Tuesday, February 18, 2014

አባ ሰረቀ ብርሃን ‹‹በታቦት ዝርፊያ›› ክስ ብጹዕ አቡነ ማትያስ ዘንድ ቀርበው ነበር

  • ‹‹ለዚህ መረጃ አቡነ ማትያስ ቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በአሁን ሰዓት 6ተኛው ፓትርያርክ፣ አቡነ ሣሙኤልና አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና›› መረጃውን የላኩልን የሎሳንጀለስ ምዕመን
  • ‹‹አባ›› ሰረቀ ታቦት ሰርቀው ተይዘዋል፡፡ ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን 12 መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
  • ‹‹አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም፡፡›› ‹‹አባ›› ሰረቀ ብርሃን በአንድ ወቅት የሰበኩት ስብከት
  •  ‹‹በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ ተደርሶባቸው..........››
    በወቅቱ አባ ሰረቀ ከጓደኛቸው ጋር ሲሰሩት የነበረ ሥራ የምዕመኑ ቃል
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት ነው። 

(አንድ አድርገን የካቲት 11 2006 ዓ.ም)፡- በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ በአባ ሰረቀ ብርሃን አማካኝነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የአባ ሰረቀን  የቀድሞ ተግባር በርካታ ምዕመን ቢያውቀውም  ብጹዕ አቡነ ማትያስ የሚያውቁትን እና በሎስአንጀለስ ምዕመናን ላይ ያደረሱትን በደል የደረሰንን መልዕክት ለእናንተው ለማድረስ ወደድን፡፡ ‹አባ› ሰረቀን ከአመታት በፊት በታቦት ሌብነት ብጹዕ አቡነ ማትያስ ዘንድ ቀርበውም እንደነበርም መረጃው ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው አሁን እየሰሩ የሚገኙት ቀድሞ  ለሰሚ ጆሮ የሚከብድ ዝርፊያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረገ ሰው ጋር መሆኑን ነው፡፡ እስኪ በወቅቱ የነበሩ ህያው ምስክሮች የላኩልንን መረጃ ይህን ይመስላል፡፡


