በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ላለፉት ሃምሳ አመታት ከዘጠኝ በላይ ገዳማትና አድባራት ለጥምቀት በዓል ሲገለገሉበት የነበረውን በሀገረ በቀል ዛፎች ያጌጠውን ጥምቀተ ባህር ለልማት በሚል ሰበብ በክፍለ ከተማው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ባለስልጣናት ከቤተክርስቲያኗ ዕውቅና ውጪ ስፍራውን አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ እየታረሰና እየወደመ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
ከዚህ ቀደም የከተማዋን የመስቀል ማክበሪያ ስፍራን ነጥቀው ሌላ ምትክ ስፍራ እንዳይሰጥ በማድረግ በዓሉን የማጥፋት ተልእኮ በማንገብ እየተንቀሳቀሱ ያሉት መናፍቃን አሁን ደግሞ ከሃምሳ አመት በላይ የቤተክርስቲያኗን የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራን ለልማት ሽፋን የማጥፋት ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ቦታው ሲወድም እስካሁን አንድም የቤተክርስቲያን አባቶችና አስተዳዳሪዎች ለምን? ብለው በመጠየቅና ጉዳዩን ለምዕመናን ለማሳወቅ አልፈቀዱም፡፡
ታላቅ ሰማያዊ አደራ የተጣለባችሁ አባቶች ከዝምታ ወጥታችሁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ አንድ ትውልድ እግዚአብሔርን የሚያመልክበትና ሃይማኖታዊ ስርዓት የሚፈፅምበት ቦታ ታስከብሩልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡
ከዚህ በፊት ጊዜ ደጋግሜ እንደተናገርኩት - ዘመነ ወያኔ/ዘመነ ትግሬ/ዘመነ አረብ የቤንጤና የእስላም መፈንጫ ዘመን መሆኑን ነበር። የአረብ ዘይት ብርና የምዕራባውያን እርዳት ድርጅት ተብየዎች (ስለላ ድርጅቶች) ገንዘብና ስልጠና እንደጉድ በያቅጣጫው ይጎርፋል ይነጉዳል በቦለቲካውም በማህበራዊ ኑሮም በስነ ጥበብም በንግዱም በዜና አውታራቱም በከፍተኛ ትምህርት ተቅዋማቱም....ወዘተ። የእኛ ቤተክርስትያን ደግሞ ማእከላዊነትን ተነጥቃ፣ በአንጃ እንድትከፋፈል የቤት ስራ እየተሰጣትና ስራውንም እየሰራች፣ እረኞቿም የመንጋቸውን ደም እየመጠጡ እንዲሁም ቦለቲካና ኮረንቲ በሩቁ የሚል አይሁዳዊ አስተሳሰብ እየሰበኩ መንጎቻቸውን በረጅም የሰመመን እንቅልፍ እያሰመጡ ይገኛሉ። የታሪካችን እውነታ እንደሚያመላክተን ከሆነ ነገሥታቶቻችንና ቤተክርስትያናችን አብረው ባይጓዙ ኑሮ፣ አገራችንም ኢትዮጵያ ቤተክርስትያናችንም ኢትዮጵያዊት ሆና በአሁኑ ዘመናችን አናገኛቸውም ነበር።ሁለቱም አይከሰቱም ነበር።
ReplyDelete