Tuesday, January 8, 2013

የጳጳሳቱ ማረፊያ



የጳጳሳቱ ማረፊያ
from face book (by Henok Haile)
 116ኛው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ 6 በፓትርያርክነት ዘመናቸው ይቀመጡበት የነበረው በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የሚገኝ አንድ ያረጀ ክፍል ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ሲኖሩ አንድ የካቶሊክ መነኩሴ ሊጎበኛቸው መጣ፡፡ ፓትርያርኩን ማረፈያ ቤትና ዕቃዎቻቸውን ሲመለከት ለክብራቸው የሚመጥን ባለመሆኑ ደነገጠ፡፡ (ፓትርያርክ የሚሆኑ አባቶች በደህና ማረፊያ ሊኖሩ ይገባል ይህም ለእነርሱ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲባል ነው፡፡) መነኩሴው አቡነ ቄርሎስን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው ‹‹እባክዎን በእንዲህ ዓይነት ቤት ውስጥ መኖር ለእርስዎ የሚመጥን አይደለም፡፡ ፈቃድዎ ከሆነ እኔ ቤትዎን ላድስልዎትና ምርጥ ምርጥ ዕቃዎችን ላስገባልዎት?›› ፓትርያርኩ ይህንን ጥያቄ ሲሰሙ ፈገግ ብለው በፍቅር ዓይን ከተመከቱት በኋላ ‹‹የእኔ ልጅ አመሰግናለሁ! እርግጥ ነው ይህ ቤት በጣም የተጎሳቆለ ነው፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን ጌታችን ከተወለደበት በረት ይሻላል!!›› አሉት፡፡
በእኚህ አባት እግር የተተኩት ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ደግሞ በግብፅ መንግሥት በታሰሩ ጊዜ  ምእመናኑ ከእስር ቤት ወጥተው ማረፊያ ቤት እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ሰልፍ ወጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳ ለሕዝቡ ንግግር አድርገው ማረፊያ ይሰጣቸው በሚል የተወጣውን ሰልፍ እንዲበትኑ ተጠየቁ፡፡ እኚህ አባትም ሕዝቡን  እንዲህ ሲሉ አረጋጉት፡፡ ‹‹ለእኔ ማረፊያ እንዲሰጠኝ ብላችሁ ሰልፍ ወጥታችኋል ነገር ግን በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!››  

5 comments:

  1. Leb yalew leb yebel! LEWLCEN!

    ReplyDelete
  2. እንዲህ አይነት አባቶች ማጣታችን እኮ ነው ችግር የሆነው። 40 ሚልዮን በምንሆን ኦርቶዶክሳውያን ልብ ውስጥ እሚገባ አባት እስካላገኘን ድረስ ችግራችን ይቀጥላል። አቡነ ጳውሎስ ነፍሳቸው ይማርና አብዛኛው ምእመን ልብ ውስጥ አልነበሩም። አሁንም አቡነ መርቆሬዎስ ቢመለሱ ያው ነው። እሳቸው ሲወጡ አስር አመቱ የነበረ ልጅ አሁን ሰላሳ አንድ አመቱ ነው። አያቃቸው አያቁትም። ለዚህ ለሃይማኖቱ ቀናኢ ለሆነና ቤት ክርስቲያኑ ለመረከብ የተዘጋጀ የዘመነ ማህበረ ቅዱሳን ወጣት መንፈሱን የሚሞላ፤ አርአያ የሚሆን አባት ማግኘት አለብን። አሁን ያለውን እድል መጠቀም ይኖርብናል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ታሳዝንአለህ!! ከቤተ መንግስት ያለህ ትመስላለህ። ኤግዚአብሔር ልቦናህን ይክፈትልህ አውነት አንድትናገር። አቡነ ማርቆርዮስ አውነተኛው ፓትርያርክ ናቸው። 30 ወይንም 20 ዓመት ቢሆነህም ስለተሰደዱ አባትነታቸውን ልትክድ አትችልም ልካደም አይቻልም። በጌታቺን በአየሱስ ክርስቶስ ላይ የተገነባች ቤተ ክርስቲያን ጠፍታ አትቀረም።
      ስብሐት ለአግዚአብሔር

      Delete
  3. " ... ነገር ግን በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!" While there are many starving in Ethiopia, there are many Papasat in the country owing 3 or more 3 story building, which outside of the church cannon.

    ReplyDelete
  4. ጥሩ ብለሀል ፤ ነገር ግን የውጬ ምእመን የአሀገር ውስጡን አባት ሳያውቅ ብሎም ሳይባረክ ኦንዲህ ሆነ ፤ የሀገር ውስጡም ኦንዴሁ የታሰረው ቐጠሮ ሳይፈታለት ኦኔህም አባት እንዳያመልጡ ሌሉውን ነገ ልንደርስበት ሰለምንቾል ቅድሜያን አንድ አድርገን ለሜለው ጶለት ቢሆን መለካም ይመስለኛል ::

    ReplyDelete