Friday, February 28, 2014

የዘመናችን የአርዮሳውያን ግብር

(አንድ አድርገን የካቲት 21 2006 ዓ.ም)፡-ኦልማን የተባለ የታሪክ ፀሃፊ 379 በቁስጥንጥንያ የነበረውን የሃይማኖት ሁኔታ እንደሚከተለው ገልፆት ነበር፡፡
‹‹ ሃይማኖታዊ ጉዳይ እንደማንኛውም ተራ ወሬ ስራ መፍቻና የቀልድና የመዝናኛ ጉዳይ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡ ቲያትር ቤት ውስጥ የነበረው ሁኔታ ወደ ቤተክርስቲያን መጣ የቤተክርስቲያን ብቸኛ ሃብት ተደርጎ ይታይ የነበረው ጉዳይ ወደ ቲያትር ቤት አዳራሽ ተወሰደ በአንድ ወቅት የተሻለ ክርስቲያናዊ ትርጉም ይሰጠው የነበረና ወደ ቀልድ መድረኮች የማይመጣው የቤተክርስቲያን ምስጢር በአደባባይ የብዙዎች መዘባበቻ ከንፈር መምጠጫ ሆነ፡፡ 

በቁስጥንጥንያ መንበር ላይ የተቀመጡት አርዮሳውያን መሪዎች ይህ እንዲሆን የሚያበረታቱ ሃይማኖትም ጉዳይ ደንታ ቢሶች ነበሩ፡፡ የቤተ ክርስቲያን የነበረውን ህዝብ ታላቅ ከበሬታ ይሰጠው የነበረውን ጉባኤ አቃለሉት ናቁት ነዋሪዋቹም እውነተኛ የነበረውን ነገር እርቃኑን አስቀሩት ቅዱስ የነበረው አለማዊ በሆኑ ሰዋች ከንፈር ተቃለለ ከዚህ ሁሉ በጣም የከፋው ሊቆጣጠሩት ያልቻሉት ቤተክርስቲያንን ማቃለልና መዘባበቻ ማድረግ ሰዋቹን ደስታ የሚሰጣቸው ነገር ሆነ ደስታ ብለው በቆጠሩት ነገር ላይ ጊዜያቸውን ማባከን ተያያዙት ቤተክርስቲያንን ወደ ቲያትር መድረክነት ሰባኪወቻቸውንም ወደ አክተርነት ለወጧቸው፡ ሕዝቡንም ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው በአዳራሽ እንዲሰበሰብና የቀደመ ማንነቱን ቀስ በቀስ እንዲረሳ አደረጉት ተሳካላቸውም፡፡ 

Monday, February 24, 2014

ወላይታ ሶዶና አቶ በጋሻው ደሳለኝ


(አንድ አድርገን የካቲት 18 2006 ዓ.ም)፡- በወላይታ ሶዶ  ኦቶና ደ/ጽ/ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከጥር 23-25 በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ አቶ በጋሻዉ ደሳለኝ የተናገራቸው ነገሮች ብዙዎችን ያስገረመ ከመሆኑ በላይም አሁንም በሌላ የምንፍቅና ክንፍና በልዩ አስተምህሮ መመለሱን ማመስከር ችሏል፡፡ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን የወጣ በዜማ የታጀበና የረዘመ ‹‹አሜን›› አባባልም ለምዕመኑ አለማምደውት ታይቷል  ፤ ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው  ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው ፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ከ20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ  የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው ፤  ያ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡ ለዚህ እማኝ ይሆን ዘንድ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን በቦታው ላይ የተከናወነውን ነገር ይመልከቱ፡፡Click here

‹‹የአብነት ት/ቤቶችን ተቋማዊ ኹኔታ የተመለከቱ አጀንዳዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ በመኾናቸው በእነርሱ አንደራደርም››



(ፋክት የካቲት 15 2006 ዓ.ም )ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ላይ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተጣለው እገዳ በማኅበሩ ላይ ይደረጋል ለሚባለው ስልታዊ ጫና ማሳያ እንደኾነ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለፋክት መጽሔት ገለጹ፡፡
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚጠራቸው አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን የተመለከቱ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር መድረኮች ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ይኹንታ የተቋቋሙ የወጣት ማኅበራት አደረጃጀቶች የአክራሪዎች ምሽግ እንደኾኑ በግልጽ የሚቀርቡ ክሦች መኖራቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

Friday, February 21, 2014

ታጣቂ ፖሊስ የቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ የሚገባው እስከ መቼ ነው?


