Thursday, April 19, 2012

በዋልድባ መንግስት ሬሳ መልቀምን ተያይዞታል


(አንድ አድረገን ሚያዚያ 11 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ጉዳይን በቅርቡ በአካል ቦታው ድረስ ሄደው የተመለከቱት ሰዎች ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በጥቂቱም ቢሆን ያዩትንና የሰሙትን አካፍለውናል ፤ ቦታው በፖሊሶች እንደተከበበ ገዳሙ የጸሎት ቦታ መሆኑ የቀረ እስኪመስል ድረስ የጦር አውድማ በሚመስል መልኩ በታጠቁ ወታደሮች ተከቧል ፤ አበው መነኮሳቱን ከበአታቸውን እንደ ወንጀለኛ  በጠገበ ወታደር እያዳፉ ሲወስዷቸው በዓይናቸው ተመልክተዋል ፤ በተነሳ ጥያቄ መሰረት ጥይት ተኩሰውባቸዋል ፤ ስውራን አባቶችም እናንተ ባላችሁበት ጸልዩ በማለት ቦታው ላይ በተገኙ ወንድሞቻችን አማካኝነት ለእኛ መልዕክት አስተላልፈውልናል ፤ መንግስትስም ለፕሮጀክቱ መፋጠን መኪኖችን ወደ ቦታው እያመሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ባለፈው ቅዳሜ 08-08-2004 ዓ.ም በቪኦኤ ላይ የገዳሙን አንድ አባት አግኝተው እንዳናገሯቸው መንግስት አሁንም አጠናክሮ ስራውን እየሰራ መሆኑን ለቪኦኤ አስረድተዋል ፤ በፊት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት አባት አንዳች ስህተት እንዳልሰሩ የተናገሩት ሁሉ ትክክል እንደሆነ ተነግሯቸዋል ፤ ግን ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ አክለው ገልጸዋል፡፡ ብጹእ አቡነ ጳውሎስና ጥቂት ጳጳሳት ለገዳሙ አባቶች ያልተከፈተ ጆሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚሰጡት ወቅታዊ አስተያየት የላይኛውን የተወካዬች ምክር ቤት ወንበር ተቆናጥተውት በኢቲቪ ተመልክተናል ፡፡



ከዚህ በፊት በቦታው ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት አንድ መሀንዲስ መሞቱን ገልጸን ነበር ፤ ከየት እንደመጡ ባልታወቁ ከዱር የወጡ አውሬዎች ቦታው ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችን እየተተናኮላቸው መሆኑን አክለን ገልጸናል ፤ አሁን ደግሞ በቦታው ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ስራውን እየሰሩ ባልታወቀ ምክንያት በየቦታው እየተፈነገሉ ይገኛሉ ፤ በቦታው ላይ የሟች ቁጥር ስድስት ደርሷል ፤ መንግስት ምክንያቱን አልደረሰበትም ፤ መንግስትም ሬሳ ለቀማውን ተያይዞታል ፤ ጊዜው ደርሶ የእነርሱም ሬሳ እስኪለቀም ድረስ ፤ ይህ ነገር በሚዲያ እንዳይወጣ ዝምታን የመረጠ ይመስላል ፤ ወሬው ቢሰማ ለስራው ጥሩ ስላልሆነ ሲሞቱ ብቻ ሬሳ ማንሳትን መርጧል ፤ እስከ አሁን ድረስ  ስድስት ሰዎች ሞተው ተገኝተዋል ፤ ነገ ደግሞ ስራቸውን ከቀጠሉ የባሰ እንደማይመጣ እርግጠኞች አይደለንም ፡፡ እነዚህ ሰዎች በምን ሞቱ ይባላል ?
‹‹ እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ›› ትንቢተ ሚልክያስ 4፤5 ከእኩይ ተግባራችሁ ተመለሱ ፡፡ ‹‹ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል›› የሐዋርያት ሥራ 26፤ 14 ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሳውልን በጊዜው እንዲህ ነበር ያለው ፤ አሁንም የመውጊያውን ጫፍ እየነኩ መከራውን እየተቀበሉ ፤ በእነርሱ እየባሰ ይገኛል ፤ ዋልድባን ነክቶ የሰላም አየር መተንፈስ የለም ፤ ለናንተ የምጥ መጀመሪያም  ሊሆን ይችላል ፡፡