አባ ሰረቀ ማን ናቸውከዚህ በፊት ያልተሰሙ ወሬዎችን ያንብቡት
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ ለማለት ቢያስቸግርም የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ፣  የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ  አንቱ  በማለቱ እቀጥላላልሁ  አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበት ሎሳንጀለስ ከተማ) ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈው ስለሄዱ አባ ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል አንዲት የቤተክርስቲያናችን አዛውንት ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው  የሚያንገሸግሻቸው አውቃለሁ። 
ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ  በሎሳንጀለስ እንዴት ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦ 
አባ ሰረቀ ብርሃን 1993 መስከረም ላይ ከኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ይህንን መረጃ የሰጡን አባት እንዲህ ያጫውቱናል። ‹‹አባ ሰረቅ ብርሃንን ለማስመጣት ሂደቱን የጀመእኩት እኔ ነኝ። 1993 ... የእህቴን ባል እባክህ ጥሩ ካህን የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ሰው ፈልግልን ብዬ ነገርኩት። እርሱም ወዲያው አንድ በጣም የተማሩ ሰው አግኝቸልሃልሁ ብሎ አጫወተኝና (በኢትዮጵያም ክረምት አካባቢ ነው) ደስ አለኝ። ደውዬም እንዳነጋግራቸው አመቻቸልኝና አባ ሰረቀን ድውዬ አገኘኋቸው። እርሳቸውም ለመምጣት እፈልጋለሁ ግን ለመጉዋጓዣ 2000 ዶላር ያስፈልገኛል ብለው ነገሩኝ። እኔም ቦርዱን አስፈቅጀ የመምጫቸውን ሁኔታ ጀመርን።2000 ዶላርም ተላክላቸው። ››
በኋላም ስለመምጫቸው ተነጋግረን ንዋያተ ቅዱሳት (ጽናጽልና መቋሚያ ) እንዲሁን ጽላትም ጭምር እንደሌለን ስነግራቸው፤ ሁሉንም ማግኘት እንደሚችሉ፤ ነገር ግን ተጨማሪ 1000 ዶላር እንደሚያስፈልግ ነገሩኝ። ያንንም ቦርዱን አስፈቅጀ ላኩላቸው።  መስከረም 1993 ... 12 ጸናጽል፣ 12 መቋሚያና ጽላት ይዘውልን ሎሳንጀለስ ገቡ። እኛም አባት ናፍቆን ስለነበረ ምንም እንኳን ያወጣነው ወጭ ብዙ ቢሆንም በደስታ ተቀበልናቸው። ስላሁሰንና ዌስት (between Slauson and West) ላይ አንድ የአድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ተከራይትን አገልግሎት ማግኘት ጀመርን። 
ትንሽ ቆይቶም አባ ተከስተ የሚባሉ መነኩሴ (የዛሬው ብጹእ አቡነ ሣᎀኤል) ወደዚህ እነደሚመጡ ተነገረንና እኔው ተቀብዬ አብረው መኖር ጀመሩ። የሚገርመው ግን አባ ሰረቀ ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ስለማይፈልጉ፤ አባ ተከስተ ጋር አለመግባባት ፈጠሩና አባ ተክስተ ወደ ሌላ ስቴት ሄዱ። 
ከዚያም እርሳቸውም ብቻቸውን እንዳይሆኑ በማለትሳንሆዜ የነበረ አንድ ይሥሐቅ የሚባል አገልጋይ ልናመጣልዎት ነበር” ብንላቸው ያሉንን እስከ አሁን አስታውሰዋለሁ ‹‹እኔ ቤት አንድ ሰው አይገባም›› ነበር  በወቅቱ ያሉት። ያን ጊዜ ነበር አባ ሰረቀ ላይ የነበረው እምነታችን እየተሸራረፈ የመጣው። እንደምንም አግባብተን ልጁን ብናመጣውም አሁንም እርሱም የአባ ተክስተ እጣ ደርሶት አባረሩትና ሄደብን። 
መቼም የኛ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ነችና ከአሪዞና አባ ወልደ ሰንበት የሚባሉ አንድ መነኩሴ ደግሞ አስመጣንላቸው። ለካስ ሁለቱም መሰሪ ነበሩና የሚከተለውን ምእመናን የማይረሱትን አሳዛኝ ሥራ ሰሩ። 
