ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን
ጉባኤ ኬልቄዶን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በመልካም አርአያነት ሊወሰድ ይገባልን?
(አንድ አድርገን ፤ ጥር 10 2005 ዓ.ም)፡- ቤተክርስቲያን እስከ 451 ዓ.ም ማለትም እስከ ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ
በመላው ዓለም ባሉ ክርስቲያኖች ዘንድ አንድ ዶግማና አንድ ቀኖና
ነበራት፡፡ ይህ ጉባኤ ግን ቤተክርስቲያንን ከሁለተ ከፈላት፡፡ ነባሩን ሐዋርያዊ አስተምህሮ የያዙት ተዋህዶዎች የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት(Oriental Churches) በመባል የሚጠሩት ኢትዮጵያ ፤ ግብጽ ፤ አርመን ፤ ሶርያና ሕንድ የያዙት መለካውያን በመባል የሚታወቁት ደግሞ የምዕራብ አብያተክርስቲያናቱ
(Occidental Churches) ላቲኖችና ግሪኮች ናቸው፡፡ በእነኚህ ሁለት ክፍሎች ጉባኤው ቤተክርስቲያንን ለሁለት ከፈለ፡፡ አስቀድሞ በ325 ዓ.ም በኒቂያ ፤ በ381 ዓ.ም በቁስጥንጥኒያ ፤ በ431 ዓ.ም በኤፌሶን የተደረጉት ጉባኤዎች (ሲኖዶስ) ቤተክርስቲያን
የገጠማትን ፈተና በመጋፈጥና በአንድ ድምጽ በመወሰን የተዋጣላቸው
ነበሩ፡፡ ጉባኤዎቹ የሚጠሩበት ምክንያትም ሐዋርያዊ ያልሆነ አዲስ የክህደት ትምህርት ተከሰተ ሲባል ነበር፡፡
አራተኛው ጉባኤ(ሲኖዶስ) ሲጠራ ግን የተጠቀሰ ምክንያት አልነበረም፡፡ በኋላ ላይ ግን ለጉባኤው መጠራት መንስኤ የነበረው የስልጣን ወይም የወንበር ሽሚያ መሆኑ ታወቀ፡፡
ውጤቱም የዶግማ ልዩነት የፈጠረና ለሁለት መሰንጠቅ ግድ አለ፡፡ ለስልጣን ሽኩቻው መነሻ የነበረው የእስክንድርያን መንበር
ነጥቆ ለቁስጥንጥንያ ለመስጠት እና የበላይ ነን ያሉ የነበሩ የሮማው
ጳጳስ በእስክንድርያው ፓትርያርክ መወገዝ የፈጠረው የመበቀል ፍላጎት
ነበር፡፡ ነገር ግን ያለምንም ምክንያት ይህንን ማድረግ ስለቸገራቸው እስክንድርያዎችን በጸብ ያለሽ በዳቦ ከጉባኤ ለማስወጣት ግድ አላቸው፡፡ 25ኛው ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ነገሩ ገብቶት
ነበርና ድንገት በመነሳት ሐዋርያዊውን አስተምህሮ ገልጦ ከዚያ የወጣ
የተወገዘ ነው ብሎ አወገዘና ከጉባኤው ወጣ፡፡
የተቀሩት ግን ጉባኤውን እንዲጠራ ካደረገው የቁስጥንጥንያው ንጉሥ መርቅያን ጋር በመሆን አዲሱን የሁለት ባህርይ የክህደት ትምህርት
አጽድቀው ወጡ፡፡ የንጉሡ ሚስት ብርክርያ አውግዞ የወጣውን
የእስክንድርያውን ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስን አስጠርታ ልታግባባው ሞከረች
፤ አልሆን ሲላትም ጺሙን አስነጭታ ፤ ጥርሱ እስኪረግፍ አስደበደበችው፡፡ ስለ አንዲት ሃይማኖቱ ሰማዕትነትን
ለመቀበል ቆርጦ ነበርና ከአቋሙና ከእምነቱ ፍንክች አላለም፡፡ ምንም ቢያደርጉት ሃይማኖቱን የማይቀይር መሆኑን ስለተረዱ እሱን በደሴተ
ጋግራ አስረውና ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ቀኖና ውጪ ከፕትርክናው ሽረው ፕሮቲሪዮስ የሚባለውን መለኮታዊ መነኩሴ በእሱ ቦታ ፓትርያርክ
አድርገው ሹመው ላኩት፡፡ በግብጽ ክርስትያኖች ግን “የእኛ አባታችን
ዲዮስቆሮስ ነው ፕሮቲሪዮስን አናውቅም አንቀበለውም” አሉ፡፡ ንጉሡ መርቅርያን በግድ እንዲቀበሉ ለማድረግ ከሠራዊቱ
2000 ያህል ላከ ፡፡ ሕዝቡ ግን ቁጣው እጅግ አይሎ በተነሳው ረብሻም አዲሱ ፓትርያርክ ሞተ፡፡ በመሀሉ በእስር ቤት ያለው አርበኛው
ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ በእስር ቤት እንዳለ ዐረፈ፡፡ እሱ ካረፈ ከሶስት ዓመታት በኋላ ምዕመናን ራሳቸው መርጠው ጢሞቲዎስን ፓትርያርክ
አድርገው ሾሙት እሱም የእነ አትናቲዎስንና የእነ ቄርሎዎስን ፍኖት የተከተለ ምስጉን ፓትርያርክ ሆነ፡፡
ጉባኤ ኬልቄዶን የፈጠረው
ችግር ግን ዛሬም ድረስ ግን ቤተክርስቲያንን እንዳመሰ አለ፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙ ደጋግ አባቶችና ነገሥታት የተለያዩ ወገኖች ጠፍቶ
መቅረት አሳስቧቸው የጠፋውን ወገን ለመመለስና ቤተክርስቲያንን ለማዋሃድ ብዙ ጥረት አድረገዋል፡፡ ፈጽሞ ሊሳካላቸው