  •  የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ሲከናወን መስቀል ይዘው የሚመጡ ብጹአን አባቶች ትተው ፓትሮል ሙሉ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች  የሚጋብዙም የቤተክርስቲያን አስተዳደሮችን ተመልክተናል፡፡



(አንድ አድርን የካቲት 15 2006 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉት አብያተክርስቲያናት ውስጥ አስተዳደራዊ በደሎች እየበረከቱ ይገኛል፡፡ ማኅደረ ስብሐትልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፤ በተለምዶ አዲሱ ሚካኤል እና ግቢ ገብርኤል እና መሰል አብያተ ክርስቲያናት ስማቸው ከአስዳደራዊ በደል ጋር በየጊዜው ሲነሳ ይሰማል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአስተዳደር በደል እና መሰል ጥያቄዎች ጋር አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ስሟ እየተነሳ በየጊዜውም ሁከት እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ በቦታው በአሁኑ ሰዓት እጅግ በጣም ትልቅ እና ዘመን ተሻጋሪ ሕንጻ ቤተክርስቲያን እየተገነባ ይገኛል፡፡ ቦታው ላይ ያለ ምዕመንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ገንዘብ ያለው በገዘቡ ገንዘብ የሌለው በጉልበቱ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ እንዲያልቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ፤ በሳምንት አንድ ጊዜ በእለተ ሰንበት ከምዕመኑ ለሕንጻው ማሰሪያ የሚሆን ቢያንስ ከ15ሺህ ብር ያላነሰ  በአውደ ምህረት ላይ ይሰበሰብ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በዋነኝነት የቅድስት ማርያም ታቦት ሲኖር በተጨማሪ ደግሞ የቅዱስ ኡራኤልና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሀንስ ታቦቶች ይገኛሉ፡፡ በዚህ ቦታ ላይ በዓላት ሲከበሩ እጅግ ብዙ ብር ሲሰበሰብ በጆሯን ሰምተናል በአይናችን አይተናል፡፡ ነገር ግን የሚሰበሰበው ብር መዳረሻ በአሁኑ ወቅት ሕንጻው የሚገኝበት ሁኔታ እና በቦታው ላይ አለ ስለሚባለው አስተዳደራዊ ችግር ምዕመኑን ጥያቄ እንዲያነሳ አስገድዶታል፡፡


Wednesday, February 19, 2014

የእምነቱ ተከታዮች የበላን ሆዳችንን፣ የእምነት አባቶች የምታኩልን ጀርባችንን

ከሚካኤል ጎርባቾቭ
  •  ‹‹የበላኝ ሆዴን፤ የሚያኩት ጀርባዬን›› ሀገርኛ ብሂል
በሁለቱም አድራሻ እንገኛለን ይጎብኙን

(አንድ አድርገን የካቲት 12 2006 ዓ.ም)፡- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ ዕለት የካቲት 08/2006 ዓ.ም በድረ-ገጹ የዜና ዓምድና በፌስ ቡክ ገጹ ላይ “ቤተመንግሥቱን የከበበው መስቀል የሃይማኖት መሪዎቹን አነጋገረ” በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ ማስነበቡን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች በጽሑፉ ዙሪያ ተሰጡ፡፡  ከእነዚህም መካከል አዲሱ ፀጋው የተባለ ፌስ ቡከኛ እንዲህ የሚል አስተያየት ከጽሑፉ ሥር ለጠፈ አረፈው፡-

Addisu Tsegaw ለመላው ከኪራይ ሰብሳቢ ለጸዳ የህወሓት ታጋይና ለህወሓት ጀግና ዝባቸው ኩራት ለሆኑ የሴት ታጋዮች በሞላ እንኩዋን 39ኛው አመት የህወሓት በኣል አደረሰን! አብረሐት አብዱ በሙዚቃ እንደገለፀችው የህወሓት ድል ከሰማይ የወረደ አይደለም!ብዙ የደምና የህይወት ዋጋ የተከፈለበት ነው!ሀወሓት/አዴግ ወደፊት ይመርሻል!