Tuesday, March 19, 2013

መናፍቃን “ሁዳዴ ጾምን ከኦርቶዶክስ ጋር አብረን እንፁም” እያሉ ነው


  • ይህን አቋም በኢቢኤስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ለ8 ወራት ያህል አውርደናል አውጥተናል፡፡
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነች ረዥም ዓመት በወንጌል አገልግሎት በወንጌል የቆየች ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ከዚች ቤተክርስቲያን ጋር ቀን ወስኖ መጾም በረከቶችን ያመጣል ፤ በአንድነት በኅብረት ሲጸለይ ሲጾም እግዚአብሔር ዘንበል ይላል፡፡
  • ይህንን ስንል የቤተክርስቲያኗ የተለመደ ስርዓት አለ ፤ ቤተክርስቲያኗ የኛ ናት ፤ አካላችን ናት በማለት ማክበራችንንና ማስተዋላችንን ለማሳየት ነው፡፡
  • እኛ የራሳችን የሆነ ማንነታችንን የሚያሳይ  ጤነኛ የባህል እጦት አለብን፡፡



(አንድ አድርገን መጋቢት 11 2005 ዓ.ም)፡- ቀድሞ ከአስርና ከሃያ ዓመታት በፊት ቤተ ክርስቲያኒቱን በቅርቡ የማያውቋት ወገኖች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፍጹም ከወንጌል ያፈነገጠች ፤ ባህላዊ ነገር የሚበዛባት ፤ ከወንጌል ጋር ግንኙነት የሌላት አድርገው ይሰብኩ ነበር ፡፡ ይህ አካሄድ እንደማያዘልቃቸው የተረዱት ወገኖች ቀስ በቀስ በመንሸራተት ቤተክርስቲያን ያስቀመጠችውን ስርዓት በመውሰድ ሲጠቀሙ እየተስተዋሉ ይገኛሉ ፡፡ ማንም ባይጠይቃቸውም ከበሮውን ፤ ጽናጽሉን ፤ መቋሚያውን ፤ እና መሰል መገልገያዎችን ወደ አዳራሾቻቸው ካስኮበለሉ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአገልጋዮቿ የምትሰጠውን የማዕረግ ስም መጠቀም ከጀመሩም ሰንበትበት ብለዋል፡፡ መጋቢ ሐዲስ ፤ መጋቢ ብሉይ እና መሰል ማዕረጋት በቤታቸው ይገኛሉ ፡፡ ቤተክርስቲያን ለመዘምራን ፤ ከቀሳውስት ፤ ለዲያቆናት እና ለመነኮሳት ለይታ ያስቀመጠቻቸውን አልባሳትን ከንዋየ ቅዱሳት መደብሮቻችን መግዛት ጀምረዋል ፡፡ የቅዱስ ያሬድን ዜማ ቤተ ክርስቲያን ባስተማረቻቸው ሰዎች አማካኝነት አባሎቻቸውን በማስተማር ፍጹም አይን ያወጣ ዝርፊያ በማድረግ እንደ ተሐድሶያውያን መዝሙር መሳይ ዘፈኖቻቸውን መስራት ጀምረዋል ፤ ምንም የግጥምም ሆነ የዜማ ለውጥ ያልተደረገባቸው መዝሙሮቻችን የአዳራሾቻቸው ማሞቂያዎች ከሆኑ ቆይተዋል ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በበገና የታጀበ መዝሙር ለገበያ አቅርበዋል ፤ ስብከቶቻቸው ላይም ስለማያውቁት ቅዱስ ያሬድ በማንሳት ሰማያዊ ጸጋን ከአምላክ መቀበሉን እየሰበኩ ይገኛሉ ፤   .. ታዲያ እኝህ ሰዎች ምን ቀራቸው ?

ከወራት በፊት ወደ አሰላ ከተማ ባደረግነው ጉዞ ፤ አሰላ የሚገኙ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በ40 እና በ80 ቀን  በአዳራሾቻቸው ልጆቻቸውን ክርስትና ማስነሳት መጀመራቸውን ሰምተናል ፡፡ ለእማኝም ይሆን ዘንድ ፎቶዎችን ተመልክተናል ፡፡ እኛን የገረመን የ40 እና የ80 ቀን በማለት ቤተክርስትያን ልጇቿ የሥላሴ ልጅነትን የምትሰጥበት ትርጉሙን አንብበውም ይሁን ከሰው ጠይቀው ሊያውቁት ይችላል ፡፡ ግን ልጆቹን ሲያጠምቁ ምን አይነት ጸሎት እንደሚያደርጉላቸው ማወቅ ነበር የጓጓነው ፤ ማን ያውቃል ያስኮበለሉት አገልጋይ ሊኖርም ይችላል ፡፡ ሌላው ልጆቹን ሲያጠምቁ ስመ ክርስትና እንደሚያወጡ እና እንደማያወጡ በጊዜው ማወቅ አልቻልንም ፡፡