ግን አልቻለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው ነገሥታት ጣልቃ ገብነትና
የሥልጣን ሽኩቻ ቤተክርስቲያንን ለምን ዓይነት ችግን እንደሚዳርጋት ምሳሌ ሆኖ ሲጠቀስ ይኖራል፡፡ በእርግጥ ከዚህ አስቀድሞ
ቤተክርስቲያንን የነጠቀና ለእንደዚህ አይነት የከፋ አደጋ የዳረገ አይሁን እንጂ የመንግሥት መሪዎች ጣልቃ ገብነት በቤተክርስቲያን
ላይ ችግር ሲፈጥር ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ ለመንበረ ማርቆስ 20ኛ ፓትርያርክ የነበረው በሊቅነቱ እና በተጋድሎ ርዕሰ-ሊቃውንት
ወጻድቃን በመባል የሚጠራው ቅዱስ አትናቲዎስ የደረሰበት ችግር ምክንያት ሰባት ጊዜ መንበረ ፕትርክናውን ጥሎ እንዲሰደድ ሲያደርጉት
አምስት ጊዜ ደግሞ እንደገና እየመለሱ ሹመውታል፡፡
ሌላው ደግሞ በትምህርት
ጣዕምና አመስጥሮው “አፈወርቅ” የሚል ቅጽል የተሰጠው የቁስጥንጥንያው
ሊቀ ጳጳስ ዮሐንስም ጨካኟ ንግሥት አውደክያስ የሰው ንብረት በመቀማቷ የተቀማው ሰው መጥቶ “አባቴ ሆይ ፍረድልኝ ንብረቴን በግፍ
ወሰደችብኝ” ብሎ ሲያመለከተው እንድትመልስላት ለመናት ፤ ንግሥት አውደክያስ እምቢ ስትለው አወገዛት፡፡ በዚህ አቂማ ቤተክርስቲያን
ላይ መከራ ለማምጣት ዛተች፡፡ ሕዝቡ ሁሉ “ስለ አባታችን ለመሞት ዝግጁ ነን” ብለው ቤታቸውን ጥለው ሌት ተቀን ይጠብቁት ያዙ፡፡ እሱ ግን በእኔ ምክንያት
ሕዝቡንና ቤተክርስቲያንን ለችግር አልዳርግም ብሎ ራሱን ለውጦ በለሊት ሀገረ ስብከቱን ጥሎ ተሰደደ፡፡ እነኚህና ሌሎችም አባቶች
እንዲህ በማድረጋቸው እንደ ክህደት አልተቆጠረባቸውም ፤ ይልቁንም
ሰማዕታት ተባሉ እንጂ፡፡ አስቀድሞ ክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌሉ ሐዋርያትን ጠርቶ ወደ ዓለም ሲልካቸው “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ
ወደ ሌላይቱ ሽሹ” ማቴዎስ 10፤23 ብሎ አዝዟችዋልና፡፡
እንግዲህ የእግዚአብሔር
ቃል የሚለው ይህንን ሆኖ ሳለ ዛሬ ግን ብጹአን አባቶች ምዕመናን
ምንም አያውቁም በሚል አስተሳሰብ ይመስል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን
በደረሰባቸው ችግር በመሰደደዳቸው ጥፋት እንደሰሩ ፣ ምንም ቢደርስባቸው መጋፈጥ እንደነበረባቸው በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ይስተዋላሉ፡፡
አቡነ መርቆሬዎስን ይህ ጠፍቷቸው ሳይሆን ጳጳሳትም ሳይቀሩ ሲተባበሩባቸውና
በጊዜው ከአንድ አባት በስተቀር በቁርጠኝነት በጎናቸው የሚቆም ሲያጡ ግን ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና ተሰደዱ፡፡ በሌላ በኩል
ግን ብጹአን አባቶች ከላይ የጠቀስናቸውን እነ አትናቲዎስ ፤ እነ
ዲዮስቆሮስን ፤ እነ ዮሐንስ አፈወርቅን እና ሌሎችንም የተዋህዶ አርበኞች በማለት በኩራት ይዘክራሉ ፤ ያወድሳሉ፡፡
የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ
ዛሬ አባቶቻችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እጣ ፋንታ የሚወስን ከባድና አሳሳቢ ጉዳይ እጃቸው ላይ ወድቋል፡፡ ሊያደርጉት እየተዘጋጁበት ካለው ጉዳይ አንጻር ግን
የጉዳዩን አሳሳቢነትና ክብደት እንዳልተረዱትና ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ነገሩን ያለቅጥ አቅልለው እንዳዩት ያመለክታል፡፡ ዛሬም ቆራጥና
አስተዋይ መንፈሳዊ አባቶች ካሉን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከዚህ ከተጋፈጠችው አደጋ ለመታደግ አይደለምና ቀላሉን ነገር ነፍሳቸውንም
አንኳ ለመስጠት ራሳቸውን ከማዘጋጀት ወደ ኋላ የሚሉ አይሆኑም፡፡ የሚገርመው ግን የተጋፈጠውን ፈተና ይህንን ያህል መስዋዕትነት
እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አለመሆኑና ፍቅርን በማሳየት ፤ እልህንና ካፈርኩ አይመልሰኝ በመተው ፤ ከግል ጥቅም በመተው ቤተክርስቲያንን
ጥቅም በማስቀደም ፤ ለተቀቡበት ሰማያዊ አገልግሎት ታማኝነትን በማሳየት በቀላሉ የሚፈታ መሆኑ ነው፡፡
በሌላ በኩል ግን ይህ