‹‹ቀኑ እሁድ ነው አስታውሳለሁ አባ ስረቀና አባ ወልደ ሰንበት ቅዳሴ ቀድሰው ሲያበቁ አባ ሰረቀ ለእኔና ለጓደኞቸአባ ወልደ ሰንበት ወንድሙ ስላረፈ ልናረዳው ነው ምን ትላላችሁአሉ። እኛም አዝነን አሁን ቅዳሴ ቀድሰው ከምንነግራቸው ለምን ሳምንት ወይንም ነገ አንነግራቸውም አልናቸው። እርሳቸውም እሺ ብለው እኛን ከላኩ በኋላ ረድተዋቸው ነበርና ወዲያው ደውለው አርድቻቸዋለሁና ተባልን በጣም ሁላችንም ተመልሰን መጣን እውነት መስሎን በጣም አዝነን አባ ወልደ ሰንበትንም አጽናንተን ተመለስን። ከዚያም ወደ ሀገራቸ መመልስ እንደሚፈልጉ አባ ሰረቀ ነገሩን እኛም አዝነን ያለንን አዋጥተን ላክናቸው። ትዝ የሚለኝ ለቤተሰቦቻቸውም አምነዋቸው ብር አድርሱልንም ያሉ ሰዎች ነበሩ። ግን አባ ወልደ ሰንበት ሳያደርሱላቸው ብራቸውን በዚያው በልተው ቀርተዋል። 
ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ የአባ ወለደ ሰንበትን እህት ወይዘሮ አብርኸትን የሚያውቅ አንድ የቤተ ክርስቲያናችነ አባል፤ አዲስ አበባ ሄዶ ወይዘሮ አብርኸትን ያገኝና ‹‹እባክሽ የወንድማችሁን መሞት ሰምተን እኮ አባን አጽናናቸው ቢሏት››  የምን ወንድም ነው የምታወራው? ትለዋለች። ለካስ አባ ወልደ ሰንበት ወድማቸው ሞተ ትብሎ የተነገረው የውሸት ኑሯል። አባ ሰረቀና እርሳቸው የፈጠሩት ውሸት መሆኑን አወቅን። ከዚያ በኋላ ይኸው አባ ወልደ ሰንበት በወቅቱ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እንደዘገበው በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ ተደርሶባቸው መጀመርያ ወደ ጀርመን አሁን ደግሞ መቼም ጅብ በማያውቁት ሀገር እንደሚባለው በገለልትኞች ሲኖዶስ ጳጳስ ሆነው ካናዳ ይኖራሉ። 
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና አባ ሰረቀ አባ ወልደ ሰንበትን እንዲህ አድርገው ከአጠገባቸው ካራቁ በኋላ ከቤተ ክርስቲያን አባልት ጋር መግባባት አልቻሉም። ከእለታት አንድ ቀን እንደውም ‹‹ቤተክርስቲያን የለችም አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም ›› በማለት ሲስብኩ አስታውሳለሁ። ይህ በእምነታችን የሌለ ኑፋቄ ነው። ከዚያም በኋላ ከቤተክርስቲያናችን ተለይተው ‹‹የአቡነ ጳውሎስ እንደራሴ ነኝ እኔ ማንንም መነኩሴ ጳጳስ እንዲሆን አስደርጋለሁ››  ከሚለውና እዚሁ ሎሳንጀለስ ከሚኖረው ቄስ ጋር ገጠሙና ከእኛ ጋር መጣላት ጀመሩ። ከዚያም አቡነ ማትያስ ለጥቅምት አቡነ አረጋዊ ሲመጡ ምእመናን ክስ አቀረቡ። ውይይቱ የተደረገው በወዳጃችን በ አቶ ዕቁበ ጽዮን ቤት ነበር። ብጹእ አባታችንም ቢመክሩዋቸው አልሰማ አሉ። አባ ሰረቀንም ብጹእ አቡነ ማትያስ ምእመናኑ ምንም አልበደሉምና ‹‹ተሳስባችሁ አብራችሁ ኑሩ›› ቢሉዋቸው አባ ሰረቀ ‹‹ከአሁን በኋላ እዚህ አላገለግልም›› ብለው ካበቁ በኋላ ትንሽ ቆይተው ለአቡነ ማትያስብርሌ ከነቃ…” የሚል መልስ ሰጧቸው። 
ብጹእ አቡነ ማትያስም ‹‹እንግዲያውስ እናንተም ሌላ ካህን ፈልጉ እርሳቸውንም መጓጓዣ ከፍላችሁ ላኳቸው ፤ እርሳቸውም ንዋያተ ቅዱሳቱን ፤ ታቦቱን ጭምር ያስረክቧችሁ›› ተባለ  (ይህንንም በዚያን ጊዜ አባ ኢሳይያስ- የሳንዲያጎ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩ- የአሁኑ ብጹእ አቡነ ኢሳይያስ ያረካክቡዋችሁ ተባለ)  እኛም አዝነን እሺ ብለን 700 ዶላር ከምዕመናን ሰበሰብንና / ኃይሉ አቶ ጥላሁንና አንድ ሌላ ሰው ወክለን አባ ኢሳይያስን ይዘው እንዲረከቡ ላክናቸው። 
