Wednesday, February 19, 2014

የእምነቱ ተከታዮች የበላን ሆዳችንን፣ የእምነት አባቶች የምታኩልን ጀርባችንን

ከሚካኤል ጎርባቾቭ
  •  ‹‹የበላኝ ሆዴን፤ የሚያኩት ጀርባዬን›› ሀገርኛ ብሂል
በሁለቱም አድራሻ እንገኛለን ይጎብኙን

(አንድ አድርገን የካቲት 12 2006 ዓ.ም)፡- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ ዕለት የካቲት 08/2006 ዓ.ም በድረ-ገጹ የዜና ዓምድና በፌስ ቡክ ገጹ ላይ “ቤተመንግሥቱን የከበበው መስቀል የሃይማኖት መሪዎቹን አነጋገረ” በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ ማስነበቡን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች በጽሑፉ ዙሪያ ተሰጡ፡፡  ከእነዚህም መካከል አዲሱ ፀጋው የተባለ ፌስ ቡከኛ እንዲህ የሚል አስተያየት ከጽሑፉ ሥር ለጠፈ አረፈው፡-

Addisu Tsegaw ለመላው ከኪራይ ሰብሳቢ ለጸዳ የህወሓት ታጋይና ለህወሓት ጀግና ዝባቸው ኩራት ለሆኑ የሴት ታጋዮች በሞላ እንኩዋን 39ኛው አመት የህወሓት በኣል አደረሰን! አብረሐት አብዱ በሙዚቃ እንደገለፀችው የህወሓት ድል ከሰማይ የወረደ አይደለም!ብዙ የደምና የህይወት ዋጋ የተከፈለበት ነው!ሀወሓት/አዴግ ወደፊት ይመርሻል!

