Wednesday, February 22, 2012

በስልጤ ዞን የተቃጠለችው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን መንግስት የሰጠው መፍትሄ



 (አንድ አድርገን የካቲት 15 ፤2004 ዓ.ም)፡-  በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አርብ 15 /03/04 በሙስሊም ፖሊስ አባላትና እነርሱን ከሚመስሏቸው ማህበረሰብ አካላት ጋር ሆነው ቤተክርስትያኗን ማቃጠላቸው ከ3 ወረር በፊት ዘግበን ነበር በጊዜው የቤተክርስትያኒቷ ጉልላት በፖሊስ አዛዡ ግቢ ውስጥ መገኘቱን በዓየይናችን ተመልክተነዋል በዞኑ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ አማኞች የሚደርስባቸው ግፍ አስመክቶ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ  18/03/2004 .  በደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር /ቤት  አቤቱታ አቅርበዋል፤  የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ቃል አቀባይ የሆኑት እስከ 10 ሠዓት ድረስ ሲሳለቁባቸው ውለው ያለ ምንም መፍትሄ መሸኝታቸውን ገልፀን ነበር::
በጊዜው  አቤቱታ አቅራቢዎቹ ተመልሠው ወደመጡበት አካባቢ ቢመለሱ የመኖር ህልውናቸውናቸው አስጊ በመሆኑ በመጀመሪያ የደቡብ ክልል ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ከዞኑ ፖሊስ ለሚደርስባቸው ጫና ገለልተኛ በሆኑ ፖሊስ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቀጥሎም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ በባዶ ሆዳቸው መሪር እንባ እያነቡ ሲናገሩ ላያቸው ያስለቅሱ ነበር፡፡


ይህ እንዲህ እያለ መንግስት ከፌደራል ጉዳዮች ቢሮ ጉዳዬ የሚመለከታቸው ሰዎችን በማደራጀት ቦታው ድረስ በመሄድ ሁኔታውን በመመልከት መፍትሄ ለመሻት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ነበር ፤ ጊዜ ቢወስድም ከመንግሰት የተወከሉ ሰዎች እና እና የክልሉ  ጸጥታ ጉዳይ አቶ አሰፋ አብዮ በስልጤ ዞን ስልጢ ከተማ በመገኘት በተቃጠለችው በአርሴማ ቤተክርስትያን  ዙሪያ የቤተክርሰትያን አባቶችን እና የሚመለከታቸው የእስልምና አባቶችን ፤ የወረዳው ባለስልጣናትን አንድ ላይ በመሆን በማናገር ከዚህ የሚከተለው ውሳኔ ተደርሳል

1.      ቦታው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የጥምቀት ቦታ ሆኖ እንዲረጋገጥ
2.     ሙስሊሞች በቦታው ሰግደናልሚሉት ተኣማኝነት ስለሌለው የኦርቶዶክስ ሆኖ እንዲጸና
3.  የወረዳው ባለስልጣናት የወል መሬት ነው ለምን ለቤተክረስቲያና ብቻ ይሆናል ? ያሉት በአዲሱ መንግስት ህግ በተፋሰስ ጥበቃ ምክንያት የወል መሬት ስለማይኖር የጥምቀት ቦታ ሆኖ በቋሚነት እንዲጸና
4.  በአቅራቢው ያለው የሙስሊም መቃብር ነው የሚባለው ቦታ ከበፊትም የጠየቀውም ሰውም ሆነ  የነካው ስለሌለ ለሙስሊሞች ሆኖ እንዲጸና አዛው ቦታው ላይ እንዲሆኑ ፤ ወደ ኦርቶዶክሶቹ ቦታ እንዳይመጡ
5.     ቦታው ክርክር ስለጸናበት ለቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን  ማሰሪያ ሌላ ቦታ እንዲሰጥ እንጂ ቦታው ላይ ቤተክርስቲያን መስራት መፍቀድ እንደማይቻል( በአሁኑ ሰዓት የሀይማኖት ቦታ ክርክር ያለባቸውን ቦታዎች መንግስት የሚፈታው ከሁለቱም በማንሳት ለሌላ አላማ በማዋል መሆኑን በማውሳት ነገር ግን የጥምቀት ቦታ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኑ ተለዋጩ የአርሴማ ቤተክርስትያን  መስሪያ ቦታ ለልማት የጠየቁትም ጭምር በዞኑም ሆነ በወረዳው አስተዳደር በአስቸካይ እንዲሰጥ)
6.     ለጠፋውና ለተቃጠለው በሽምግልና እንዲፈታ
7.      የእርቅ ፕሮግራም በስልጢ ከተማ አቶ አሰፋ ባሉበት በስልጢ ከተማ የካቲት 17 እንዲደረግ
8.     እርምጃሚወሰድባቸው በለስልጣናት በደረጃው እንደሚወሰድ ፤

