Monday, April 16, 2012

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዋልድባን በማስመልከት ዛሬ ይተነፍሳሉ ተብሏል

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 9 2004 ዓ.ም)፡- ክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየጊዜው የመንግስታቸውን የስራ ክንውን እንደሚያቀርቡ ይታወቃል ፤ አብዛኛውን ጊዜ የሚቀርቡት ሪፖርቶች ወቅታዊ ነገሮችን የሚመለከቱ ናቸው ፤ ከወራት በፊት ስለተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሰረት አድርገው ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ሪፖርት ነበር (ስለ ኤርትራ ጉዳይ ፤ ስለ ባልደረባችን ‹‹ኑሮ ውድነት›› ፤ ስለ ነገ ህልማችን ትራንስፎርሜሽን …… etc) ፤ አሁን ባለንበት ጊዜ በርካታ አነጋጋሪ ነገሮች በሀገሪቱ ላይ ተከስተዋል የመጀመሪያው ቀድሞ የተጀመረው እንቅስቃሴ የሙስሊሞች ‹‹መጅሊስ ይውረድ ፤ ያልመረጥነው መጅሊስ እኛን አያስተዳድርም›› የሚል ሲሆን ነገሩ ለወራት ተንከባሎ ባለፈው የካቲት 26 የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አማካኝነት ጉዳዩን ለዘብ የሚያደርግ መልስ ተሰቷቸዋል ፤ መንግስት በሰጠው መልስ ‹‹ ህጋዊ መጅሊስ ለመምረጥ ጊዜ ይጠይቃል እና ጥያቄያችሁን ተቀብለናል ነገር ግን በትእግስት ጠብቁ››የሚል ነበር ፤ ትእግስት እስከ መች እንደሚያስቆይ ባናውቅም ፤

በዚህ ጉዳይ ‹‹መጅሊስ እኔን አይወክለኝም›› የሚል ቲሸርት የለበሱ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ ከተማ አካባቢ ባለ ጣቢያ በመታሰራቸው ሌሎች ከ20 የሚበልጡት ደግሞ ይህን ቲሸርት አድርገው በመምጣት ‹‹እኛንም እሰሩን›› ብለው ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ ሲቆሙ ፤ ነገሩን ለማብረድ በማለት የታሰሩትን ሰዎች ሊለቋቸው ችለዋል ፤ ይህ ጽሁፍ የከተማን ጸጥታ ከማበላሸት አኳያ ምን ያህል ሚና እንደሚጫወት አናውቅም ፤ ነገር ግን ጥያቄያቸውን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ ቢቻል ሰውም ባልተነሳሳ ነበር ፤ የጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጊዜው በረዘመ ቁጥር ያልታሰበ ችግር እንደሚያመጣ መንግስት የተገነዘበው አይመስለንም ፤ እነሱን በፌደራል ፖሊስ ሲሰግዱ ከቦ ከመጠበቅ ለጥያቄያቸው ተገቢ የሆነ መልስ በጊዜው መስጠት መልካም ነው እንላለን ፤ ጥያቄያቸው ሀገሪቱ የምትመራበትን ህገ መንግስት እስካልተጻረረ ድረስ መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን ፤(ለእነሱ የሚሰጠው መልስ እኛም ጥያቄያችን እንድናቀርብ በር ይከፍትልናል፡፡) ስለ እነርሱ እዚህ ጋር ገታ ላድርግ ፤