የገጠመን ፈተና ያለንን ጥንካሬና ጽናት የፈተነና ያጋለጠ ሆኗል፡፡ በቀላሉ ፈተና እንዲህ የሆንን መስዋዕትነት የሚጠይቅ ከባድ ፈተና
ቢያጋጥመን ኖሮ ቤተክርስቲያንን እንዴት ልናደርጋት ኖሯል ? በትንሹ
መታመን ያልቻልን በብዙ ፤ በቀላሉ መታመን ያልቻልን በከባዱ እንዴት ነው ልንታመን ልንጸና የምንችለው? የሚል ትዝብት ያዘለ ጥያቄ
ለራሳችን እንድናነሳ አድርጓል፡፡ እንግዲህ የአዲስ አበባዎቹ ብጹአን አባቶች በ”ካፈርኩ አይመልሰኝ” ስሜት በመገፋፋትና በመገደድ
አዲስ ፓትያርክ ለመሾም በወሰኑበት ወቅትም ስደተኛው ሲኖዶስም እኛ
ያጎደልነውም የጣስነውም ሕገ-ቤተክርስቲያን ባለመኖሩ የምናፍርበት ፤ መንፈሳዊ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት የምናቆምበት አንዳች
ምክንያት የለም በሚል ስሜት እየተናገሩ ነው፡፡ እንደሚባለው ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሳያርፉ በሳቸው መንበር ሌላ ፓትርያርክ
መርጠው የሚስቀምጡ ከሆነ ቤተክርስቲያኗ ለሁለት መከፈሏ ገሀድ ይሆናል ማለት ነው፡፡
በቤተክርስቲያን ታሪክ
ሥልጣንን አመካኝቶ የሚፈጠር መከፋፈል ፍጻሜው የት እንደሚያደርስ በተደጋጋሚ ታይቷልና የዚህኛው ችግር እጣ ፈንታም ካለፉት የቤተክርስቲያን ፈተናዎች የተለየ አይሆንም፡፡ ይህንን አደጋ ለማስቀረት ብጹአን አባቶች ብልህ ፤ አስተዋይ ፤ ትሁት ፤ ታጋሽ ፤ እንዲሁም ይቅር
ባይ ሆነው ወንጌሉን በተግባር አልተረጎሙልንም ፤ አባቶች ቤተክርስቲያንን
ከሚጎዳ ራሳቸውን በታሪክ ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ወገን የሚያስቆጥር
ውሳኔ ላይ እንዳይደርሱ ብዙ ተጥሯል፡፡
ማንም የቤተክርስቲያንን
ታሪክ አውቃለሁ ፤ ለአምላክ ታማኝ አገልጋይ ነኝ የሚል አባት ይህንን ግልጽ ያፈጠጠ እና ያገጠጠ አደጋ ሊረዳ የማይችልበት አንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ ቢመስለን ነው እንጂ ይህንን የተሳሳተ ውሳኔ
በመወሰን ምንም የምናተርፈውና የምንጠቀመው ነገር አይኖርም፡፡ የምንጎዳው ፤ የምናጣው ፤ የምናጎለው ግን በእርግጠኝነት ይኖራል፡፡ ከምንም በላይ ቤተክርስቲያንን እናጣታለን፡፡ ሊመጣ ያለው አደጋ እንዲህ ግልጽ
በሆነበት ሁኔታ በቤተክርስቲያን ላይ ያንዣበበ ምንም አይነት አደጋ እንደሌለ የሚቆጥር ወይም የሚስብና የተጋፈጠውን ችግር ማየት
የማይፈልግ ሰው ካለ ይህ አርቆ የማሰብ ችግር ሳይሆን የአላማ ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡ በቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተክርስቲያን የገጠሟት
ፈተናዎችና ችግሮች የበግ ለምድ ለብሰው የገቡ ተኩላዎች እንደፈጠሩት ሁሉ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም መሰል እንቅስቃሴዎች ተከስተዋል
ለማለት ያስደፍራል፡፡ በእግጥ ከሁለቱም ወገኖች በስም ተለይተው የሚታወቁ በሊቃውንት የተገሰጹ እንዲህ አይነት ግለሰቦች እንዳሉ
ይተወቃል፡፡ የገበያ ግርግር ለምን ያመቻል እንዲሉ አሁን ቤተክርስቲያናችንን የገጠማት ችግር ለእነኚህ ግለሰቦች የጥፋት ዓላማ ስኬት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ የማይቀርና ግልጽ ነው፡፡
እንግዲህ ያለው ነገር
ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ካህናትና ምዕመናን ቤተክርስቲያናቸውን ለመታደግ መንቃት ግዴታችን ይሆናል ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሔር
ቸርነት ሁኔታው የሚረጋጋና መስመር የሚይዝ ከሆነ ለቀኖና እንዲበቁ
ለማድረግ እንዲሁም ይህን ታሪካዊና ቀኖናዊ ስህተት ያለበትን ውሳኔ
ለመወሰን እያደቡ ያሉትን ሰዎች ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሳይገባቸው በየዋህነት እያገዙ ያሉትን አባቶች ደግሞ በተቻላቸው አጋጣሚ
ሁሉ በመቅረብ ከዚህ ቤተክርስቲያንን ለአደጋ የሚዳርግ ስህተት ውሳኔ
እንዲታቀቡ ጉዳዩን በሚገባ በማስረዳት የተጣለብንን ክርስቲያናዊ ግዴታ
መወጣትና ቤተክርስቲያናችንን መታደግ ይኖርብናል፡፡ ነገሩ እንዴት ነው ወገን ? እንደ አንድ አማኝ ኃላፊነትም ይሰማን እንጂ ?
