Monday, February 24, 2014

‹‹የአብነት ት/ቤቶችን ተቋማዊ ኹኔታ የተመለከቱ አጀንዳዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ በመኾናቸው በእነርሱ አንደራደርም››



(ፋክት የካቲት 15 2006 ዓ.ም )ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ላይ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተጣለው እገዳ በማኅበሩ ላይ ይደረጋል ለሚባለው ስልታዊ ጫና ማሳያ እንደኾነ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለፋክት መጽሔት ገለጹ፡፡
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚጠራቸው አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን የተመለከቱ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር መድረኮች ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ይኹንታ የተቋቋሙ የወጣት ማኅበራት አደረጃጀቶች የአክራሪዎች ምሽግ እንደኾኑ በግልጽ የሚቀርቡ ክሦች መኖራቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካሏ በኾነው በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ መተዳደርያ ደንብ አጽድቃ የአገልግሎት ይኹንታ የሰጠችው ማኅበር ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ የኾነው ማኅበረ ቅዱሳን መኾኑን ምንጮቹ አረጋግጠው፣ ሚኒስቴሩ በዚህ ማኅበር ውስጥ መሽገዋል የሚላቸውንና ለይቶ የማይጠቅሳቸውን አካላት እየተጠቀመና ማኅበሩ ለፀረ ዴሞክራሲ ፍላጎቶች ከለላ እንደኾነ በመክሠሥ፣ ይኹንታ ከሰጡት የሃይማኖት አባቶች ጋራ ‹‹ውጦአችኋል፤ መቆጣጠር አልቻላችኹም፤ ከአቅማችኹ በላይ ኾኗል፤ መሥመር አላስገባችኋቸውም›› በሚል ፍጥጫ ውስጥ እንዲገባ ስልታዊ ጫና እተየፈጠረበት ነው ብለዋል፡፡
ማኅበሩ ከየካቲት 7 – 9 ቀን 2006 .. በግዮን ሆቴል፣ በብሔራዊ ሙዝየም አዳራሽ እና በኢትዮጵያ ባህል የስብሰባ ማእከል ያዘጋጀው ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ከቀትር በኋላ ፓትርያርኩ ለዋና ሥራ አስኪያጁ በጻፉት ደብዳቤ መታገዱ ተዘግቧል፡፡
በአሥራ አንደኛው ሰዓት የተጻፈው ደብዳቤ ለእግዱ የሰጠው ዋናው ምክንያት፣ ማኅበሩ የጉባኤውን መካሔድ ለሚመለከተው አካል ካለማሳወቅ ጋራ የተያያዘ ቢኾንም የማኅበሩ አመራሮች ጉባኤው በማኅበሩ ዓመታዊ ዕቅድ የተካተተና መምህራኑ የተጋበዙባቸው አህጉረ ስብከት ከአንድ ወር በፊት እንዲያውቁት ተደርጎ መምህራኑ በየአህጉረ ስብከቱ ዕውቅና ለጉባኤው የተጋበዙ መኾናቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡
በመሀል ለተፈጠረው የተግባቦት ክፍተት የማኅበሩ /ቤት ዋና ሥራ አስኪያጁን በደብዳቤ ይቅርታ መጠየቁ ተገልጧል፡፡ ይኹንና ለጉባኤው ተዘጋጅተው የነበሩት የአብነት /ቤቶችን ተቋማዊ ኹኔታ የተመለከቱ አጀንዳዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ በመኾናቸው የማይደራደርባቸውና ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋራ በመነጋገር መከናወናቸው አይቀሬ መኾኑን የማኅበሩ አመራሮች ማስታወቃቸውን ምንጮቹ ለፋክት መጽሔት ገልጸዋል፡፡

4 comments:

  1. To day is not yesterday or tomorrow. today is your day. you have to repent and abide by the rule of the church. enough is enough. we do know you very well what you have been doing in the name of the Ethiopian Orthodox Tewahdo church.. if you really want to support the Abnet Tmihrt bet or if really your aim or goal is helping the mother church, you have to be united with church. be not foolish enough, maybe you can run but you can not find any bush to hide yourself . we do know much better than you know yourself.

    ReplyDelete
  2. Tsedalu do not make yourself as a patriarch or govt body. stand by your own. your are only and only enemy of the abnet school.

    ReplyDelete
  3. ስላሴ ፩ ያድርጉን።

    ReplyDelete
  4. ስላሴ ፩ ያድርጉን።

    ReplyDelete