Monday, January 14, 2013

በዋልድባ አራት መነኮሳትና ሶስት አርሶ አደሮች ታሰሩ


አንድ አድርገን (ጥር 05 -2005)፡- መንግሥት በዋልድባ አካባቢ እገነባዋለሁ የሚለውን የስኳር ፕሮጀክት ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል ፡፡ አንድ ጊዜ በጸባይ ሌላ ጊዜ ደግሞ በፈርኦናዊው ጡንቻው በማስፈራራት አላማውን ከግብ ለማድረስ ብዙ እየሞከረ ይገኛል ፡፡ መነኮሳቱን በጎጥና በቋንቋ እንዲከፋፈሉ ሁለትም ሃሳብ እንዲሆኑ ብዙ ጥሯል ፤ ዋልድባ ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ገዳም መሆኑን ወደ ኋላ በማለት ቦታውን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አካል እንጂ የአማራ ክልላዊ መንግስት አይደለም ስለዚህ በገዳሙ ላይ ሃሳብ መስጠት የሚችሉት የክልሉ ተወላጅ የሆኑት መነኮሳት እንጂ ማንም አይደለም የሚል ሃሳብ በማንሳት ጉዳዩን ወደ ሌላ መንገድ ለመውሰድ ተሞክሯል ፤  በየጊዜው በቦታው ላይ የሚካሄደው ነገር ለመገናኛ ብዙሃን በማሳወቅ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙትን አባት እሳቸውን ለጠቆመ የኮንዶሚኒየም ቤት እና ብዙ ሺህ ብር እንደሚሰጠው መንግሥት ለአካባቢው ነዋሪዎች ሲገልጽ ተስተውሏል ፤ ግንባታውን የጀመሩት አንድ ሀገር በቀል እና አንድ አለም አቀፍ ተቋማት ስራውን በተለያዩ ምክንያቶች መስራት ተስኗቸው በአሁኑ ወቅት ሶስተኛ አለም አቀፍ ኮንትራክተር ወደ ቦታው ለሁለቱ ያልተሳካውን ሊሞክር ስራውን ጀምሯል ፡፡ የሥኳር ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ አባይ ጸሃዬ ለኢቲቪ እንደተናገሩት ከሆነ ሶስተኛው ኮንትራክተር ስራውን ከመጀመሩ በፊት በዛሬማ አካባቢ የሚሰራው ግድብ ጥቂት በሚያሰራ መልኩ ማስተካከያ እንደታከለበት ጠቁመዋል፡፡ የቦታውን ሁኔታ ለቪኦኤ የገለጹት መነኩሴ እንዳሉት አዲስ የገባው ኮንትራክተር የጣሊያል ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ “መነኮሳቱ ከአካባቢው ካለቀቁ ስራውን ለመስራት እንቸገራለን” እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