እግዚአብሔርንም እንፍራ መድኃኒዓለም ክርስቶስ የቸርነቱን ስራ ይስራልን ፤ እንደ ስራችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ይቅር ብሎ ይታረቀን
፡፡ቤተክርስቲያንን ከመፍረስ ይታደግልን… አሜን
የአንድ ሰው ሃሳብ
የልጅ ልጆቻችን በእኛ ዘመን በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ሁለት የሆነችውን ቤተክርስቲያን ልናወርሳቸው ግድ የሆነብን
ይመስላል ፡፡ እኛ በዚህ ዘመን ሆነን ደጋጎቹ አባቶቻችን ስለ ቤተክርስቲያን ብለው ያደረጉትን መልካም ጉባኤያት በመጥቀስ በዚህ
ጊዜ እንዲህ ሆነ እንላለን ፤ ልጆቻችንስ የእኛን ዘመን ምን ብለው ያንሱት ? የምንሰራውን ብቻ ሳይሆን ሰርተን የምናልፈውንም ነገር
እናስተውል ፤ ልጆቻችን ሙት ወቃሽ አናድርጋቸው ፤ በእኛ ችግር እነሱ ለምን ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ? እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ለሚያልፍ
ዕድሜያችን ጥሩ መስራት ቢያቅተን እንኳን ያለውን ማስቀጠል ያቅተን ?
ሞት አንዱን ከቅዳሴ አንዱን ከህዳሴ ሲጠራ እየተለመከትን እንዴት እኛስ አንማርም ? ከዚህ በላይ የሰላም አጋጣሚ ማግኝት እንደ ሰውኛ አዳጋች ይሆናል ብለን እናስባለን
፤ በዚህ ወቅት ያልጠበቡ ልዩነቶች ከአሁን በኋላ በሚደረጉ ድርድሮች ይጠባሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ፤ አንድም ምክንያት ይኑረን
መቶ ከሁለት በላይ የሆነች ቤተክርስቲያንን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ተዘጋጅተናል ፡፡ ሀላፊው ጠፊውና ከዘላለማዊው በአንድ መንገድ
ለማስኬድ እየሞከርን እንገኛለን ፡፡ በዘመን ሰው ማጣት አለመታደል ነው ፤ አሁን አባቶች የያዙት አካሄድ ለሁላችን የመጀመሪያ ሽንፈት
ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ ግን መሸነፍ ያለብን አይመስለንም ፤ ከሁለት ያጣች ሆነን ያሳለፍነው 20 ዓመት ሁለት መቶ ሆኖ እንዳይመጣብን
በዓላማ ለዓላማ በአንድ ልንቆም ይገባናል ፡፡ እርቀ ሰላሙን እንዲህ ዘጉት …ቀጣዩ የፓትርያርክ ምርጫስ እንዴት ይሆን ?
ጉባኤ ኬልቄዶን ቤተክርስቲያንን ሁለት ቦታ ሰነጠቃት… ይህን የእኛን ዘመን ደግሞ ጉባኤ ምን እንበለው…?
Thank you for the very interesting article and I agree with you. But, at one point I completely disagree and your explanation at that specific point seems to spoil the whole idea of your nice article. I quote “…ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን በደረሰባቸው ችግር በመሰደደዳቸው ጥፋት እንደሰሩ ፣ ምንም ቢደርስባቸው መጋፈጥ እንደነበረባቸው በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ይስተዋላሉ፡፡ አቡነ መርቆሬዎስን ይህ ጠፍቷቸው ሳይሆን ጳጳሳትም ሳይቀሩ ሲተባበሩባቸውና በጊዜው ከአንድ አባት በስተቀር በቁርጠኝነት በጎናቸው የሚቆም ሲያጡ ግን ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና ተሰደዱ፡፡”
ReplyDeleteYes fathers could flee to other places when persecuted but not the Holy Synod. Be reminded that the term persecution refers to life threatening situation. No in church history any exiled father took the Holy Synod with him. The Holy Synod is the congregation of fathers not the Patriarch alone, and its stays at the center of the people where it serves. Whenever the Patriarch exiles in the time of persecution, the Holy Synod stays with the congregation of fathers at the Holy See of the Patriarchate.
By the way let me ask these questions? Has His Holiness Merkoriwos faced life threatening persecution at the time of his dethronement? Where is his learning from His Holiness Abune Tewoflous, a martyr?
When I say this, I am not legitimizing what is going on at the Holy Synod in Addis. Simply I put their act in few words: they are fathers who don’t have due regard to the church but are egoistic people striving for worldly fame, wealth and power, and who staunchly serve the government rather than God who appointed them to lead His people. The same are the fathers in exile who staunchly serve their interests rather than God who appointed them to lead His people.
While saying this I am not forgetting the true fathers from both sides. They continue to live in our hearts and they will get their prize from God and their graces will continue to pour upon us. May God bring good time to the true fathers of our own and may He hear the cries of his children.