መንግስት በህገመንግስቱ ዘወትር ‹‹መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም›› ይላል ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው የዋልድባ ገዳም አባቶች ምህላ እንኳን በህብረት ሆነው ወደ አምላካቸው እንዳያደርሱ ተከልክለዋል ፤ ምህላ ጸሎት ነው ፤ ጸሎት ማድረግ በመንግስት ከተከለከልን እንዴት መንግስት ጣልቃ አልገባም ማለት እንችላለን ? ፤ የምህላውን ውጤቱን ከኛ ይልቅ እነርሱ የተገነዘቡት ይመስለኛል ፤ የዛሬ 20 ዓመት ገዳሙን የጦር ካምፕ ለማድረግ ሲያስቡ ፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲፈፅሙ የደረሰባቸው አደጋ ትምህርት ሊሆናቸው አልቻለም ፤

እግዚአብሔር በርካታ ጊዜ በሙሴ አማካኝነት ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎ በቀጥታ ነግሮታል ፤ ፈርኦንም ልቡን ክፉኛ አደንድኖ ነበር ፤ በስተመጨረሻም እግዚአብሔር በተዓምር ህዝቡን አስለቅቋል ፤ አሁንም ይህን የስኳር ልማት እንዳትሰሩ ፤ ህገ ወጥ ስራችሁ የገዳሙን ህልውና እንዳይፈታተነው በርካታ ጊዜ በአባቶች እና በምዕመኑ ተመክራችኋል ተዘክራችኋል ፤ ልቦናችሁ ደንቁሮ ዝም ብላችኋል ፤ አሁን አንድ በአንድ እያለ ይለቅማችኋል ፤ እናንተን ሲለቅም እኛን ቁጭ ብለን አንቆጥራለን ፤ የእግዚአብሔርንም ስራ በእምነት እናደንቃለን ፤ ሲጀመር የመጀመሪያው ሰው ሞት ገርሞን ነበር ፤ አሁን ግን ስድስት ሰው መድረሱን ማወቅ ችለናል ፤ እናንተ ልባችሁን ለማደንደን ባሰባችሁ ቁጥር መቅሰፍቱ ከአንድ ሰው ወደ ስድስት ሰው እያደገ ይሄዳል ፤ አምላካችን ዋድባን በተአምር ያስለቅቃችኋ ፤ የአቡነ ተክለኃይማኖት ፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፤ የአቡነ እስትንፋሰክርስቶስ ፤ የቅድስት አርሴማ አምላክ እኛን አይተወንም ፤ እንደ እኛ ሐጥያት ሳይሆን እንደ አባቶቻችን ጸሎት ብሎ ገዳሙን ከአደጋ እንደሚጠብቀው ጽኑ እምነታችን ነው፡፡

የሐዋርያት ሥራ 1፤14 ላይ ‹‹በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።›› ይላል ፤  እስኪ እኛም በአንድ ልብ ሆነን ስለ ዋልድባ ገዳም በርትተን እየጸለይን  እንትጋ ….የእግዚአብሔርንም እጅ እንጠብቅ ፡፡
የሚቀጥለውን ተዓምር ይጠብቁን 

47 comments:

  1. gena bizu resa yilekimal,yenekawu eko yekidusan amlak yehonewun geta new yersu mewugia degimo enbi lalut eskemechershawu yemiyatefachewu new!

    ReplyDelete
    Replies
    1. gena bizu resa yilekimal,yenekawu eko yekidusan amlak yehonewun geta new yersu mewugia degimo enbi lalut eskemechershawu yemiyatefachewu new!

      Delete
    2. zare resa yelekemal nege degemo yeenesu resa yelekemal

      Delete
    3. waldiban yemitneku yemechereshachu yihonal.

      Delete
  2. በዋልድባ መንግስት ሬሳ መልቀምን ተያይዞታል
    then what do you want?
    is this information(new and vital messege)??
    it is already known.