አዲስ አድማስ ያስነበበን ጽሑፍ የሚያወራው አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አጥር ዙሪያ ላይ ስላሉት የዘውድ ምልክትና መስቀል ጉዳይ ሲሆን ይህ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የተጨነቀው ስለ ህወሓት በዓል ነው፡፡ ይህን ሰው ውስጡን የሚኮረኩረው፣ ስሜቱን የሚቀሰቅሰው፣ ሌሊት በህልሙ፣ ቀን በሀሳቡ የሚወጣው የሚወርደው፣ ኩላሊቱ የሚያጤሰው፣ ልቦናው የሚያቃጥለው፣ ኅሊናው የሚያብላላው ነገር ቢኖር ሌላ ሲሆን በዚህ ጽሑፍ ሥር ያስቀመጠው አስተያየትም የስሜቱንና የራሱን ፍላጎት ማሳያ እንጂ ከአዲስ አድማስ ጽሑፍ ጋር የሚገናኝ ሆኖ በቦታው የተለጠፈ እንዳልሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ሆኖም ግን የእርሱ አስተያየት ከተሰጡት አስተያየቶች ሁሉ የተለየ ትርጉም ሰጠኝና ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ እንደሚባለው ሀገረኛ ተረት አስተያየቱ ሆኖብኝ የሃይማኖት አባቶቻችንም የጉባዔያቸው አጀንዳ የቤተ መንግሥቱ አጥር ዘውድና መስቀል ከመሆኑ ጋር ሄዶ ቢገጥምብኝ ለማሳያነት ያቀረብኩት እንጂ አዲሱ ፀጋው ጉዳያችን ሆኖ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባዔ በአንድ በቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ኪያር ሙሐመድ አማን አነሱት የተባለው ጥያቄና ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሰጡት ተብሎ የተነገረው መልስ በመሠረቱ የሚናቅ የሚደነቅ ባይሆንም የሚጣል ግን አይደለም፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ጉባዔ የመወያያ ርዕሰ ነገር ሊሆን ባልተገባው ነበር፡፡ ይህን የመሰለ የሃይማኖት አባቶች ጉባዔ ለሚዲያ ተላልፎ ሊሰጥ የሚችል እጅግ በርካታ የሆኑ ሀገራዊ አጀንዳዎች ኖረዋቸው ሊከራከሩ፣ሊወያዩና ሊተማመኑ ሲገባ የቤተ መንግሥት አጥር የዘውድና የመስቀል ምልክት የውይይቱ አዳማቂ መሆን ባላስፈለገው፡፡
ሀሳቡ ከተነሳ አይቀር ግን ይህንና ይህን የሚመስል የውስጥን ስሜትና ፍላጎት አመላካች የሆኑ ነገሮች በተደጋጋሚ በተለይም ከእስልምና ወገኖች ይነሳል፡፡ ሁሉም ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ግን መንገዳቸው አንድ ይሆንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን መዳረሻ ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ ያህልም ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ስለመሆኗ፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች ቁጥር ከክርስቲያኖች ይበልጣል ማለት፣ የአክሱም ላይ መስጊድ እንሥራ ጥያቄ፣ የንጉሥ አርማህ እምነት ከክርስትና ወደ እስልምና ተለውጧል፤ የንጉሡም ስም አል ነጃሺ አህመድ ነው ማለት፣የሀገሪቱ መሪ እስላም መሆን አለበት፣ ኢትዮጵያም የዐረብ ሀገራት አባል መሆን አለባት የሚሉና የመሳሰሉትን ጥያቄዎችና ተቃውሞዎችን አሰምተዋል፡፡
ዛሬ ደግሞ የቤተ መንግሥቱን አጥር ምክንያት ያደረገ ጥያቄ በፕሬዝዳንቱ በኩል ተነሥቷል፡፡ ነገ ደግሞ የመስቀለኛ ቅርጽ ያላቸው ነገሮች ሁሉ ከምድሪቱ ይነሡልን፤ ያ እስካልሆነ ድረስ ደግሞ የሃይማኖት እኩልነት የለም ይባልና ድፍረታቸው ሲያይል የግሸን አምባሰል የመስቀል ተራራ ይናድ፣ የመስቀለኛ መንገዶች ይፍረሱ… ወዘተ ሊባልልን ነው፡፡
የእምዬ ምኒልክን አሻራ ተከትሎ በአጼ ኃይለ ሥላሴ የተስፋፋው የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት እና የስድስት ኪሎው ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት /የአሁኑ 6ኪሎ ዩኒቨርስቲ/ አጥር ላይ የዘውድና የመስቀል ቅርጽ መኖሩ እሙን ቢሆንም ዛሬም ድረስ መኖሩ ግን ስህተትነት የለውም፡፡ በነገራችን ላያ የሃይማኖት አባቶቹ በጉባዔያቸው ላይ ይህን አንስተው መነጋገራቸው ደግም ክፉም ይኑረው መታሰብ ያለበት ነገር ግን ከእዛ ባሻገር ያለው ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ  የስድስት ኪሎውን የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ከዩኒቨርስቲው ጎን መሆን በመቃወም ለወጡት ሙስሊሞች ማካካሻ እንዲሆን ታስቦ ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ ላይ ምንም ዓይነት የምህንድስና አስተሳሰቦችንና ተያያዥ የሆኑ ማኅበራዊ ብሎም የትራፊክ ፍሰትን ያላገናዘበ የመስጊድ ግንባታ እንዲከናወን ተደርጓል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ስሜታዊነት እየተለመዱ እኛም ዝም አልንና ወደ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ተወርዷል፡፡ በነገራችን ላይ የ6ኪሎው ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ዩኒቨርስቲው አልሄደም፤ ዩኒቨርስቲው ነው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ይዞታ የመጣው፡፡ ይህን እንኳ የሚያገናዝብ አካል አልነበረንም፡፡
የአራት ኪሎም ቤተ መንግሥት ጥያቄ ከዚህ የወጣ አይደለም፡፡ ቤተ መንግሥቱ ዙሪያውን ከፊት የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ በታችኛው በኩል ደግሞ የታዕካ ነገሥት ቅድስት በዓታ ለማርያም ገዳም እና ግቢ ገብርኤል ሲኖሩ በውስጥ ደግሞ ሥዕል ቤት ኪዳነ ምኅረት ይገኛሉ፡፡ አሁን ጥያቄውን ማን የቤተ መንግሥቱ አጥር ላይ ዘውድና መስቀል ነው ይለዋል!? ለዚህ ማሳያ ይሆን ዘንድ አዲስ አድማስ በጻፈው ጽሑፍ ሥር ከተሰጡት አንዱን አስተያየት ማየት በቂ ይሆናል፡፡
Geda Ganamo @all, why u move around z bush? let we focus on z issue! Do we have truly secular gov't? How about z churchs around z palace?
ይህን መሰሉን ነገር ካስተዋልን በተደጋጋሚ ከእስልምና ወገኖች የሚነሱ ጥያቄዎች ክርስትናንና ቤተ ክርስቲያንን ከቻሉ የሚያጠፉ ካልሆነም የሚያዳክሙ ሲሆኑ መጨረሻቸውም የሀገሪቱ ታሪካዊ አሻራዎች ክርስቲያን ክርስቲያን እንዳይሸቱ ማስቻል ነው፡፡ በእርግጥ ይህ የሁሉም ሙስሊሞች ፍላጎት ነው ማለት አይቻልም፡፡ መልስ መስጠት የምንችለው ግን እነዚህን ሀሳቦች ለሚያነሱ ሙስሊም ወገኖች ሲሆን ጥያቄው ጥያቄያቸው ያልሆኑ ሙስሊሞች ግን እውነቱን የመግለጥ ሀገራዊም ታሪካዊም ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሳልገልጥ አላልፍም፡፡
በአንጻሩ ግን የሃይማኖት መሪዎች ጉባኤ ሊነጋገርበት የሚገባ ቁም ነገር ቢኖር የአጥር ላይ ዘውድና መስቀል ሳይሆን ሀገሪቱንና ሕዝቡን ሊያነጋግር በሚችልና መፍትሔ በሚሰጥ ብርቱ ጉዳዮች ላይ መሆን አለበት፡፡ የእምነቱ ተከታዮች የበላን ሆዳችንን፣ የእምነቱ አባቶች የምታኩልን ጀርባችንን፡፡ እንዴት ይሆናል!! ማንን ለማዘናጋት!!! ማንንስ ለመምታት!!!!
መንግሥትም ሆነ አባቶቻችን ይህ ባይጠፋችሁም ቅሉ ሲሆን ሲሆን የሃይማኖት መሪዎች ጉባዔ ነውና “ዳር ድንበርን ጠብቃ፣ ሀገርና ህዝብን አስተሳስራ፣ ክብርና ሰንደቅን ከፍ አድርጋ፣ ዘመን ቀምራ፣ ፊደል ቀርጻ፣ እርሷ እንደጧፍ ነዳ ለሌሎች ብርሃን ስለሆነች ባለውለታችን ምን እንክፈላት? በተለይም እስልምና እንደ ሃይማኖት ተከብሮ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ትልቁን አስተዋፅኦ ላበረከተችውና ለልጆቿም ምን ውለታ እንመልስ? ይህቺውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡“ ነበር አጀንዳችሁ መሆን የሚገባው፡፡ እንጂ መስቀልና ዘውዱ፣ ታሪክና ቅርሱ ይነሱ፣ ይፍረሱ ማለት አልነበረም፡፡ ወርቅ ላበደረ ሆነና ነገሩ፡፡
የጽሑፌን ሀሳብ መቋጫ ልዋስና “ቤተመንግሥቱን ስለከበበው መስቀል የሃይማኖት መሪዎቹን አነጋገረ” በሚለው የአዲስ አድማስ ጽሑፍ ላይ “መጠርጠር ደጉ” የተባለ ፌስ ቡከኛ የሰጠውን አስተያየት ልጥቀስ
መጠርጠር ደጉ ያሰሩት ጃንሆይ ናቸው:ቤተመንግስቱ የሳቸው መታሰቢያ ነው:እሳቸውን ለመዘከር እንዳለ መቀመጥ አለበት:አስተያየቱ ይደመጥ ቢባል እንኳን መንግስት ነው ግቢውን መልቀቅ ያለበት። በዚህ አካሄድ ሼኩ ገና ግቢው ውስጥ ያለው / ይፍረስ: በደብር ቁጥር /ብዛትና ይዞታ አንሰናል ወዘተ እያለ መቀጠሉ አይቀርም።የሙስሊሙን ሌጅትመሲ ለማግኝት እንዲህ ያለ አካሄድ መከተል የሚያዋጣ አይመስለንም።የወረዳና ቀበሌ ምርጫ አሸናፊ የተከበሩ ...........።
/እኔ ስጽፍ እነሱ ሲያነቡ፣እኔ ስጽፍ እነሱ ምላሽ ሲጽፉ፣ እኔ ስጽፍ እነሱ አስተያየት ሲሰጡ … ቀለም እስኪደርቅ ወረቀት እስኪረቅ/