Sorry being such rude and using bad words but their unfatherly acts forced me to do so and I keep their dignity and pay due respect only if they are able to discharge their fatherly responsibility and keep the unity of the church. Otherwise, they are no more different from ordinary people.
Little bro. from Germany
Egziabher yestelen ,betam teru tentane newe
ReplyDeleteasteway lebona yalew sew ketgegne.
At this point I have known who is the major enemy of the church. The fake fathers are running for the sake of their luxiorous life.I am sorry about them. I am talking about Addis ababa's fathers.
ReplyDeleteጽሑፉ መልካም ነው ትምህርታዊ ነው። እስቲ በድንብ ነገሮችን ማጤን እንጀምር እንደምታውቁት በውጪው ዓለም መኖር ብቻ እውቀትን ያዳብራል የሚል ግምት ካለ ከአእምሮአችን ልናወጣው የሚገባን ነገር ነው። አብዛኛው ህብረተ ሰብ የሚኖረው በቡድን አስተሳሰብ ስለሆነ ውሸትም ይሁን እውነት ቡድናዊ አመለካከት ስለሚኖረው ብዙ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ሆነ በማህበራዊ ኑሮ ይህ ሁኔታ ይንጸባረቃል። ይህ ማለት የፖለቲካው ሽኩቻ አንዱ ትልቁ ምክንያት ሆኖ ሳለ ቦታ እንኳን የማይመርጥ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያንም አካባቢ ሆነ በማህበራዊ ኑሮ ዙሪያ የሚታዩት ሁኔታዎች በጣም አሳዝኝም አንዳንዴ ተስፋ የሚያስቆርጡም ናቸው። ብዙም ባይሆን መልካም ነገሮችም እንዳሉ አይካድም ይህንን ካልኩ ዘንድ መቼም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ምን ይሁን ምን እዚሁ በህገራቸው ቢቆዩ መልካም ነበረ ለጸሎትም ቢሆን የሚመቸው ኢትዮጵያ እንጅ አሜሪካ አልነበረም። በደለም ካለ እግዚአብሔር መልሱን ይሰጥ ነበረ ነገር ግን በግርግር መጠቀም የሚፈልጉ በፊትም ሆነ አሁን አብረዋችው ስለአሉ የሳቸው ከህገር መውጣትም ሆን መመለስ በነሱ እጅ ስለሆነ ፓትሪያርኩ ምንም መብት እንደሌላቸው እኔው እራሴ አሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ አይቼአለሁ። እርግጥ ወደ ሀገር ይግቡ ቢባልም እንደተባለው በተወሰነ ቦታ ሁሉ ነገር ተሟልቶላቸው እንዲኖሩ ተቀባይነት ቢኖረውም ወደ መንበራቸው መመለስ ግን አሁን ያለው መንግሥት ፈቃደኛ እንደማይሆን ምንም ጥርጥር የለውም። ለዚህ ምክንያቱም በደርግ መንግሥት የፓርቲ አባል ነበሩ ስለሚባል በትግራይ ሕዝብ ላይ በተደረገው ጭፍጨፋ ተባብረዋል በሚል ነው። እርግጥ ሲኖዶስ አቋቁምው ኤጲስ ቆጶሳት መሾማቸው ከፍተኛ ስህተት ላይ ጥሎአል በጊዜው የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ይስሃቅ አንድ ሲኖዶስ አንድ መንበር በሚል መለየታቸውን እኔም አውቃለሁ። ዋናው ቁም ነገር የቤተ ክርስቲያን ችግር የሚፈታው በመንፈሳዊነት እንጅ በዓለማዊ አስተሳሰ እንዳልሆነ ማንም የሚረዳው ነው። አሁን ግን እንደሚታየው እርቅ ሳይሆን የሚያራርቅ ነው ምክንያቱም በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተደረገውን የእርቅ ሁኔታ እንኳን በተለይ ክኢትዮጵያ የመጡ አባቶች ሌላ ሰው እንዳያገኛቸው የሚደረግ ያልነበረ ተጽእኖ አልነበረም እኔ ራሴ በዓይኔ ያየሁት ነው። ከላይ እንደጠቀስኩት የፖለቲካና የጥቅም ነገር ስለአለበት እርቁም ያልተሳካው ለዚሁ ነው እላለሁ። "ይሄይስ ተአምኖ በእግዚአብሔር እምተአምኖ በሰብእ" ነውና ቤተ ክርቲያንን እግዚአብሔር አየተዋትምና ሁሉም የእጁን ዋጋ ያገኛል ብዙም አያስጨንቀን ሁሉም በጊዜው ይሆናልና። ስለዚህ የውጪው ዓለም ትውልደ ኢትዮጵያ አብዛኛው ንግግር እንጂ ለውጥ ያመጣል ብዬ ብዙም አልጓጓም። በህገራችን ያለው ሕዝብ ግን እምባውን አንድ ቀን እግዚአብሔር ቆጥሮ ለቤተ ክርስቲያኗ መፍትሔ እንደሚሰጣት አምናለሁ።
ReplyDeletekelkedon
ReplyDeleteGubae ***KELQEDON*** 2tengaw ke tir 6-7 addis abeba ETHIOPIA
ReplyDeleteየአርዮስ እዉቀት
ReplyDeleteበጋራ ሆነን ስህተቱ ን እናርም አድነት ሃይል ነው
ReplyDeleteGUBAE aby stehaye , GUBAE sibehat nega ye 21ngw k/z KELQEDON be ETHIOPIA 06-07/05/2005 Tetenaqaq!!!!