በሌላ ጊዜ በአንድ የሥራ ገበታ ላይ የምንውል አንድ የስራ ባልደረባችን አባቱን በጠና ይታመምና ከስራ ይቀራል ፡፡ ስልክም ደውለን ለምን እንደቀረ ስንጠይቀው “አባቴን ስላመመው ላቆርበው ነው” ብሎ ሲመልስልን እጅጉን ገረመን ፤ ነገሩን ለማጣራት ባደረግነው ሂደትም በአዳራሻቸው የጌታ ደም የሚባለው ከውጭ የሚመጣ ልዩ ወይን አለ ፤ የጌታ ስጋ የሚሉትም በምን እንደሚሰራ የማያውቁት ነገር መሆኑን ስናውቅ እጅጉን አዘንን፡፡ እነዚህን ቀላቅለው በመስጠት ቁርባን የሚባለውን ስርዓትም  ጥቂቶቹ ጀምረዋል፡፡


ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ “ፆም” የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት “ክፉ ከማየት ዐይንን ፤ ክፉ ከመስማት ጆሮን ፤ ክፉ ከመስራት እጅን ፤ ወደ ኀጢአት ከመሄት እግርን ፤ ክፉ ከመናገር ምላስን ፤ ክፉ ከማሰብ ልብን መከልከል ማለት ነው” በማለት ትርጓሜውን ያስቀመጡለትን ከስርዓተ ቤተክርስቲያን አንዱ የሆነውንና ጾምን በአሁኑ ጊዜ መናፍቃን “ሁዳዴን ከኦርቶዶክሳውያን ጋር አብረን እንጹም” ብለው ተነስተዋል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በኢ.ቢ.ኤስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ለረዥም ጊዜ ቅስቀሳ ተደርጎበታል ፡፡ በኢትዮጵያምም ይሁን ከሀገር ውጪ ያሉትን አማኞቻቸውን  የማሳመን ስራ ሲሰሩም ሰንብተዋል ፡፡ ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ አቋም ቢሆንም ሃሳቡ ደጋፊ እና ተቃዋሚ ፈጥሯል፡፡ 




ቄስ በሪሁን የዛሬ ዓመት ከነጋድረስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ራሱን ሲያስተዋውቅ “ቄስ በሪሁን እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት ወሎ ክፍለ ሀገር ነው፡፡ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርን በአዲስ አበባ እና ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ተከታትያለሁ፡፡ እንደ ማንኛውም ወጣት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነው ያደኩት፡፡ መካነ ኢየሱስ አጠገቤ ስለነበረች የወንጌል ሙቀትን ከሷ ነው ያገኝሁት” በማለት ነበር ራሱን ያስተዋወቀው፡፡ ይህው ሰው ከጌሤም መጽሔት ቅጽ 3 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም ዕትም ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር፡፡ ቃለ መጠይቁን እንዲህ አቅርበነዋል


ጌሤም፡- የአሁን ወደ አዲስ አበባ አመጣጥ ለእረፍት ነው ወይስ ለተለየ እቅድ አለህ?

ቄስ በሪሁን፡- እንግዲህ የአሁኑ ጉዞዬ ትንሽ ለየት ያለ ነው ፡፡ በኢቢኤስ ለስምንት ወር ያህል በተከታታይ ስናገርበት የነበረና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአብይ ጾም በአንድነት እንድንጾም በአብይ ጾሙ ዙሪያ ላይ የሚመለከታቸው ሰዎች ለማነጋር 2005ትን አብይ ጾም አብረን በመላው አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት  ስለሀገራችን ፤ ስለህዝባችን ፤ ስለወንዞቻችን ፤ ስለተራሮቻችን ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ ቃለ እግዚአብሔር በሚያዘው መሰረት ወደ እግዚአብሔርፊት በሥላሴ የምናምን በሙሉ እንድንቀርብ ለማስተባበር ነው የመጣሁት፡፡ ይህንን ጉዳይ ብዙ ሕዝብ ሰምቶት አስተያየታቸውንም በስልክ ፤ በኢሜል ለእኔም አሜሪካ ሀገር ባለኝ ኢሜልና አድራሻዬ ስልክ እንዲሁም ደግሞ አዲስ አበባ ባለው ቢሯችን በስልክ ምላሽ ሰጥቷል ፤ ጥያቄዎችንም አብራርቼአለሁ አሁንም ይቀጥላል፡፡ 