ከዚያም አባ ሰረቀ በለመዱት አንደበታቸው የተወከሉ ምእመናንን ታቦቱን ነው የያዝኩት ብለው ብሪፍ ኬዝ ይዘው መጡና ይህንን ለመነኩሴው ለአባ ኢሳይያስ ብቻ ነው የማስረክበው በማለት ወደ ውስጥ ሁለቱ ብቻ ገቡ። ብዙ ቆይተው ሲወጡ አባ ኢሳይያስን የተወከሉት ሰዎች ‹‹ታቦቱን ተረከቡ ወይ?›› ሲሉዋቸው ታቦት ተረከብኩም አልተረከብኩም አይባልም አሏቸው። 
ተወካዮችም ግራ ግብቷቸው ሲመለሱ አባ ኢሳይያስም ለብጹእ አቡነ ማትያስ ደውለው ታቦቱን እንዳልተረከቡ እንደውም ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ አባ ሰረቀ ብሪፍ ኬዙን ሳይከፍቱ ይረከቡ ይሏቸዋል። አባ ኢሳይያስም ‹‹ይክፈቱት እንጂ እንዴት ዝም ብዬ እረከባለሁ›› ይሉና ተቀብለው ቢከፍቱት የተገኘው ታቦት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ፤ ከዚያም አባ ሰረቀ እግራቸው ላይ ወድቀው ‹‹እባክዎን አልተቀበልኩም ብለው ለተወካዮች አይንገሩብኝ ፤ ታቦቱን ዲሲ ልኬዋለሁ እዚያ ሄጄ ለአቡነ ማትያስ እሰጣለሁ ወይንም እልከዋለሁ›› ብለዋል ይሏቸዋል። 
ይህንን ነገር አቡነ ማትያስ ሲሰሙ በጣም አዝነውና ተናድደው ነገሩን ምእመናን እንዲሰሙ ያደርጋሉ። ሁለቱም አባቶች (አቡነ ማትያስና አቡነ ኢሳይያስ በሕይዎት ስላሉ ህያው ምሥክር ናቸውና ስለ እውነትነቱ እነሱው ሊጠየቁ ይችላሉ።ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን 12 መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል። ምእመናንም በዚህ ተናድደን ያዋጣነውን ገንዝብ ሳንሰጣቸው ቀርተናል። ከሁሉ የሚገርመኝ ሲሄዱ አንዲት ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሰንና ብርን ይስጡን ብለን ስንጠይቃቸው ፤  ‹‹መልሳ ወስዳዋለች›› አሉን። ይህ ሁሉ እንግዲህ በሎሳንጀለስ የነበራቸው ታሪክ ነው። 
አንድ መነኩሴ ከሰረቀ ፤ ከዋሸ ፤ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ስልጣን ፤ ገንዝብና ክብርን ከፈለገ እንዴት መነኩሴ ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት የሚያደርጉት ብጥብጣ እኔ ከአባ ሰረቀ የማልጠብቀው አይደለም። እርሳቸው፤ ከሰው ጋር ተስማምተው የማይሰሩ ፣ የሚዋሹና በሃሰት ማንኛውንም ኃጢያት ሁሉ ሊሰሩ የሚችሉ ሰው ናቸው። ለዚህ ደግሞ አቡነ ማትያስ ቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ አሁን 6ተኛው ፓትርያርክ ፣ አቡነ ሣሙኤል፤ አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና ፡፡ እነሱን በመጠየቅ ወይንም ለእኔም በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኝት ይቻላል ብለውናል። 
በአጠቃላይ አባ ሰረቀ ማለት  ለእምነታቸው ሳይሆን ለሆዳቸውና ለገንዘብ የሚኖሩ ፤ ካለ ፍርኃት የሚዋሹ ፤ ካለ ሃፍረት የሚሰርቁ ፤ ከሰው ጋር ተባብረውና ተግባብተው መኖርን የማያውቁ ሰው ናቸው። 
እርሳቸው ከሄዱ በኋላ ስድስት ወራት ሙሉ ካለ ካህን እሁድ እሁድ ምእመናን ብቻችንን ተሰብስበን አቶ እቁባይ መጽሐፍ ቅዱስ እያነበቡልን እንበተን ነበር። በኋላ ይኼው እስከ አሁን የሚያገለግሉንን ታላቅ አባቶች አግኝተን እንገለገላለን፡፡ እንደውም ባለፈው ዓመት ቤተ ክርስቲያን ገዝተን ገብተናል። በአሁኑ ሰዓትም ከልብ የሚያገለግሉ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ታላላቅ ምእመናን ያላት ቤት ክርስቲያን በማግኘታችን ደስትኞች ነን። በማለት አባ ሰረቀ ቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱትን በደል ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ አቅርበውልናል፡፡
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን

12 comments:

  1. We don't understand where our saint church id going, This type of fathers are included to broke the church faith, history, culture ...Oh GOD what is your objective please save our church and the people

    ReplyDelete
  2. የዘመኑ "አርዮስ - ማርቲን " ፣ የ "ሰረቀና ግብር አበሮቹ" ምንፍቅና

    ይህ ሰው ፓስተር ሰረቀ ከነተከታዮቹ እኮ ተረፈ አሪዎሳዊ ነው፡፡ ‹‹ስም አልባው›› … አናንተንም ጨምሮ!!! ስለዚህ በኒቂያ፣ በኤፌሶን .. ጉባኤ ተለይተው እደተወገዙት አሪዎሳውያን ወይ ከነ ግብር አበሮቻችሁ ተወግዛችሁ ትለያላችሁ ወይም ስጋችሁ ተጎትቶ ከቤተክህነቱ፣ ከጉልላቱ ይወጣል…፡፡ ይህንን ደግሞ ጊዜ ይፈጅ ይሆናል እንጂ እናንተ አሪዎሳውያን በአይናችሁ ታዩታላችሁ፣ በጆሮዋችሁ ትሰሙታላችሁ፤ ምክንያቱም ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!›› የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም ነውና!!
    ‹‹በቤተክርስቲያናችን በአውደ ምህረቱ በአደባባይ ላይ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በአማላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በንጽህተ ንጹሀን በቅድስት ድንግል ማርያም፣ በቅዱሳኑ፣… ላይ የሚነዛው የአሪዎሳዊ፣ የማርቲን … የምንፍቅና፣ የክህደት ትምህርት ዋና ምንጩ የቤተክህነቱ የውስጥ ፓስተር ጉዳይ አስፈጻሚ እኮ ሰረቀ፣‹‹ስም አልባው››ና … ሌሎች ብዙ መሰሎቻችሁ ናችሁ!››
    የዚህች ቤተክርስቲያን ልዕልና መደፈር፣ የቤተክህነቱ የሙስናው፣ የዘረኝነቱ፣ የአድልዎ ቅጥሩ፣ ሙዳይ ምጽዋቱ ሰበራው …. የእናንተ አይን አያይም፣ ጆሮ አይሰማም፣ … ለነገሩ ዓላማችሁ ይህ ነውና፣ … ኩሎ ለጊዜ!!!
    ‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም!!!››

    ReplyDelete
  3. beewnetu betam new yemitasazunut and adrgenoch yeman bedel new eyetenagerachut yalachut? yebetekristian sim eyatefachut yalachut mk sleteneka new? betam tgermalachu gn demo alememarachu new yemiyasayew ok ? wake uppppppp

    ReplyDelete
  4. this post don't build any one. Just remove it please.

