Friday, April 20, 2012

‹‹ደርግ VS ኢህአዴግ ›› የቤተክርስትያን ፈተና


ይህን ጽሁፍ ስታነቡ
‹‹አንድ አድርገን›› ብሎግ ኢትዮጵያ ውስጥ ይሰራል ማለት አይደለም  ፤ መረጃም ከናንተ ዘንድ ለማድረስ የሚገታን አንዳች ነገር ፤ የለም የምንጽፈው ጽሁፍ የምናስተላልፈው መረጃ ሰዎች ዘንድ እንዳይደርስ ተደርጓል

 
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 16 ፤ 2004 ዓ.ም )፡- የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ክብር ባህል እምነትና ስርዓት መንግስትና ቋንቋ ያቋቋመች የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ከሔኖክ ፤ ከኖህ ፤ ከመልከ ጼዴቅ ከነብያትና ከሀዋርያት ተላለፈውን ትምህርት ስርዓት ፤ እምነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ የኖረች በማስተላለፍ ላይ ያለች ፎኖተ ህይወት መሆኗ የተረጋጠ ነው፡፡ ቅዱሳን አበውን ፤ ኃያላን ነገስታትን ፤ ልዑላን መሳፍንትን ፤ ክቡራን መኳንንትን ፤ ዐይናሞች ሊቃውንትን በስጋ በነፍስ ወልዳ ያሳደገች ፤ የሌላ የማትፈልግ የራሷ የማትለቅ ዕጥፍ እናት ፤ ስንዱ እመቤት ናት፡፡

በቅዱስ መጽሀፍ ስለ ቅድስናዋ እግዚአብሔር ደጋግሞ የመሰከረላት አገራችን ኢትዮጵያም ቅድስት ክብርት ሐገር ናት ፡፡ ሰይጣን በእባብ አድሮ አዳምንና ሔዋንን እንደተዋጋቸው ሁሉ በልዩ ልዩ ሥጋውያንና መንፈሳውያን የውጭ ጠላቶች አድሮ ኢትዮጵያን ሲዋጋ ኖሯል፡፡  ዛሬም በመዋጋት ላይ ነው ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትጥቋን አጥብቃ ከቆመች ሳታርፍ ፤ ከዘረጋች ሳታጥፍ በኖረችበት ዘመን ሁሉ ኢትዮጵያ ሳትደፈር ኖራለች፡፡ በ10ኛው መቶ ዓመት የጉዲት ወረራ ፤ የ16ኛው መቶ ዓመት የግራኝ ወረራ ፤ ከ17ኛው እስከ 20ኛው መቶ ዓመት ተደጋግሞ የደረሰው የካቶሊክ ፤ የፕሮቴስታንት ፤ የቱርክና የግብጽ እስላማዊ ወረራ ተደጋግሞ የከሸፈው ባልተበረዘውና ባልተከለሰው የኢትዮጵያ  ቤተክርስትያን  የእምነት ኃይል ነው፡፡ የአምስት ዓመት የፋሽስት ወረራም ጉዳት ማድረሱ የታወቀ ቢሆንም ከስሩ የተነቀለው ፤ ቁጥቋጦው የተመለመለ ፤ እንደ አንበጣ በዝቶ የመጣው የፋሽስት ሰራዊትም የውሀ ሽታ ሆኖ የቀረው በኢትዮጵያ ቤተክርስትያን የእምነት ኃይልና በልጆቿ ደም ነው፡፡

ዛሬ ሁሉ ባለ ሀገር ነኝ በማለት ለአገሪቱ ባለ ውለታ መስሎ ይታይ እንጂ ለ3000 ዓመታት ለኢትዮጵያ ቆማ የኖረች የሰላም ፋና የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ብቻ ናት፡፡ ታሪክን መለስ ብለን ስንመለከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሌላ ሃይማኖት ፤ ከኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ሌላ የሃይማት ክፍል ለመሻት ፤ ለመጠጋት ነገስታቱ ወይም ህዝቡ በሞከሩ ጊዜ ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣና ቅጣት አለ፡፡ ሲመለሱ ይመለሳል ፡፡ ይህም ዝንባሌ ከስጋዊ ወገን እንጂ ከኢትዮጵያ ቤተክርስትያን አበው በኩል የታየበት ጊዜ የለም፡፡
የነብያት ፤ የሐዋርያት እምነት ከተሰበከበት ጊዜ ጀምሮ በሐዋርያት ዘመንም ሆነ በተከታታዩ ዘመን በውጭ የታየውና የተነገረው የመናፍቃን ትምህርትና ግብር በኢትዮጵያ የታየበት ጊዜ የለም፡፡ ይልቁንም በ444 ዓመተ ምህረት በኬሌቄዶን በተደረገው ጉባኤ ምክንያት በውግዘት መለያየት ከተደረገ ወዲህ ኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ከሮምና ከቁስጥንጥንያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳታደርግ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ኖራለች፡፡