ጌሤም፡- ፆምን በተመለከተ ያለን አመለካከት ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የተለየ ነው፡፡ይህ የአብይ ፆም አብሮ መጾም አንዳንድ ከተረዳናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ጋር መተላለፍ አይፈጥርም? አንተ ይህን የተረዳህው እንዴት ነው?

ቄስ በሪሁን ፡- መሰረታዊው ነገር ወንጌላውያን አብያተክርስቲያንም ይሁን ቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ትሁን ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንም ትሁን በሥላሴ የሚያምኑ አብያተክርስቲያኖች በሙሉ  ፆም በመጾም ያምናሉ ፡፡ እና ጾም ሲፆም ራስን በአምላክ ፊት ማዋረድ ፤ የአምላካችን የእግዚአብርን ፊት መፈለግ ነው፡፡ ይህ መሰረታዊ እና የሚያግባባንና የሚያስማማን ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ካስማማን ሌላው ቀላል ይመስለኛል፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን  ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነች ፡፡ ረዥም ዓመት በወንጌል አገልግሎት የቆየች ቤተክርስቲያን ነችና ባህላዊውንም ከወንጌላውያን የተሻለ ዓይነት ሁኔታ ታውቃለች፡፡ ታሪካዊ አመጣጧ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይህን ያህል ዘመን ጸንቶ ፆሙ የመቆየቱ ሁኔታ የጥንካሬው ምክንያት የቤተክርስቲያቱ ሊቃውንቶች ቢያብራሩት ይሻላል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ መሰረታዊው የሚያግባባን ነገር ጾም በመጾም ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ የሚለው ዋንኛና  አንኳር አርዕስ ሊሆን ይችላል፡፡  ጾም ስንጾም ራሳችንን በእግዚአብሔር  ፊት ማዋረድና ማቅረብ ነው፡፡ ይች ቤተክርስቲያን ደግሞ የሁሉ ቤተክርስቲያን እናት ነች ፤ ታሪካዊ ነች ፤ አውራ ነች ፤ ስለዚህ ከእሷ ጋር ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ሲጾሙ በሀገራችን ላይ በረከት ይመጣል፡፡ ረድኤት ይመጣል ፤ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታም ችግር የለውም፡፡ ቲዎሎጂካልም ሊያነጋግር አይችልም ፤ ሊያነጋር የሚችለው ነገር ‹‹ደህና ነን›› ‹‹ሰላም ነን›› ብዬ ብሰብክ ሊመረመር ይገባዋል፡፡ 


ጌሤም ፡- ሥላሴዎች ላይ ያለን አንድነት እንደተጠበቀ ሆኖ ፆሙን ከመጾም ባሻገር  አንዳንድ የእምነት ወሰኖቻችንን የሚያፋልስ ነገር  አይፈጠርም ትላለህ? ምን ውጤት ይኖረዋል ብለህ ታስባለህ ?