ቀጥሎም ሁለተኛው በሀገሪቱ ላይ የተከሰተው በቪኦኤ እና መሰል የውጭ የመገናኛ ብዙሐን ሽፋን ያገኝ ፤ በጠቅላይ ሚኒስትርና በፓትርያርኩ ቢሮ ጆሮ ዳባ የተባለው የዋልድባ ገዳም የስኳር ልማት አጀንዳ ነው ፤ ይህ ጉዳይ የገዳሙ አባቶች ገዳማችን ታርሷል ብለው ሲናገሩ የስኳር ሚኒስትሩ አቶ አባይ ጸሀዬ አልታረሰም ፤ ገዳሙ ጋር አልደረስንም ፤ ገዳሙ ቅዱስ ቦታ እንደሆነ እናውቃለን የተነሱት 27 አስከሬኖች ብቻ ናቸው(ስንቱ ቅዱሳን እንደሆኑ አምላክ ይወቀው እንጂ ያረሰው ዶዘር ሊያውቀው አይችልም) ብለዋል ፤ በጉዳዩ ላይ ቤተክህነቱ የላካቸው ሰዎች ክርስትያኑን አንገቱን የሚያስደፋ ሪፖርት አቅርበዋል ፤ ይህ ጉዳይ ይመለከተኛል ያለው የአማራው ብአዴን በጎንደር ከተማ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት እና የስኳር ሚኒስትሩ ባሉበት ትልቅ ስብሰባ ማድረጉ የሚታወቅ ነው ፤ ስብሰባውን ማድረግ በራሱ የሚያስመሰግናቸው ስራ ነው ፤ የህዝብን ጥያቄ እስከ አሁን መልስ ባይሰጡ ለመስማት መዘጋጀታቸው መልካም ነው ፤ ፕሬዝዳንቱ በጊዜው ‹‹እነ አቦይ ጸሀዬ የሚሰሩትን ስራ በቅርብ ሆነን የምንከታተለው ይሆናል›› ብለው ቃል ገብተው ነበር ፤ እስከ አሁን ድረስ ያደረጉትና የተራመዱት እርምጃ ባይኖርም ፤ ቀጥሎም ማህበረ ቅዱሳን ከመንግስት ፍቃድ በመውሰድ ጉዳዩን የሚመለከቱ አባላት ከቀናት በፊት ወደ ቦታው እንደሚንቀሳቀሱ መረጃ ነበር ፤ ቦታው ላይ የላካቸው ሰዎች ይሂዱ ፤ አይሂዱ ፤ ሄደው ይመለሱ ምንም የምናውቀው ነገር ባይኖርም ፤ በመሰረቱ ይህ ጉዳይ ትንሽ ከበድ ያለ ስለሆነ ነገሮች ሁሉ ሌላ አቅጣጫ ይዘው አላስፈላጊ እሰጣ ገባ ውስጥ ከመንግስት ጋር እንዳይፈጠር በአካሄዶች ሁሉ ጥንቃቄ የሚያስፈልግ ይመስለናል ፤ ቦታው ድረስ ሄዶ ፕሮጀክቱ ምን ቦታ ላይ እንደሚያርፍ ፤ ከገዳሙ ጋር ያለው ርቀት ፤ የወደፊት ስጋቶች ፤ በአካባቢው ላይ ይነሳሉ የተባሉት 18 አብያተክርስትያናት እና መሰል ነገሮችን ተመልክቶ ሚዛናዊ የሆነ ያዩትን እና የተመለከቱትን ነገር ማንንም ሳይፈሩ በተገቢ ሁኔታ ማስቀመጥ ጥሩ ነው የሚል እምነት አለን፡፡

የማይጸብሪ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በገዳሙ ተወክያለሁ ያሉት አባት ገዳሙ እንዳልወከላቸው ፤ መነኩሴም እንዳልሆኑ ጨምረው ገልጸው ነበር ፡፡ ቃለ ምልልሱን የሰጡት አባት ቆባቸውን ከመርካቶ ገዝተው እንዳላደረጉ ፤ ያመነኮሷቸው አባት የገዳሙ አበምኔት እንደሆኑ ፤ ይህ ጉዳይ ክርስትያን ስለሆንኩኝ ብቻ ይመለከተኛል ብለው ቃለ ምልልሱን እንዳደረጉ አስረድተዋል ፤ ኢቲቪም በጉዳዩ ላይ የስኳር ሚኒስትሩን በመጋበዝ ስለ ፕሮጀክቱ ገለጻ እንዲያደርጉ አድረጎ ነበር ፡፡ ገለጻው እውነታን መሰረት ያደረገ ባይሆን እንኳን ፤ ኢቲቪ በተጨማሪ ‹‹በሀይማኖትን ሽፋን አድርገው ያልተደረገን ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ተቃዋሚዎች እያዋሉት ይገኛሉ›› ብሎ የጉዳዩን መስመር በማስለወጥ ሌላ መንገድ እንዲይዝ አድርጎታል ፤

