በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ከተቃጠለ በኋላ የምእመኑ ለቅሶ ….
(አንድ አድርገን የካቲት 2 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- 2004 ዓ.ም ዓመት ውስጥ የቤተክርስትያናችን ፈተና ከቀን ቀን እየከፋ የሄደበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ፤ የውስጥ ፈተናችን እንዳለ ሆኖ ከውጭ ከመናፍቃን እና ከአክራሪ ሙስሊሞች የሚቃጣብን ጥቃት እየጨመረ ይገኛል ፤ ይህ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ መንግስት ህዝቡን ወደ ማይፈለግ የእርስ በእርስ ቀውስ ውስጥ ይከተዋል ፤ ከዚህ በፊት የተቃጠሉብን ቤተክርስትያናት ፍትህ ከመንግስት ሳናገኝ ሌላ ተጨማሪ ጥቃት እየደረሰብን ይገኛል ፤ ይህን ጉዳይ መንግስትም ሆነ ጠቅላይ ቤተክህነት ዝምታ መምረጣቸው ለምን እንደሆነ አልገባልም፤ ጠቅላይ ቤተክህቱ ሁኔታውን ተከታትሎ የደረሰውን አደጋ ለምዕመኑ ማሳወቅ ፤ ይህን ጉዳት ያደረሱትን ሰዎች ከፖሊስ ጋር በመተባበር ፍርድ ቤት የማቆም ፤ የተቃጠሉት አብያተ ክርስትያናት የሚሰሩበትን መንገድ ከሀገረ ስብከቶቹ አስተዳዳሪዎች ጋር በመሆን የማሰራት ኃላፊነት አለበት ፤ ይህን ዜና ከድህረ ገፅ ውጪ በጋዜጣ እና በመሰል የመረጃ መስተላለፊያ መንገዶች መተላለፍ እና ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀም ምእመኑ ቤተክርስትያን እንዲጠብቅ ሃላፊነቱን እንዲወጣ መንገድ ከፋች መሆንም ይጠበቅበታል ፤ በየጊዜው ይህ የመሰለ ጥቃት ቢደርስብንም መፍትሄ ግን የሚሰጥ አካል አላገኝንም ፤ መንግስት ሰላም እንዲያስጠብቁ የመደባቸው ፖሊሶች በዚህ ዙሪያ ተሳታፊ መሆናቸው ጥቃቱ ምን ያህል እንደሆነ ያሳየናል ፤ አሁንም ጊዜው አልመሸም ፤ ጊዜው አልሄደም ፤ ይህን ያደረጉትን ሰዎች ለሚመለከተው ክፍል በቪዲዮ እና ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎች ከፌደራል ጉዳዮች ለተወከሉ ሰዎች ተሰጥቷቸዋል ፤ ፍትህ ላለመስጠት ዝም የተባለበትን ሁኔታ እኛን አልገባልም ፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱሰ ሲኖዶስ አባል፣ የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ሓላፊዎች፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የደብር አለቆች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፌደራል ፖሊስ ጸጥታ አስከባሪዎች በቦታው ተገኝተው ምዕመናንን ለማረጋጋትና ለማጽናናት ችለዋል፡፡ ከዚህ በተያያዘ በወረዳው የሚገኙ አጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ምዕመናን ወደ ወረዳው ከተማና ቤተ ክርስቲያኑ ወደ ተቃጠለበት ቀበሌ በመድረስ ህዝቡን አጽናንተው የአብሮነት ስሜታቸውንም ሲገልጹ እንደነበር በምስሉ ተመልክተናል፡፡
‹‹ፍትህን ከመንግስት ብናጣ ፤ ከእግዚአብሔር እውነተኛ ፍርድን አናጣም››
abetu endechernetih enji endebedelachin ayhun
ReplyDeleteየኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ እምነቱን ለመበረዝ አልሳካ ሲላቸው መናፍቃኑ ወደ ለየለት ሽብርተኝነት ተሸጋግረዋል ይህንንም ቅድስት ቤተክርስትያን በማቃጠል መጨረሻ ወደ ሌለው ሽብር ሀገሪቷ እንደትገባ እያደረጉ ይገኛሉ መንግስት ሆይ አገርን ከማሳደግ በፊት ሰላም ይቀድማል ቢታሰብበት! ለመላው ምእመን መፅናናትን እመኛለሁ::
ReplyDeleteይህ ህዝብ ቢከፋ ሄዶ ብሶቱን የሚተነፍስባት፣ ቢደሰት እልል የሚልባትን ቤተ ክርሰቲያንን የዚህን ያህል ነው የሚወዳት ሁላችሁም እወቁ፡፡ይህ እንባ የት ያደርሳቸው ይሆን?
ReplyDeletePlease Every Body Gud kemawrat lemin tselot anitseliyim. yegna hatiyat eco new. Pleaseeeeesssss
ReplyDeletetselehu, tselehu....Abetu yahonabenen aseb!!!
ReplyDeleteEnem Alekesku...Abbetu Yehonebnin Asib!
ReplyDeleteእኔን፡የማይገባኝ፡መንግስት፡አውቆ፡ነው፡እንጂ፡በማያገባው፡ሱማሌ፡ድረስ፡ሄዶ፡ሽብርተኛ፡አጠፋለሁ፡ከሚል፡እነኚህን፡አገር፡ ውስጥ፡ያሉ፡የዲያቢሎስ፡ተከታዮች፡አያጠፋልንም፡፡ለነገሩ፡አመራሩስ፡ያው፡የሚከተለው፡ዲያቢሎስን፡አይደል፡፡ እግዚአብሔር፡ለሁሉም፡የስራውን፡ይከፍለዋል፡፡
ReplyDeleteአምላካችን፡ሀገራችንን፡ይጠብቅልን!!!