ቄስ በሪሁን ፡- አሁን እያነሳሁት ያለሁት ስለ ልዩነት ሳይሆን ስለ ፆሙ ነው፡፡  ወንጌላውያን ቀን ወስነው የሚጾሙበት ጊዜ አለ፡፡ ስለዚህ ቀን በአንድነት ወስኖ መጾሙ ምንም የሚያስገባን ሌላ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም ሌላውን በሂደት እንመክርበታለን፡፡ ፆሙ ምን ጥቅም ያመጣል ለሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ ነው የሚታየው እና ይህ ሲታይ ጾም የፆሙ ሰዎች ምንድነው ያገኙት? ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስንመለከት ሰዎች ራሳቸውን ወደ እግዚአብሔር ፊት አዋርደው በሚቀርቡበበት ጊዜ ሀገራዊ ችግራቸው እንደሚለወጥ ቃለ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡  ከኦርዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር ወስኖ መፆም ጥቅም አለው ፡፡ ጥቅሞቹ አንደኛ ይች ቤተክርስቲያን  በሥላሴ የምታምን  ቤተክርስቲያን ነች  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ ፤ እንደሞተ ፤ ደሙ እንደፈሰሰ ዳግመኛ እንደሚመለስ መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ የምታምን ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ከዚች ቤተክርስቲያን ጋር  ቀን ወስኖ መጾም በረከቶችን ያመጣል፡፡ አንደኛ የሚያመጣውን በረከቶች ያለማወቅና ያለ እውቀት ወራቶቻችንን አናባራቸውም፡፡ በአንድነት ስንፆም ሊገለን የመጣውን እናባረዋለን፡፡ የቅደም ተከተል ጉዳይ ይሆናል እንጂ ሊገለን የመጣው ሁላችንንም ይገላል ፤ ሊያጠፋን የመጣው የቅደም ተከተል ጉዳይ ሁላችንንም ያጠፋናል፡፡ ስለዚህ በአንድነት መሆናችን በዚህ አቅጣጫ ጠቀሜታ አለው፡፡ ሁለተኛ መንፈሳዊው ጠቀሜታ አሁን እንደዘረዘርኩት በአንድነት በህብረት ሲፀለይ ፤ ሲፆም እግዚአብሔር ዘንበል ይላል ፤ ቅጠሉ ራሱ ይወዛል ፤ አፈሩ ራሱ ይወዛል ፤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ  ወንዞቻችን አፈር መሸርሸራቸውን ያቆማሉ ፤ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች እውቀትን ይሰጣል ፤ አዕምሮን ያበራል ፡፡ ስለዚህ ከዚች ቤተክርስቲያን ጋር  ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ በረከቱ በብዙ አቅጣጫ ነው፡፡


ጌሤም፡- በዚህ ጉዳይ ላይ  ምን አይነት እንቅስቃሴ እያደረግህ ነው?

ቄስ በሪሁን፡-  በመጀመሪያ ፆሙን እንፁም ብለን ሃሳቡን ያቀረብነው በቅዱስ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  ስርዓት ነው፡፡  ይህንን ስንል  የቤተክርስቲያኗ የተለመደ ስርዓት አለ ፤ ቤተክርስቲያኗ የኛ ናት ፤ አካላችን ነች በማለት ማክበራችንንና ማስተዋላችንን ለማሳየት ነው፡፡ ይሄንን በመጀመሪያ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች የስነ መለኮት ሊቃውንት አባቶች እንደሚገነዘቡት ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡

ሌላው ይህንን ሃሳብ እግዚአብሔር በውስጤ ሲያመጣ ያደረኩት ነገር በኢትዮጵያ ላሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች በልቤ የተቀመጠውን ሀሳብ ማስገዛት ነው፡፡ ይህንኑ በየደረጃው ላሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን  አብያተክርስቲያን መሪዎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሁሉ አሳውቄአለሁ፡፡


ጌሤም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት  በሌሎች እምነቶች እንዳይጠፉ ትልቅ ተግባር የፈጸመች ብትሆንም ባህላዊው ነገር መሰረታዊ የክርስትና  መርህ እያደበዘዘው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ አንተ ምን ትላለህ?

ቄስ በሪሁን ፡- ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ባህላዊ ሰርአቷ በዝቶ  ክርስትናውን ደፍቆታል ብሎ ያስባል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀሉ ሚስጥር በብዙ ባህላዊ ጉዳዮች ተሸፍኗል ነው የምትለኝ?፡፡ይች ቤተክርስቲያን ከሺህ አመታት በላይ የሄደች ቤተክርስቲያን ነች ፤ ይህ ሁሉ ዘመን ስትሄድ በመጀመሪያ መነሻዋ ምንድነው? ብለን ብንጠይቅ ከጣኦት አምልኮ  ነው ወደ ክርስትና የመጣችው? አይደለም፡፡በዚያ ዘመን የነበሩ የነበሩ አባቶች በጥንቃቄ የክርስትና እምነትን ሕግንና ወንጌልን በመቅደስ ውስጥ ሲያስኬዱ ስለነበሩ ነው ፡፡ በአንጻሩ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት  የተወለዱባቸውና ያደጉባቸው ባህል ስንመለከት የአሜሪካ ባፕቲስት ባህል ወይም የአውሮፓ ሉተራን ባህል ነው፡፡ የአይሁድን እምነት ከነጭራሹ አያውቁትም ፤ ታሪካዊ እይታቸው የትላንትና ነው፡፡ ወንጌሉ የ2000 ዓመቱ ነው ፡፡ እኛ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያን ዘለን የገባነው እዚያ ባህል ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ የራሳችን የሆነ ማንነታችንን የሚያሳይ  የባህል እጦት አለብን፡፡          
 …….