    ReplyDelete
  3. Yemafyaw budne kechaka jemero siltan lay eskewotana kezam behuala lebetekrstian andm ken tegnetolat ayawkm gin amlak bechernetu leserut wonjel yensha gize bisetachewm ahunme kekfu serachew memelesena lensham lebachew ende feron seledenedene Egziabhere ende Musse Yale abate eskiazegajelene betselotna hizbe kirstianun beyesebeka gubaiewna benseha abatoch bekule hulume betselotna Yechegrochachenen meftehe ke Egisiabehere meteyeke Yasefelgal
    'በርትተን እየጸለይን እንትጋ ….የእግዚአብሔርንም እጅ እንጠብቅ'

    ReplyDelete
  4. ክብርና ምስጋና ለእግአብሔር ይሁን "አሜን፡

    ReplyDelete
  5. gena bizu resa yilekimal,yenekawu eko yekidusan amlak yehonewun geta new yersu mewugia degimo enbi lalut eskemechershawu yemiyatefachewu new!

    ReplyDelete
  6. kesew bititala tunchahin temekiteh new ke egziabher gar sitital gin min yizeh ne "egziabher hyal new" ato melles mejemeria sewn naku ahun degmo egziabherin beiwnet kehone egziabherin niko kidist bhagre ethiopian memret aytasebm awedadekachihu yekefa new yemihonew.

    ReplyDelete
  7. Dear Andadregen Egziabhere Yestachu teru melkam zena new , Hulachinim Beselot
    Entiga Egziabhere Bizu Yasayenal.

    ReplyDelete
  8. ወይኔ ልቤ ፈራ ..... የኢትዮጵያ መጨረሻ ምን ይሆን???? መካሰሳችንን ትተን ሁላችንም ንሥሀ እንግባ. የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ መምጫው የደረሰ ሁሉ መሰለኝ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወይኔ ልቤ ፈራ ..... የኢትዮጵያ መጨረሻ ምን ይሆን???? መካሰሳችንን ትተን ሁላችንም ንሥሀ እንግባ. የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ መምጫው የደረሰ ሁሉ መሰለኝ

      Delete
    2. ወይኔ ልቤ ፈራ ..... የኢትዮጵያ መጨረሻ ምን ይሆን???? መካሰሳችንን ትተን ሁላችንም ንሥሀ እንግባ. የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ መምጫው የደረሰ ሁሉ መሰለኝ

      Delete
  9. ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን ዝም ብሎ ይመልከት ተብሎ ተጽፏልና ይህ ይሆን ዘንድ በእምነት መነፅር ማየት ትልቁ ጉዳይ ነው!

    ReplyDelete
  10. የእግዚአብሄርን ደግነት እንደ ሞኝነት አይቁጠሩ!!!
    እኛ ዝም ብንል የእስራዔል አምላክ እግዚአብሄር ዝም አይልም :

    እግዚአብሄር ርስቱን ይተብቅልን ::
    አሜን አሜን አሜን!!!

    ReplyDelete
  11. ትጉሁ ወጸልዩ ከመ ይትባሁ ውስተ መንሱት!!

    ReplyDelete
  12. zare resa yelekema nege degemo ye enesu resa yelekemal

    ReplyDelete
  13. ንሴብወ ለእግዚአብሔር

    ReplyDelete
  14. ገና ምን አይታቹ ድንግል እኮ ከኛ ጋር ናት

    ReplyDelete
  15. egziabher amlak libonachewun yimelislin

    ReplyDelete
  16. ዓፅም በክብር ተነስቶ ልማት መሰራቱ ምን ጉዳት አለው በህይወት ያለው መጠቀሙስ ከሞተው ይለቅ?

    ReplyDelete
    Replies
    1. mene lemalete felegehe/she newe?