ህዳር 18 ቀን በተደረገው ጉባኤ ይፈርሳሉ የተባሉትን በርካታ ቤተክርስቲያናት መንግሥት በወከላቸው ሰዎች አማካኝነት ለሚፈርሱት አብያተክርስቲያናት ካሳቸውን ተቀበሉ በማለት በስብሰባው ላይ ለተገኙት 30 መነኮሳትን ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል ፡፡ መነኮሳቱም “ይህ እኛ የምንወስነው ጉዳይ አይደለም ፤ ቤተክርስትያንን ሽጠን ካሳ አንቀበልም ፤ ለመነኮሳት ማኅበር ይህን ጉዳይ እናሳውቃለን እንጂ እኛ የምንቀበለው ነገር የለም ፤ ይህ ጉዳይ  መነኮሳቱ በጠቅላላ ተሰብስበው ሃሳባቸውን የሚሰጡበት ጉዳይ ነው” በማለት በጊዜው ሃሳባቸውን ለተወከሉት ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡ ይህን ጉዳይ ይዘው የሄዱት መነኮሳት ባደረጉት ጉባኤ በሰርጎ ገቦች እና የመንግስን ታርጋ በለጠፉ ሰዎች አማካኝነት አንድ ነጥብ ላይ ሳይደረስ በመቅረቱ ፤ “ይህ የጸለምት ወረዳ ነው ፤ ከሌሎች አካባቢ የመጡ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ሰዎችን ከአካባቢው ማስወጣት አለብን ፤ እነዚህ የልማት ጠር ናቸው ፤ መንግሥት ለሚሰራው ሥራ እንቅፋቶች እነዚህ የመሰሉ መነኮሳት ናቸው” በማለት ይዝት በነበረበት ወቅት በገዳሙ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች “ገዳሙ እስኪጠፋ ቆመን መመልከት የለብንም  ፤ ይህ ጉዳይ የመነኮሳቱ ጉዳይ ብቻ አይደለም ፤ ሃይማኖታዊ ግዴታችንን መወጣት አለብን” በማለት የጸለምትና የአድርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች ታህሳስ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በጋራ በመሰብሰብ መንግሥት በአካባቢው ላይ የሚያካሂደውን ልማት በመቃወም በመረጧቸው ሰዎች አማካኝነት ሃሳባቸውን ለማይጸብሪ ወረዳ አስተዳደር ለመግለጽ በሄዱበት ወቅት ፤ የቦታው አስተዳደሪ “ማንም ሰው በቦታው መሰብሰብ አይችል ፤ እናንተ ምን አገባችሁ ? ተሰብስባችሁ ብናገኛችሁ እናስራችኋለን” የሚል ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል ፡፡ እንደ ዛቻና ማስፈራሪያቸውም ሶስቱን አርሶ አደሮች እና አራት መነኮሳን በዚህ ጉዳይ በሁለት ቀን ውስጥ እስር ቤት ውስጥ አስገብተዋቸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዋልድባ አራት መነኮሳት እና ሶስት የአካባቢው አርሶ አደሮች በጠቅላላው ሰባት ሰዎች በያዙት አቋም እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ ባላቸው ያልተለሳለሰ አቋም ለእስር የተዳረጉት አባቶች አባ ገብረ ሕይወት ፤ አባ ገብረማርያም ፤ አባ ወልደ ገብርኤል ፤ መናኝ ታዲዎስ ሲባሉ   በአካባቢው ላይ ካሉ አርሶ አደሮች እና “የዋልድባ ጉዳይ የእኛም ጉዳይ መሆን መቻል አለበት ለመነኮሳቱ ብቻ የምንተወው ጉዳይ አይደለም” ያሉት አቶ አለምሸት ቱሉ ፤ አቶ ተክሌ ገብረኪዳንና አቶ አምባቸው በጸጥታ ሰዎች አማካኝነት ወደ እስር ቤት መግባታቸው ሊታወቅ ችሏል፡፡

