(አንድ አድርገን ጥር 16 ፤ 2004ዓ.ም)፡- እነዚህ ሰዎች በጥምቅቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የታገዱ እና ህገወጥ የተባሉ ሰባኪያን እና ዘማሪያን መሰል የተኩላው ለምድ የለበሱ ሰዎች (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው) በየትኛው በር ገብተው ነው የቤተክርስትያናችን አዳራሽ የተፈቀደላቸው ? እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከቅዱስ ሲኖዶስ የትኛውም አውደ ምህረት ላይም ሆነ የትኛውም ቤተክርስትያን ላይ የመስበክ ፍቃድ እንዳይሰጣቸው እና ቤተክርስትያንን የማይወክሉ መሆኑን ገልፆ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመላው አዲስ አበባ ውስጥም ላሉ ፤ ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ አብያተክርስያናት በሀገረስብከታቸው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጎ ነበር ፤ ታዲያ ይህን ጉባዬ ለዛውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ማን ፈቀደላቸው?
ፍቃድ የተሰጠው ገቢ ማሰባሰቢያ
አዘጋጆች፡- (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው)
፡
አሁን ግን እያልን ያለነው እነዚህ በአውደ ምህረት ላይ የመስበክና የመዘመር ፍቃድ የተነፈጋቸው ሰዎች አቅጣጫቸውን ለውጠው በዚህ መልክ ብቅ ማለታቸው ገርሞንም ደንቆንም ጭምር ነው ፤ የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ የተሀድሶያውያን ሁለተኛ መናህሪያ ከተማቸው ባደረጓት በሐረር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ የታኦሎጎስ አንደኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈልጉትን ሀሳብ ለማስተላለፊያ ያመቻቸው ዘንድ በጠቅላይ ቤተክህነት በወረደ ቀጭን ትእዛዝ በአላቸውን ሲያከብሩ ተመልክተናል፤ የሲኖዶሱ ውሳኔ የማይከበር ከሆነ ለምን ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ መሰብሰብ አስፈለጋቸው ?
በተሀድሶ አቀንቃኝነት ስሙ ዘወትር የሚነሳው አስግድ ሳህሉ ሳይቀር ፤ ከመላ አባሎቻቸው ጋር የገቢ ማሰባሰቢያ በሚል ሰበብ አዳራሹን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃጅነት ሊዘሉበት ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀው ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ፤ ያገሬ ሰው ‹‹በጅብ ላይ ስጋ አይጫንም››የሚል ብሂል አለው ፤ እኛም ሲጫን አይተን አናውቅም ፤ ጅብን አምኖ ስጋ ቢጫን እንኳን የተላከው ቦታ እንደማያደርስ እሙን ነው ፡፡
ሰው መሳይ በሸንጎ ጨዋ ለመምሰል ከሆነ ፤ ጅብ ጨዋ ሆኖ አያውቅም እና ምዕመኑን አትሸውዱ ፤ ይህ ጉባኤ ከለባት ነው፡፡ የውሾቹን ጉባኤ ማስቆም የሁላችንም ድርሻ ፤ ልብሳቸው ተዋህዶ ውስጣቸው ተሀድሶ አስመሳዮች አሰካሁን የዘረፋችሁት ይበቃል ፤ ለእስካሁኑ ሃጥያታችሁ ንስሃ ያስፈልጋችዃል ፤ በማን ነዉ የሚሳለቁት? ደርሶ አዛኝ ! ባገኘዉ አጋጣሚ መዝረፍ የለመደ ህሊና መቼም ሊያርፍ አይችልም አያርፍምም ፤ ዛሬም ምእመኑን ሊበጠብጡ አፈር ልሰው ተነስተዋል ፤ ከትላንት ተምረናልና በአግራሞት ቆመን የምናይበት ጊዜም አልፏል ፡፡ምዕመኑ እነዚህም ሰዎች ይህን የመሰለ በጎ አድራጎት ስራ ለመስራት ስጋዊ ጥንካሬ መንፈሳዊ ስብእናና ብቃት የሌላቸው መሆኑን አውቆ ሊጠነቀቅ ይገባዋል ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ከአንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ የቅድስት ማርያም ማኅበር ብለው የቤተ ክርስትያን ብር መብላታቸውን በቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ (ዜና ቤተ ክርስትያን ) ላይ ተገልጧል ፤ ብሩን መልሱ ቢባሉም ብሩም ሊመልሱ አልቻሉም ፤ የ‹‹ቋንቋዬ ነሽ ድንግል›› የዘማሪ ዲያቆን ልዑል ሰገድ ለህክምና የገቢ ማሰባሰቢያ ይረዳው ዘንድ ለመሸጥ የወሰደውን ቲኬት ሂሳብ ያልመለሰው የአቶ በጋሻው ደሳለኝን ስራውን አንረሳም ፤ ደግሞ እነዚህን ሰዎች የቤተክርስትያንንና ፤ የባለቤቱን ብር የቆረጠሙ ለሰውስ ብር በምን ይታመናሉ? ታዲያ ይህን ድርጊታቸውን ዘርዝሮ ያወጣው ‹‹ዜና ቤተክርስትያን›› ጋዜጣ የሚታተመው በጠቅላይ ቤተክህነቱ ሆኖ ሳለ ለመሰል አላማ ሲንቀሳቀሱ እየተመለከተ ፤ የሲኖዶሱን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ዋናውን አዳራሽ ፈቅዶ ዝለሉበት ማለት ምን ይሉታል ? ለዘመናት ታፍራና ተከብራ የኖረች ቤተክርስቲያን አሁን በኛ ዘመን ደረሰችና መጫወቻ አደረጓት ፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ያፈራች የበጎች ቤት ዛሬ የተኩላ መዝለያ ሊያደርጓት አዳራሹን ፈቀዱላቸው፡፡
ይህ ከእገዳው በኋላ ሁለተኛ መድረካቸው ነው ፤ በፊት በወር 30 ቀን ሙሉ በውሎ አበል እየዞሩ በአውደ ምህረቱ ላይ እንዳይጨፍሩ ማድረግ መቻላችን ጥሩ ሆኖ ሳለ አሁንም ደግመው እንዳይነሱ በምግባራቸውና በእኩይ ስራቸው ምዕመኑ እንዳይረብሹ ተግተን መስራት መቻል አለብን ፤ የዛሬ አዳራሽ እና አውደ ምህረት ለአልባሌ ሰዎች ፈቃጆች ነገ ስም አጠራራቸው እስኪረሳ ድረስ ያልፋሉ ፤ ይህች በማእበል የምትናጠው ቤተክርስያናችን ግን ቃሉ እስኪፈፀም ፀንታ ትኖራለች ፡፡
