Monday, April 2, 2012

እግረ መንገድ


(አንድ አድርገን መጋቢት 24 ዓ.ም)፡- ባለፈው ሳምንት በአንዱ ቀን ወደ ቅድስት ስላሴ 4ኪሎ ቤተክርስትያን አምርቼ ነበር ፤ ፊት ለፊት ላይ በስተ ግራ በኩል ሶስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ የአቡነ ተክለሃይማኖት ሀውልት በሸራ ተሸፍኖ ተመለከትኩኝ ፤ ጠጋ ስል ሁለት በእድሜ ጠና ያሉ አባቶች እንደ እኔው ሊሳለሙ የመጡ ቆም ብለው ስለ ሀውልቱ እያወሩ ደረስኩኝ ፤ አንደኛው አባት ‹‹ እኔ ዘወትር እዚህ ግቢ ስመጣ ይህን የአባታችን ሀውልት ሳይ ፤ እምነበረዱ ተፈነቃቅሎ ስመለከት  ውስጤ በጣም ያዝን ነበር ፤ የቤተክርስትያኑ አስተዳዳሪዎች ምን ነክቷቸው ነው ዝም ያሉት ? የሚል ሀሳብ ውስጤ ይመጣ ነበር ›› ብለው ሳይጨርሱ አብረዋቸው ያሉ እድሜአቸው ከ70 የዘለለ አባት ‹‹ እውነት ነው ቦሌ መድሀኒአለም ላይ በቁመተ ስጋ እያሉ ሀውልት ሲያቆሙ የእኝህ ደግ አባት ሀውልታቸው ሲፈርስ መመልከት መልካምም  አይደል ፤ ውስጥን ያሳዝናል ፤ ክፉኛም ያስቆጫል  እንዴት ያሉ አባት ነበሩ እኮ ፤ በጾም በጸሎት የሚተጉ ለሀገርም ሆኖ ለቤተክርስትያን የሚጸልዩ አባት ነበሩ ፤ እኔ በቅርብ አውቃቸዋለሁ ፤ ጫማ እንኳን በእግራቸው ያጠለቁበት ጊዜ አልነበረም…..›› ብለው በሀሳብ ሁለት አስርት አመታትን ወደ ኋላ ነጎዱ ፡፡
እኔ ከመስማት ውጪ የእርጎ ዝምብ እንዳልሆን በመጠንቀቅ ዝምታን መርጫለሁ ፤ በህይወት ዘመናቸው ያከናወኗቸውን መልካም ስራዎች እያነሱ ብዙ ተጨዋወቱ ፤ የገዳም አባት ስለሆኑ ብር ራሱ በአግባቡ የሚለዩ አባት አልነበሩም ፤ መቶ ብር እና ሀምሳ ብር ያላቸውን ይዘት ቀለም መጠን መጀመሪያ አያውቋቸውም ነበር ፤ ምንስ ሊሰራላቸው ብር ? ፤ ስራቸው ጸሎት ጾም ብቻ ነበር ፤ ምግብ ብዙ አይመገቡም ነበር ፤ አብዝተው ይጾሙ እንደነበር አነሱ ፤ ፓትርያርክ ተብለው ሲሾሙ በእግር በፈረስ በብዙ ገዳማት ተፈልገው ታተው ነበር ፤ በጊዜው እሳቸውን እዚህ ቦታ ናቸው ያለ ሰውም ለማግኝትም አልተቻለም ፤ የእግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነውና እሳቸው ራሳቸው በገጠር ያለን አንድ ቤተክርስትያን ለማቋቋም ፈልገው ወደ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተክህነት ለማስፈቀድ እና ጽላት ለማስባረክ ሲመጡ ነው አግኝተዋቸው ፓትርያርክ ያደረጓቸው፡፡ እኔም በሰማሁት ነገር ተገርሜ አደመጥኩ ፤ ስለ እኝህ አባት ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ ፤ በዓይኔ እሳቸውን ለማየት ባልታደልም ፤ ከአሁኑ ጊዜ ጋርም ለማወዳደር ለማነጻጸር ፈልጌ ነበር ፤ 300 ሺህ እስከ 500 ሺህ እንደ ካርዲናል አባ ሰረቀ ጳጳስ ለመሆን ያቀረቡት እጅ መንሻም በአእምሮዬ መጥቶ ነበር ፤  ስጋውያንና መንፈሳውያንን ማወዳደሪያ መስፈርት ሳይኖር ለማወዳደር መሞከር ከስህተት መውደቅ ስለሆነ  ግን ለምን? ብዬ ራሴን በመጠየቅ ማነጻጸሬን ተውኩት ፡፡

