የቀስተ ደመና ማህተብ ሊሆኑ ይገባል፡፡
·    አንዲቱ ዕለት ሰንበት ቅዳሜ መሆኗን ፤ እሁድ ግን ዕለተ ሰንበት አለመሆንዋን ምስጢር አዋቂው ቀናኢ ነብይ ኤልያስ ለአባቶቻችን አረጋግጦ ነግሯቸዋል፡፡
·  ኤልያሳውያን ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህ ነው ይላሉ “የኢትዮጵያ ቅዱሳን ያዘኑበት የአመጸኞች ስብስብ ፤ ምን ያህል ያጌጠ ሽፋን እንደተከናነበ በውስጡ ግን ምን እንደሚካሄድ ግልጽ ነው ፤ ይህ ካለ እኔ ለቤተክርስቲያን ማንም የለም እያለ ከመናፍቃን ፤ ከጳጳሳት ጋር ሽር ጉድ የሚል……”

(አንድ አድርገን መጋቢት 13 2005 ዓ.ም)፡- የዚህ የአራት ኪሎው ቡድን አካሄድ ከአመት በፊት ብናውቅም በጊዜው ስለ እነርሱ ያሉንን መረጃዎች ብናወጣ ለእነሱ ማታወቂያ መስራት ይሆናል ብለን በማሰብ እስከ አሁን አዘግይተነዋል፡፡ አሁን ግን በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኝት ያስችላቸው ዘንድ በኢግዚቢሽን አዳራሽ መርሀ ግብር ለማዘጋጀት እየሰሩ ስለሆነ ስለ ቡድኑ ያለንን መረጃ ደረጃ በደረጃ ለማውጠት ግድ ሆኖብናል፡፡

አራት ኪሎ የመሸገው የኤልያሳውያን ቡድን ምን አይነት ፍልስፍና እና አስተምህሮ እንደሚከተል ሰዎች እንዲያውቁት ለማድረግ ያስችል ዘንድ “በዘመናችን ከብሔረ ህያዋን የወረደ ቅዱስ ኤልያስ የገለጠው ስውር ረቂቅ ምስጢራት” በሚል አርዕስት የተጻፈ እና ለአባሎቻቸው በሀርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ የተሰራጨውን ባለ ዘጠኝ ገጽ ወረቀት አለፍ አለፍ ብለን መሰረታዊውን የቡድኑን አስተምህሮ እና አካሄድ ከጽሁፉ ላይ ቀጥታ በመውሰድ ጥቂት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ (በፒዲኤፍ ለማንበብ ) 

  • “ኦርቶዶክስ” በሚለው ላይ ያላቸው አስተምህሮ

 በዚህ ላይ ያለውን አስተምህሮ ጽሁፉ ሲገልጽ “ኦርቶዶክስ የሚለው ስያሜ ለቅድስት ቤተክርስቲያ ተገቢ ነውን? የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ እናንሳ ፤ ልዑል እግዚአብሔር ለፍጥረት ሁሉ መዳኛ መመኪያ መንገድ አድርጎ የሰጣትን አንዲቷን የተዋህዶ ሃይማኖት ቀጥተኝነት ተጠራጥረን አይደለም ፤ በእርግጥ ጌታ በቅዱስ ወንጌል እንደመሰከረላት ቅድስት ቤተክርስቲያን በጽኑ የሥላሴ አለት ላይ የተመሰረተች የሲኦል ደጆች ሊያነዋውጧት  ሊቀይሯት ወይም ሊያድሷት የማይቻላቸውን በወርቅ በእንቁ የተመሰለችውን አንዲት የተዋህዶ ሃይማኖት የያዘች መሆንዋ የታወቀ እውነታ ነው ፡፡ ለእኛም ርትዕይት ቀጥተኛ እውነተኛ የሆነችዋን “ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋህዶ ከበረ” የምትለዋ አንዲቷ ተዋህዶ የምናምንባትና በሐሴት የምንታመንላት ሃይማኖታችን ናት፡፡ ነገር ግን ኦርቶዶክስ የሚለው ስያሜ ለቤተክርስቲያናችን መቼ? እንዴት? በእነማን? ለምን? አላማ ሊሰጣት ቻለ የሚሉትን መጠይቆች ስንመረምር በቤተክርስቲያን ላይ ሰይጣን የቀመመው መርዛማ ተንኮል ፤ አውሬው ያቀናበረው ስውር ደባ መኖሩን እናስተውላለን፡፡ በእርግጥ ይህ ኦርቶዶክስ የሚለው ስያሜ ብዙዎች በየዋህነት አሜን ብለው እንደተቀበሉት “ርትዕ ቀጥተኛ ሃይማኖት” ብሎ ቤተክርስቲያንን ለማመስገን የተሰጠ ስያሜ አይደለም::” በማለት ኦርቶዶክስ የሚለውን ስም ነጥለው ይተቻሉ ፤ ትክክል አለመሆኑንም ያስተምራሉ፡፡