እንደ እኛ እንደ እኛ ባገኙት አጋጣሚ የነበራቸውን ቦታ ለማግኝት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ፤ የማይወጡት ተራራ ፤ የማይገቡበት ቢሮ ፤የማይከፍሉት ዋጋ አለመኖሩን አስረግጠን መናገር እንችላለን ፤ ለዚህ ሁሉ ስራቸው የጀርባ አጥንት ሁነው ስራቸውን የሚደግፉትን አቡነ ጳውሎስን እና መሰሎቻቸውን እግዚያብሔር ሀሳብ ድርጊታቸውን የሚያስታግስበት ጊዜ ሩቅ ነው ብለን አናስብም ፤ ከጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አከርካሪያቸውን ተመተው የራቁት ተሀድሶያውያን እንደ እባብ የሞተ በመምሰል አፈር ልሰው ለመነሳት እየሞከሩ መሆኑን ልናጤን እና ልንገነዘብ ይገባል ፤ ለጊዜው ሊርቁልን ይችሉ ይሆናል ነገር ግን እደማይተውን ጭምር ማወቅ አለብን ፤ ዛሬ ቤተክህነት አዳራሽ እንዲሰብኩ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ፤ ነገ ደግሞ አውደ ምህረት ላይ እንደማይወጡ ምንም ማረጋገጫ የለንም ፡፡
የወንድማችን ህመም እግዚአብሔር ፈፅሞ እዲምረው ፅኑ ምኞታችን ነው ፤ ነገር ግን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በመርዝ የተለወሰ ትምህርታቸውን ፤ ከፕሮቴስታንት የተቀዳ መዝሙራቸውን በቤተክርስያናችን አዳራሽ መካሄዱን ፈፅሞ እንቃወማለን ፤ 20 ብር የመርጃ ቲኬት አዘጋጅቶ በመናፍቃን ተሀድሶያውያኑ የታሸውን በቀኑ ለማስተላለፍ ያሰቡትን ትምህርታቸውን እንቃወማለን ፤ መርዳት የምትፈልጉ ሰዎች በአካል ተጎጅውን አግኝታችሁ ብትረዱት ከእግዚአብሔርም መልስ ምታገኙበት ስራ ነው ፤ ያዘጋጁትን ጉባኤ ላይ መገኝት ግን እነሱን እንደማበረታታት ስለሚቆጠር ልታስተውሉ ይገባል፡፡
እነርሱ መንገዳቸው ረዥም ስትራቴጂያቸው እንደ እስስት በየጊዜው ተቀያያሪ መሆኑን አውቀን አቡነ ጳውሎስ ቢፈቅዱላቸው እንኳን እኛ ራሳችንን እና አብያተክርስትያናችንን ከመሰል የመናፍቃንን ትምህርት ለብሰው ከመጡ እና ከሚመጡ አስመሳይ ተሀድሶያውያን ነቅተን መጠበቅ ይገባናል ፡፡ ፤ እግዚአብሔርም ወንድማችንን እንዳለ ገብሬ ከህመሙ ይምረው ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው፡፡
የአንድ ሰው መልዕክት
ለዲያቆን ልዑል ሰገድ የተሰበሰበው በስንት መከራ ከመንጋጋቸው እንደወጣ በቤተክርስቲያን ስም በሚሌኒየም አዳራሽ የተሰበሰበው ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የውኃ ሽታ ሆኖ እንደቀረ የምናውቅ ቢሆንም ፤ እኛን አሁን የገደደን የብሩ ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ የተሐዲሶ መናፍቃን አቀንቃኞች ምን ያህል ቤተክርስቲያንን ለመበረዝ አጋጣሚዎችንና ቀዳዳዎችን እየፈለጉ እንደሆነ ነው፡፡ እውነት ወንድማችን ታሞ ሊሆን ይችላል: እርዳታውም አስፈልጎት ልሆን ይችላል፡፡ ግን በተሐድሶዎቹ ጫንቃ ላይ ሆኖ ፎቶ መነሳት ለምን አስፈለገ ? በእርግጥ መብቱ ነው፡፡ ግን በተሐድሶ መናፍቃን ጫንቃ ሆኖ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባት ለምን አሰበ ?ተሐድሶዎቹ ይህን ሰበብ አድርገው በቤተክርስቲያን አዳራሽ ዓላማቸውን አራምደው ምእመናንን ለማደናገር ሊጠቀሙ እንደማይችሉ ምን ማረጋገጫ አለ? ለምን የጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ተመረጠ? ምን አልባት ወንድማችን የታመመው በሥጋ ነው፡፡ እነዚህ ሐሰተኛ ወንድሞች ግን ይህን ሰበብ አድርገው በመግባት ምእመናንን በነፍስ እንዳያሳምሙ ነው እያልን ያለነው፡፡ ለሰው ደግሞ ከሃይማኖት አንጻር በነፍስ ከመታመም በሥጋ መሞትም ይሻላል፡፡ ሰማዕታት ያስተማሩን ይህንን ነው ፤ እንዲህ ጠጋ ጠጋ እያሉ ምእመኑን በማደናገር መናፍቃን በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እንዲሰብኩ መፈቀድ የለበትም፡፡ የታመመው ወንድማችን እውነት ኦርቶዶክሳዊ ከሆነ በሥርዓት በአባቶች በእውነተኛ ኦርቶክሳዊያን ጉባኤ ይዘጋጅለት፡፡ በእውነት እኛም የሚንችለውን ሁሉ እንደ አቅማችን እናደርግለታለን ሌሎችም እንዲተባበሩ ጥሪያችን እናስተላልፈለን፡፡ ወንድማችን ኦርቶዶክሳዊ ባይሆን እንኳን ትኬቱን በመሸጥም በመግዛትም እንተባበርለታለን፡፡ ይህ ሰብአዊነት ነው ፤ የክርስትና ሃይማኖት ሞራል ከሰብአዊነት ሞራል በላይ ነው ፤ ግን ይህን ማሳዘኛ ዘዴ ተጠቅመው ምእመናንን በነፍስ በሽታ ሊመርዙ ላሰፈሰፉ አጽራረ ቤተክርስቲያንና በእነርሱ አቀናባሪነት ለሚዘጋጅ ጉባኤ የቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በምንም ዓይነት መልኩ መፈቀድ የለበትም፡፡
yefekedut eko abune philipos nachew. minew esachewn resachwacew?
ReplyDeletewey abune pawelose.....eskemchan new gen yechin betekerstiyan siyasdeferu yeminorut????emberah hoy lejochshen tebiky
ReplyDeletewushetam ante or mahberu and lemareg sayhone bewushet lemekefafel yetenesah tsere-tewahido silehonk/silehonachew kezare jemre unfriend aregachewalehu.yesewun photo copy iyaregu sem matfat hatyat new.mejemerya rasihn atseda
ReplyDeleteatimetsadek! Ante maneh
Deleteyediablos yegibr lijoch ebakachihu kidist bete kirstianachin lay ende meziger tetabkachihu yememenanin dem memtet yibikachihu.
Deleteebacachihu yebka mechkachke ferage anhun GOD becha new ferage libachinen keften kin honen enguaz then Egziabhere yeredanal.