በጊዜው የነበረው የዞኑ አስተዳዳሪ መንግስት ከመደበው ቦታ ተነስቶ ችግሩ ከተፈጠረበት ጊዜ በኋላ  አዲስ አበባ በሌላ የመንግስት የስልጣን ቦታ ላይ መመደቡን ለማወቅ ችለናል፡፡ ይህን የመሰለ ስራ ለሰሩ ከለላ በመስጠት እና በመተባበር ለእኩይ አላማቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገን ሰው ስራ ተመርምሮ ለህግ መቅረብ ሲገባው ቦታ ለውጦ ሌላ ሀላፊነት መስጠት ምን ይሉታል ? ይህን የመሰለውን የመንግስት አካሄድ እንቃወማለን ፤ ወደፊት የት እንደተመደበ ፤ ቦታው ፤ የስራ ሀላፊነቱን በሰፊው እናቀርብሎታለን ፤ አሁን ይህ ነገር ፕሮሞሺን ነው ዲሞሺን ? ያጠያይቃል


በቦታው ላይ ደግማችሁ ቤተክርስያ መስራት አትችሉም ለሚለው ለጊዜው ምንም የምንለው ነገር ባይኖረንም በቪዲዮ የተቀነባበረ ቦታውን የሚመለከት የአንድ ሰዓት ፊልም እናቀርብሎታልን ፤ እርስዎም ላይ ላዩን ሳይሆን ስለቦታው በቂ መረጃ ይኖሮታል:: ነገሩን ከማርገብ እና ቦታው ላይ ሰላማዊ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ የተወሰደው እርምጃ ከሞላ ጎደል ደህና ነው የሚል እምነት አለን ፤ ማህበረሰቡም በእምነት መካከል ያለውን ተቃርኖ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመሆን እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ቀላል ነገር አይደለም ፤ እኛም እንደ እምነቱ ተከታዮች ለተቃጠለችው ቤተክርስትያና የቻልነውን አቅማችን የፈቀደውን ነገር በእውቀት ፤ በገንዘብ ልንረዳቸው ግድ ይለናል ፤ በሌሎች አካባቢዎች ያሉትን አብያተክርስትያናት ከዚህ አይነት አደጋም ቀድሞና ነቅቶም መጠበቅ ያለብን ይመስለናል ፤ እንደ እኛ እምነት በፊት ከነበረችው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን በተሻለ ዲዛይን እደምትሰራ እርግጠኞች ነን ፤ 
የሀገረሥብከቱ ሥራአስኪያጅ   መጋቢ ሀይማኖት አብርሐም   ስልክ  0911551516 ሲሆን አዲስ ለምትሰራው ቤተክርስትያን የምትረዱበት መንገድ በዚህ ስልክ ደውለው ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
‹‹ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።›› 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፤27-28 

20 comments:

  1. Egziabher Yistilin. melkam zena new. Beagliglotachihu Yatsinachihu.

    ReplyDelete
  2. Egiziabiher yisitiln. beketayum cher were yaseman

    ReplyDelete
  3. Thanks to God,and thanks to you who gives us the information on time, and let us build the new church!!!.

    ReplyDelete
  4. Kidanemariam Ze Negelle BoranaFebruary 23, 2012 at 2:51 AM

    ...እለት አለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው፡፡

    ReplyDelete
  5. Thanks for your information and News. Many Blessings to you. I have contacted the person in charge for an immediate reconstruction.