ባለፈው አንድ ምዕት አመት ውስጥ ቤተክርስቲያንን ለማጥመድ አውሬው የዘረጋቸው ዋና ዋና ወጥመዶች በማለት ነጥቦችን በማስቀመጥ እንዲህ ይተነትናሉ፡-
1.     የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የተባለው መመስረቱ ፡- “ቅድስት ቤተክርስቲያን ከልዑል እግዚአብሔር ያገኝችውን ከነቢያት ከሐዋርያት የተረከበችውን ንጹህ ቃለ እግዚአብሔር በጥንቃቄ አዘጋጅታ ልጆቿን መመገብ ሲገባት መርዛማ ጥርጥር ከሚነዙ መናፍቃን ጋር መጽሐፍ ቅዱስን  ለመጻፍ ማኅበር መግባቷ ለብዙዎች ማሰናከያ ወጥመድ ሆኗል፡፡”
2.    የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማኅበር መቋቋሙ ፡- “ቤተ ክርስቲያን በጽናት በሥላሴ አለት ላይ ቆማ አላውያንን መናፍቃንን ገስጻ የሰው ልጆችን ሁሉ ወደ ተዋህዶ እንዲገቡ ማድረግ ሲገባት በገንዘብ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ወዳጅነት ከመናፍቃን ጋር መመስረቷ ለብዙዎች መውደቅና በአውሬው መማረክ ምክንያት ሆኗል፡፡” በማለት የአብያተክርስቲያናት ማኅበር መቋቋሙን ይቃወማሉ፡፡
3.    ተዋህዶ ሃይማኖታችን ኦርቶዶክስ ተብላ መሰየሟ፡- “የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ከአርያም ከልዑል መንበር የተገኝ መንፈስ ቅዱስ የፈቀደው ሰማያዊ ልሳን ስለሆነ ሰይጣን ባዘጋጀው ምንነቱ ባልታወቀ  አነጋገር መጠቀም ፈጽማ አይገባትም ነበር ፡፡ ነገር ግን አውሬው እረኞችን ከተኩላ ፤ ስንዴውን ከእንክርዳድ በመቀላቀልና ብዙዎችን ግራ አጋብቶ ለማጥመድ ባዋቀረው ተንኮል ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ በሚል ስያሜ ስትጠራ ኖራለች ፤ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብሎ ከመሰየም ይልቅ ካቶሊክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብሎ መሰየም አስር እጥፍ የተሻለ ነበር ፤ ነገር ግን ሁለቱም (ኦርቶዶክስና ካቶሊክ) የመናፍቃን ማለትም ክርስቶስ ሁለት ባህሪ ነው የሚሉ የንስጥሮስ ጭፍሮች ስያሜዎች ስለሆኑ ለቤተክርስቲያን ፈጽሞ አላስፈላጊ ህገወጥ ስያሜዎች ናቸው ፡፡” በማለት ያምናሉ፡
4.    በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ የሰንበት ት/ቤቶች መቋቋማቸው፡- ጽሁፉ ይህን በተመለከተ እንዲህ ይላል “በዘመናችን ብዙዎች በየዋህነት የሰንበት ት/ቤት ማለት የፍጹማን ለቀናችው ሃይማኖት ቀናኢ የሆኑ የመላእክት ማኅበር ነው ብለው ያምናሉ፡፡ነገር ግን ከጥንት ከጠዋት ሰንበት ት/ቤት ለምን አላማ ? በምን አይነት አኳኋን