Deleteyerasachinen hatiat teten sele sew anrut he is the only guge Amen.
It has been commented again and again that our problem is paulos the devil. These are just the TELATEL (worms) I mean insignificant figures assigned to put evil's plan to action.
ReplyDeleteAs long as that person is in power they will continue disrupting. The best way is to force them out of our church!! "Might is righr"
this is one of stupied thing for our church why we say for our patriaric abun pawelos you are not orthodocs you are catholic or protestant mission so we can remove him from his power...ok sorry it doesn't matter he will go to tomb soon ...we have to think us now who is the next patriaric for our church? abun fanuel? abun gorgorios? aba serek? ato begashaw? who? we have to think for the futur b/c it must be stop those stupied things from our church.
ReplyDeleteበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ReplyDeleteአንደማታወጡት አውቃለሁ። ነገር ግን ካነበባችሁትም መልዕክቴ ይደርሳችሁአል።
በጣም የምትፈራገጡ የበረሃ ጊንጦች ናችሁ። ውሃና ዘይት ያለቀባችሁ ባዶ እንስራዎች። ቀንደኛ መንፍቅስ እናንተ የወንጌልና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶች። የቤተክርስቲያናችን መዥገሮችና ካንሰሮች። አስመሳይ የእግዚአብሔር ሰዎች ነን ባዮች ፈሪሳዊያን፣ ምን ብየ
እንደምገስፃችሁ ቃላቶች ያጥሩኛል እንደው በደፈናው ዶማ ራሶች ስለሆናችሁ አታስተውሉም እንጂ የቃየልን ሥራ በአቤል ላይ እየደገማችሁ
ሰለሆነ ስማችሁን ኦፊሻሊ ማህበረ ቃየል በሉት። ከእንደናንተ ያሉ ሃሳዊ መሳይ ባዶ ቀፎ ጭንቅላት ካላቸው ሰዎች፤ አምላከ እስራኤል የኢትዮጵያን ህዝበ ክርስቲያን በመንፈስ ይጠብቅልን። እናንተ ከጠላት ዲያብሎስ ጋር ሆናችሁ ስማቸውን ለማጥፋትና በህዝበ ክርስቲያኑ ለማስጠላት
ብትጭሩም እንኩአን፤ህዝበ ክርስቲያኑም ሆነ ቤተክርስቲያናችን እናንተን ማን እንደሆናችሁ በደንብ ስላወቀ ከአሁን በሁዋላ ዳግም ልታሳስቱት
አትችሉም። እግዚአብሔር ደግሞ ልጆቹን ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር እቅፍ ድግፍ እድርጎ ይዙአቸዋል። ወደፊትም
መታመኛቸው አምላካቸው ስለሆነ አሸናፊውም እሱው ነው። አሜን።
ወንድማችን መጋቢ ሐዲስ ዲያቆን በጋሻው ደሳለኝን፣ ዘማሪ ዲያቆን ትዝታውን፣ ዘማሪ ምርጥነሽን፣ ዘማሪ ዲያቅን አሸናፊን፣ ዘማሪት ዘርፌን፣ ወንድማችን አሰግድ ሳህሉንና፣ እንዲሁም ሌሎችን በስም ያልተጠቀሱትን የእግዚአብሔር ልጆችና ክርስቲያኖችን እጅግ አድርገን በእግዚአብሔር ፍቅር እንወዳቸዋለንና ለቀቅ አድርጉአቸው። ባዶ ቤት ስላልሆኑ አትገቡባቸውም። እነሱ በማሰሮአቸው ያለው ንፁህ የኢየሱስ ክርስቶስ ዘይት\ቅባት\ ሙሉ ነው። ቆሻሻ ዘይት ለመጨመር ቦታ የለውም። ስለዚህ ወገኖቼ ንፁሁን ዘይት ፍለጋ አይናችሁን ያብራላችሁ እንጂ በሰው ንፁህ ዘይት በቅናት ተቃጥላችሁ አትሙቱ። ቅናት ትልቅ ሐጢያት ነውና ንስሃ ግቡ።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለሙ አሜን።
እነ በጋሻው ያስተማሩህ ስድብ ስለሆነ እንፈርድብህም:: ደግሞ ማኅበረ ቃዬል መባል ያለበት ሐውልት ይሚያቆም(ለፓትርያርኩ ) እና የቤተ ክርስቲያን ብር ዘርፎ የሚጠፋ(ዜና ቤተ ክርስቲያንን አንብብ) ማኅበር ነው ወይስ ሌላው? የአንተ "ወንጌላውያን" ያንተ "ዘማሪዎች" ያነተ "በማሰሮአቸው ያለው ንፁህ የኢየሱስ ክርስቶስ ዘይት\ቅባት\ ሙሉ" የቤተ ክርስቲያንን ብር የዘረፉ(የሰረቁ ማለትም ይቻላል እንዳንተ ዝም በሎ መቀባጀር ካልሆነብኝ)እንዲሁም ሐውልት የሚያቆሙ(የትኛው ወንጌል ይሆን ሐውልት አቁሙ የሚለው) ናቸው:: ስለዚ እነሱን አንተ "ተከተላቸው" እኛ ግን እውነተኛ የክርስቶስ ወንጌል የሚሰብከትን እንሰማልን
DeleteWho are you? በመጀመሪያ አፋችን ከመከፈቱ በፊት እራስህን/እራስሽን መፈትሽ ኃይማኖት ሌላ መውደድ ሌላ ለማንኛውም አስተዋይ ልቦና ይስጣችሁ፡፡
DeleteWho are you? በመጀመሪያ አፋችን ከመከፈቱ በፊት እኔ ማነኝ ብሎ እራስህን/እራስሽን መፈትሽ፡፡ ኃይማኖት ሌላ መውደድ ሌላ ለማንኛውም አስተዋይ ልቦና ይስጣችሁ፡፡
Deleteበሰው ንፁህ ዘይት በቅናት ተቃጥላችሁ አትሙቱ lOOOOl
Deleteአይ ወዳጄ! ምነው ይህን ያህል አመለክሃቸውሳ፤ ኧረ ለጨጓራህ እዘንለት፡፡ ደግሞ በአካል ነው የወለዱህ እኮ!! አይገርምም! ስድብህ…. ልክ እንደነርሱ፡፡ የስድብ አፎች!!! በምንም ተአምር አላማችሁን ማሳካት ስለማትችሉ አትድከሙ በላቸው ይልቅ፡፡
Deleteእግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ፡፡
እኔ እስከማውቀው ድረሰ ባዶ ያልሆነ ቤት ማለት በምግባር በትሩፋት የተንበሸበሸ የመንፈስ ፍሬዎች ያሉት ነው እንግድህ ያንተ ወንድሞች እነዚሀ አላቸው ፍርዱነ ለእግዚአብሄር እንተወው አንተ ግን ቢያንስ ክርስቲያነ ከሆንክ ላለመሳደብ ሞክረ ለነገሩ ደቀመዛሙርታቸው ከሆንክ ምን ትል
Deleteውድ ወንድሜ anonmyusከእግዚአብሄር ይልቅ ሰው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ይልቅ ከሃድያኑ በልጠውብህ ነው? ለነገሩ የዘሩት በቅሏል የተማርከው ርግማንና ስድብ ስለሆነ የተቀበልከውን አፍርተሃል እነሱስ አባቶቻችንን ለመሳደብ አፋቸው መች አፈረ? አምላክ ልቦና ይስጠን!