ReplyDeleteከእንግዲህ ወዲያ ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ነን ማለት አይቻልም
ReplyDeleteየአዲሳባዎቹ አዛውንት አባቶች ጎረምሳዎቹ ከ ጋር ሆነው በማስፈራራት
የመንግስት ተባባሪዎች እነ ሆነው አባ አብርሃም ቤተክርስቲያንን እየገለባበጡ ነው
አሁን ያለው ምርጫ ከሽማግሌዎቹ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች
ጋር ሆነን መጸለይ ነው
በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው። በዘመናችን ታራቂ የሆኑ አባቶች ማጣታችን በእርግጥ ያሳዝናል። ያሳፍራልም። ምክንያቱም እናንተ በትክክል እንደገለጻችሁት አሁን የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ከዚህ የተሻለ ጊዜና አጋጣሚ ማግኘት ማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን ነው። ደግሞም “የሚገርመው ግን የተጋፈጠውን ፈተና ይህንን ያህል መስዋዕትነት እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አለመሆኑና ፍቅርን በማሳየት ፤ እልህንና ካፈርኩ አይመልሰኝ በመተው ፤ ከግል ጥቅም በመተው ቤተክርስቲያንን ጥቅም በማስቀደም ፤ ለተቀቡበት ሰማያዊ አገልግሎት ታማኝነትን በማሳየት በቀላሉ የሚፈታ መሆኑ ነው፡፡’’ አሁን ቁምነገሩ ያለውና ልናተኩርበት የሚገባው የተጋረጠውን አደጋ እንዴት እንቀንስ የሚለው ነው። እኔ በተለይ ምእመናን የሚከተሉትን ብናደርግ እላለሁ፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።
ReplyDelete1. በአባቶች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ምንጩ ዓይን ያፈጠጠ የሥልጣን ሽኩቻ እና ዘረኝነት መሆኑ እርግጥ እየሆነ የመጣ በመሆኑ በየትኛውም ወገን የቀደሙት አባቶች የሠሩት የቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት እየተጠቀሰ የሚነገረንን ሰበብ እየተቀበልን ከመለያየት መቆጠብ። ቤተከርስቲያንን አንድ የሚያደርጉ አባቶች እስከሚነሱ ድረስ በየትኛውም ጎራ የተሰለፉትን አባቶች መንፈሳዊ ስልጣን በማክበር የምንገለገል መሆኑን ነገር ግን አንዱን በማውገዝ ሌላውን በማግነን የማንተባበ መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ፤
2. በተለይ ከሀገር ውጭ የምንኖር ምእመናን በፍጹም የዋህነት መንፈስ በያልንበት የቤተክርስቲያን አስተዳደር ጸንተን አገልግሎት በመስጠትና በመቀበል መጽናት። የቤተክርስቲያንን ትምህርትና ሥረዓት ሳይበርዙ በየትኛውም አስተዳደር የሚያገለግሉ ካህናትንና የሚገለገሉ ምእመናን ከመውቀስ/ከመንቀፍ መቆጠብ። ይልቁንም በዓላትን በአንድነትና በፍቅር በጋራ ማክበር። ለቤተክርስቲያን በሚጠቅሙ ሥራዎች ሁሉ አስተዳደራዊውን ድንበር ተሻግረን መተባበር።
3. ቤተክርስቲያናችን የፖለቲከኞች መፈንጫ እንዳትሆን (የወያኔም ሆነ የተቋዋሚዋቹ) በንቃት መጠበቅ። ከፖለቲከኞች ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያንን ጥቅም አሳልፈው ከሚሰጡ ካህናትና ሰባኪያን መለየት።
4. ውሉን ማግኘት ከሚያስቸግረውና በቀላሉም መቋጫ ከማይገኝለት የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግሮች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ የራሳችንና የመጪውን ትውልድ መንፈሳዊ ሕይወት በሚያንጹ ተግባራት መጠመድ።
5. በማንኛውም ሁኔታ መለያየትን ከሚያስከትሉ ተገባራት በመቆጠብ በማናቸውም ምክንያት ቤተክርስቲያናችን በጥቂት መነኮሳት ጥል እንደማትከፈል ማረጋገጥ፥
6. አስተዳደራዊውን ክፍተት ተጠቅመው የቤተክርስቲያንን ትምህርት ለመቀሰት የሚያደቡትን በንቃት መጠበቅ
7. እውነተኞቹ የወንጌል መምህራንና ካህናት ምእመናን ከዚህ አሳፋሪ የመለያየት መንፈስ ወጥተው በአንድነትና በፍቅር የሚገለገሉበትን መንገድ ማስተማርና መምራት እንጂ አንዳችም የሚለያይና የሚከፋፍል ትምህርት ከማስተማር መቆጠብ፤
Betkirstiyanachnen amelake kidusan yitebikilne! M.A.