እድሜ ካለ ነገም ሌላም ነገር እንሰማለን
ቸር ሰንብቱ





20 comments:

  1. The Angry EthiopianMarch 19, 2013 at 11:20 AM

    oh no...some pentaye are going to loose their mind....

    ReplyDelete
  2. meche telemedena ketekula zimdina beluwachew

    ReplyDelete
  3. wedet tega tega.... dimet menkusa amelwan atresa! masebachew rasu bizu saykoy yamachewal. Tsom ena menafik kemeche wedih?! Go bang your bling bling gospel Tewahedon lekek!!!

    ReplyDelete
  4. betam yigermal! egzer mistirun yigletsilet!!

    ReplyDelete
  5. Specifically on the points raised, I can say Kesis Berihun seems logical and matured!

    ReplyDelete
  6. አንድ አድርገን እግዚአብሄር ሰራችሁን ይባርክ የነዚህ ሰዎች አመጣጥ በጥናት ይመስለኛል አንድ ነን አይነት ጨዋታ ለምሳሌ የእመቤታችንን ስዕለ አድህኖ በውጭ አዘጋጅተው በውስጥ ደግሞ የራሳቸውን መርዝ የሚረጩበትን ጥቅስ አድርገው ለምዕመናን በመበተን ለመሳብ ጥረትሲ ያደርጉ አጋጥሞኛል ስለዚህም አሁንም በጾም አንድነን ለማለት እንጂ ከዚህ የራቀ በጎ አላማ የላቸውም በእርግጠኛነት ድብቅ አላማ አላማ እንዳላቸው ማወቅ አለብን ይህችን ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዴት እንደሚያፈርሱ ሲመክሩ ነው የሚያድሩት

    ReplyDelete
  7. It is at least good to see some positive thinkers about the Orthodox Church from stolen sheep. It is good if the fast and is better if they made it with us.

    ReplyDelete
  8. ሰላም ጤና ይስጥልኝ አንድ አድርገን።፡እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

    ፕሮቴስታንቶችን ለመግለጽ ”መናፍቅ” የሚለውን ከመጠቀም ይልቅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ ያወጣላቸውን ስም “ሐሳዊያነ መሢሕ” የሚለውን መጠሪያቸውን መጠቀም ይሻላል ብየ አስባለሁ። ከሺህ አመት በላይ የሆነው የአዲስ ኪዳን አንድምታ ገና ፕሮቴስታንቶች ሳይመጡ “የክርስትናን ስም በመጠቀም ክርስቲያኖችን ከኃይማኖት የሚያስወጡ” ብሎ ተርጉሞታል። ፕሮቴስታንቶች እስኪመጡ ድረስ የክርስትናን ስም በመጠቀም ክርስቲያኖችን ከኃይማኖት የሚያስወጣ እምነት አልነበረም። ካቶሊኮች ይህን ምግባር የጀመሩት ፕሮቴስታንቶች ከመጡ በኋላ በፉክክር ነው።

    ቅዱስ መጽሐፍ - ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለው? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? እንዲል እኛስ የክርስቶስ ወገኖች ከነዚህ ከሐሳዊያነ መሢሕ ጋር ምን ህብረት አለን?

    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሰላም ጤና ይስጥልኝ አቶ ኃይለሚካኤል ፡፡
      እዚህ ላይ ለንባብ ያስቀመጡልንን ሳልመለከተው በመቅረቴ አስተያየቴ ዘግይቷል ፡፡ ለማንኛውም ማንበብ ከቻሉ የኔ አስተያየት ደግሞ እንዲህ ይላል ፡፡