በዚህ ዘመን ሁሉ የአበው ስርዓት ሳይፈርስ ፤ ህጉም ውግዘቱም ሳይጣስ ተጠብቆ ኖሯል ፡፡ ልዩ ልዩ የሃይማት ተከታዮች የመንግስት መልዕክተኞች እየሆኑ ጠብ እየቀሰቀሱ ፤ ጦርነት እያስነሱ ቢፈታተኗም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን አበው ግን በመስቀልና በሰንደቅ አላማቸው ስር ሆነው ደማቸውን ሲያፈሱ ኖሩ እንጂ የመላላት ግንባር አላሳዩም፡፡ ከዚህም የተነሳ በ1928 ዓ.ም የዘመተው የፋሺስት ሰራዊት ኢትዮጵያን ሲዋጋ ስንቅና ትጥቁን አዘጋጅታ ባርካ ያዘመተችው የልዮን መንበር ስትሆን በዚህም ጦርነት ሁለቱ ታላላቅ አባቶች አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ሰማዕትነትን ሲቀበሉ ፤ በደብረ ሊባኖስ ፤ በዝቋላ ፤ በዲማ ፤በዋሸራና በሌሎች አብያተ ክርስትያን ብዙ ካህናትና ምዕመናን መስዋዕት ሆነዋል ፡፡ ይህም በጦር ሜዳና በአምስት ዓመት ሙሉ በየአቅጣጫው ከተደረገው ጦርነት ሌላ ነው፡፡
ይህ የቀደመ ታሪክ ነው ፤ ከ1967 ዓ.ም እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ በዘመነ ደርግ ያለውን ታውቁት ዘንድና አሁን ካለባት ፈተና እንድታውቁት ለመጻፍ ሞክሬአለሁኝ  ፤ መንግስታት ቤተክርስትያን ላይ ያደረሱትን መከራ መጻፍ ፖለቲከኛ ሊያስብል አይገባም ፤ በደርግ ሰዓት ህዝቡም መከራ ደርሶበታል ፤ ቤተክርስትያን ላይ የደረሰው ፈተና ግን ከባድ ነው ፤ ካላወቁ እንዲያውቁት እነዚህን ነጥቦች አንስቻለሁ
1.     ሁለተኛው ፓትርያርክ በውጭ ጠላቶች ቀስቃሽነት ፤ በቤተክርስትያን አንዳንድ አባሎች ተባባሪነት ከመንበር ወርደው ተገደሉ
2.    በመሀመድ ጋዳፊና በሊቢያ ጉባኤ ድጋፍ ‹‹ሃይማኖት አይለያየንም›› በሚል ቤተክርስትያንን ከጉልላቷ ከመስቀል ለይቶ ባዶ ራስ አድርጎ ከእስላም መስኪድ አገናኝቶ የተሳለ ምልክት ያለበት ወንጌልን የሚነቅፍና ቁራን የሚያቅፍ መጽሀፍ በቤተክርስትያን ታትሞ ተበተነ፡፡
3.    የኮሚኒስት ማኒፌስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስትያን ማተሚያ ቤት ታትሞ የተበተነ ሲሆን በዚሁ መሰረትነት የቤተክርስትያ ስብከት ፤ ወንጌልና ሶሻሊዝም አንድ ነው ፤ የኮሚኒስ ሥርዓት የሐዋርያት ስርዓት ነው በሚል መስመር  ተስፋፋ፡፡
4.    በ1970 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ‹‹ከሀገር ወዲያ ሀይማት የለም›› በሚል አርእስትና ‹‹ብቸኛው ፓትርያርክ›› በሚል አርእስት ለኢትዮጵያ በአብዮቱ የተጠመቁ ጳጳሳት ያስፈልጓታል በሚል አስተያየት የያዘ ‹‹ዜና ቤተክርስትያን›› በተከታታይ ከታተመ በኋላ ፤ ጥቅምት 14 ቀን 1971 ዓ.ም የአዲስ አበባ አድባራና ገዳማት አስዳሪዎች ፤ ቀሳውስትና ዲያቆናት ፤ መዘምራንና ማህበረ ምእመና ፤ በጊዜው የነበሩት ሶስተኛው ፓትርያርክ በተገኙበት ‹‹ አሮጊይቱ ቤተክርስትያን ትውደም ! አሮጌ ሲኖዶስ ይውደም ! ሲኖዶስ ቅዱስ አይባልም !›› በሚል መፈክር በስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከተሰማ በኋላ የፊተኞቹ አበው ጳጳሳት በጡረታ ተገለው ሲኖዶስ ፈረሰ፡፡ ጥር 13 ቀን 1973 ዓ.ም አዲስ ሲኖዶስ ተመሰረተ፡፡