ReplyDeleteBetkirstiyanachnen amelake kidusan yitebikilne! M.A. A.A
ReplyDeleteBetkirstiyanachnen amelake kidusan yitebikilne! M.A. A.A
ReplyDelete“.... ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን በደረሰባቸው ችግር በመሰደደዳቸው ጥፋት እንደሰሩ ፣ ምንም ቢደርስባቸው መጋፈጥ እንደነበረባቸው በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ይስተዋላሉ፡፡ አቡነ መርቆሬዎስን ይህ ጠፍቷቸው ሳይሆን ጳጳሳትም ሳይቀሩ ሲተባበሩባቸውና በጊዜው ከአንድ አባት በስተቀር በቁርጠኝነት በጎናቸው የሚቆም ሲያጡ ግን ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና ተሰደዱ፡፡”
ReplyDeleteወዳጄ ይሄ ነገር እኮ በየትኛውም መልኩ ብትፅፈው፥ ብትገልፀው የትኛውንም ወገን ነፃ አያወጣም። በተለይ አቡነ መርቆርዮስን።
በተጨማሪም “... ከአንድ አባት በስተቀር በቁርጠኝነት በጎናቸው የሚቆም ሲያጡ...” ያልካትን እንያት። ተሰደድን ካሉት ቢያንስ ሁለቱ አባቶች አቡነ ዜና እና መልከ ፃዲቅ በወቅቱ አብረዋቸው ነበሩ። መቼም ተቃውመው ከተሰደዱ እንዴት ሁለት አባት አልሆኑም? መልሱ ግን ውሳኔውን የተቃወሙት አንድ አባት አቡነ በርናባስ ናቸው። ሁለቱ ግን ስልጣኗን እያለሙ መውረዳቸውን ሲደግፋ ከርመው፥ ለ 1 ዓመት ያህል በሂደቱ ውስጥ ሲተባበሩ እና በመውረዳቸው ተስማምተው ቆይተው፥ ስልጣኗን እንደማያገኟት ሲያውቁ መሰደድ የሚያሳየው የስልጣን ጥምን ብቻ ነው። ይህም የስልጣን ጥም ከ20 ዓመት በኋላም ከመልከ ፃዲቅ ላይ አልጠፋም። እንጂ ቢሆንማ እንኳን የነበሩት አዲስ የተሾሙት አባቶችን ጨምሮ ሁላችንም በደለኞች ነንና ይቅር እንባባል። አምላክንም ይቅር እንዲለን እንለምን። አንድ እንሁን ይባላል እንጂ እኔ ያልኩት ካልሆነ እኔ ነኝ ትክክል ብሎ ችክ ምንድን ነው? መጀመሪያ መልከ ፃዲቅ በወቅቱ ለነበራቸው ሚና ሃላፊነት ይውሰዱ። አቡነ ዜና ወደ እውነተኛው ሃገር ሄደዋልና።
መቸም ያለመማር አለማወቅ ከጳጳሳቱ እስከ እያንዳንዱ ክርስቲያን
ReplyDeleteትልቁ ችግራችን ነው
ሲኖዶስ ማለት ምን ማለት ነው
ቃሉ ከግሪክ የተወሰደ ነው ትርጉሙም ስብስብ በአንድ ልብ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን መምራት
The word synod comes from the Greek σύνοδος (synodos) meaning "assembly" or "meeting", σύνοδος (synodos) ሲኖዶስ meaning "assembly" or "meeting",
syn meaning "together" and hodos meaning "road" or "way", means a "coming together" በአንድ ልብ የሚሰራ ስብስብ ተስማምቶ የሚሰራ ማለት ነው
ሲኖዶስ አይሰደድም የምትልሉ ሲኖዶስ አዲስአባ ግርግዳ ላይ በምስማር የተለጠፈ አይደለም
የአዲሳባው ሲኖዶስ ወይም ስብስብ በአንድ ልብ አይሰራም እርስ በርሳቸው መስማማት ያልቻሉ
የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ሳይሆን የመንግስት ትእዛዝ የሚጠይቁ ለመንግስት የሚታዘዙ ናቸው
“ዐቃቤ መንበሩ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸው ተሰማ”
“ሲኖዶሱን ውሳኔ የተቃወሙት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ” ‹‹ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም››
“በስብሰባ ከተገኙት መካከል በተለይም ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ‘’ካልተስማሙ ገዳም መግባት ይችላሉ እንደምትሉ ሰምተናል፡፡ እኛ ግን ገዳም አንገባም ቤተ ክርስቶያንን ለመከራ ትተን የትም አንሄድም፤ ሕዝቡን እያጽናናን እስከ መጨረሻው እንዘልቃለን” ማለታቸው ተነግሯል፡፡ አረጋውያኑን አባቶች ገለል በማድረግ በብልጠት እየተሠራ ያለውን ሥራ እንደማይቀበሉት የገለጹት”
ከብዙ በጥቂቱ የምንሰማው ይህ ነው
የተማረው ወንጌሉን የሚያነብ በዚህ እያዘነ ከቤተ ክርስቲያን እየራቀ ነው
thank you so much for whoever wrote this wonderful comment. If all of us have more logical and reasonable approach like you, no obstacle would be too great