ተመሰረተ ? ከተመሰረተ በኋላ ምን አይነት ድርጊቶች ሲፈጸሙበት ኖረ ? የሚለውን ስንመረምር እጅግ እናዝናለን :: ሴቶችን ከሊቃውንት በላይ አድርጎ በታቦተ ህጉ ፊት ወረብ ሲያስወርብ ላስተዋለ በሰንበት ላይ የቀናውና ያመጸው የዲያቢሎስ መንፈስ የአውሮፓን ከንቱ ባህል አምጥቶ ሰንበት ትምህርት ቤት (Sunday School) ብሎ ሲመሰርት ለምን አላማ እንደሆነ ምስጢሩ ግልጽ ነው፡፡ በአጭሩ የሰንበት ት/ቤት አውሬው የቤተክርስቲያንን  ልጆች ለማጥመድ የመሰረተው ረቂቅ ስውር ወጥመድ ነው ፡፡ ለዚሁ ትልቁ ማስረጃችን ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ያዘኑበት የአመጸኞች ስብስብ ነው ፤ ምን ያህል ያጌጠ ሽፋን እንደተከናነበ በውስጡ ግን ምን እንደሚካሄድ ግልጽ ነው ፤ ይህ ካለ እኔ ለቤተክርስቲያን ማንም የለም እያለ ከመናፍቃን ፤ ከጳጳሳት ጋር ሽር ጉድ የሚል የኢትዮጵያ ቅዱሳንን ቃል የሚያስተሀቅር ትእቢተኛ ጎራ …” በማለት ለማኅበረ ቅዱሳንና ለሰንበት ትምህርት ቤት ያለውን አቋም ያስቀምጣል፡፡ ድሮም ይሁን አሁን ከቤተክርስቲያቱ በተቃራኒ ጎራ የቆመ ሰው ማኅበሩን እጅጉን ይጠላዋል ፤ ያልሆነ ስምም ሲሰጠው ይስተዋላል ፤ መጽሀፍ ጽፎ በማሳተም ጥላቻውን ይገልጻል ፤ እነዚህ ቡድኖችም ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከተሃድሶያውያን የተለየ አቋም የላቸውም ፡፡
ጽሁፉ በመቀጠልም እንዲህ ይላል “በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ ይዞ ቅዱሳንን ሁሉ አስከትሎ ከሁለት ሺህ ዓ/ም ጀምሮ ወደዚህ አለም የመጣው ቅዱስ ኤልያስ ከቅዱሳን ገዳማውያን አባቶች ጋር ቃል በቃል ተነጋግሮ ምስጢራትን ገልጾላቸዋል፡፡ እኛ የአንዲቷ ቀጥተኛ የተዋህዶ ሃይማኖት ልጆች ሁሉ ማር ተቀብቶ  የቀረበልንን መርዝ ባማሩ ቃላት አጊጦ የተጫነብንን የሰይጣን ተንኮል ማስተዋልና ማወቅ ስለሚገባን ከእነዚያ ቅዱሳን አባቶቻችን የተናገሩንን ዋና ዋና ነጥቦች እናሳስባችኋለን” በማለት ይቀጥላል፡፡
1.     ስለ ዕለተ ሰንበት፡- “ብዙዎች በየዋህነት ጌታ ያዘዘው ሐዋርያት የደነገጉት ነው ብለው እለተ እሑድን ሰንበት ነች እያሉ እንደሚያስቡ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን እሑድ መቼ? በእነማን? ለማን አላማ ? ሰንበት ተብላ ልትሰየም ቻለች ብለን ስንመረምር የሰይጣን ተንኮልን  እናስተውላለን፡፡ ይህውም የሮም ጣኦት አምላኪዎች የጌታ የዕረፍት ዕለት ሰንበት(ቅዳሜ) አስቀርተው የራሳቸውን የጣኦት ቀን (የፀሐይ ቀን) በማክበር የጠነሰሱት ሴራ መሆኑን ታሪክ ይነግረናል፡፡ ይህ የቅዳሜና የእሁድ ጉዳይ ከአራተኛው መቶ አመት ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ታላቅ ሁከት ማስነሳቱን ነገሥታቱም ለስልጣናቸው ሲሉ ሁለት ሰንበት የሚል አጉል ውሳኔ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ ስድስት ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ያረፈባት ፤ በታቦተ ጽዮን ላይ በጣቱ አክብር ብሎ የጻፈላት  ፤ አንዲቱ ዕለት ሰንበት ቅዳሜ መሆኗን ፤ እሁድ ግን ጌታ ስራ የጀመረባት የተጸነሰባት ፤ ከሙታን የተነሳባት ፤ እንጂ ስራ ሰርቶ ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባት ዕለተ ሰንበት አለመሆንዋን ምስጢር አዋቂው ቀናኢ ነብይ ኤልያስ ለአባቶቻችን አረጋግጦ ነግሯቸዋል” ብለው ያምናሉ ይሰብካሉም፡፡
2.    ስለ ማህተባቸውና ልብሳቸው፡-“እግዚአብሔር አምላክ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ጎልቶ የሚታየውን የቀስተ ደመና ህብረ ቀለም ልዩ የከበረ ምልክት አድርጎ እንደመረጠው ቅዱሳን መጻህፍት ያስረዳሉ፡፡ በመጀመሪዋ እለተ እሁድ መላእክር ሲፈጠሩ ሱራፌል ፤ ኪሩቤል ጌታን በመንበረ ጸባኦት ላይ በዚህ ቀስተ ደመና ህብረ ቀለም ምሳሌነት ነው ተመልክተው የሰገዱለትና ያመሰገኑት(ራዕ 4) ፤ ጌታ ለአዳም በኋላም ለአባታችን ለኖህ ቃል ኪዳን ሲሰጠው የፍጥረት ሁሉ እናት የድንግል ማርያም ምሳሌ የሆነውም የቀስተ ደመና ምልክት አድርጎ ነው፡፡ በአጭሩ የቀስተ ደመና ህብረ ቀለም የሥላሴ ምሲጥራዊ ሀልዮት ፤ የድንግል ማርያም ርህራሄ ፤ ቃል ኪዳኗን ፤ አንዲቷን ተዋህዶ ሃይማኖትን የሚያጠይቅና የሚገልጽ የከበረ ምልክት ነው፡፡ አባቶቻችን ኢትዮጵያ የድንግል ማርያም ሀገር  የእርሷ ምሳሌ መሆንዋን ለማጠየቅ ድንግል ልጇን ታቅፋ  እንዳለች የሚገልጠውን ምስጢር በሰንደቅ አላማ ላይ የይሁዳ አንበሳ(የጌታን) ምስል በመሳል አቆይተውልናል፡፡  ስለዚህ የተዋህዶ ልጆች ሁሉ ልብሳችንን ጸአዳ ፤ የልብሳችንን ዘርፍ  ፤ የአንገታችንን ማህተብ የቀስተ ደመና ማህተብ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ጥቁር ልብስ ጥቁር ማህተብ ተስፋ ትንሳኤ ላለን ክርስቲያኖች ፈጽሞ አይገባም ፤ የታሪክ መዛግብት እንኳን  ክርስቲያኖች ጥቁር እንዲለብሱ የተገደዱት በእስላሞች ተጽህኖ መሆኑን ያስረዳሉ” በማለት ስለ ልብሳቸውና ስለ አንገት ክራቸው ምን መሆን እንዳለበት ለአማኞቻቸው ይመክራሉ፡፡
3.    ይሁዳ ፤ አይሁድ ፤ አይሁዳውያን ስለሚለው የክብር ስም፡-……….
4.    
ስማቸው ስለተሰወረ ቅዱሳን፡-  ……
በማለት ነጥቦቻቸው ግልጽ አድርጎ በማስቀመጥ አስተምህሯቸው ምን እንደሆነ በዘጠኙ ገጽ ጽሁፍ ላይ ይተነትናል ፡፡

