በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የአከባቢው ምንጮች ገለጹ፡፡ እንደ ደረሰን መረጃ ከሆነ የእሳት ቃጠሎው ሊከሰት የቻለው በአከባቢው የሚኖሩ የኢሳ ጎሳዎች የገዳሙ ሀብት የሆኑትን እንስሳት ለመዝረፍ ባደረጉት ሙከራ መነኮሳቱ ለመከላከል ሲሞክሩ በኢሳዎቹ በተከፈተ ተኩስ ነው፡፡
ትላንት የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠቃቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ የኢሳ ጎሳ አባላት ወደ ገዳሙ ክልል በመዝለቅ የገዳሙን እንስሳት ለመዝረፍ ይሞክራሉ፡፡ የገዳሙ መነኮሳትም ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ኢሳዎቹ በከፈቱት ተኩስ እሳቱ ሊቀሰቀስ ችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ ገዳሙ ላይ በአራቱም አቅጣጫ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡
ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ ተግዳሮቶች የተዳከሙት እና ቁጥራቸው እየተመናመነ የመጡት መነኮሳት የድረሱልን ጥሪ ማቅረብ ተስኗቸዋል፡፡ እስካሁን እሳቱን ለማስቆም አንድም አካል ወደ ገዳሙ አልተንቀሳቀሰም፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ አስራ አንድ ሄክታር የሚሆን የገዳሙ ደን እንዲሁም ልዩ ልዩ እንስሳት መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን!!!
እናቴ ቤተ-ክርስቲያን ምነው ፈተሽ በዛ? ጌታ ሆይ ታንኳዋን ማዕበሉ እያናወጻት ነውና አንተ ድረስልን! አቤቱ ይህ ሁሉ ባለማመናችን፣ በዓመጻችንና በኃጢያታችን ብዛት ነውና ማዕበሉን ጸጥ አድርግልን!!!
ReplyDeletei agree on this idea may God give us his mercy
Deletei agree on this idea may God give his mercy to all of us
Deleteegzianher becherenetu yitebikachew
ReplyDeleteamen cher yaseman
ReplyDeleteጸሎት ጠፋ ክፍፍል በዛ ጭቅጭቅ በረከተ እግዚያብሄር ሆይ ህዘብህን አድን ረስትህን ባርክ ከሰው ፍቅር ሰላም ጠፍቶዋልና አንተ ይቅርበለን አስታራቂ የለ፣ ይቅር ባይ የለ ፣ይቅርታ ጠያቂ የለ፤ ድንግል ሆይ አንቺ የማታዊቂው የለምና መርምረሽ ከልጅሽ አማልጂን!!!!!!
ReplyDeleteጸሎት ጠፋ ክፍፍል በዛ ጭቅጭቅ በረከተ እግዚያብሄር ሆይ ህዘብህን አድን ረስትህን ባርክ
ReplyDelete