      ከኘሮቴስታንቶች ጋር ያለን የክርስቶስ ትምህርት ልዩነት ፣ እነርሱ የሰውነት በህርዩን አግዝፈውና ትርጉም አሳስተው (ዘላለማዊ የየዕለት ካህናችን በማለት) አሁንም በየቀኑ እየለመነ ፣ እየጸለየ ከአብ ያማልደናል ስለሚሉን ነው እንጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆንና የአምላክነት እምነት ላይ ክህደት የለባቸውም ፡፡ ከዚህኛው መጠነኛ ልዩነት ይልቅ በሌሎች ዶግማዎችና የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች የማንስማማባቸው ርዕሶች በጣም ብዙና የጐሉ ናቸው ፡፡ ማለትም በነገረ ማርያም ፣ ነገረ ድኀነት ፣ ነገረ ቅዱሳንና ጻድቃን ፣ ስለ መስቀልና ቅዱሳን ስዕላት ፣ ስለ ትውፊትና አዋልድ መጽሐፍት ፣ ስለ ጾምና ጸሎት ፣ ስለ ምንኩስናና ንስሓ … … …. የምንለይባቸውን ትምህርቶችና እምነቶችን ማለቴ ነው ፡፡ እኒህን ከነገረ ክርስቶስ ውጭ ያሉትን የሃይማኖት ትምህርቶችና ዶግማዎች ስለሚክዱና ስለሚያጐድሉም “መናፍቅ” (ገመሰ ፣ ከፈለ ፣ አጎደለ እንዲል) የሚለው መግለጫ ትክክለኛ ባህርያቸውን ያንጸባርቃልና መጠቀሙ ስህተት አይደለም ፡፡ ሃሳዊ መሲሕ ሊባሉ የሚገባቸው ሌሎች የክርስቶስን አምላክነት ፣ ሰውነት ወይም ሰውነትና አምላክነትን የሚክዱ ወገኖችን ወይም ዓለምን ለማዳን የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተቃውሞና ክዶ ፣ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ ለሚነሳ ዋሾ መሆን አለበት ፡፡

      አስተያየቱ የቀረበው ለኘሮቴስታንት ቤተ እምነት ለመከራከርና ጥብቅና ለመቆም ሳይሆን እውነቱንና ሐሰቱን ለይተን ማወቅ ስለሚገባን ፣ ራሳችንንም ከስህተት ትምህርቶች እንድንጠበቅ ሃሳብ ለማካፈል ነው ፡፡ አሁን የርሶን ትርጉም ህዝብ ቢማርና አንድ ኘሮቴስታንትን በክርስቶስ ታምናለህ አታምንም? ብሎ ቢጠይቀው ፣ በመልሱ ለተዘጋጀ ወጥመድ አሳልፈው እንደሰጡትና እንደተጋለጠ ስለተሰማኝ ነው ፡፡ መልዕክቱ የክርስቶስን ሰው መሆንና አምላክነቱንም ስለተመሰከረለት ብቻ በመናፍቃን ስብከት እንዳይሳሳት ለማስገንዘብ ነው ፡፡

      አመሰግናለሁ

      Delete
    2. ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
      መድኃኔ ዓለም የተመሰገነ ይሁን።

      አቶ “ም” ... ከሐሳዊያነ መሢሕ (ከፕሮቴስታንት) ጋር ያለዎትን ሞቅ ያለ ፍቅር ካየሁት ቀደም ብያለሁ። በዚህ በጻፉልኝ ሀተታ አልገረምም። ስማቸውን “አባ እገሌ” ብለው የጠሯቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መነኩሴ ነኝ የሚሉ ሐሳዊ መሢሕ በአሜሪካን አገር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ የፕሮቴስታንትን እምነት በመስኮት እያስገቡ ስንቶቹን የዋህ የተዋህዶ ልጆች ከኃይማኖት እንዳስወጧቸው በአይኔ አይቻለሁ።

      ሐሳዊያነ መሢሕ በኢየሱስ ስም የሚመጡና ድንግሏን የሚያሳድዱ ስለሆኑ በዓለም ላይ ከፕሮቴስታንት የበለጠ በሐሳዊ መሢሕነት የሚሠራ ሌላ ድርጅት የለም። በመጽሓፍ ቅዱስ በሠፈረው መመዘኛ ቡድሂዝም፣ ሲክ፣ እስላም ወዘተ ሁሉ አህዛብ ይባሉ እንጂ እንደ ፕሮቴስታንት ሐሳዊያነ መሢሕነትን አያሟሉም።

