Sunday, February 16, 2014

የቤተክህነቱ የእግድ "ቀጭን" ትእዛዝ ምን ያመለክተናል?


(አንድ አድርገን የካቲት 9 2006 ዓ.ም)፡-በዚህ ሳምንት ማህበረ ቅዱሳን 200 በላይ የአብነት /ቤቶች መምህራንን ከተለያዩ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር በመሆን በችግሮቻቸው ዙሪያ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን በሚያበረክቱት ግልጋሎት ላይ ለመምከር ያዘጋጀውን ጉባኤ ከፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ በተላከች አንዲት ደብዳቤ ሊታገድ ችሏል። ለመሆኑ ይህ እግድ ምን ይነግረናል?

1
. የመጀመሪያው እና ዋናው ነገር በቤተክህነቱ ውስጥ ምን ያክል አምባገነናዊነት እንደነገሰ ያሳየናል።  ማህበሩ በድምጸ ተዋህዶ ሬድዮ ፕሮግራሙ እንዳሳወቀን በዚህ ዓመት ጉባኤውን እንደሚያካሂድ በአመታዊ እቅዱ ውስጥ እንዳካተተና በአመቱ መግቢያ ላይ ለሚመለከተው የቤተክህነቱ አካል አሳውቋል። ቤተክህነቱ በወቅቱ ይህን ማህበሩ ማከናወን እንደማይችል ማሳወቅ ይችል ነበር። ለወራት ያለምንም ተቃውሞም ሆነ አስተያየት ከቆየ በኋላ ጊዜው ሲደርስና ማህበሩም ለዝግጅቱ ከፍተኛ ወጪ ካወጣበት በኋላ ሰዓታት ሲቀሩት የእግድ ደብዳቤ ማስጠት ከአምባገነንነትም በላይ ነው። ያሳዝናል! ያሳፍራልም!

2. ቤተክርስቲያንን እንደመዥገር ተጣብቀዋት አላንቀሳቅስ ያሉ ሰዎች አሁን ደሞ ፓትርያርኩን እንደከበቧቸው ያሳየናል። ይህ ጉባኤ ምን ያህል ቤተ ክርስቲያንን እንደሚጠቅም የቤተክህነቱንም ስራ እንደሚያግዝ ሆን ተብሎ በነዚህ ሰዎች ፓትርያርኩ እንዳያውቁ ተደርጓል ወይም የተንሻፈፈ መረጃ እንዲደርሳቸው ሆኗል። ይህ ደሞ ከማበሩ ጋር ፓትርያርኩን ለማጋጨት ሆን ተብሎ የተዘየደ እንደሚሆን ግልጽ ነው። 
3. በቤተክህነቱ ውስጥ ህገ ወጦች ምን ያክል እንደነገሱበት ያሳየናል። ማህበሩ ጉባኤውን እንደሚያዘጋጅ ከወራት በፊት በተገቢው ህጋዊ መንገድ ከማሳወቁም በላይ ወቅቱም ሲደርስ ለቤተክህነቱ ሃላፊዎች በተገቢው ህጋዊ መንገድ አሳውቋል። ሆኖም ግን በተመሳሳይ ወቅትና ህጋዊ መንገድ ማገድም ካስፈለገ በምክንያት ማገድ ሲቻል ሰአታት ሲቀሩት እግድ ደብዳቤ ማውጣት የቤተክህነቱ ሃላፊዎች ምን ያክል በህግ እንደማይመሩ የሚያመለክት ነው። 
4. ቤተክህነቱን የወረሩት ወሮበሎች ጦርነታቸት ከማህበሩ ጋር ብቻ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። ይህ ጉባኤ ቢካሄድ ጥቅሙ "በሩ አዘጋጀ" ከመባል ውጪ የማበረ ቅዱሳን እንዳልሆነ ለማናችንም ግልጽ ነው። በጉባኤው ላይ የተገኙትም አባቶች ኪሳቸውን አያደልቡበትም ይልቁንም ቤተ ክርስቲኗ ለዘመናት መፍታት ያልቻለችውን የልማት ችግር እንደሚያግዝ ሰው የሆነ ሁሉ ሊረዳው የሚችል ጉዳይ ነው። ስለዚህ በአባ ሰረቀ አቀነባባሪነት የተሰራው ይህ ወንጀል ሰዎቹ ምን ያክል የቤተ ክርስቲያን ጠላትነታቸውን ያሳዩበት ገጠመኝ ነው። 