Deletei do't knw wt i say but give every thing for God if u are really CRISTIYAN
Deleteለመሆኑ አንተ የማን ተከታይ ነህና ደህና ነገር ትናገራለህ ሌቦች ናቸውና ቤተክርስቲያን የምትታመሰው በነሱ ክፉ ስራ ነው ስለዚህ ከላይ እንደተገለጸው አታምልካቸው የፈጠረህን ብቻ አምልክ የጓዳ አይጦች ናቸው የሚበዘብዙ
Deleteእረ እግዚአብሔር ይቅር ይበለን!!!
Deleteእየተወያያችሁና ተቃዉሟችሁን እያሰማችሁ ያላችሁት ዋናዉ ቁም ነገር የሃይሞኖት/እምነት ጉዳይ፣ የመንፈስ ጉዳይ ሆኖና በትህትናና በጥንቃቄ መገለጽ ሲገባዉ ነገር ግን እናንተ ከላይ ሃሳብህን ያሰፈረከዉ/ሽዉ ወንድሜ/እህቴ ፍፁም መንፈሳዊ ይዘት በገደለዉ ተራ አገላለጥ በተለይ በስድብ መፃፍ ነዉር ነዉ፡፡ ስለዚህ አሳባችሁን ለመከተልና አንብበን ለመረዳት ይረዳን ዘንድ መነበብ የሚችልና መነበብ የሚገባዉን አሳብ ብትፅፉ እላለሁ፡፡ ለማንኛዉም እግዚዓብሔር ጥፋተኞችን ስለሚያበጥር ጊዜ ቢወስድም ከእርሱ እጠብቃለሁ፡፡
Deleteአመሰግናለሁ!!
dedebe kededeb mene yetebekal anonymous
DeleteCan someone open an organization that constantly fights this tehadeso people. Other wise you guys will keep informing us and we will just keep read and burn inside. Nothing will be done. But if there is some kind of organization who watches this people's act and confront right there, will be a great thing. And we will see some change. Otherwise there will be no act. I wish if I were in Ethiopia at this time. Or at least let's open a face book group that fights Tehadisoian. So that Christians who really want to protect their church can join. Let's do something and make a difference.
ReplyDeleteAre you married. Wey Sira Fetoch... Zibrikrik hulu...
ReplyDeletezemee malte ylbnnme ensunme entateme metefate alebachu
ReplyDeleteAnd adrgen sihitet endayidegem eferalehu. bagegnachihut medrek kezih yeteshale mesrat endemichalim asayun andande yemiyabereta neger nigerun.Eyeteseru yalu bizu aberetach negeroch eko alu Geta Yemiserawunim neger eyenegerachu liseru yetenesutinm abertu menged lay yalutin erdu. yene asteyayet new.
ReplyDeleteየተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳውያን
ReplyDeleteእሑድ 4:30 በቦታዊ በጠቅላይ ቤተክህነት በመገኘት ለቅዱስ ስኖዶስ ውሳኔዎች ተፈጻምነት አጋሪነታችንን በመግለጽ ተሐዲሶዎቹ በቤተክርስቲያን እንዳይጨፍሩ በማድረግ የቤተክርስቲያን ልጅነት ግዴታችንን እንዲንወጣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን::
እስከዚያው ላልሰሙት በማሰማት ተግተን እንሥራ::
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳውያን
ReplyDeleteእሑድ 4:30 በቦታዊ በጠቅላይ ቤተክህነት በመገኘት ለቅዱስ ስኖዶስ ውሳኔዎች ተፈጻምነት አጋሪነታችንን በመግለጽ ተሐድሶዎቹ በቤተክርስቲያን እንዳይጨፍሩ በማድረግ የቤተክርስቲያን ልጅነት ግዴታችንን እንድንወጣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን::
እስከዚያው ላልሰሙት በማሰማት ተግተን እንሥራ::
ከላይ አስተያየት የሰጠው ቀንደኛ መናፍቅ ነው፡፡ አካሄዳቸውን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ መቼም እንደማይተኙ……የእኛ መጋቢ ሀዲስ……..የውሸት ማዕረግ……..ሰጪውም ተቀባዩም የመናፍቃን አቀንቃኞች……እባካችሁ ውድ ክርስቲያኖች የተዋህዶ ልጆች….የዲ/ን ዳንኤል ክብረት የሲኦል ደጆች አይችሉአትም ሚለውን ቪሲዲ በመመልከት የተሀድሶን አይነተኛ አካሄድ እንዲሁም ወደ ቤ/ያን ሰርጎ ለመግባት የሚሂዱበትን ዘዴ በመረዳት ላልሰሙት በማሰማት እንድትገነዘቡ እጠይቃለሁ፡፡ ድንግል ከእኛ ጋር ትሁን
"ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ"። ፩ኛጴጥ ፩፥፳፪
ReplyDelete34trbvtb
ReplyDeleteSew(Men ) Egziabher kalredaw endet aynet kifu new , Anbesa(Lion) sikota yastawikal , nebroch(Tigers) liyatekun silu yastawikalu , Ebab(Snake) linadef sil enleyewalen , libu ke Eg/r yerakew yegziabher sew gin eyesake lewedaju meriz yabelewal , eyesake gudguadun yikofrletal , le ewinet yekome le eg/r hasab yetekorkore bememsel yegeza wendimun sayraralet asalifo yisetewal . Sew eg/r kalredaw endet kebad fitur new , ye eg/r amsal teblen yedabilosin sira asfesami kemehon eg/r yirdan !! Ebakachihu ene salhon hiyaw eg/r new yemileminachu, bichalachihu le sew hulu melkam hunu , tenkol kifat , haset ye sew bahiri aydelem enezih yedabilos bahir nachew.Egna bedemu yegezan ye kirstos lijoch nen endih aynet kifu sirawoch le bahiryachin aysmamunim . Eg/r amlakina abat lehulachin mastewalun yisten !