      Delete
    2. awo men malet felgeshe or felgeh new????????? embat lebeshen or lebehn taberalh/she

      Delete
    3. ayshalihim minalebet bitilina andegnahin ketehadiso gora beteselef yishalihal maninm yetewahido yehone lij lebetekrstian bemekorkor yabatochen rist yilal enji endet minalebet tilaleh ebakihen tinishim bihone hasabihin geta argena asbebet . yabatoch atsem tenestonew ye ethiopia hizb yesekuar timun yemikortew lenegru kalus endhi yil yele
      ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
      2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥
      3 ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
      4 ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
      5 የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።
      6-7 ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትንም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።
      8 ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።
      9 ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።
      10 አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤
      11 በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።
      12 በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።
      13 ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።
      14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤
      15 ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
      16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

      Delete
    4. Ante demo wegegna neh. Ahun man yimut lehager limat minamin asebeh new? Neger gin you are not Orthodox Christian. So nothing important is expected from you.

      Delete
    5. Bekumih yemotk!

      Delete
  17. sew mote bilo medeset min yibalal ?yemiseraw limat lehager lewgen yemireda bemehonu min kifu neger alew ? ethiopia diha hegar nat sewm sira yelewim dirjtu wede lela hager alhedem Gezeb wede Bank Mahibere Kidusan 4 Kilo Beullding Geneba Abune Pawlos 4 Palas Aseru yihi lehagerna lewegen yakoral ahunim weyane Genzebun wede sira keqeyere melkam neger yimeslegal siseru atisiru malet mikeginet yimeslal

    ReplyDelete
    Replies
    1. Mehibere Kidusan hone Abune Pawlos beseru betegebew bota new yehe gen minem ketseru egig betam tilek behonem yebetekerstian bota lay tegebe ayedelem alen engi lematu tikekel ayedelem altebalem. Kaltefa bota lemen waldibba?

      Delete
  18. dengel hoy kemchawem geza belay erdatashen... tsloteshen.. meljashen enfelgalen atelyen

    ReplyDelete
  19. Selfu ye Egziabher new, Egziabher degmo ashenafi new, silezi Waldiban endemitadeg enamnalen

    ReplyDelete
  20. Selfu ye Egziabher new. Egziabher degmo hule ashenafi new. ye abatochachin amlak Waldiban yitadegal.

    ReplyDelete
  21. ዋልድባን ነክቶ የሰላም አየር መተንፈስ የለም!!!

    ReplyDelete
  22. ጌታ ና እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ እናንተ አይደሉም ፍፁም አትመስሉዋቸውም

    ReplyDelete
  23. በእውነትዋልድባን ነክቶ የሰላም አየር መተንፈስ የለም !!!!
    የአባ ሳሙኤል አመላክ ዝም አይልምና፡፡

    ReplyDelete
  24. ይህ በዓለም የሚታየው ነገር ሁሉ ሊሆን ግድ ነው ፡፡ የነበረው፣ ያለው እና የሚኖረው አልፋና ኦሜጋ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላከ ቅዱሳን፣ ክቡራን፣ ንዑዳንና ብፁዓን እግዚአብሔር የሚያደርገውን ሁሉን ያውቃልና መሰዳደቡን፣ ጥላቻውን፣ በሰው ሞት መደሠቱን፣ ወሬ ማናፈሱን፣ የሰውን ስሜት በክፉ መፈተኑን ትተን የአምላክን ሥራ (እንቅልፍ የሌለበትን ትጉህ እረኛ) በትዕግሥት እንጠብቅ!! እርሱ የቅዱሳኑን ሥፍራ ለክፉ ነገር አያውልም፡፡ እኛ በእምነት ያለን ሰዎች በፀሎት እንትጋ፡፡ ምናልባት የሕዝቡን ስሜት / ደም / በክፉ ኃሣብና ሥራ ለማሞቅ የሚፈልጉ ሰዎች ከዚህ ድርጊታቸው ቢቆጠቡ መልካም ነው፡፡ ምነው የጣልያን ወረራን፣ የነ ግራኝ መሐመድንና የነ ዮዲት ጉዲትን ታሪክ ብናወሳ በፀሎት መሰለኝ እኮ አገራችን የእግዚአብሔርን እርዳታ ያገኘችው እንጂ የትኛው የመሣሪያ ብዛት እና ሥልጣኔዋ ነው ለማንኛውም በቅድሥት ሥላሴ የምታምን ዜጋ ሁሉ ወደ ራስህ ተመልከት እና አንድ አቡነ ዘበሰማያት ድገም ይህ መሰለኝ የሚሻለሁ፡፡ ለሁላችንም ልቡና ይስጠን፤፤፤

