- ማኅበረ ቅዱሳን ከሰለፊ/ከአልቃይዳ ጋር ፈጽሞ ሊመሳሰል አይችልም::
- (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም) ለቪኦኤ የተናገሩት የዋልድባው አባት በፖሊስ እየታደኑ ነው
- (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም) የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የአቡነ ፋኑኤልን ማስፈራርያ እንደማይቀበሉ አረጋገ
- (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ) ከክህነት ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት
- (መጋቢት 27 2004 ዓ.ም)፡-የሰሜን አሜሪካ እና የካናዳ ምእመናን ለሦስተኛ ጊዜ በዋልድባ ገዳም ጉዳይ በተመለከተ ስብሰባ አካሄዱ
- (መጋቢት 26 2004 ዓ.ም)፡- ክህነትን በደብዳቤ ማገድ ይቻላል ?
- (መጋቢት 26 2004 ዓ.ም)፡- “ጥይት እንደሌለው ጠመንጃ፣ ሥልጣን የሌለው ‘ውግዘት’” ከአንባብያን ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል የተላለፈ መልዕክት
- (መጋቢት 25 2004 ዓ.ም)፡- የአቡነ ሺኖዳ ልዕልና
- (መጋቢት 25 2004 ዓ.ም)፡- “የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ አስተዳደር ከእናት ቤተ ክርስቲያን ጋራ አንድነት መስርቷዋል” ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል የጵጵስና ማዕረግ ለማግኘት እጅ መንሻ ያደረጉ ንግግር
- በዋልድባ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል
- ይድረስ ለአባ ጳውሎስ
- ገዳመ ዋልድባን ለመታደግ የፖለቲካ እና የብሔር ልዩነቶቻችን ሊያግዱን አይገባም!!!
- “ጥያቄው ከስኳር እና ከዋልድባ መምረጥ አይደለም” አቶ መስፍን ነጋሽ
- የዋልድባ ገዳም ህልውና "ሳይቃጠል በቅጠል"
- Ethiopian Christians Protest in Washington DC (VOA 3/26/2012)
- በሰሜን አሜሪካ ምእመናን የዝቋላ አቦ ገዳም በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደዋል::
- በአሰቦት ገዳም አንድ ህጻን ተገደለ
- የአቡነ ሺኖዳ ቀብር በቀጥታ
- መ/ር ዘመድኩን በአስቸጋሪው የታራሚዎች ዞን ሐዋርያዊ ተልእኮውን እየፈጸመ ነው
- የአብነት ትምህርት ቤት ለመደገፍ የግንባታና የቋሚ ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ቀረበ
- ለማንም የማይጠቅም ተግባር ‹‹ጦርነት››
- ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ
- የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንድነትና እርቅ ጉባዔ በሐምሌ ይቀጥላል
- የአሰቦት ገዳም እሳት
- የእሳት ቃጠሎ በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም
- አስር አውቶቡስ ወደ ቤተክህነት
- ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው
- ፋይሉን ወደ መዝገብ ቤት
- ትልቁ መርዛማ እሾህ ተነቀለ
- ስለይምርሃነ ክርስቶስ መጽሐፍ ታተመ
- ቤተክርስትያኒቷ በስነ ተዋልዶና በጤናማ እናትነት ዙሪያ በሰፊው ለመስራት ተዘጋጅታለች
- በሃይማኖት አክራሪነት እና ጽንፈኝነት ዙሪያ የተጀመረው ውይይት ቀጥሏል
- እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም ይንቀሳቀሳል የተባለው ዋሃቢያ በአክራሪነት ተፈረጀ
- “አቡነ ጳውሎስን እና አቡነ መርቆሬዎስን የማስታረቁ ጥረት ቀጥሏል”
- __________________________________________________________
የተሀድሳውያን ጉባኤ በዱባይ
ታላቅ የተሀድሳውያን ጉባኤ በዱባይ ሊደረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል:: ታዲያ የዚህ ጉባኤ ተብዬ ዲስኩር ምን ያወሩ ይሆን? መቼም ዛሬም አባ ዮናስ የወለደው በምንፍቅና እየኮተኮተ ያሳደገው ልጁ በጋሻው አሮጊቷ ሳራ ወልዳናለች ካላቸው አጋሮቹ ጋር ማለትም ምርትነሽ ትዝታው እና ሌሎችም በአንድነት ምንፍቅናን ለማስፋፋት ከሀገር ቤት አልፎ በተለያዩ ሀገራት በመሔድ ምንፍቅናን ለማስፋፋት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው::