5. ይህ ጉዳይ አባ ሰረቀን ብቻ ያገዱት አይመስልም ፤ የቅዱስ ፓትርያርኩ ፍቃድ ካልታከለበት በቀር አንድ ተራ ዘወትር ክፋትንና ጉድጓን የሚቆፍር ሰው ይህን ያህል ትልቅ ጉባኤ ያግዳል ማለት ይከብዳል ፤ ሲጀመር ቅዱስ ፓትርያርኩን ባልሆነ የፈጠራ ወሬ ስለ ጉባኤው የተዛባ መረጃ የተሰጣቸው ይመስላል ፤ ምንም የተዛባ መረጃ ቢሰጣቸው የአብነት መምህራኑ ሀገር አቋርጠው መምጣታቸውን ብቻ በመመልከት ችግርም ቢኖር መፍቀድ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን የቀድሞ በጥልፍልፎሽ የተሞላው ዘርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገው  አስተዳደርና የውስጥ አሰራር  እንዲመለስ የሚፈልጉ ዘወትር ቤተ ክርስቲያን ላይ እሾኽ የሆኑ ሰዎች አሁንም እንዳሉ ያመላክተናል፡፡
6 ቅዱስ ፓትያርኩ መንበሩን ሲረከቡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልዕልና እና ትልቅ ቦታ መድረስ አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸው ነበር፡፡ አሁን ዓመት ያልሞላን አስተዳደር ለመተቸትም ሆነ ለማመስገን ጊዜው ባይሆንም ከስራቸው የሚገኙትን ሰዎችን አበክረው ካላዩ እና የሚሰራውንና የሚተነኩለውን ካለዩ በቀር ዳግም ያለፈው 20 ዘመን ላለመመለሱ ምንም ምክንያት አይኖርም ፤ ቀድሞ ስናማር የነበረውን አስተዳደር መልኩንና መንፈሱን ሳይቀይር እዛው ወንበሩ ላይ ይገኛል ፤ አሁንም ከዚህ አስተዳደር መልካም ነገርን መጠበቅ የዋህነት ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ስለዚህ የአሁኑ የእግድ ደብዳቤ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ከቅዱስ ፓትያርኩ መምጣት በቀር ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ ያመለክተናል፡፡
ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የሚራወጡ ሰዎች ለዘመናት መልካቸውን እየቀያየሩ ሲያስቸግሩ ኖረዋል ወደፊትም ይኖራሉ። አሁን በእኛ ዘመን ደሞ እነዚ መጥተዋል እኛም ስለ ማንነታቸውም ሆነ ስለሚሰሩት አፍራሽ ተግባራት በንቃት መከታተል ስናውቅ ደሞ ላላወቁ የማሳወቅ ግዴታ አለብን። እግዚአብሄር አምላክም ከቤተክርስቲያን ጋር ነውና መጥፋታቸው እውነት ነው።
From Melese Zenebework

3 comments:

  1. የዘመኑ "አርዮስ - ማርቲን " ፣ የ "ሰረቀና ግብር አበሮቹ" ምንፍቅና

    ይህ ሰው ፓስተር ሰረቀ ከነተከታዮቹ እኮ ተረፈ አሪዎሳዊ ነው፡፡ ‹‹ስም አልባው›› … አናንተንም ጨምሮ!!! ስለዚህ በኒቂያ፣ በኤፌሶን .. ጉባኤ ተለይተው እደተወገዙት አሪዎሳውያን ወይ ከነ ግብር አበሮቻችሁ ተወግዛችሁ ትለያላችሁ ወይም ስጋችሁ ተጎትቶ ከቤተክህነቱ፣ ከጉልላቱ ይወጣል…፡፡ ይህንን ደግሞ ጊዜ ይፈጅ ይሆናል እንጂ እናንተ አሪዎሳውያን በአይናችሁ ታዩታላችሁ፣ በጆሮዋችሁ ትሰሙታላችሁ፤ ምክንያቱ ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!›› የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነውና!!
    ‹‹በቤተክርስቲያናችን በአውደ ምህረቱ በአደባባይ ላይ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በአማላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በንጽህተ ንጹሀን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በቅዱሳኑ፣… ላይ የሚነዛው የአሪዎሳዊ፣ የማርቲን … የምንፍቅና፣ የክህደት ትምህርት ዋና ምንጩ የቤተክህነቱ የውስጥ ፓስተር ጉዳይ አስፈጻሚ እኮ ሰረቀ፣‹‹ስም አልባው››ና … ሌሎች ብዙ መሰሎቻችሁ ናችሁ!››
    የዚህች ቤተክርስቲያን ልዕልና መደፈር፣ የቤተክህነቱ የሙስናው፣ የዘረኝነቱ፣ የአድልዎ ቅጥሩ፣ ሙዳይ ምጽዋቱ ሰበራው …. የእናንተ አይን አያይም፣ ጆሮ አይሰማም፣ … ለነገሩ ዓላማችሁ ይህ ነውና፣ … ኩሎ ለጊዜ!!!
    ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!››

    ReplyDelete
  2. የዘመኑ አርዮስ፣ የማርቲን ተከተታየይ የ "አባ" ሰረቀና ግብር አበሮቹ" ምንፍቅና የ100 ዓመት እስትራቴጂ ዕቅድ ውጤት ነው፡፡

    ይህ ሰው ፓስተር ሰረቀ ከነተከታዮቹ እኮ ተረፈ አሪዎሳዊ ነው፡፡ ‹‹ስም አልባው›› … አናንተንም ጨምሮ!!! ስለዚህ በኒቂያ፣ በኤፌሶን .. ጉባኤ ተለይተው እደተወገዙት አሪዎሳውያን ወይ ከነ ግብር አበሮቻችሁ ተወግዛችሁ ትለያላችሁ ወይም ስጋችሁ ተጎትቶ ከቤተክህነቱ፣ ከጉልላቱ ይወጣል…፡፡ ይህንን ደግሞ ጊዜ ይፈጅ ይሆናል እንጂ እናንተ አሪዎሳውያን በአይናችሁ ታዩታላችሁ፣ በጆሮዋችሁ ትሰሙታላችሁ፤
    ምክንያቱ ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!›› የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነውና!!
    ምክንያቱ ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!›› የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነውና!!

    1ኛ. ‹‹በቤተክርስቲያናችን በአውደ ምህረቱ በአደባባይ ላይ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በአማላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በንጽህተ ንጹሀን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በቅዱሳኑ፣… ላይ የሚነዛው የአሪዎሳዊ፣ የማርቲን … የምንፍቅና፣ የክህደት ትምህርት ዋና ምንጩ የቤተክህነቱ የውስጥ ፓስተር ጉዳይ አስፈጻሚ እኮ ሰረቀ፣‹‹ስም አልባው››ና … ሌሎች ብዙ መሰሎቻችሁ ናችሁ!››

    2ኛ. የዚህች ቤተክርስቲያን ልዕልና መደፈር፣ የቤተክህነቱ የሙስናው፣ የዘረኝነቱ፣ የአድልዎ ቅጥሩ፣ የሙዳይ ምጽዋቱ ሰበራው፣ የነፈፍስ ግድያው …. የእናንተ አይን አያይም፣ ጆሮ አይሰማም፣ … ለነገሩ ዓላማችሁ ይህ ነውና፣ …

    3ኛ. በዚህ 10 እና 15 ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ እንኳን ከ10 ሚሊዮን በላይ ኦርቶዶክሳዊ የተዋህዶ ልጅ መናፍቅ መሆኑ፣ ከእና ቤ/ክ መኮብሉ የማን ደባና ስራና ይሆን? የፓስተር ሰረቀ፣ … እና መሰሎቻቸው የ100 ዓመት እስትራቴጂ ዕቅድ ነው፡፡ ኩሎ ለጊዜ!!!

    ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!››

    ReplyDelete