እኛ እስከ አሁን ድረስ ፖለቲከኛ ሰው ገዳም ሲገባ አላየንም ፤ የበፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትራቹ አሁን ላለው ሁለት ሲኖዶስ ተጠያቂ ሰው ፤ አቡነ ጳውሎስን ከምድረ አሜሪካ ያመጣ የነበሩትን አባት በኬንያ ለመሰደድ በር የከፈተ ፤ እምነት የለሽ ሆኖ ያጣላቸው ፤ መናፍቅ ሆኖ አባቶችን ለማስታረቅ የፈለገ ፤ 1984 ዓ.ም በሀረርጌ በደኖ ለተጨፈጨፉ ሰዎች በጊዜው ቀጥታ ትእዛዝ ያስተላለፈ ፤ የበርካታ ንጹሀን ሰዎች ደም እጁ ላይ ያለበት ፤ ስኳር በመላስ የተሳሳተው ፤ ኢቲቪ ላይ ‹‹ተመክሬ ተዘክሬ አልሰማ ብየ ነው›› ብሎ ቃሉን የሰጠው ሰው አቶ ታምራት ላይኔ ከእስር ሲፈታ ገዳም ሳይሆን መናፍቃን አዳራሽ ነው የገባው ፤ የእርሱን ጌታ ቦሌ አየር መንገድ አግኝቶት አሜሪካ ነው የወሰደው ፤ ቀንም ሆነ ለሊት ጨለማ በሆነ እስር ቤት ለሱ ብቻ ቀድሞ ከመንበሩ የተዋረደው ጌታ አናገረው ፤ እኛ ይህን ነው ይምናውቀው ፤ እርሱም ገዳም አልገባም …. ዋልድባ ፖለቲከኛ አታገኙም ፤ ዋልድባ ወንጌሉን የሚኖሩ አባቶች ብቻ ነው ያሉበት…..

የወረዳው አስተዳዳሪም ጉዳዩን ከፖለቲካ ጋር አቆራኝተው አስተያየታቸውን ለቪኦኤ ሰጥተዋል ፡፡ ይህ ሲገርመን የአሜሪካው አቡነ ፋኑኤል በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሁኔታው ግድ ባሏቸው ‹‹ተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉት ሰዎች ቤተክርስትያንን የማይወክሉ ናቸው›› ብለው ከሳቸው የማይጠበቅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ አሜሪካ ኢምባሲው ጽፈው ነበር፡፡

አሁን ከማይጸብሪ ወረዳ አስተዳዳሪ ጀምሮ ፤ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ፤ የስኳር ሚኒስትሩ የሁሉንም ቃል ሰምተናል ፤ የትግራይ ክልል በጉዳዩ ላይ አንዳች ነገር አለመተንፈሱ አስገርሞናል ፤ ጆሯችንም ወሬያቸውን ጠግቧል ፤ አሁን ከባለስልጣኖቻን ቀረ ብለን የምናስበው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ቃል ብቻ ነው ፤ ይህንን መሰረት በማድረግ ዛሬ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ይነሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ፤ ለምን ቢባል ህገመንግስቱ አንቀጽ 74 ቁጥር 11 ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣንና ተግባር ሲተነትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ፤ በመንግስት ስለተከናወኑ ተግባራት እና ስለ ወደፊት እቅዶች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየወቅቱ ሪፖርት ያቀርባል ›› ስለሚል ነው ፡፡

ብጹእ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አባታችን በየጊዜው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሪፖርት ለማድመጥ ከተመራጮች እኩል በፓርላማ መሰብሰቢያ ውስጥ በቴሌቪዥን መስኮት እናያቸዋለን ፤ አሁንም ቀጣይ ሪፖርት ለማድመጥ ደብዳቤ ደርሷቸዋል ፤ በሪፖርቱ ላይ አሁን ሀገሪቷ ያለችበት ሪፖርት ይቀርባል ይላል ፤ ይህም ሚስጥር አይደለም ፤ ደብዳቤው ባይናገርም የዋልድባ ጉዳይም ተነስቶ ይወያዩበታል ተብሏል ፤ ከመንግስት ጎን በመቆም በስብሰባው አዳራሽ በቴሌቪዥን መስኮት ይመለከቷቸዋል ፤ እሳቸውን ብቻ አይደሉም ሌሎች የሀይማኖት አባቶችንም በቦታው ይገኛሉ ፤ ከእሳቸው ጋር ብዙ ቦታ አብረው የሚሄዱ አባቶችም ይከተሏቸዋል ፤ በዋልድባው ጉዳይ አጨብጭበው ለመውጣት ተጠርተዋል ፤ የዛ ሰው ይበላችሁ ታያላችሁ ፤ ጠቅላይ ሚኒትሩ ቢሮ በክብር የመጣው የዋልድባ ገዳም አባቶች ጥያቄ በጊዜው መልስ ይሰጡበታል ፡፡