    ReplyDelete
  6. የፌድራል መንግሥቱ የወሰደው እርምጃ ገለልተኛ ሆነን ካየነው መልካም ነው::

    ReplyDelete
  7. Egziabiher Yimesgen!! Eski Egziabiher wesagnochin bewusaneyachew Yatsinalin.

    ReplyDelete
  8. Egziabiher Yimesgen. Eski Egziabiher wesagnochu wusaneyachewun endiyatsenu Yadirgilin.

    ReplyDelete
  9. "በጊዜው የነበረው የዞኑ አስተዳዳሪ መንግስት ከመደበው ቦታ ተነስቶ ችግሩ ከተፈጠረበት ጊዜ በኋላ አዲስ አበባ በሌላ የመንግስት የስልጣን ቦታ ላይ መመደቡን ለማወቅ ችለናል" አይነተኛ የኢሃዲግ ጠባይ። ወረዳ ላይ የበደለ ዞን ላይ በትልቅ ስልጣን እና ደሞዝ ይመደባል። ዞን ላይ ህዝብን ያስለቀሰ እና በሙስና የዘቀጠ አዲስ አበባ ላይ ሚነስቴር ይሆናል አልያም ትልቅ ስልጣን ያገኛል። ቤተክርስቲያንን ያቃጠለ ግን እንዲህ ሲደረግ ዝም አንልም። ለፍርድ ቀርቦ ማየት እንፈልጋልን። ትዝ ይላችኋል ሀዋሳ ላይ ቁራን ተቀደደ ተብሎ የነበረውን ጋጋታ? ቀደደ የተባለው ተማሪ(ያለምንም ማረጋገጫ) ከት/ት ገበታው ታግዷል። በመጨረሻ ላይ ተቀደደ የተባለው ግን ቅራን አልነበረም። ቤተክርስቲያን ያቃጠለን መንግስት የሚቀጣልን በመሾምና በመሸለም ነው? ተዋህዶ ንቃ!!!

    ReplyDelete
  10. Ebakachu YIH beki ayidelem yetekatelew meskid bihon eko asbut yemfeterewun neger orthodox eyetaden yitared neber. Yih bekinew belen zim malet ayigebam berget menm enquan ende musilimoch megdel ena makatel tikikl new belen banamnem enka, yakatelewun makatel bayatsedkim ayaskonenm.

    ReplyDelete
  11. yeh hulu beteleyaye akitacha yemnenor ortodox yemiyaneka new bertu beawunu gize yeche bet yemitebkat yebetektistian abatm wone yemengist akal ataratari selehone ortodox neka menm kemanm antebk

    ReplyDelete
  12. Agame takame yehonawe mangistachne Orthodoxn sechkune yetayal yeha gene lerasue tifatine mametau ayekarime!!

    ReplyDelete
  13. Betam Yeazazenal telaten ensafer ebakachu

    ReplyDelete
  14. Betam Yeazazenal telaten ensafer ebakachu

    ReplyDelete
  15. Yeazazena., egziaber kegna gar yiun

    ReplyDelete
  16. herq ke tikikilegna firid behuala new mehon yalebet. betekirisitian eyaqatelu ye silitan ediget, beshimigilina mecheres minamin....

    ReplyDelete
  17. egzeyaber hoy be meret ayne gobgnen abetu getaye hoy le telatoch lebona sitachew!!!!

    ReplyDelete
  18. MESGANA LEDENGEL MARYAM LEG LE AMLAKACEN EYSUS KERSTOS YEUNEEEEE AMEN MESMAR ENA KERSTYAN BETEMETA KUTER EYTEBKE ENDMHEDE YALWKU KALU LEYWEKU YEGEBAL GENA BEZU TAMER BEZMENACEN ENYALEN BE HAYMANOTACEN BECA TENTEN ENGEGGGGGGGG GETA MEKTATUN GEMROAL BE HOSAENA YETEGEMERW KETAT GENA BEULUM YEKERSTYANOCE TKWAMYOCE LAY YEKTELAL KEGA GAR YALEW KENSU GA KALEW YEBELTAL ENA

    ReplyDelete