3 comments:

  1. የካቲት12 ቀን 2006 ዓ.ም አንድ አድርገን ብሎግ ላይ በተጻፈው ጽሑፍ ውስጥ "በተለይም እስልምና እንደ ሃይማኖት ተከብሮ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ትልቁን አስተዋፅኦ ላበረከተችውና ለልጆቿም ምን ውለታ እንመልስ? ይህቺውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነች" የሚል ዐረፍተ ነገር ተጽፏል። ለመሆኑ ይህ አባባል ቤተ ክርስቲያኗን ለማስክበር ነው? ወይስ ለማዋረድ? እንዴት ቤተ ክርስቲያን የእስልምና ሃይማኖት እንዲስፋፋና እዚህ ደረጃ እንዲደርስ አስተዋፅኦ ታደርጋለች? ይህ በምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያን ዓላማ ሊሆን አይችልም።ቤተ ክርስቲያን በአዳኝዋ በኢየሱስ ክርስቶስ ያላመኑትን አሕዛብ አስተምራና አሳምና የክርስቶስ ተከታይ እንዲሆን ታደርጋለች እንጂ "የእስልምና ሃይማኖት እንዲስፋፋና እንዲያድግ አስተዋፅኦ አታደርግም። ይህን እንደማታደርግ ክርስቲያን አይደለም የክርስትና ተቃወሚዎችም ያውቁታል። ቤተ ክርስቲያን የእስልምና ሃይማኖት እንዲያድግ አስተዋፅኦ የምታደርግ ከሆነ የእስልምና ሃይማኖት ከተጀመረበት ዘመን ጀምሮ እስክ ዛሬ ድረስ ለምን ልዩ ልዩ መከራና ስቃይ ትቀበላለች? ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አስከበርን ብላችሁ ለምትናገሩትና ለምትጽፉት ሁሉ ልትጠነቀቁ ይገባል፣ ያላዋቂ ሳሚ አትሁኑባት።በቀራንዮ ደሙን ያፈሰሰላት የቤተ ክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን።

    ReplyDelete
    Replies
    1. AnonymousFebruary 20, 2014 at 6:16 PM

      I think you missed the point. Remember how the first muslims came to Ethiopia. The Chirstian poeple and Christian leaders host the Muslim strangers. How do you explain this?

      Delete
  2. thank you sewayetefa!!
    Tarik Ayetefa

    ReplyDelete