የሚነጋገሩበት ነገር የሙስሊሞችን ጥያቄ እንደተለመደው ‹‹የሀይማት ከአክራሪነትና የሀይማኖት አባቶች ሚና›› ጋር በማያያዝ ያነሱታል ፤ የእኛን የዋልድባ ገዳምን ጉዳይ ደግሞ ‹‹ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኝት ሲባል በሚሰራው ስራ መንግስት ምን እርምጃ እየወሰደ ነው ›› በማለት በጥያቄና መልስ መልክ ይሰሙታል ፡፡ ይህን ጥያቄ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገቢ የሆነ መልስ የሚጠብቅ ሰው የዋህ መሆን መቻል አለበት ፤ ነገሮችን ከሀይማኖት አኳያ ብቻ አይቶ የሚናደድ ካለ እንዳይናደድ ለመጠቆም ጭምር ነው ፤ መጀመሪያውኑ ቢሮ ድረስ መጥቶ ‹‹እናንተ ደፋሮች ይህን ጥያቄ ብላችሁ የአንድን ሀገር መሪ ልታነጋግሩ መጣቹ›› የተባሉት አባቶች ጥያቄያቸውን ሀገር ውስጥ ባሉ ጋዜጦች ፤ በቪኦኤ ፤ እና በአንዳንድ ድረ-ገጾች አማካኝነት ምዕመኑ ጋር አድርሰው ምክር ቤቱ በጥያቄ መልክ ቢያነሳው ከመጀመሪያው የተለየ ነገር መልስ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዳትጠብቁ ፡፡ ‹‹ሴትየዋ የባሌን ጸባይ የማውቀው እኔ ነኝ›› አለች አሉ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ‹‹ይህን ጉዳይ የፖለቲካ ጥቅም ጋር በማያያዝ የሚሰጡትን መልስ እስከ አሁን የሰማችሁትን ነገር ደግማችሁ ትሰሙታላችሁ ፤ በተጨማሪም እንደ ከዚ ቀደሙ የሀይማኖት ጉዳይ ሲነሳ አባቶች በምክር ቤቱ በእንግድነት ተጠርተው ለገዳማውያን አባቶች ያልተከፈተ ጆሯቸው የመንግስትን ሪፖርት ለማዳመጥ ይከፈታሉ ፤ እነርሱን በቀጣዩ ስብሰባ ላይ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው ተጠርተው የመንግስትንና የአባቶችን አቋም በአንድ ላይ ለማናደምጥበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ በምትሰሙት ነገር ላለመናደድ ራሳችሁን አዘጋጁ ፡፡

‹‹የአካባቢው ወረዳ አስተዳዳሪ በዋልድባ ገዳም ውስጥ የሚገኙ አብያተክርስትያናት ፕሮጀክቱ አይደርስባቸውም ነገር ግን ፕሮጀክቱ ጋር ግድብ ለመገደብ ስለሚያስቸግር 20ሺህ ሰዎች ፤ በርካታ የጤና ተቋማት ትምህርት ቤቶች እና መሰል ተቋማት ይነሳሉ እነሱ ውስጥ ደግሞ 18 አብያተክርስትያናት አሉ ፤ እነሱ ላይ አሁን የደረሰ ነገር የለም ወደፊት ከሲኖዶስ ጋር በመነጋገር የሚደረግ ነገር ነው ›› ብሎ ቃሉን ሰጥቷል ፤ ይህ ማለት ነገ ስለሚፈርሱ ቤተክርስትያናት ሲኖዶሱን ስብሰባ ጠርተው አጀንዳ ቀርጸው ይነጋገሩበታል ፤ ከዚያ በኋላ ከአባቶች አቅም የመንግስት ጉልበት ስለሚያይል ውጤቱ ምን እንደሚሆን እኛው እናውቀዋለን ፤ ስብሰባውንም መከታተል አያስፈልገንም ፤ እኛ ግን ምን እናድርግ ?