ReplyDeleteለእኔ አዲስ ነገር አይደለም አስቀድሞ ኢየሱስክርስቶ ስለተናገረ ሆዳቸው አምላካቸው፣ ሃሳባቸው ምድራዊ ነው ተብሎ ስለተፃፈ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ሁለተኛ አምላክ ማምለክ ስለሆነ አካሄዳቸው፣ ጉዞአቸው፣ ሃሳባቸው ሁሉ በክርስቶስ ላይ እምነት ሳይሆን ገንዘብን እና ሃብትን ማከማቸት ስለሆነ በጅምሩ እረዳ ነበር፡፡ ስለዚህ ከበፊትም ጀምሩ አዲስ ነገር የለውም አሁንም እየሠሩ ያሉት ገንዘብ መሰብሰብ ስለሆነ ህዝበክርስቲያኑ ሊረዳው ይገባል፡፡
ReplyDeleteMEGABE HADDIS BEGASHAW DESALEGN, MEMIHIR ASEGID, KESIS ASHENAFI, DIAKON TIZITAW,MEMEHER TEREFE,MEMEHER TARIKU,ZEMARIT MIRTINESH,ZEMARIT ZERFE,ZEMARI EZRA,ZEMARI DAGMAWI,ZEMARI HABTAMU,... YEKIRSTOS LIB YALACHEW WONGELU BEDENIB GEBTOACHEW YEMIYAGELEGILU DINK YETEWAHIDO LIJOCH NACHEW. EGZIABHER LE
ReplyDeleteWENDIMOCHACHININA LE EHTOCHACHIN TSGAWUN YABIZALACHEW. BEZEMENACHIN YEWONGEL TELATOCH HONACHIHU YETENESACHIHU YEWENDIMIN SIM MATIFATINA MASADED YECHRISTINA MENGED ADIRGACHIHU YEMITIKOTIRU,YEMENGAW MEBIZAT YEMAYASDESITACHIHU,CHRISTINAN BESIM ENJ BETEGBAR LEMEGILETS YALTADELACHIHU,SILE SIMACHIHU ENJ SILE BETECHRSTIYANIM HONE SILE MENGAW DENTA YELELACHIHU,YE AHZABIN GIBR YEMITFETSIMU WONDIMOCHIN BEDINGAY YEMITWOGIRU ENANTE,EGZIABHER BIZEGEYIM SILE MENGAW YIGEDEWALINA SAYIFERIDBACHIHU NISEHA GIBU. DINGAY YEHONEWUN LIB AWUTUNA YEKIRSTOSIN LIB TEKEBELU.EGZIABHER YIRDACHIHU. YE EGZIABHER CHERNET YE EMEBETACHIN AMALAJINET AYILEYEN. AMEN.
ምነው ባክህ ከነሱ ውጪ ወንጌሉ የገባው የለም ማለት ነው? አንንተ ምንፍቅና እንጂ የኢትዮጲያን ታሪክ አላስተማሩህም እንዴ 'መምህራኖችህ'(እነበጋሳው)?እባክህ ወንድም አምላክ ሆይ እርዳኝ ብለህ ጸል።
Deleteወንዲመ ሆይ ሃሴት ምስኪር ትሊክ ወልጀል መሆኑን አቲዘንጋ .ለሚን ታድያ ክርስቲአን እነሱ ብቻ ናችሀው ክርስቲያን ለላ የለሚን ? አቲሳሳት አንተ በተግባር ክሪስቲናን ቲገልጻለህን ? ራሲሂን መርሚር ስለ እነሱ ቲተህ ስለ ራሲህ እንኳ አታውቅም ወንድሜ ጌታ ሆይ ማረን ብለህ ጸሊይ
Deleteእግዚአብሄር ለሁላችሂን ዪማረን ተሃዲሶ ለሚሉም ልብ ዪስጣቸው አሜን!!
እነዚህን ሶዎች የማናይበት ጊዜ መቸ ይሆን እባካችሁ ሌላ ቢዝነስ ሞክሩ ቤተክርስቲያንነ ለቀቀቅ አደርጉአት እንደዳታንና አንደአቤሮን በግድ አይሆንምነ
ReplyDeleteእናንተ ማህበረ ቅዱሳን በሌላ ስማችሁ ከፋፋዮችና ፀብ ጫሪዎች ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ፡፡ ቤክርስቲያንና ምእመኑን አታምሱ፡፡ ለራሳችሁ ጥቅም ስትሉ እንጂ ለቤተክርስቲያንና ለእምነቱ ብላችሁ እንዳልሆነ ሁሉም ነቅቶባችኋል፡፡
ReplyDeleteአይ መጋቢ ሐዲስ ከየት ተምሮ የት አውቆ ነው እንደሸንበቆ ሳያስበው የተመዘዘ እንጂ እሱን በሎ ደግሞ ሲጀመር በስድብ የመጣ በጥባጭ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ የቤ/ክን ትምህርት ሳታውቁ የተዋህዶ ልጆች ናቸው ትላላቸሁ እነ የአይጥምስክር ዲንቢጦች ምን አውቃችሁ ከሆይ ሆይታ በስተቀር ጨፋሪ ሁሉ ሂዱ እና መናፍቃን አዳራሽ ጨፍሩ እኛ አናስጨፍርም አሁንም አንተኛም እነርሱን ለመቃወም ምክንያቱም ዲያብሎሶች ናቸውና፡፡
ReplyDeleteእኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን እሺ የተዘጉ አብያተ ቤ/ክን ሲያስከፍት፣ ለተጎዱ ሲረዳ፣ የአባቶቹን ትምህርት ጠንቅቆ ሲያውቅ፣ በአለም ሁሉ ፀጋው በዝቶለት ሲገንን፣ በስርዓት ሲሄድ፣ እንደ ማንም መናፍቅ ሳይልከሰከስ አረ ምኑ ቅጡ መልካም ሥራው ብዙ ነው ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ በማታውቁጥ እየቀባጠራችሁ የማህበሩን ስም ለማጥፋት አትነሱ እግዚአብሔር ይደግፈዋል ሕዝብም አውቆታል በፊት የሚቃወሙት እንኳን ከማህበሩ ወዲያ እምነት፣መልካምነት ለአሳር ብለዋል እንግዲህ ምን ትሆኑ!!!!
ReplyDeleteLong live to Mahebere kidusan!,they are the savior for Orthodox religion!
ReplyDeleteanete lerasek satak selesew tenageralek anete kenesu weset nek
DeleteMenew bezih zemen semaet tefa? yebetekrestiyanen denber yemiyastebek ? betun lewenbedewoch asalfen eyeseten new.
ReplyDeleteጥርሳችሁ ተስተከክሎ ሀጫ በረዶ መስሎአል ትንሽ ውፍረት ቀንሱና ጥሩ ሞዴል ይወጣችሁአል ሌላ ሌላውን እንካን ተውት
Deleteበነገራቸን ላይ የናንተን ፎቶ ሳይ ቶሎ ማነ ትዝ እንዳለኝ ታውቃላችሁ እነ ሀዋርያው ቅዱሰ ፓውሎስ የተጋዙበት መንገድ ምን ያህል በሞኝነት የተሞላ ነበር አያችሁ እንደእናንተ ቢዝነስ አልገባቸውም ክርስትናን ወደገንዘብ ወደዝና መለወጥ አልቻሉም እውነተኛውን የእግዚአብሄርን መንገድ ህይወት የሆነውን የክርስቶስ ብርሃን ይዘው ሲንገዳገዱ ይሀው እናካን እነርሱ የመንፈስ ልጆቻቸው እንካን ይህችን አለም ንቀው ተሰደዱ እናንተ ግን እጅግ የገባች ናችሁ
i think u guys have really unsolved problem....let God give u mind to see things from different side.