በስተመጨረሻ አንደኛው አባት ‹‹ይህንን መልካም ስራ አስበው ለማደስ መሞከራቸው የሚያስመሰግናቸው ስራ  ነው ፤ ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ነገሮች የሰበካ ጉባኤውን ፤ የቤተክርስትያኒቱን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ገፅታ ስለሚያበላሽ ታይቶ መታለፍ የሌለበት ነገር ነው ›› ብለው ተናገሩ፡፡ እኔም ለብሎግ ተመልካቾች ሁኔታው ቢያዩት መልካም ነው ብዬ በማሰብ በካሜራዬ የማደስ ተግባሩን ማስቀረት ቻልኩ፡፡


ምናለ እግዚአብሔር ልቦና ሰቷቸው ቦሌ ላይ የቆመውን ጣኦት ቢያፈርሱት ፤ ይህ ጣኦት  የቤተክርስትያኒቷን  ገጽታ ከማበላሸት አኳያ ትልቁን ቦታ ይይዛል ፤ እኛን የማይወክለንና የማይገልጸን ነገር መሀል ከተማ ላይ ሲቀመጥ ስማችንን የማንም አፍ ውስጥ እንደ ማስቲካ እንዲላመጥ በር ይከፍታል ፤ ቤተክርስያኒቷ በአንድ አባት አቋም ስትብጠለጠል እስከመቼ ትቆያለች ? እነዚህ ሁለት አዛውንቶች በሁኔታው በጣም አዝነዋል ፤ ነገር ግን ውስጣቸው እያዘነ ፤ ውስጣቸው እየተቃጠለ በዚች አጋጣሚ እርስ በእርስ ሲነጋገሩ  ውስጣቸውን ለመመልከት ችያለሁኝ ፤ የሁሉም ክርስትያን ውስጡ ከዚህ የተለየ ነገር አይሆንም ፤ 




11 comments:

  1. በረከታቸው ይደርብን!

    ReplyDelete
  2. የሀይማኖት ጸር በተባለው ደርግ ዘመን እንዲህ አይነት የተቀደሱ አባት ነበሩ በአሁኑ የሃይማኖት ነጻነት አለበት በተባለበት ዘመን ደሞ.....አቤቱ አምላክ ሆይ አስበን

    ReplyDelete
  3. selam andadrigenoch, email addrashachehun endet new magegnet yemichalew.

    ReplyDelete
  4. ሰላም ለነገሩማ የማርክስ ኤንገልስ ሌኒን ምስልና ሐውልት ደርግ ሲወርድ አብረው ወድቀዋል ............ታድያ

    ReplyDelete
  5. Your articles are VERY interesting, but I cant read it, please change to PDF so we can all read what you are writing.

    ReplyDelete
  6. andadirgen tilalachu. Gin mechem andi atihonum. Poletikana haymanot tetamro yetim ayadersenim. wede andu tewesenu !

    ReplyDelete
  7. አባታችን፡በእውነት፡ትልቅ፡አባት፡ነበሩ፡፡ቢሆንም፡በእምነታችን፡ሐውልት፡ማቆም፡ክልክል፡ነው፡፡ስዕል፡ነው፡የሚፈቀደው፡፡እሳቸውም፡ቢሆኑ፡እንዲቆምላቸው፡የሚፈልጉ፡አይመስለኝም፡፡ይሄ፡ጊዜ፡ያመጣው፡የካቶሊኮች፡ሴራ፡ነው፡፡አቡነ፡ጳውሎስም፡ቢሆኑ፡በካቶሊክነታቸው፡ነው፡ያስቆሙት፡፡በመንበረ፡ፀባኦት፡ቅድስት፡ስላሴ፣በቅድስት፡ማርያም(አራት፡ኪሎ)፡እና፡በሌሎችም፡ያሉትን፡ለማስነሳት፡መጣር፡ነው፡እንጂ፡ማደስም፡ሆነ፡አዲስ፡ማቆም፡ተገቢ፡አይመስለኝም፡፡
    የአባታችን፡በረከት፡ይደርብን!!!

    ReplyDelete
  8. why? we are say stop! aba pawlos. because he is not committed our church he is not good Shepperd. pleas why we are discus change our (melkam yalhonu abat). by the way when and how change patriarch in our church rule(kenona). pleas start discussion with your blog about stop! stop! stop! this is enough (atfru "firhat atsiat new")

    ReplyDelete
  9. thanks for the informetion. please God protect our church and religon.

    ReplyDelete
  10. Aba pawlos kegnehe abate mene yemaru yehone libona yesetachwe ye Egziabhere Endrase sayehonu esachwe ye TPLF wtadre nachwe lmeine betekrestiyanachinene aylkulenme yesirachwene yesetachwe laba pawlos. ABATACHINE ABUNE TEKLHAMANOTE GINE BREKETACHWE YEDREBINE!!!

    ReplyDelete