Tuesday, January 22, 2013

አዲስ አበባ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን ተቃጠለች



ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተነሳ ፎቶ




ቤታቸውን በፍቃደኝነት ዳግም በመስራት ላይ ያሉ ወጣቶች


ቀድሞ ቤተክርስቲያኒቱ እዚህ ቦታ ላይ ነበረች


  • ትላንትና ከቀኑ 7 ሰዓት በተነሳ እሳት ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ከሚገኙ ታቦታት   ከመጽፍትና ከመስቀል ውጪ ሙሉ በሙሉ አውድሟታል :: ቤተክርስቲያኒቱ በጠራራ ጸሀይ ፤ በቆርቆሮ የተሰራው ግድግዳ እና ድንገት በተነሳ እሳት በአንድነት በመሆን የደረሰውነ ጉዳት  ከፍ አድርገውታል
  • እስከ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ከ200 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል ፤ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ምዕመናኖች ቦታው ላይ በመገኝት ቤተክርስቲያኒቱን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ 
    •      ከትላንት ማታ ጀምሮ የተጀመረው ስራ አሁንም ቀጥሏል ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከተቃጠለች 24 ሰዓት ሳይሞላት ማገር አቆመው የጎን ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተጠናቋል፡፡
      •     አካባቢው ያለው ሰው ስራውን ለሚሰሩት ሰዎች እንጀራ ወጥ ፤ ለስላሳ ውሃ እና አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ ከ48 ሰዓት በፊት ስራን ለመጨረስ እየተረባረበ ይገኛል
      •                የእሳቱን መነሻ አሁንም እየተጣራ ይገኛል  ; እሳት አደጋ ተደውሎለት በሰዓቱ ባለመምጣቱ አደጋውን የከፋ አድርጎታል 
  • የእመቤታችን የቅዱስ ዮሃንስና የቅዱስ ኡራኤል ታቦቶች ምንም አለመሆናቸው እጅጉን አስገርሟል
  • በርካታ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት ተረባርበው ነበር
  • ትላንትና 70 ሺ ብር ከምዕመኑ መሰብሰብ ተችሏል ፤ ዛሬ ጠዋትም ቤተክርስቲያኒን ለመስራት ብር እየተሰበሰበ ይገኛል
  • ዛሬ ጠዋት በርካታ ወጣቶች ቤተክርስቲያኒቱን ዳግም ለማቆም እየተረባረቡ ይገኛ
  • የአካባቢው ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉት መረባረብ እጅግ ያስገረመ ነበር ፤ አሁንም ቤቷን ለማቆን ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛል ፤
     

2 comments:

  1. እሳቱ በተነሳበት እለት ቅዳሴ ከነበረ ወይም ማዕጠንት ታጥኖ ከነበረ ምን አልባት ፍሙን ሳያጠፉ ሄደው ሊሆን ይችላል መቸም መሃል አዲስ አበባ አይን እያየ ገብቶ ቤተ ክርስቲያን ሊያቃጥል የሚሞክር ጠላት ይህን ድፍረት ያገኛል ማለት ይከብዳል፡፡ ለሁሉም ወላዲተ አምላክ በአይነ ምሕረት ትመልከተን ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን ጠቅላላ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተነሳውን አንድነትና ፍቅር የማጣት እሳት በናትነት ልመናዋ ታጥፋልን

    ReplyDelete
  2. Very great post. I just stumbled upon your weblog and wanted to say that I have truly loved surfing around your blog posts.
    After all I will be subscribing for your feed and I am hoping you write again very soon!
    Here is my site ... cures for insomnia

    ReplyDelete