Deleteahunes betame yekenat endehone betame eysetaweke new lekeke areguachewe......besemeam,,,,mendenew....beka game over ..weyyyyyyy
ReplyDeleteyegeremegne S.No yelewum ,endayitawok yihon
ReplyDeleteእነ ሆዶ ማህበር አሄሄ ሄሄሄይይይይ አሁንማ ተነቃቅተናል! ሃብታሞች ምነው አሁን ኪሳቹ ጎደለ እንዴ በሉ ያለፈው ይብቃችሁ የቤተክርስቲያናችንን ብር ዘርፋችሁ መኪናና ቪላ የገዛችሁት ይብቃ አሁን ቀልድ የለም 20ብር ለእናንተ ሁሁሁሁ እንዴት ተቀልዷል!!!!
ReplyDeleteIs it awesome? is that apart of our believe? Please everyone should be pray with broken heart to remove unethical 'SEDEBE MELEWAWETE " and to give GOD love B/n us.
ReplyDeleteegna bmetfo gebere eybertane deyabelosen enasarefwalen ygremal
ReplyDeleteamelakachen lebonachwen melese
ReplyDeleteሁለቱንም ወገኖች ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር ይበላችሁና አስተዋይ ልቦና ይስጣችሁ፡፡
ReplyDeleteበተለይ ለተሐድሶ መናፍቃኖች ጌታ የተሳሳታችሁበትን መንገድ አስተካክሎ በይቅርታው ይጐብኛችሁ፡፡ "አሜን"
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳውያን:-
ReplyDeleteበመናፍቃን ሴራ ልናውቅባቸው ይገባል::
በባለፈው የጥቅምት ስኖዶስ መናፍቃን ከተለያየ ቦታ ተሐዲሶዎቹን ደግፈው ኦርቶክሳዊ መስለው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ተገኝተው ነበረ:: ከምዕራብ ወለጋ የመጣውን የ"መካነ ኢየሱስ ቄስ "መጥቀስ ይቻላል:: እኔም በወቅቱ "ከአዋሳ በጋሻውን ደግፌ ማጥቻለሁ" እያለ ተመካክረው መምጣታቸውን በምገልጽ መልኩ ማተብ እንድታይ ሆን ብሎ አንገቱ ላይ ከፍ በማድረግ ፊት ፊት ሲል በአንድ አስተዋይ ወንድም ተይዞ ወደ ፖሊሶች ቀርቦ ስጠየቅ ደንባራ ነበረና ጉዳዩን ስዘከዝክ በቦታው ነበርኩ::
መንግሥት ለእውነት የቆመ ብሆን እነዚህን ያለ ሃይማኖታቸው ሁከት ለመፍጠር አገር አቁዋርጠው የሚመጡትን ለፍርድ አቅርቦ ለፍትሕ መቆሙን ባሳየን ነበረ:: ዳሩ ግን ሀገር አቁዋርጠው የመጡት መናፍቃን በአቡነ ፓውሎስ 10000 ብር "አይዞኣችሁ" በሚል ስላክላቸው ኦርቶዶክሳውያኑ ከጀርባችሁ ያለው ማነው በመባል ተጎረጎሩ:: በሊብሬ ዋስትና ያውም ምንም ጥፋት ስላልተገኘባቸውና እንደ ዕድል ማንም የተቃሚ ፖለቲካ አባል የሆነ ዘመድ ስለሌላቸው ተፈቱ:: ያለ ሃይማኖታቸው ሁከት ለመፍጠር የመጡ መናፍቃንም እኩል ታዩ ተፈቱም::
የት አለ ፍትሕ? የት አለ ሕግ?
እኛ ኦርቶክሳውያን በጣም ፈሪ የሆነን ይመስለኛል:: ወይም ለየተኛ ነው በዝምት ጸሎት ብቻ የሚደረገው የትኛው ነው ከጸሎት ጋር በተግባር መጋፈጥ ያለብን የሚለው ላይ የተዛባ ግንዛቤ ያለ ይመስለኛል::
እስኪ ተመልከቱ አሕዛብ አንድ የአወልያ ትምህርት ቤት ተዘጋ :ተቁዋረጠ ብለው እንደዚህ በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን ሲያሰሙ(http://www.youtube.com/watch?v=KTYAGk25aug) እኛ ስንት ግፍ ስንት በደል አይተን ሰምተን አንድ መሬት የሚያርፍና መፍትሔ የሚሰጥ ነገር አልሠራንም::
እንግድህ ቤተክርስቲያን የሚንላት ቤተክርስቲያን የት አለች? የቅዱስ ሰኖዶስ ውሳኔዎች ወደ ጎን መደረግ ከተጀመሩ ስንት ጊዜ አለፈ? ከእንግድህ ምን እስኪሆን ነው የምንጠብቀው?
መንግሥት ከቤተክርስቲያን ጫንቃ ይውረድ:: አቡነ ፓውሎስ ይገቱ:: እስኪ ተመልከቱ የመንግሥትን ደኅንነት አባላት ባንፈራ ሐውልቱን እስካሁን አናፈርስም ነበር? በ2002 ፓፓሳትን የደበደቡት የመንግሥት ካድሬዎች አይደሉም እንዴ? አቡነ መልኬጼዴቅን ካድሬዎቹ "የትግሬን መንግሥት ለመቃወም አይደል?" በማለት ሆዳቸውን አሽተው አሽተው ከለቀቁ በሁዋል ደም እያስቀመጣቸው አይደለም እንዴ የሞቱት?
የፓፓሳቱ ሞት በቶሎ ቶሎ የነበረውና አሁን መጠራጠር ስንጀምር የቆሞው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በጽሑፋቸው እንዳሉት ወያኔ ትግራይን ለመገንጠል የኢትዮፕያ ቤተክርስቲያንን ማዳከም የመጀመሪያው ምዕራፉ ነው ከሚለው ጋር እንደማይያያዝ ምን መረጋገጫ አለን?
ስለዚህ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ይህን ጉባኤ ለመቃወም ስንመጣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወይም የሰበካ ጉባኤ አባልነት ደብተር በመያዝ በሰበካ ጉባኤ አባልነት በቤተሰብ ስም ያለንም የቤተሰብን ኮፒ በማድረግ በመያዝ እንድንመጣ ይሁን::
Long live to Mahebere kidusan!,they are the "savior" for Orthodox religion!Don't make mistakes. Savior is our Lord Jesus Christ.
ReplyDeleteበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ReplyDeleteውድ ክርስቲያኖች ሆይ ይች ቤተ-ክርስቲያም ከአሁን ቀደም ብዙ ሊቃውንትና ምእመናን በቸህሎታው የሚያደንቁት አርዮስ የሚባል ሊቅ አስቸግሯት የነበረና በቁርጠኛ የእግዚአብሄር ታማኝ በሆኑ አባቶች ተዎግዞ ከቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰናበትባ ትምህርቱም ስህተት እንደሆነ ተጽፎልናል፡፡
ከዛም በኋላም የተለያዩ ኢ-አማናውያንና ባለስልጣናት ተነስተውባት በሰማእታት ተጋድሎ የመጡባቸውን አስቸጋሪዎች ተቋቋቁመው ለዚህ በቅታለች አሁን በእኛ ዘመን ደግሞ ፈተናው ቀጥሎ ሌላ ባህሪውን ዘመናዊ ያደረግ አሪዎሳውያን ብቅ እንዳሉ እያየን ነው የነዚህኛዎቹ ከበፊቱ አሪዎስ የሚለዩት በቤተክርስቲያኒቱ ሳይፈቀድላቸው ጠባቂ ነን ባሉ ሰዎች ጥላ ስር መሆናቸው ከቀደመው ለየት እንዲሉብኝ ሆኗል፡፡
ለምን ቢባል የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበላይ መሪ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ ይታዎቃል ይህ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አባቶች ስብስብ የተዋቀረም ነው ስለዚህ እነዚህ አባቶች የወሰኑት ይሁን ያሉት ባስፈጻሚዎች ይተገበር ነበር ጳጳሳቶቹ የወሰኑትንም ፒያትሪያሪኩ ብቻቸውን አይሽሩትም ወይም መሰረታዊ ለውጥ አያደርጉለትም ነበር ግን አሁን ይህ ድረጊት ህገ-ቤተክርስቲያኑን ይጥሳል ስለዚህ ይፍረስ ፤ እከሌ እከሌ አስተምሮታቸው እስኪጣራ ድረስ በየትኛውም መድረክ እንዳያስተምሩ ይሁን የመሳሰሉትን ቢዎስኑም ተፈጻሚ ሊሆን አልቸሀልም ስለዚህ ሁላችንም ቆም ብለን ለምን ብለን ማሰብ ይኖርብናል ም/ቱም እምነታችን በመሆኑ ፡፡
ብዙ ጊዜ እነዚህ እንዳያስተምሩ የተከለከሉ ሰዎች መድረክ የሚፈቀድላቸው ከፒያትራሪኩ በሚዎጡ ትእዛዛዊ ደብዳቤዎች ነው ስለሆነም ፒያትራሪኩ በግብርም በአመለካከትም የእነዚህ ሰዎች ድጋፍና ጠበቃ ናቸው ይህ የሆነው ደግሞ ሰውየው ስጋዊ ስልጣንና ጥቅም ፈላጊ በመሆናቸው ባሁኑ ስቸት ካሉት ባለስልጣናት በካከል የበላዮቹ መናፍቃንና ዮርቶዶክስ ጠላት በመሆን ጥምቀትን በካርኒቫል ሌሎችንም በሊላ በመቀየር ለማዳከም ሲሞክሩ ፒያትራሪኩን መጠቀማቸው አይቀሬ ነው ለነገር ሰውየውስ የእኛ መሆኑን በልብስ እንጅ….፡፡ ስለዚህ ከላይ አሪዎስ ሲዎገዝ ብቻውን ሳይሆን ተከታዮቹና ደጋፊዎችም ጭምር በመሆኑ ሰዎቹን ለነብሱና ለእግዚአብሆር ክብር የሚቆሙ አባትች እስከሚፈጠሩ ድረስ ሁላችንም ለአሁን በግል ለዎደፊት በጋራ ከዚህ ቀን በኋላ መቃዎም እንጀምር፡፡
ዎስብሃት ለእግዚአብሄር
አሜን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ReplyDeleteውድ ክርስቲያኖች ሆይ ይች ቤተ-ክርስቲያም ከአሁን ቀደም ብዙ ሊቃውንትና ምእመናን በቸህሎታው የሚያደንቁት አርዮስ የሚባል ሊቅ አስቸግሯት የነበረና በቁርጠኛ የእግዚአብሄር ታማኝ በሆኑ አባቶች ተዎግዞ ከቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰናበትባ ትምህርቱም ስህተት እንደሆነ ተጽፎልናል፡፡
ከዛም በኋላም የተለያዩ ኢ-አማናውያንና ባለስልጣናት ተነስተውባት በሰማእታት ተጋድሎ የመጡባቸውን አስቸጋሪዎች ተቋቋቁመው ለዚህ በቅታለች አሁን በእኛ ዘመን ደግሞ ፈተናው ቀጥሎ ሌላ ባህሪውን ዘመናዊ ያደረግ አሪዎሳውያን ብቅ እንዳሉ እያየን ነው የነዚህኛዎቹ ከበፊቱ አሪዎስ የሚለዩት በቤተክርስቲያኒቱ ሳይፈቀድላቸው ጠባቂ ነን ባሉ ሰዎች ጥላ ስር መሆናቸው ከቀደመው ለየት እንዲሉብኝ ሆኗል፡፡
ለምን ቢባል የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበላይ መሪ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ ይታዎቃል ይህ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አባቶች ስብስብ የተዋቀረም ነው ስለዚህ እነዚህ አባቶች የወሰኑት ይሁን ያሉት ባስፈጻሚዎች ይተገበር ነበር ጳጳሳቶቹ የወሰኑትንም ፒያትሪያሪኩ ብቻቸውን አይሽሩትም ወይም መሰረታዊ ለውጥ አያደርጉለትም ነበር ግን አሁን ይህ ድረጊት ህገ-ቤተክርስቲያኑን ይጥሳል ስለዚህ ይፍረስ ፤ እከሌ እከሌ አስተምሮታቸው እስኪጣራ ድረስ በየትኛውም መድረክ እንዳያስተምሩ ይሁን የመሳሰሉትን ቢዎስኑም ተፈጻሚ ሊሆን አልቸሀልም ስለዚህ ሁላችንም ቆም ብለን ለምን ብለን ማሰብ ይኖርብናል ም/ቱም እምነታችን በመሆኑ ፡፡
ብዙ ጊዜ እነዚህ እንዳያስተምሩ የተከለከሉ ሰዎች መድረክ የሚፈቀድላቸው ከፒያትራሪኩ በሚዎጡ ትእዛዛዊ ደብዳቤዎች ነው ስለሆነም ፒያትራሪኩ በግብርም በአመለካከትም የእነዚህ ሰዎች ድጋፍና ጠበቃ ናቸው ይህ የሆነው ደግሞ ሰውየው ስጋዊ ስልጣንና ጥቅም ፈላጊ በመሆናቸው ባሁኑ ስቸት ካሉት ባለስልጣናት በካከል የበላዮቹ መናፍቃንና ዮርቶዶክስ ጠላት በመሆን ጥምቀትን በካርኒቫል ሌሎችንም በሊላ በመቀየር ለማዳከም ሲሞክሩ ፒያትራሪኩን መጠቀማቸው አይቀሬ ነው ለነገር ሰውየውስ የእኛ መሆኑን በልብስ እንጅ….፡፡ ስለዚህ ከላይ አሪዎስ ሲዎገዝ ብቻውን ሳይሆን ተከታዮቹና ደጋፊዎችም ጭምር በመሆኑ ሰዎቹን ለነብሱና ለእግዚአብሆር ክብር የሚቆሙ አባትች እስከሚፈጠሩ ድረስ ሁላችንም ለአሁን በግል ለዎደፊት በጋራ ከዚህ ቀን በኋላ መቃዎም እንጀምር፡፡
ዎስብሃት ለእግዚአብሄር
አሜን
egizabihar hoy hayimanotachinen kemenafiqan fetena tebiqat!!!!
