Sunday, June 21, 2015

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን አካላት በወቅታዊ ጉዳዮች እያነጋገረ ነው



  • ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችሁ እሰሩልን›› ያሉ አስተዳዳሪዎች የፖሊስ እና  የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት ወቀሱ
  • ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን እንደተቋም መወንጀል አትችሉም፤ ፖሊስ የእናንተ ብቻ አይደለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› // ሺፈራው ተክለ ማርያም


    
በሙስና መንሰራፋት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፍትሕ ዕጦት ሳቢያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየተደረገ ካለው የአገልጋዮች እና የምእመናን መነሣሣት ጋር በተያያዘ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የቤተ ክርስቲያኒቱን አካላት ማነጋገር ጀመረ፡፡ ብልሹ የሰው ኃይል አስተዳደር እና የፋይናንስ አሠራር በተከታዩ ዘንድ የሚፈጥረው የተከማቸ ቅሬታ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ እምነት እንዲያጡ ምክንያት እየኾነ እንዳለ በሥልጠና ሰነዶቹ የሚገልጸው ሚኒስቴሩ፣ በቅርቡም የወሳኝነትና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸው የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር እና የአገልግሎት አካላት የሚሳተፉበት ተከታታይ ውይይት እንደሚያካሒድ ተጠቁሟል፡፡በሚኒስቴሩ ጥያቄ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተመረጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ከትላንት በስቲያ ከቀትር በኋላ ከሚኒስትሩ / ሺፈራው ተክለ ማርያም እና ከሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው ጋር የውይይቱ ቅድመ ዝግጅት ነው የተባለ ምክክር አድርገዋል፡፡በዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተመሩ የኻያ አምስት አድባራት አስተዳዳሪዎች በተካፈሉበት በዚኹ ምክክር፣ ‹‹በማኅበራት ሰላማችንን እያጣን ነው፤ ሰንበቴ ሲከበን እናንተም የላችኹም፤ መንግሥትም የለም፤ አልደገፋችኹንም፤ አልረዳችኹንም›› የሚሉ ክሦች እና አቤቱታዎች ከአንዳንድ አለቆች መቅረቡ ተጠቅሷል፡፡ካለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ ጀምሮ የሀገረ ስብከቱ ሰንበት /ቤቶች ሙስና እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደርና ፍትሕ እንዲሰፍን፣ እምነትና ሥርዐት እንዲጠበቅ በሰልፎችና በስብሰባዎች  የሚያካሒዱት እንቅስቃሴም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ልብሱን ለውጦ የመጣበት ነው›› ብለዋል - አስተዳዳሪዎቹ፡፡


የሰንበት /ቤት አባላቱ የመለያ ልብሶቻቸውን (ዩኒፎርሞቻቸውን) ለብሰው በመውጣት በሚያደርጓቸው ሰልፎችና ስብሰባዎች መንግሥት የጸጥታ ርምጃ ሳይወስድ በዝምታ መመልከቱን የተናገሩት አስተዳዳሪዎቹ፣ የፖሊስ እና የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት በመውቀስ፣ ‹‹ወጣቶቹን እሰሩልን›› ብለው ሲጠይቁ ተሰምተዋል፡፡የቤተ ክርስቲያንን ሀብት ለግላቸው በማካበት ከገቢያቸው በላይ የሚኖሩ አለቆች በሥነ ምግባርና በፀረ ሙስና ኮሚሽን እየተመረመሩ በሀገሪቱ ሕግ እንዲጠየቁ የሰንበት /ቤቶቹ የሚጠይቁ ሲኾን  ዋና ሥራ አስኪያጁ እና አንዳንድ አለቆች በአንፃሩ፣ ‹‹ዶልፊን እና ሃይገር የሚያቆሙ ናቸው፤ ቢዝነስ አድርገውታልበማለት ይከሷቸዋል፡፡በምክክሩ ወቅት ብሶት ነው የሚያስጮኸኝ በማለት በከፍተኛ ድምፅ የተናገሩ አንድ አስተዳዳሪ፣ማኅበረ ቅዱሳን አባላቱን የሰንበት /ቤት ዩኒፎርም አስለብሶ መውጣት ጀምሯል፤ ሕንፃውን ከየት አምጥቶ ነው ያቆመው?” ሲሉ በሰንበት /ቤቶቹ መነሣሣት ማኅበሩን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ወጣቱን ዩኒፎርም እያስለበሱ ይልካሉያሉ የሌላ ደብር አስተዳዳሪም፤እንዴት አድርገን  መከላከል እንዳለብን አሠልጥኑን እንጂ ስለሰላም ምን ያደርግልናልበማለት የሚኒስቴሩን  ሓላፊዎች አስደምመዋል ይላሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች፡፡ፖሊስ እና የጸጥታ አካላት የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት የሚጠብቁ መኾናቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ / ሺፈራው ተክለ ማርያም፣ ‹‹ፖሊስ ለእናንተ ብቻ ነው እንዴ?›› ሲሉ አለቆቹን ጠይቀዋቸዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በሲኖዶስ ዕውቅና የተሰጠው ሕጋዊ ማኅበር መኾኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰው፣ ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ይኖራሉ እንጂ ማኅበር እያችሁ በጅምላ መጥራት የለባችኹም፤ ተቋሙን በጅምላ መፈረጅ ወንጀል ነው፤›› ብለዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱን ጨምሮ አስተዳዳሪዎቹ በሚመሯቸው አድባራት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ለምእመናንና ለሰንበት /ቤቶቹ ወጣቶች ምሳሌ መኾን እንደሚገባቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ሰው እሰሩ ያላችኹት ሌላ ችግር ነው የሚፈጥረው፤ የምናስረው ሰው የለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› በሚል ለአለቆቹ የእሰሩልን ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በሚኒስቴሩ ዕቅድ መሠረት ይካሔዳል የተባለውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ከሚታየው የአገልጋዮችና የምእመናን መነሣሣት ጋር የተገጣጠመው ይኸው የቅድመ ውይይት ምክክር፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መዋቅር የወሳኝነት እና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸውን የማኅበረ ካህናትን፣ የማኅበረ ምእመናንና የሰንበት /ቤቶች ተወካዮችን   ሊያካትት እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡

በዘመናዊ አሠራር፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰላም ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ዋናው ውይይት፤ በሚቀጥሉት ኹለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር የሚኒስቴሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ የውይይቱን አቅጣጫ ለማመቻቸት በሚል ከትላንት በስቲያ በሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ከተመሩት የአድባራት አለቆች ጋር ከተካሔደው ምክክር ፍጻሜ በኋላ ‹‹ዘመናዊ አሠራር ዴሞክራሲዊነት እና ብዝኃነት›› በሚል ርእስ በሚኒስቴሩ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ እንደተሰጣቸውም ንጮቹ ገልጸዋል፡፡

Source :- Addis Admass

No comments:

Post a Comment