እስኪ ምን እንደሚሉ እንሰማለን

7 comments:

  1. wond tefa b etyopia
    lemen anemotem menor gin min yetekmal

    ReplyDelete
  2. Diabilose KESIRATU YEFETAL,BESEWOCHE LAEADRO ZARIE SEL WALEDIBA YINAGERAL.SINAGERE EGIZIABEHER YEKIDUSAN AMLAK TAMIRATUNE YASAYEN,AMEN ::

    ReplyDelete
  3. ዋሊ
    ገዳመ ዋሊ(ዋልድባ) በሚል ርዕስ
     ከገዳሙ አመሠራረት እስከ አሁን ያለውን ሁኔታ
     የገዳመ ዋልድባ ልዩ ልዩ ባሕርያትን (ገዳመ ዋልድባን ከሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት ልዩ የሚያደርገውን)
     በቅርቡ የተከሰተውን የስኳር ፋብሪካና ገዳማውያኑ አሁን ያሉበት እውነተኛ ሁኔታ እንዲሁም የመንግሥት አቋም
     ከመንግሥት/ከማየ ጸብሪ ወረዳ አስተዳደር፣ ከአማራ ክልል ብአዴን፣ ከስካር ፋብሪካው የበላይ ኃላፊ አቦይ ጸሐዬ፣ ከጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ(በቅርቡም ሚያዝያ 9 አካባቢ ለተዋካዮች ምክር ቤት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን)/፣ ከቤተክህነት/ ከሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፣ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በሊቀካህናቱ መሪነት የተሰጠውን መግለጫ፣ እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን የተላኩት አጣሪ ኮሚቴዎች ያጣሩትንና የዘገቡትን ምን እንደሚመስል፤ (ማኅበረ ቅዱሳን የማጣራቱን ሥራ ሰርቷል ወደፊት ዘገባ ያወጣል ተብሎ የሚጠበቀውን)
     ገዳሙ ለመንግስትና ለተለያዩ የቤተክህነት ቅርንጫፎች የጻፈውን ደብዳቤ
     በገዳመ ዋልድባ ውስጥ ስለሚገኙት የማኅበር ገዳማት(አብረንታንት፣ ዳልሽህ፣ ሰቋር)
     በአብረንታንት ገዳም ውስጥ ስለሚገኙት ቤተ ሚናስና ቤተ ጣዕማ፤ ትምህርታቸው፣ልዩነታቸው፣…. ምን እንደሚመስል
    ……..በቅርቡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይዤላችሁ እቀርባለሁ፡፡ ዋሊ

    ReplyDelete
    Replies
    1. egzieabhir yirdah

      Delete
    2. ጥቂት ቀናት ብላችሁን በዚያው የውኃ ሽታ እንዳትሆኑ አደራ!!!

      Delete
  4. በአንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት በኩል ያለው ድፍረት የተሞላበት አነጋገር በጣም ያሳፍራል፡፡ የመንግስትን አቋም የሚገልጥ ነው ብየም አላስብም፡፡
    በተቃራኒው ደግሞ ስለልማቱ በአግባቡ አስቦ የሚናገር ሰው አለመኖሩ ያሳዝናል፡፡ እኔ ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያኔ እሰጣለሁ፡፡ ልማቱም ቢሆን ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ እንዳይሆን እፈልጋለሁ፡፡ ቢሆንም ግን ለልማቱም ማሰብ እፈልጋለሁ፡፡-ግዴታየም ነው፡፡-እንደ ሃገር፡፡
    ስለዚህ ቀርቦ መወያየትና መፍትሄ መፈለግ እንጂ ሁልጊዜ ነገሮችን በማጧጧፍ መፍትሄ አይገኝም፡፡ የቤተ ክርሰቲያን አባቶችም ሁለቱንም ጽንፍ በማስታረቅ መናገር አለባቸው፡፡
    ማኅበረ ቅዱሳንም ቢሆን ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ረጋ ባለ መንፈስ በማሰብ ጥናቱን ማቅረብ አለበት፡፡ በፍጥነት ማውጣቱም እኔ መፍትሄ ነው ብየ አላምንም፡፡ መፍትሄ ማምጣት የማይችል ከሆነ እውነትን መነገር ጽድ ነው ብየ አላስብም፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለውና፡፡
    ውድ የተዋሕዶ ልጆች አሁንም ቤተ ክርስቲያን ተጠቃሚ የምትሆነው በውይይት ውስጥ በሚኖረው መግባባት ነው እንጂ በሰልፍ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን በጉልበት ማገዝ አንችልም፡፡ ማለቴ ጉልበት ከእርሱ በላይ ማንም የለምና፡፡ የሚሆነውን እኛ ማስቀረት ማምጣትም አይቻለንም፡፡ ገዳማውያኑ እንዳሉት ቤቱን እርሱ ይጠብቃል፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው በሚገባው መስመር ለቤተ ክርስቲያን መከራከርና ዘብ መቆም ነው፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. wijinbir lemin tifetrubinalachiw yehe yiohnal eyalachihu siders ansemawim endie ......... tenkuway nachiw meselegn????????

      Delete