ReplyDeleteGospel should not only be preached but also shown in practice,so all Ethiopians help this brother.
ReplyDeleteዉድ ወንድሞች በሁለት ጎራ ላላችሁ እባካቹህ መንገዳችሁን አትሳቱ ። እኛ ልጆቻችሁ እንዲህ አይነት ያላዋቂ የሚመስል ስድብ አዘል ንትርክ አትንገሩን;; በተቻለ መጠን እራሳቹህ እዚያዉ ጨርሱት። ወንጌልን እና መንፈሳዊ አስተምሮት ስጡን ። መምህር ይመራል ደግነትን ያስተምራል ። ክርስትና ክፋትን በበጎ ይመልሳል በዚህም ድልን ይቀናጃል ትሉን አልነበር? እባካቹህ አባቶችንም አክብሩ። ስህተት እንኳን ቢኖር በመሳደብ ለዉጥ ማምጣት አይቻልም ።
ReplyDeleteአባት ሆነዉ እስካሉ ድረስ እናክብር ዳቢሎስም ደስ አይበለዉ። ። ወደተሳሳተ መንገድ ለሄዳቹህ እግዚአብሄር ልቦናውን ይላክላቹህ ። ወደ እውነተኛይቱ እንድትመለሱ እግዜር ይርዳቹህ።
ልቦናችሁን ይመልስላችሁ ዘንድ እኛም አምላካችንን እንለምናለን ። ማንም በግ መጥፋት የለበትም። እ/ር አንድ ያድርገን። አሜን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1
woyo gud enes tewzegagebku(confusion) mine geta hulun neger leyto bekelalu biyasayegn,min malet new betechrstiyan endih mehona,neg,nege,nege hulachinm endanwengagel,be ergit tru new gin were bicha minm ayseram,eski ene endamnachu
ReplyDeletelela matakesh email or website stugn,ohhooooooooooooooooooohhhhhhhhhhhh,wey geta ethiopian bilom addisabeban fetneh gobgant ena give penalty if necessary,and like that.....
EBAKACHEHU SEDEB LEMEN TASTENAGEDALACHEHU!!
ReplyDeleteye wesht amd eko new yenante
ReplyDeleteይሄ የሐይማኖት አይመስልም ጭፍን ጥላቻ ነው የሚመስለው መሰዳደብ ብታም ያሳዝናል እባካችሁ ወንጌል አስተምሩን ጌዜያችሁን በትላቻና መከፋፈልን ተው ነገር አብርዱ በነብስ የምትፈላለጉ ትመስላላችሁ አድማ ምን ደርጋል አንድም ጊዜ ትምህርት የለም ጭቅጭቅ ብቻ አምለክ ልቦና ስጣችሁ፡፡
ReplyDeleteለመጋቢ ሃዲስ በጋሻው ደሳለኝ
ReplyDeleteሰላም ላንተ ይሁን
ጥር 20 2004 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ የተዘጋጀውን ጉባኤ ለመታደም ተገኝቸ ነበር ፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ፕሮግራሙ መሰረዙን መስማት የነበረብን ቀደም ብሎ ነበር፡፡
ሁለተኛ ከእናንተ ከአዘጋጆቹ ወገን ቢያንስ አንድ ሰው እዚያዉ በቦታው ተገኝቶ ይቅርታ እየጠየቀ ሊያሰናብተን ይገባ ነበር ፡፡
ትኬት ቀድሞ ተሰራጭቷል፡፡ እርግጥነው ትኬቱን የገዛነው ቃለ እግዚአብሔርን ልንሸምትበት አይደለም፡፡ ወንድማችንን ለመርዳት እንጂ
ከዚህ ሁሉ በኋላ ስልኮቻችሁን የሚያውቁ ሰዎች ሲደውሉ እንኳ ለማንሳት ፈቃደኛ አይደላችሁም ፡፡
እውነት ለመናገር አዝነናል፡፡
አረ ምንድነው ጉዱ?!
ReplyDeleteegzyabhr lebon yest lela men yebalale
Deletemasetewl menew tesanaheu
Deletemasetwal menew tesanahu
Delete' LETEHADISO MENAFIKAN BOTA YELENM .YEDIYABILOS YEGIBR LIJOCH HOY EBAKACHHU LIB GIZU'.
ReplyDeletemasetewal menew tesanen yetenebet mefsmy kemehn egezyabehr yetebek
ReplyDeleteere bakachu alem bemiyayew website lay atenakoruben. tenesh ayidebrachehum? Menale ensun egzeabher leb yistachew betelu? letelat ber mekfet men tekem alew? Demo bezu sew hayimanotun endiyawk madregachew ayikadem. Politics yimesel andun mansat andun metal.... betam yastelal. Behayimanotu yaltenekere sew mesenakeya lemen tehonalachu? Selfish, genzeb afkari.... egzio malet new
ReplyDeletesele sew bemetawerubet seat menale wengelen betastemerubet?
ReplyDeletehttp://www.youtube.com/watch?v=-pdCOL9p4bg&feature=related ስለ ኢትዮጵያ የተነገረ ትንቢት
ReplyDeleteEnante wegegnoch! Enantes man nachew????? Zelalem yematlewetu zeregnoch ayedelachihim? Min serachu???? sIRACHU SEWUN MADAN SAYHON MEGDEL NEW! Ine lenante biyye beten altewim! Weradoch!!!!!!!Inesum yetim ayehedum!Demo ehe yemahbere kidusan sera new!
ReplyDeletefeker yalew yehen aysefem, yeahnen yesafew yesawem hona yekrstos feker yelalew new
ReplyDeleteyefikirin tirgum tawukewaleh lemehonu Anoniymus
ReplyDeleteየ ኣሳ ግማቱ ከኣናቱ። ጋሼ ጳውሎስ ማን ሆነው፣ የ vatican best freind ayidelu:: ተሃድሶዎችን እሽሩሩ ማለታቸው ኣይደንቀኝም። ኣላማቸው ቤተክርስቲያንን ማዳከም ነውና።
ReplyDeleteyememeleshawun menged egzeabhar yasayachihu.
ReplyDelete