Deleteand neger menager efelegalew esum kelay betetsafew tshuf lay abune merkoriyos amarach selalneberachew tesededu belachewal yihun eshi gen lela seynodos memesretachew lek new wey??? endegeletsacheut yekedemut abatoch sesededu enesu tesededu enji betesededubet seynodos almeseretum.ewenet enenegager ketebale esachewen keager yaswetagn mengest new kalu ahunem yalew erasu yaw mengest new selezi ethiopia yalew seynodos lay chana ayadergem belachu tasebalachu??? lemen belugn ager bet beteleyaye mekneyat ashebare nachew eyale wegenochachenen yemeyaser mengest enant america lay kuch belachu yemetseruten yawekal malete bepoliticaw west yalachehun tesatfo malete new sele ethiopia hezb mekomachu baytelam eadegen menfesawi mengist atadergut egziabher yimesgen enantem agerachu endetegebu tefekdo altekebelachutem enji lemen endehone degmo betam yegebanal semaetenet enkuan bemeta lemekebel zegeju aydelachum malet new becha yerasachehun menged becha tekikil new belachu atasebu.egziabher and yadergen
ReplyDeleteበአሁኑ ዘመን እውነት ይህ ነው ማለት አይከፋም። አሁን እዚህ ያሉት አባቶች ተሰደድን የሚሉት ሁሉንም ኢትዮጵያ ባለሁ ጊዜ አውቃቸዋለሁ ወደዚህም ህገር እንደመጣሁም ተግናኝተናል። የሆኖ ሆኖ ጥፋቱ የሚብሰው በውጪ በአሉት አባቶች ናቸው ምክንያት የሚሆንው ኤጲስ ቆጶሳት መሾማቸው ነው። ለዚህ ተጠያቂ አባ መልክ ጼዴቅ ናቸው ሌሎቹ በዚህ አይጠየቁም ምክንያቱም በአቡነ ጵውሎስ ሲመት ላይ ነበሩ "ይደልዎ" ይገባዎታል ካሉ በኋላ የመንኩሴ ቆብ በማጥለቅ ማንነታቸው እንዳታወቅ ወደ ኬንያ ሸመጠጡ ይህ ከራሳቸው አንደበት የሰማሁት ነው። አባ ዜናም ቀጠሉ ከዚያም ፓትሪያሪኩን አስኮበለሉ። ፓትሪያርኩም ለዓመታት በኬንያ በቆዩበት ጊዜያት በገንዘብ እርዳታ የሚያደርጉት ብጹኣ አቡነ ይስሃቅ በጊዜው የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ እንደነበሩ እኔም አውቃለሁ። በዚህ ዓይነት በአሜሪካ ከተሰባሰቡ በኋላ በየቦታው ያሉትን መነኮሳትና መምህራን ሙሉ ለሙሉ የጎንደር ተወላጆችን ከየቦታው አሰባስበው የቡድን ጉዞ ቀጠሉ ብጹእ አቡነ ይስቅም ሲኖዶስ አይሰደደም አንድ መንበር ነው ባሉ ብዙ ውለታ ያደረጉላቸውን አባት ለዩ። አባ መልክ ጼዴቅ ለፓትርያርክ ቴዎፍሎስ የማይታዘዙ ክንጉሡ ጉያ በመግባት ቆራጭ ፈላጭ በመሆን በቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቅ ጉዳት የፈጸሙ ምሆኑን ብዙ ሰው ያውቀዋል። እዚህም ሌሎቹን አባቶች በማስፈራረት የጊዜውን ፓለቲካ መጠቂሚያ በማድረግ ልዩነትን በማስፋት እንዲቀጥል አድርገውታል እስካሁን ስለተደረገው የእርቅ ሙከራ የሰው አፍ በመፍራትና የፓለቲካውም እየቀዘቀዘ በመምጣቱ እንጅ ፈልገውትም አይደለም። ለመጨረሻም ጊዜ በተደረገው ስብሰባ ማለት በዳላስ አንድም እርቁ እንደማይሳካ ቢታወቅም ቢያንስ እንኳ ትላልቅ አድባራት ከሚባሉት የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በገለልተኛነት የቆየውን እጅ ለማስገባት የተደረገ እርምጃ ሲሆን በሌላ መልኩ ይህ መንግሥት እያለ ኣባ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው እንደማይመለሱ እየታወቀ ቅድመ ሁኔታ በመደርደር እርቁ እንዳይቀጥል ምክንያት ሲሆን ይህም በውጪ ያለነው ሰላም ፈላጊ ስንሆን የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላሙን መንገድ ዘጋው በሚል የፖለቲካውን ድጋፍ ለማደስ የተደረገ እንጅ ምንም እውነት ነገር የለውም። ይህንንም በሂደት ወደ ፊት እናያዋለን። እግዚአብሔር እድሜ ይስጠን።
ReplyDeleteYgermal lhulum amlak yidrsiln wladit amlak wede lijua tasasblin zend fekadua yihun amen.
ReplyDelete"መቸም ያለመማር አለማወቅ ከጳጳሳቱ እስከ እያንዳንዱ ክርስቲያን ትልቁ ችግራችን ነው" ይህን የጻፉት እውነት አስበውበት ነው ወይስ በስሜት በመገፋት ነው? አገላለጽዎ ንቀት የተሞላበት እንጅ የአዋቂም አይመስልም ምክንያቱም እርስዎ አስተምረው አልገባም ያላቸው ካሉ ስም ጠቅሰው ለይተው መናገር እንጅ በደፈናው ከዳር እስከዳር መጨርገድ እንኳን እንደርስዎ በውእቀት የተራቀቀ ይቅርና ትምህርት ቤት ደጃፍ ያልደረሰ እንዲህ ዓይነቱ አገላለጽ አጸያፊ መሆኑን ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ። "የሲኖዶስ" ትርጉሙን ከመናገር የዘለለ ችሎታ አለዎት ለማለት ያቀረቡት ሀሳብን ሳነበው እንኳን አስተማሪ ሊሆን ይቅርና ከወገናዊነት ወይም ክጊዜው ፖለቲካ አመለካከት ያለውን ዝምድና እንኳን በትክክል አይገልጠውምና ለውደፊቱ ህሳብዎን በሰክነ ሁኔታ ቢያቀርቡት አንድም ያስተምሩበታል ወይም ይማሩበታል። አበው ሲናገሩ "ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል" እንዲሉ እርስዎም ሲጽፉ ተረጋግተው ይጻፉ ክእግዚአብሔር በስተቀር የሚያዮት የለምና።
ReplyDelete