መንግሥታችን ብረት እንጂ ልብ መግዛት አቅቶታል ፤ ፈርኦን የደነደነው ልቡ ከአስራ አንድ ቁጣና መቅሰፍቶች  በኋላ ባህረ ኤርትራ አስጥሞታል ፤ እግዚአብሔር በርካታ ጊዜ ፈርኦን ልብ እንዲገዛ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ አስተምሮታል ፤ ከጥቁር ድንጋይ ይበልጥ ልቡ ደንድኗልና ሰራዊቱ መጨረሻው መስጠም ሆኗል ፤ መጽሐፈ ምሳሌ 29 ፤1  እንዲህ ይላል “ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።” ስለዚህ መንግሥት ስራው ከተጀመረበት ጀምሮ ያለውን በአካባቢው ላይ የሆነውን የተደረገውን ነገር በማየት ልብ ቢገዛ መልካም ነው ፤ ለ1000 ዓመት ታፍሮ እና ተከብሮ የቆየውን ገዳም ድንበሩን ስታፈርሱ ለስራችሁ ከሰው መልስ ባታገኙበት እንኳን አምላክ በጊዜው እጁን እንደሚዘረጋ አትዘንጉ ፤ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው ድምጸ አራዊትን ታግሰው በጾም በጸሎትና በምናኔ ህይወት የሚገኙትን አባቶች ለዘመናት በቦታው ላይ የቆዩትን መነኮሳት “ካልተነሱ” ማለት የተቀመጡበትን አለማስተዋል ነው ፤ እግዚአብሔር ሊዋጋ ጦር አይመዝም ፤ ሰራዊትም አያዘምትም ፤ በተቀመጣችሁበት በአይን ጥቅሻ ሰዎች ለጭንቅላታቸው ማመን በሚያቅታቸው ጥበብ ዘመንን ይቆርጣል ፤ እምባም ቢፈስ ማቅም ቢለበስ የፈሰሰ ውሃ ሆኖ ይቀራል ፤ ይህን ለማስረዳት ዘመን መጥቀስ ስምም መጥራ ያለብን አይመስለን ፤ ዘመናችሁ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ እንዳይፈጥን ፤ ያለተስፋም እንዳያልቅ እጃችሁን ከዋልድባ ላይ አንሱ ፡፡ 

መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6 ፤ 16 ላይ ከኤልሳዕ ጋር ያለው እግዚአብሔር ከጠላት በኩል ከተሰለፈው እልፍ አዕላፍ ሰራዊት እንደሚበልጥ ሲጠቁም ነብዩ በፍርሃት ላለው ለሎሌው እንዲህ አለው አትፍራ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና” ከዛም “ኤልሳዕም። አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም  በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር” ይላል፡፡ እኛም እንላለን “በዋልድባ ከአባቶቻችን ጋር ያለው እግዚአብሔር እናንተ ጋር ካለው  ይበልጣል”፡፡
“ስለ ቤተክርስቲያን ጸልዩ”

5 comments:

  1. Abetu Kindhen geltse hailhenem asayachew , Yabatochachen gefe beztoal ena temelket , Amlake Kidus Giyorgise Teradan ebakhen . Mastewalenem lemishu Anete setachew . Betkristian Lezere ena Lekuankua bota yelatem ena yehenen mate ketselot betachen Betamerh Aswetalen . Ebakehen Geta hoy

    ReplyDelete
  2. God of Israel, Abraham and the God of Ethiopia never sleep...... today maybe they think they can do anything with their worldly power but God will destroy them in his owen time in a blink of an eye. Walba is a monastery that has invisible hermits who walks with GOD.....

    I believe they are fighting with GOD, and it tells me that their governance days of Ethiopia is coming soon an end.

    May GOD bless Ethiopia.

    ReplyDelete
  3. Abay Tsehaye and other woyanes, please open your blind eyes. The death of Melese and 'aba' Paulos should be your lesson. The next person to die may be you, Abay Tsehaye. why don't you use your mind? who could have imagined that Melese was going to die? you see that is for eternity. he will never come back. done. have you ever thought of the idea of burning in hell not for a few million or billion years but for eternity? Many powerfull and vey wealthy people died with that enormous amount of wealth and power left behind. you guys have ammased and stolen huge amount of money from the poor Ethiopian people for the last 20+ years. enough is enough. stay away from our holy monastry! period. The ALMIGHTY already gave you a lot of miracles to act as a lesson. otherwise, HE will call you in the day that you never expected.

    ReplyDelete
  4. Selam Mimenan!
    I think the meeting is Going in a wrong Direction From what we want so let us make ourself ready to say something on sunday after kidase let us make it a big voice "beyedebrachin Self enwta"I care About my church"
    "peace first Election next" 'We need Response" so next sunday beyedebrachin enizegaj. Astedadariwoch bedebdabe ena bsilk demsachinin astelalfuln Eyaschegernachu endehone nigerulin"
    God Bless!

    ReplyDelete
  5. IS IT NOT THE WAR BETWEEN GOD AND devil?

    ReplyDelete