5.    ቤተክርስትያኒቱ ለኮሚኒስት ስርዓት የጀርባ አጥንት ሆና ከመገኝቷ የተነሳ እንኳን መዘምራኑ ፤ ዲያቆናቱ ፤ ቀሳውስቱና መነኮሳቱ ሳይቀሩ የቀበሌ ሊቃነ መናብርት  ፤ አብዮት ጥበቃ ሰራዊት ፤ የሸንጎ አባል በመሆን የክርስቶስንና የሰውን ደም አንድ ላይ ሲቀዱ ኖረዋል ፤ በጠቅላይ  ቤተክህነት የኮሚኒስቶች ድርጅት ተቋቁሞ ሲያራምደው የኖረው ሥርአት በአቶ መኮንን ታደሰ የመኢሰማ ሊቀ መንበርነት በ1970 ዓ.ም በኮሚኒስት ሰንደቅ አላማ የቤተክህነት ግቢ አስጊጦ ደም ለማፍሰስ ተዘጋጅቶ የነበረው የአመጻ ዝግጅት እግዚአብሔር ባያበርደው ኖሮ ውጤቱ አሳዛኝ በሆነ ነበር፡፡ ነገር ግን ያን ኃያል እግዚአብሔር ባወቀ ስለ ሻረው ብዙዎች ቢጨፈጨፉም ስር ሳይሰድ ተነቅሎ ቀርቷል፡፡ ለዚያ የአመጽ መንግስት የቤተክርስትያን አባሎች ባደረጉት ድጋፍ የሀይማኖት እኩልነት ከመደገፋቸውም በላይ መስቀል ለጨረታ ቀርቧል ፤ በእናት ሀገር ጥሪ ምክንያት ጾም ተሽሮ ስጋ እንዲበላ ሲደረግ  የቤተክርስትያኒቱ መሪዎችም እየባረኩ በልተዋል፡፡ ‹‹በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ›› በማለት ፈንታ ‹‹በስመ ሌሊን ወማርክስ ወኤግልስ›› ብንል ምናለበት ? ይቤ ማቴዎስ ፤ ይቤ ማርቆስ የሚባል ከሆነ ይቤ ሌኒን ማርክስ ፤ ይቤ ኤንግልስ ብንል ምናለበት  በማለት ሁሉም ነገሮች በስላቅ ተከናውነዋል
6.    በከፍተኛ የቤተክርስትያኒቱ አባላት ሳይቀር የኮሚኒስት ደብተር የተያዘበት ጊዜም ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ ከልዩ ልዩ ሀይማኖቶች ክፍሎች ጋር በአፍሪቃ አዳራሽ ሳይቀር የአንድነት ስብሰባ ተደርጓል፡፡ በዚህም ጊዜ ሁሉ ከቤተክርስትያኒቱ መልእክተኞች ለሌሎች ‹‹ወንድሞቻን›› የሚል ቃል ሲቀርብ ከሌሎች ግን መልስ አልነበረም፡፡
7.    ኢትዮጵያ ጠብቃው የኖረችውትምህርተ ሀይማኖት በአበው ተጠብቆ የኖረውን ያህል ፤ ቃሉ ተለውጦ  እምነቱ ተናውጦ  መሰረቱ ፈርሶ በኑፋቄ ጠባይ ተዘጋጅቶ የቀረበው መጽሀፍ ቅዱስ ‹‹በሲኖዶስ ታይቶ ተመርምሮ ተፈቅዷል››  የሚል መግለጫ ይዞ ወጣ ምእመናን በጊዜው  በታላቅ ችግር ላይ ነበሩ ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉ አቤት ባዮች አልጠፉም ፡፡ በተለይም የሊቃውንት ጉባኤ የተደጋገመ አቤቱታውን አቅርቧል፡፡ ግን ሰሚ አላገኝም ፡፡ ከዚህም ጋር ‹‹ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን መሰረተ እምነት›› ፤ ‹‹ ትምህርት መለኮት››፤ ‹‹የዋልድባ ታሪክ›› በሚሉ ስሞች የኢትዮጵያ ቤተክርስትያንን ትምህርት የሚቃረኑ መጻህፍት ታትመው ተበትነዋል፡፡ እነዚህም መጻህፍት ፤ ‹‹እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የውርስ ኃጥያት አለባት ›› ፤ ‹‹መንፈስ ቅዱስ አካሉ ዝውር ነው ፤ መለኮት በአካል ሶስት ነው፤›› የሚል ትምህርት የተሰራጨባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን አስር እጥፍ የሚሆኑ ነገሮችን መጥቀስ ይችላል ፤  የአሁን ፈተናችን ለናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው የሚሆነው ስለዚህ ባልጽፈውም በተግባር እያየቻሁት ስለመሆነ  ተገቢ አይደለም ፡፡ ያለንበትን ፈተና እየኖርንበት ስለሆነ ለመጻፍ አልወደድኩም፡ 




ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት ነገር ታሪክ ካለማወቅ ሊሆን ይችላል ብለን አንገምትም ፤ እባብም ባንሆን የዋሆችም አይደለንም ፤ እንደ እኔ ሀሳብ እኛ መቼ ፈተና አየንና ነው የምናማርረው ?  ፤ ያሳለፍነውን ፈተና ተመልክተን ዛሬ ላይ በርትተን ለራሳችን ለቤተሰባችን ፤ ለቤተክርስትያናችን ዘብ እንቁም

5 comments:

  1. Could you list all damage by Weyane, it looks as you are bowing for weyane

    ReplyDelete
  2. 'ለወንድሜ' ኤፍሬም:

    ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ!!!!!!!!!

    በመጀመሪያ ደረጃ ባሕር ማዶ በሞቀ ኑሮ ላይ ሁነህ እዚህ አገር ቤት ባለነው የሁሉም ችግር ገፈት ቀማሾች ብቻ ሳንሆን ጭልጥ አድርገን ጠጪዎች ላይ የስንፍና አንደበትህን ባትከፍት መልካም ይሆን ነበር:: የለም የመጻፍና የመናገር ሱስ አለብኝና ዝም ማለት ፈጽሞ አልችልም ያገሬና የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል ያንገበግበኛል ለማለት ከሆነ ግን 'ያልተነካ ግልግል ...ነውና' ዝም ብትልና የሚሆነውን ብትመለከት ወይም እንደገባው እውነተኛ የጌታ ተከታይ ብትጸልይ ይሻልህ ነበር:: ተርፈህ ታተርፋለህና::

    አዎ! በውጭ ሆነው ወይም በዳር ቆመው እርስበርሳችንን ሊያዋጉን የሚፈልጉ የአፍ ጀግኖች ሞልተውናል:: ታሪካችን ይህን በመሰሉ የድል አጥቢያ ባንዳ አርበኞች የተሞላ መሆኑን ያለፈው ተመክሯችን (በጣሊያን ጊዜ ሳይቀር) በሚገባ አስተምሮናልና ለአሁኑዎቹ አንተን መሰል ዳር ቋሚ እሳት ጫሪዎችና ለአንተ ለራስህ ግን ይህ ዓይነቱ አካሄድ አያዋጣችሁም ለአራችንና ለቤተ ክርስቲያናችንም አይጠቅምምና ዝም በሉ ወይም በል የሚል ምክሬን እለግስሃለሁ::