    ReplyDelete
  5. ሰላም ደጀሰላማዊያን፣
    "አባ" ሰረቀ እኮ ከ አባ ፓውሎስ ጋር አብሮ የተቀበረ መስሎን ነበር።በጣም የሚገርመው ግን ወገቡን እነደተመታ እባብ እራሱን ቀብሮ አፈር ልሶ ተነሳ።እናም ዛሬ የጥቃት ጥይቱን ሲተኩስ ሌሎች ያልተሰሙ ጉዶችን ለማሰማት ወደዳችሁ።ወገቡን በተመታበት ስአት እንደተጀመረ መጨረስ ቀላል ነበር ነገር ግን የሞተ መስሏችሁ ፋይሉን ዘጋችሁት ምዕመኑም ዝም አለ።አይ መዘናጋት!!! የሰው ልጅ ሲነካ ብቻ አይደለም መጮህ ያለበት ይነካኛል ብሎ ሲያስብም ጭምር እንጂ።

    ReplyDelete
  6. if you want to know about Aba Serekebirhan, you should ask the scholars of the church. he is the true son of the Ethiopian Orthodx Tewahdo Church. highly educated person. do not be foolish. because we do know who Mk is and his agenda. three to four years ago, Aba Serekebirhan has straggling the evil one (MK) almost alone. but now as you see millions are following .him. because he is a real son of church and he is fighting face to face the enemy of church which is MK the accuser of our fathers and brothers who are working for the church in the church. however, if you have ear let me give you some advice. what you have to do is; abide by the bay low of the church and you have to return back to the right way of the church. We love you Aba and may God be on your side

    ReplyDelete
  7. we do know that: You are not going to post the good news and a good work of our beloved father Aba Serekebirhan Woldesamuel. but you will see soon the answer from the founder of our beloved church Jesus Christ. shem on you MK.

    ReplyDelete
  8. ENANENTEN BELO ANDEADRGIN WUSHETAMOCHE TSERE KERISTOS

    ReplyDelete
  9. በጣም ትገርማላችሁ የናንተ ጉድስ ማን ይናገር?

    ReplyDelete
  10. Ebe yemigermegn ye ato sereke gud endih badebabash shih gize eyetenegere sinodosu/ betekrstiyanitu ye zihon joro... bila zim maletua lemin endehone new enji. Esachewma yimrta esuma zim ketebale gena million gud sisera enayewalen . Yih kemehonu befit gin ewnetegnaw fera kg EGZIABHER yejun yasayen . Betekrstiyanachininm ke endersu yalu leboch , wushetamoch ena asmesayoch yitebklin.

    ReplyDelete
  11. Mk the time is now. you see!! you. are revealed and we new you already who you are. enough is enough .no one can trust you. we know all our fathers. you are the seed of the accuser which is the evil spirit.
    repent and come back from your sin.

    ReplyDelete
  12. በዚህ ግዜ እንኳን ህሊናችን አይጾምም? የወንድምን ሸክም እኛ መሸከም አቅቶን ሌላውን ሰው ህሊና ማቆሸሽ ማን ይሆን ያስተማረን? ጌታ እኒህን ሰዎች በድለው እንኳ ቢያገኛቸው ምን ይላቸው ይመስለናል? እኔስ አልፈርድባችሁም ደግማችሁ አትበድሉ ወይስ እናንተም ስደቧቸው….ወንጌል መስማታችን መማር ማስተማራችን ጥቅሙ መቼና ለምን ይሆን? ለመስደብ ሌላውን ሀጢአት ለማውራት ለቤተክርስቲያን መቆርቆር ምን ይሆን ወገኖቼ ትርጉሙ? ሀሜት በብሎግ ማለት ይሄ ነው ፡፡
    ቅዱስ ያሬድን ልብ ብለን እንስመው ዐይን ክፉ ከማየት፤ጆሮ ክፉ ከመስማት አንደበት ክፉ ከመናገር ይጹም… ጾም ማለት መራብ ማለት አይደለም፡ ትህትና እንጂ፡፡ አድህነኒ እግዚኦ እስመ ሀልቀ ሄር ወውህደ ሃይማኖት እም ገጸምድር
    ቀሲስ መ/ር ንዋይ ካሳሁን

    ReplyDelete