      እግዚአብሔር ይመስገን።
      ኃይለሚካኤል

      Delete
    3. ስለማያውቁኝ ስለሆነ ሞቅ ያለ ፍቅር ማለት የቻሉትና ቅር አይለኝም ፡፡ እንደ ወንጌል ቃል ክርስቲያን የሆነ እግዚአብሔር የፈጠረውን ከዲያብሎስ በስተቀር ማንንም ፣ ምንንም አይጠላም ፡፡ ከወንጌል ተቀዳሚ ትምህርትም ቀጥሎ የሚሰበከው ፍቅር ነውና ወንጌሉን በሥርዓቱ የሚያነቡት አልመሰለኝም ፡፡ ለማይስማማዎትንና ለሚለይዎት እንኳን ጸልዩ ብሎ ነው የሚያስተምረን እንጅ ካይላ በሏቸው አይልም፡፡ ለወዳጅዎ ብቻ ቢጸልዩ ግብዞችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን ? ቤተ ክርስቲያናችንም በጸሎቷ ለእነ እገሌ ብላ አትለይም ፤ ለአገራችንና ለሕዝቦቿ ፣ ቀጥላም ለዓለም ሕዝብ ነው ጸሎት የምታቀርበው ፡፡

      አባ እገሌ እያሉ የወቀሷቸው ወንጌልን በተረዱትና ቤተ ክርስቲያን ባስተማረቻቸው ልክ መጽሐፍትን እየጠቀሱ ማስተማራቸውን ነው የማውቀው ፡፡ አውግዛ ለይታቸው ከሆነ ማስረጃዎትን ይጥቀሱልን ፡፡ ከዛ ውጭ ርስዎም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነው ብለው የሚሉትን ወደ አውደ ምሕረት ይዘው ቢመጡና ቢያስተምሩን ከርሶም እንኳን ለመማር ዝግጁ ነኝ ፡፡
      አመሰግናለሁ

      Delete
    4. የዘነጋሁትን ማብራሪያ ለማከል ፡-
      አህዛብና አረመኔ የሚባሉ መግለጫዎች በእግዚአብሔርና በሰጠው ህግጋት የማያምኑትን ለማመልከት እንጅ ክርስቶስን ከመቀበልና ከማመን ወይም ከመካድ ጋር አይገናኝም ፡፡ አምላክ ብለው የሚያመልኩት እግዚአብሔርን አይደለም ወይንም እንደ ሳምራውያን በእግዚአብሔር አምልኮ ላይ ባዕድ አምልኮን ይቀላቅላሉ ፡፡ እንዲያ ስለሆነምም ነው ቅድመ ክርስቶስ ፣ ማለትም በሥጋ በዚህች ምድር ከመመላለሱና ራሱን ከመግለጡ በፊት አሕዛብ የተባሉ ወገኖች ይጠሩ የነበሩ ፡፡ ክርስቶስን ስላልተቀበሉ የሚሰጥ ስያሜ ቢሆን ቃሉ ከዘፍጥረት እስከ ወንጌል መዳረሻ በየምዕራፉ ባልተጠቀሰም ነበር ፡፡
      የደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላትም አሕዛብን ሲተረጉም ቊጥራቸው የበዛ አረመኔዎች ፣ በፍጡር የሚያመልኩ ፣ ለጣዖት የሚሰግዱ ሕዝቦች ፣ ጨካኞች ይላቸዋል ፡፡ ሐዛቦች ፣ አሕዛቦች የአማርኛ ሲሆን አሕዛብ ቃሉ የግእዝ ነው ፡፡ መዝ 117፡1 ፣ ሮሜ 15፡11

      Delete
    5. ሰላም ጤናይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
      ምስጋና ለእግዚአብሔር።

      ከሰይጣን ጋር እኮ ያለን ግንኙነት አለመስማማት አይደለም። ጠላትነት ነው። ሐሳዊያነ መሢሕ ከምእራብ ወደ ሀያ ሚሊዮን የሚጠጉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና አማኞችን በማታለል ከኃይማኖት አስወጥተዋል። በዚህም ምክንያት እስላሞች በቁጥር የበላይነትን አግኝተናል እያሉ የኢትዮጵያን ሥርዓት ወደ እስላምኛ (አረብኛ) እንቀይራለን እያሉ ሲዝቱ አላዩም መሰል። ጁምአት፣ ሸሪያ ወዘተ።

      መጸለይ ያስፈልጋል። የተዋህዶን በጎች ዉጦ እንዲጨርስ ፕሮቴስታንትን ከፍ ከፍ አድርግልን እያልን ሳይሆን ሰይጣንን ገስጽልን ብለን ነው። ሰይጣንን እንደ ጸሎት የሚያስደነግጠው ነገር የለም። ጸሎቷን ለማስቀረት ነው ተዋህዶን የሚያሳድደው።

      አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንዲሉ እርስዎም አይኔን ግንባር ያርገው አላይም፣ ጆሮየም ይደፈን አልሰማም እያሉን ነው። ለርስዎ ሳይሆን ቅን ልቡና ላላቸው አንባቢያን ይሆን ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ ሐሳዊ መሢሕ ብሎ የጠራው አንድም ነጥብ ጠብ ሳይል ፕሮቴስታንትን መሆኑን በተለይ ራእይንና መጽሐፈ ዳነልኤልን በማንበብ ማወቅ ይቻላል። ለምሳሌ የትኞችም አይነት ሌሎች እምነቶች ሊያሟሉት የማይችሉትን አንዳንድ ነጥቦች በጥቂቱ እንይ።

      - ሐሳዊነ መሢሕ የሚመጡት ከምእራቡ ዓለም ነው - ዳንኤል ፰፥፭ ፣
      - ሐሳዊነ መሢሕ ኢየሱስን ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ይላሉ። እስካመንን ድረስ ድነናል ይላሉ። ማቴዎስ ም ፯ ፥ ከቁጥር ፳፩ እስከ ፳፫
      - ሐሳዊነ መሢሕ ክርስቲያኖችን በኢየሱስ ስም ከሃይማኖት ያስወጣሉ - ዳንኤል ፯፥፳፭
      - ከብዙ ህዝቦች ጋር ውል ያደርጋሉ፣ እግራቸው አያርፍም፣ የማይደርሱበት የዓለም ክፍል የለም - ዳንኤል ፱፥፯ ፣ ምሳሌ ፯ ከ ፲፩፥ ፲፬
      - በእየሩሳሌም የአይሁድን እርኩሰት ይተክላሉ - ዳንኤል ፱፥ ፳፯ ፣ ማቴዎስ ፳፬፥ ፲፭
      - ሐሳዊነ መሢሕ ከተቀማጠሉና ካጌጡ ከተሞች የወጡ ናቸው። ራዕይ ፲፰፥ ፲፬


      እግዚአብሔር ይመስገን።
      ኃይለሚካኤል

      Delete
    6. መጽሐፍ “ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።” 2 ጴጥ 1፡2ዐ-21 ፤ ይልብዎታልና ፣ ቃሉን እያጣመሙ ወደሚፈልጉት አግጣጫ አይውሰዱት ፡፡

      Delete
    7. እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ የሠፈሩና ከትርጓሜ መጽሐፍ የተገኙ ናቸው።

      Delete
  9. የተሻለ እምነት ያለው ሰው የደከመውን ይቀበላል ፣ እንደዚህ እንደዛ አሉ ማለት ሳይሆን ወንድሞቻችን ይህን ያህል ከመጡ የተቀረውንም መድሀንያለም ይግልፅላቸው ዘንድ መፀለይ ፣ ከእነሱ ጎራ የሆኑ ብዙ ወንድሞቻችን እውነቱን እንዲረዱልን በትህትና እንቀበላቸዋለን ፣ጠላታችን በውስጣቸው ያለው እንጂ እነሱ ወንድሞቻችን ናቸው ።

    ReplyDelete
  10. ለጤና አይደለም

    ReplyDelete
  11. አሁን ያለንበት ግዜ የአብይ ፆም የመጀመሪያ ሳምንት ሲሆን ምዕመናን ለዚህ ፆምና ተጋድሎ ራሳቸውን አዘጋጅተው ከጀመሩት አንድ ሳምንት ሆኗቸዋል፡፡ታዲያ ስንፆም ምን ማድረግ አለብን?የዛሬው ወንጌላችን ይህንን የሚያሳየን ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን "ስትፆም በፍፁም ሰው አይወቅብህ"ይለናል፡፡ምንም እንኳን አብይ ፆም ትልቁ ፆምና ሁሉም ምዕመናን የሚፆመው በመሆኑ፤ሁሉም ጿሚ እርስ በራሱ ቢተዋወቅም፤ለሌሎች ግን ለእይታ ማድረግ እንደሌለብን መገንዘብ ይገባናል፡፡የምንፆመውም ከስጋ፣ከወተትና ከወተት ውጤቶችብቻም ሳይሆን የስጋ ምኞቶቻችንን ከሚያበዙብን ከአልኮልና ከመሳሰሉት ነገሮች ሁሉ መታቀብ ይገባናል፡፡
    እዉነት ይቻላችዋል መጀመርያ ከሆደ አምላክ ወደ ክርስቶስ ተመለሱ

    ReplyDelete
  12. very good comment march 25,2013,at 10:51 pm

    ReplyDelete