    ReplyDelete
  25. በዳላስ ያለነውን የተዋህዶ ልጆች በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር እያመለከ ያለውን ህዝብ የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት አንድ ቄስ አንዳንድ የማህበሩን አባላትን ይዘው የራሳቸውን ርካሽ ጥም ለማርካት ለመሳሪያነት ዘርና ፖለቲካ እያራገቡ ቤተክርስቲያናችንን ሊከፍሉ ህዝቡን ሊለያዩ ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. Can you talk something that makes sense. This is non sense. So please follow what is being said. We know that you are trying to divert people's attention on this issue. It is not acceptable. We will talk about mahibere kidusan on its own title, time and place. Now the issue is about WALDEBA, if you understand.

      Delete
  26. (ke Egziyabeher gar yemitalu ydekalu) ehil labedere afer work labedere teter. Andand yemikawomu sewochin enditimeleketu eleminachiwalew endenezy yalu sewoch legeza wodachew enigi leamelakachew aygezoom yilal metsaf kedus manim bekawm mekisefitun yayewal

    ReplyDelete
  27. Ewunet Ethiopia yale betecrstian Hager nech? yeteresaw yhe new :ende Adwa yimeskr egziabher mastewalun yisten

    ReplyDelete
    Replies
    1. woyane eysra yalew be waldeba lay ye mayrsa guday new, Tarik yeferdew,,,,,,, ehe hulu ye Tigrayn hizb klelaw wogeno gar ebdaynor new ,,,

      Delete
  28. You guys you had better on other burning issues ratherthan discussing this kind of triky mirky kind teret

    ReplyDelete
    Replies
    1. You yourself tirkimirki!One day you will understand what you said and confess for what you said or you will be punished for what you said. Oh trust me!Not kidding.

      Delete
  29. ህያዋንን ትታችሁ ስለ ሙታን የምታወሩ ምናለበት ሰለ እምነት እኩልነትና መቻቻል ብትሰብኩ! የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ስለጠፋችሁ አይመስለኝም የተደበቀና ስውር ፖሌቲካዊ አላማ ስላላቸሁ ነው! እባካችሁ ራሳቸሁን ከፖለቲካ አፅድታችሁ እምነታችሁን ከማጠንከር ይልቅ ምእመኑን ሜዳ ላይ ትታችሁ ለነጣቂ ተኩላ አሳልፋችሁ ሰጣችሁት!

    ReplyDelete
    Replies
    1. yema menafeqe nehe..tekula yepolitica alamahene yezehe weta!!!tekula

      Delete
  30. EGEZEHABEHAR BATUN YETABEK

    ReplyDelete
  31. I've read what u all wrote. From what i can see, this is 1 of the many reasons why God himself is paying us back in full for what we've forwarded. Asteyayetu lay and mehon yakaten endet lehaymanotachen mekom enchelalen? Andandu sew comment yaderegew ewnetm tekula neh yemiyasbel new. Fikir atan, genzeb wededn, Ethiopia yetsenachew be kiristina emnet mehonun eresanew, mot yelele asmeselnew, cherash blen blen amlak dejaf regten nibretun linkemaw ashan. Tadiya endet aykotan? Tadiya endet ayketsfen.
    Ene bebekule yemasbew, mengist kalataw bota waldeba hedo fabrica lisra yemilew bota ato sayhon tenbitu yifetsem zend new.
    Tenbitun maskeret anchelm but atleast gudatun or the degree of sufferingun mekenes enchelalen.
    Keminim belay gin egziabher tsinatun, bertatun yisten, nitsuh tselote helina yisten. Yetseleynat tselot andituam meret satker ESKE tsebaot tidreslen, AMEN!

    ReplyDelete
  32. meche yehon ye torent negarit memetat yemetakomut?

    ReplyDelete