እንደ አርቲስት ጀማነሽ ፤ ጥቂት የቲዎሎጂ ተማሪዎችን ፤ የቤተክርስቲያኑቱን አገልጋዮችን ፤ ግራ እና ቀኛቸውን ያልለዩትን ሰዎች በመሰብሰብ ማታ ማታ ከምሽት አንድ ሰዓት እስከ ውድቅት ለሊት ድረስ መርሀ ግብር በመያዝ አስተምህሯቸውን በሰዎች ጭንቅላት እየጫኑ ይገኛሉ ፡፡ አርቲስቷም ከዚህ አስተምህሮ እግዚአብሔር ከሚያስወጣኝ ቢገለኝ እመርጣለሁ ብላለች ፤ ሰዎቹ ምን ያህል ስራ እየሰሩ መሆኑን ለመገንዘብ አስምህሯቸው ከህይወት ጋር ንጽጽር ውስጥ የገባበትን ሁኔታ እየታየ ይገኛል፡፡

ቀድሞ “ተሃድሶ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ምዕመኑ በቂ መረጃ ቢኖረው ኖሮ ራሱንና ቤተክርስቲያኒቱን በአግባቡ መጠበቅ በቻለ ነበር፡፡ ምዕመኑ ተሃድሶያውያንን በአግባቡና በጊዜው ባለማወቁ ቤተክርስቲያንን ብዙ ዋጋ አስከፍሏታል፡፡ ጊዜው ደርሶ ጥቂቶች ሰነድ ተጠናክሮባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ እስኪለዩ ድረስ ብዙ ምዕመን ብዥታ ውስጥ ይገኝ ነበር ፡፡ ተሃድሶያውያን ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ያሰቡት ባይሳካላቸውም ጥቂት ምዕመናንን ግን ማስኮብለላቸው ያየነው እውነት ነው፡፡ ያሬድ አደመ እና አቶ በጋሻው ደሳለኝ ከሀዋሳ ከቅዱስ ገብርኤል ሲለዩ አብረዋቸው የነበሩትን ሰዎች ቀጥታ ወደ አዳራሽ ነበር ይዘዋቸው የሄዱት ፡፡ አሁንም አዳራሽ ተከራይተው ያስኮበለሉትን ምዕመን በመጥራት እንደ ፕሮቴስታንታውያን መርሀ ግብራቸውን በአዳራሽ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ተሃድሶያውያን ጊዜውን መምሰል በሚል ስትራቴጂያቸው ከሁለት ሳምንት በፊት የካቲት 23 እና 24 በሲዳማ ባህል አዳራሽ “ውዳሴ መለስ ወጳውሎስ” በሚል አርዕስት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊና 5ኛው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የሞቱበት ስድስተኛ ወራቸውን የማሰብ መርሀ ግብር ለታይታ አካሂደዋል፡፡