    ከዚህ በተረፈ ማን ምን እየሠራ ነው? ዓላማውስ ምንድነው? ወዘተ ለሚሉት በርካታ ጥያቄዎች መልስ ግን እንኳን አገርን እመራለሁ ለሚል መንግሥት ይቅርና ለእኛ በአገሪቱ ውስጥ የሚሆነውንና እየሆነብን ያለውን ለምናይ ኗሪ ምስክሮች ብቻ ሳይሆን ለእናንተም (በዓላማችሁ ታውራችሁ እንጂ) የተሰወረ አይደለም::

    ስለዚህ እባካህ 'ወንድሜ' ኤፍሬም ከመሰል የግብር ወንድሞችህ ጋር የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁና ለአገርና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም አስቡ ተነስታችሁም ፍሬ ያለውና የሚታይ ሥራ ለመሥራት ሞክሩ:: በተጋለጠ የማንነት ሥራችሁ ላይ እንደገና የማይመስልና የማይታመን ነገር በመጻፍ ደግማችሁ ደግማችሁ ሕዝብ ለማታለል አትሞክሩ ወይም ከተቻላችሁ ሌላ የማታለያ ስልት ቀይሱ:: ለእንደዚህ ያለ በሬ ወለድ ነገር ብርቱዎች ናችሁና::

    'እውነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠስም' እንዲሉ ስለ ማህበረ ቅዱሳንና ስለተሃድሶ ማንነት ለማዎቅ የሁለታችሁም የሥራ ፍሬ እየገለጣችሁ ስለሆነ ሚዛኑን በዚች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሆን ወደ ሰማይ ለምናነባ የቤተ ክርስቲያኒቷ ምእመን ተውት:: እንባን የሚያብስ የጌታ ቀን መገለጫው ቀርቧልና::

    'አመጸኛው ወደ ፊት ያምጽ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ
    ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደ ፊት
    ይቀደስ አለ::' (የዮሐንስ ራእይ 22:11)

    የሞጣው ጊዮርጊስ የቆሎ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በመላው ያገራችን አድባራትና ገዳማት ውስጥ 'በማህበረ ቅዱሳን' (ዲያቆን ሙሉጌታ ግብራቸውን ተመርኩዞ ያወጣላቸውና ለመጽሐፉ የሰጠው ማሀበረ ሰይጣን የሚለው ስም ይስማማኛል) የፈሰሰውና እየፈሰሰ ያለው የንጹህ ወገኖቻችን ደም አሁንም ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው አምላካችን በመጮህ ይጣራልና ወዮ! ወዮ!! ወዮ!!! ለኤፍሬምና ለመሰሎቹ::

    እግዚአብሔር አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችንን በመካከላችን ከሚገኙ ተናካሺ ውሾች ይጠብቅ!!!! አሜን::

    ሰላም ለሁላችን ይሁን!!

    በዚህ ጉዳይ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር የዘወትር ሙግት ያለኝ እና የሁሉንም ወገኖቼን እውነተኛ ሰማያዊ ፈውስ የምሻ እህታችሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ማፈሪያ ነገር ነህ

      Delete
    2. አንቺ ደደብ ዳቢሎስ ከዚህ ምን አመጣሽ? እንዳበደ ውሻ የምትጮሂበት አዳራሽ አለሽ አይድል እንዴ? በናትሽ ተኩላ መሆንሽን እናውቃለን!!! ከእግዚአብሔር ጋር የምሟገት ማለትሽ ትክክለኛ ዳቢሎስ መሆንሽን አሳወቅ። ሙግትሽ ግን ከንቱ ነው። ዳቢሎስ እግዚአብሔርን ቀርቶ በእግዚአብሔር የሚያምኑ ምዕምናንን ሊያሸንፍ አይችልምና!!!!!!

      Delete
    3. የእግዚአብሄርን ሰዎች መንካት እግዚአብሄርን እንደመዋጋት ይቆጠራልና እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጡትና ከእኩይ ተግባራችሁ ተመለሱ፣ይሄ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፣ የሀይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ዋልድባ ማለት የመንግስት ፕሮፖጋነዳ መንዣ ቦታ አይደለም እግዚአብሄር የሚከብርበት ቦታ ነው፡፡ሰው እንዴት ለሀገር ህልውና መሰረት የሆነን የፀሎትና የአምልኮ ቦታ ለማጥፋት ይነሳል!!! መንግስትን ተውት እኛ ግን በፀሎት እንትጋ፡፡

      Delete