Tuesday, June 30, 2015

ሰበር ዜና – ከብር 4.6 ሚልዮን ብር በላይ ገንዘብ የመዘበሩ ሒሳብ ሹም እና ገንዘብ ያዥ ቃሊቲ ወረዱ

ለትውስታ፡- የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሶስት ዓመት ውስጥ 4.6 ሚሊየን ብር መመዝበራቸው ተገለጠ (ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የጥቅምት 2006 . ዕትም)
  •  
  • የታገድነው በደብሩ የተፈጸመውን ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ በማጋለጣችን ነው (ሰበካ ጉባኤው)
  • ጉዳዩን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዮን ተይዟል፡፡ 

(አንድ አድርገን ጥቅምት 28 2006 ዓ.ም)፡- በአዲስ አበባ ደቡብ ክፍለ ከተማ የሚገኝው የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ጳግሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ሕገ ወጥ ተግባር ፈጽሟል  በሚል በመታገዱ ችግር መፈጠሩ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ የመጋቢ ሐዲስ ቀሲስ ይልማ ቸርነት ፊርማና ማኅተም ያለበት በቁጥር 450/25/06 በቀን 03/01/2006 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የታገደው የሥራ ዘመኑን መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ቢያጠናቅቅም ሌላ የሰበካ ጉባኤ ሳይመረጥ በመቅረቱ በተለያየ ጊዜ ጭቅጭቅ ንትርክና ሁከት እንዲፈጠር በማድረጉ ማታገዱ ይገልጣል፡፡

Sunday, June 21, 2015

የድረሱልን ጥሪ ከአቃቂ ቃሊቲ ምዕመናን!!!


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ላለፉት ሃምሳ አመታት ከዘጠኝ በላይ ገዳማትና አድባራት ለጥምቀት በዓል ሲገለገሉበት የነበረውን በሀገረ በቀል ዛፎች ያጌጠውን ጥምቀተ ባህር ለልማት በሚል ሰበብ በክፍለ ከተማው  የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ባለስልጣናት ከቤተክርስቲያኗ ዕውቅና ውጪ ስፍራውን  አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ እየታረሰና እየወደመ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡


ከዚህ ቀደም የከተማዋን የመስቀል ማክበሪያ ስፍራን ነጥቀው ሌላ ምትክ ስፍራ እንዳይሰጥ በማድረግ በዓሉን የማጥፋት ተልእኮ በማንገብ እየተንቀሳቀሱ ያሉት  መናፍቃን አሁን ደግሞ ከሃምሳ አመት በላይ የቤተክርስቲያኗን የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራን ለልማት ሽፋን የማጥፋት ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ቦታው ሲወድም እስካሁን አንድም የቤተክርስቲያን አባቶችና አስተዳዳሪዎች ለምን? ብለው  መጠየቅና ጉዳዩን ለምዕመናን ለማሳወቅ አልፈቀዱም፡፡


ታላቅ ሰማያዊ አደራ የተጣለባችሁ አባቶች ከዝምታ ወጥታችሁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ አንድ ትውልድ እግዚአብሔርን የሚያመልክበትና ሃይማኖታዊ ስርዓት የሚፈፅምበት ቦታ ታስከብሩልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን አካላት በወቅታዊ ጉዳዮች እያነጋገረ ነው



  • ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችሁ እሰሩልን›› ያሉ አስተዳዳሪዎች የፖሊስ እና  የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት ወቀሱ
  • ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን እንደተቋም መወንጀል አትችሉም፤ ፖሊስ የእናንተ ብቻ አይደለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› // ሺፈራው ተክለ ማርያም


    
በሙስና መንሰራፋት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፍትሕ ዕጦት ሳቢያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየተደረገ ካለው የአገልጋዮች እና የምእመናን መነሣሣት ጋር በተያያዘ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የቤተ ክርስቲያኒቱን አካላት ማነጋገር ጀመረ፡፡ ብልሹ የሰው ኃይል አስተዳደር እና የፋይናንስ አሠራር በተከታዩ ዘንድ የሚፈጥረው የተከማቸ ቅሬታ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ እምነት እንዲያጡ ምክንያት እየኾነ እንዳለ በሥልጠና ሰነዶቹ የሚገልጸው ሚኒስቴሩ፣ በቅርቡም የወሳኝነትና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸው የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር እና የአገልግሎት አካላት የሚሳተፉበት ተከታታይ ውይይት እንደሚያካሒድ ተጠቁሟል፡፡በሚኒስቴሩ ጥያቄ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተመረጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ከትላንት በስቲያ ከቀትር በኋላ ከሚኒስትሩ / ሺፈራው ተክለ ማርያም እና ከሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው ጋር የውይይቱ ቅድመ ዝግጅት ነው የተባለ ምክክር አድርገዋል፡፡በዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተመሩ የኻያ አምስት አድባራት አስተዳዳሪዎች በተካፈሉበት በዚኹ ምክክር፣ ‹‹በማኅበራት ሰላማችንን እያጣን ነው፤ ሰንበቴ ሲከበን እናንተም የላችኹም፤ መንግሥትም የለም፤ አልደገፋችኹንም፤ አልረዳችኹንም›› የሚሉ ክሦች እና አቤቱታዎች ከአንዳንድ አለቆች መቅረቡ ተጠቅሷል፡፡ካለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ ጀምሮ የሀገረ ስብከቱ ሰንበት /ቤቶች ሙስና እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደርና ፍትሕ እንዲሰፍን፣ እምነትና ሥርዐት እንዲጠበቅ በሰልፎችና በስብሰባዎች  የሚያካሒዱት እንቅስቃሴም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ልብሱን ለውጦ የመጣበት ነው›› ብለዋል - አስተዳዳሪዎቹ፡፡