የእመቤታችን፡ምልጃ፡አይለየን!
እኔ የምፈራው አንድ ነገር ነው፡፡ብዙ ጊዜ የሆነ ክፉ ነገር ሲነገርና ምንም መፍትሄ ሳይሰጠው ከቀረ፤ በተለይ የምንሰማና የምናነብ ሰዎች እንዲህ ያለውን ክፉ የጭካኔ ስራ ጆሮአችን እንዳይለምደው ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም ብዙ ነገሮችን ሰማን ሰማን ሰማን ግን ምንም ነው መጨረሻው እና ይህ መፍትሔ አለማግኘትና ክፉ ወሬን ሰምቶ የእናት ቤተክርስቲያንን በደል ተመልክቶ ዝም ማለት ትንሽ ቆይተን እንዳንለምደው ነው ፍርሃቴ፡፡ እርሱ መድሐኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከኛ ይልቅ ለቤቱ ቀናኢ ነውና እኛ ዝም ብንልም፤ የዘገየ ቢመስለንም ቤቱን ግን ያጸዳል፡፡ የቅዱሳን አምላክ እርሱ ይፍረደን እንጂ ሌላ ምን ይባላል፡፡ እመቤቴ ድንግል ማርያም የአስራት አገርሽን አትርሻት፡
ReplyDeleteSelam le'enante yihun
ReplyDeleteEgzeabher firdun kejemere yihin hulu kifat yemiyadergew telat megbiyaw yet yihon? ene yemazinew bezih se'at yebetekrstianachin ras honew letekemetut new yekedemut abatochachin mak lebsew befitsum hazenina lekso Amlakachewin yileminu neber! Abetu Amlakachin hoy ewnetegna tebaki tselotegna Abatochin atasatan. Egzio Meharene Kiristos!!!!
Welete Sellassie
Selam le'enante yihun
ReplyDeleteEgzeabher firdun kejemere yihin hulu kifat yemiyadergew telat megbiyaw yet yihon? ene yemazinew bezih se'at yebetekrstianachin ras honew letekemetut new yekedemut abatochachin mak lebsew befitsum hazenina lekso Amlakachewin yileminu neber! Abetu Amlakachin hoy ewnetegna tebaki tselotegna Abatochin atasatan. Egzio Meharene Kiristos!!!!
Welete Sellassie
በእዉነት የሃይማኖት እኩልነት በአገራችን እንዳሌለ አሁን ተረዳሁ፡፡እኛዉ በእግድነት የተቀበልናቸዉ መጤዎች በገዛ አገራችን ሲያጠቁን ዝም ብሎ ማየትና በምላስ ከሚደልለን መንግስትና አቡኑ መፍትሔ መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፡፡ ደግሞም ቁራናቸዉ ከዚህ የተለየ ስላልሆነ ከዚህ በኋላም የተሻለ ነገር ከእነሱ አንጠብቅም ስለ ፅዮን ዝም አልልም እንደ ተባዉ ስለ ቤ/ክ ዝም ልንል አይገባም፡፡
ReplyDeleteእኔ የምፈራው አንድ ነገር ነው፡፡ብዙ ጊዜ የሆነ ክፉ ነገር ሲነገርና ምንም መፍትሄ ሳይሰጠው ከቀረ፤ በተለይ የምንሰማና የምናነብ ሰዎች እንዲህ ያለውን ክፉ የጭካኔ ስራ ጆሮአችን እንዳይለምደው ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም ብዙ ነገሮችን ሰማን ሰማን ሰማን ግን ምንም ነው መጨረሻው እና ይህ መፍትሔ አለማግኘትና ክፉ ወሬን ሰምቶ የእናት ቤተክርስቲያንን በደል ተመልክቶ ዝም ማለት ትንሽ ቆይተን እንዳንለምደው ነው ፍርሃቴ፡፡ እርሱ መድሐኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከኛ ይልቅ ለቤቱ ቀናኢ ነውና እኛ ዝም ብንልም፤ የዘገየ ቢመስለንም ቤቱን ግን ያጸዳል፡፡ የቅዱሳን አምላክ እርሱ ይፍረደን እንጂ ሌላ ምን ይባላል፡፡ እመቤቴ ድንግል ማርያም የአስራት አገርሽን አትርሻት፡
ReplyDeleteበእዉነት የሃይማኖት እኩልነት በአገራችን እንዳሌለ አሁን ተረዳሁ፡፡እኛዉ በእግድነት የተቀበልናቸዉ መጤዎች በገዛ አገራችን ሲያጠቁን ዝም ብሎ ማየትና በምላስ ከሚደልለን መንግስትና አቡኑ መፍትሔ መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፡፡ ደግሞም ቁራናቸዉ ከዚህ የተለየ ስላልሆነ ከዚህ በኋላም የተሻለ ነገር ከእነሱ አንጠብቅም ስለ ፅዮን ዝም አልልም እንደ ተባዉ ስለ ቤ/ክ ዝም ልንል አይገባም
be abune pawulos zemen gena bizu tifat einayalen
ReplyDeletewho burn the church must be mesanger of woyanie other wise if there is government must take serious action! if does not get licence no body can not touch or pass by there.
ReplyDelete