አባቱን የማያከብር የሰማይ አባቱን አያከብርም ይህ ደግሞ በጋሻው በአደባባይ አባቶችን የእንጨት ላይ ሽበት ብሎ የሚሰድብ ሰባኪ ወይም ዲያቆን ቤተክርስትያን አልወለደችም:: አባ ዮናስ ግን ወልዷል ልጀቹን ደግሞ አሁን በጉባኤ ቤርያ ላይ ምንፍቅናን ሲደሰኩሩ ምንፍቅናን ሊዘምሩ ይሆን? የመዝሙር ዳንኪራ ሊያሳዩን ወንጌልን በምንፍቅና ለመበረዝ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው::
ከነዚህ የበግ ለምድ ከለበሱ አውሬዎች ይሰውረን አሜን
ከተዋሕዶ የቁርጥ ቀን ልጆች
ይህ መልዕክት ደርሶን ነበር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አንድ አምላክ በሚሆን አሜን
ውድ አንድ አድርገን፣
እንደምን ሰንብታችኃል፣ እኛ የኢ/ኦ/ተ/ ልጆች በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የምንገኝ ይህንን ደብዳቤ ስለ ወቅቱ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮችን አስመልክተን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ልከናል እናንተም ይህንን ከዚህ መልዕክት በማድረስ እንድተባበሩን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡አክባሪያችሁ የተዋሕዶ የቁርጥ ቀን ልጆች
እኛም ይህው ለእናንተ ለአንባቢያን በዚህ መልክ አቅርበናል በpdf ያንብቡ To Read in Pdf
_______________________________________________________________________
3 ክርስትያኖችን በድንጋይ ገደሉ
ደሴ አሬራ እየተባለ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኘው የደብረ ሣህል ቅዱስ ዐማኑኤል ፀበል ተፀብለው ወደ መኖሪያ ቤታቸው እየተመለሱ በነበሩ ወጣቶች ላይ፣ ጳጉሜን 3 ቀን 2003 ዓ.ም ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በአካባቢው ያሉ አክራሪ ሙስሊሞች አስበው እና አልመው ሲጠብቋቸው በነበሩ ክስርትያኖች ላይ የድንጋይ ናዳ በማውረድ ጥቃት አድርሰውባቸው ወዲያው አንድ ሰው የገደሉ ሲሆን ፤ ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ከገቡት ብዙ ክርስትያኖች ውስጥ አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ በህክምና ላይ እያሉ የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ አካላቸውን በጥቃቱ የተጎዱ ክርስትያኖች በሆስፒታሉ ይገኛሉ፡፡የመጀመሪያው ሟች ከፍተኛ ጉዳት ልቡ ላይ ደርሶበት ነው፡፡
በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች ጠይቀን እንደተረዳነው ጉዳቱ የደረሰባቸው በጠመጠሙ አክራሪ ሙስሊሞች መሆኑን የተረዳን ሲሆን ደጀሰላም ላይ የተዘገበው ግን ‹‹አንዳንድ ምንጮች ለጥቃቱ በሰኔ ወር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእገዳ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው “መምህር ግርማ” የተባሉትን አጥማቂ ተከታዮች ››እንደሚጠረጠሩ ብለው የዘገቡት የተሳሳተ እና የተዛባ መረጃ ስለሆነ እንዲስተካከል ስንል እንጠይቃለን፡፡ ይህን መረጃ ቦታው ድረስ ሄደው ወይንም ጉዳቱ ደርሶባቸው በሆስፒታል ያሉትን ሰዎች አናግሮ እና አጣርቶ መዘገብ ያለበለዚያ ደግሞ ጉዳዩ እስኪጣራ እና ጉዳት ያደረሱት ሰዎች እስኪለዩ ድረስ በይሆናል የተሳሳተ መረጃ ለክርስትያኑ ማድረስ ተገቢ አለመሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
________________________________________________________________________
ሀሰት አንናገር እውነትን አንደብቅም
‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››