 አሁንም እነኚህም ኤልያሳውያን “ተዋሕዶ” ነን ባዮችን ምዕመኑ ቀድሞ ካላወቃቸውና አስተምህሮታቸው ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያፈነገጠ መሆኑን ተረድቶ ካልተቃወማቸው ወደፊት ተሃድሶያውያን ያደረሱትን ጉዳት ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ሊያደርሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቅርቡ በኢግዚቢሽን አዳራሽ ትልቅ የሚባል የመጀመሪያ መርሀ ግብር ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያሉ ስለሆነበቤተክርስቲያኒቱ ስም በመጠቀም ሌላ ውዥንብር ምዕመኑ ላይ እንዳይፈጥሩ ቤተክርስቲያኒቱ ይህ ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን እንደማይመለከት ቀድማ በመገናኛ ብዙሀን ማሳወቅ ይኖርባታል፡፡ ያለበለዚያ እንደ 2002 ዓ.ም የቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ የተሃድሶ ጉባኤ ምዕመኑ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እንደ በግ ሊነዳ ይችላል፡፡

አንድ አድርገን የዚህን ራሱን “ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ” ብሎ የሚጠራውን ቡድን ምዕመናን አካሄዳቸውን አውቀው ቀድመው ይዘጋጁ ዘንድ ራሳቸውንም ከዚህ አይነት አስተምህሮ ይጠብቁ ዘንድ በቡድኑ የተጻፈ ለአባሎቻቸው የተበተነውን ይህን ጽሁፍ በፒዲፌ መልክ አቅርባላችዋለች፡፡በፒዲኤፍ ለማንበብ ይህን የጫኑ


እነዚህ ቡድኖች ገዳሞች ላይ በመዘዋወር ምን አይነት ስራ አካሄዱ? በምን ስራቸው ታሰሩ? ለምንስ ተፈቱ ? እና መሰል ተጨማሪ መረጃዎችንና አስተምህሯቸውን ወደፊት ለአንባቢያን እናደርሳለን……

ቸር ሰንብቱ  

5 comments:

  1. ትልቅ ሥራ ነው እየሠራችሁ ያላችሁት ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ፡፡ ይኸ መረጃ እስከ አሁን የትም ሥፍራ ላይ ቀርቦ አላየሁትም ፡፡ ንቀው ትተውት ወይም አደገኛነቱን ሳያውቁት ቀርተው እንደሁ አላውቅም ፡፡ እናንተ ግን ለማስተማር በርቱ ፡፡ እምነታቸውና ትምህርታቸው በሥርዓቱ ከታወቀ ራሳችንን በቀላሉ ከእነ እንደዚህ ዓይነቶቹ መጠበቅ እንችላለን ፡፡

    ReplyDelete
  2. AndADergen.First of all thank you for making us
    know such devil-drive concepts of anti-Tewahido
    conspiracy organized by our former enemies "tehadis
    o".They can exert utmost effort to attack us.but
    they will never win.What is surprising thing is that every enemy targets Mahibere Kidusan.Why?
    We know that our children who working in Mahibere
    kidusan are the backbone of Tewahido.We too are.

    ReplyDelete
  3. እኔ ስህተታቸዉ ምን እንደሆነ አልገባኝም!

    ReplyDelete
  4. ገና ሰይጣን አይን አውጥቶ ይመጣል:: ይህንን ሥራ በዋናነት ሲያከናውን የነበረው ሰው (ምን አልባትም ከፍተኛ አመራር)ዛሬ ሳይሆን ከሶስት አመታት በፊት አውቀዋለሁ የሚገርመው ግን በቅዱሳን አማላጅነት በመላእክት ተራዳዕይነት ቤተክርስትያን ለማገልገል ደፋ ቀና የሚሉትን ማህበረ ቅዱሳንንና ሌሎች ተመሳሳይ ማህበራት አጥብቆ መጥላቱና መፍረስ በተቻል ፍጥነት መወገድ አለባቸው ብሎ ማመኑና መትጋቱ ይገርመኝ ነበር::ሁልግዜም እነርሱ በቻ ትክክል እንደሆኑ በቅርቡ ዓለም እንደምታልፍ(በኛ እድሜ) ይነግረኝ ነበር::ከተሃድሶ ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነትም እንዳላቸው ምንም ጥርጥር የለውም ::እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅልን እኛም የሚጠበቅብንን እንስራ ::

    ReplyDelete
  5. አባቶች እነዘህ ቅባት ጸጋ ዘመኝ መለኮት እና ተኃድሶ በውስታቸው ያለማውገዝ አክፈው ይዘው እነዚህ በመካወም ቢነሱ ኦርተዶክስ የሚለውን
    ከመካወማቸው ውጭ ከዘመኑ ከመናፍካን ጋር ለሆዳቸው አድረው ቤተ ክርስትያንን ከውስጥ ከምያፈርሶት ቢበልጡ እንጂ..............

    ReplyDelete