Monday, May 29, 2017

After 20 years…አሰግድ ሣህሉ ተወገዘ………አሰግድ ሣህሉ ማነው ?




  • ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀኝ ቆሞ ያማልዳል፤›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ተቀበልንም አልተቀበልንም ለውጥ የለውም›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› የተባለ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅት የመሠረተ ነው
  • ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አማኞች የጸሎት ቤት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሰሎቹ ጋራ ተካፍሎ ሲወጣ ተደርሶበታል
የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ - አሰግድ ሣህሉ እንደ ማሳያ

አሰግድ ሣህሉ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የተሐድሶ ኑፋቄን ለማስፋፋት፣ አንዳንድ የሰንበት ት/ቤቱን ወጣቶች ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወደ ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አዳራሽ ለመውሰድ ሲያደርግ የቆየውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጥብቅ ሲከታተል በቆየው የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ኮሚቴ የተዘጋጀው ባለ 40 ገጽ ሰነድ ያስረዳል፡፡ እንደ ዘገባው ማብራሪያ አሰግድ ሣህሉ ከሚኖርበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤት ቁጥር 417 በተለምዶ ቡልጋሪያተብሎ ከሚጠራው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል - የከርቸሌው ሚካኤል አካባቢ ያለሰበካው ወደ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ በዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት በ1985 ዓ.ም የተመዘገበው ሰንበት ት/ቤቱ በወቅቱ ያጋጠመውን የአገልግሎት መዳከም ተመልክቶ ስውር የተሐድሶ ኑፋቄ ተልእኮውን ለማራመድ እንዲያመቸው ነው፡፡

የቅዱስ ያሬድ የዕውቀት ጎዳና


By በሔኖክ ያሬድ  
‹‹የያሬድ ስም ገናና የሆነው በዝማሬው ብቻ አይደለም፡፡ የቃላቱ ጣዕም፣ የቅኔዎቹ ረቂቅነትና የሐሳቡ ምጥቀት እኩያም የለው፤ እንዲያው ቀረብ ብለን ብናጠናው ለመላ የባህል ታሪካችን ዋና ምንጭ መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ ግን ሊቃውንቶቻችን በጸሎትነት ሲዘምሩት፣ በተመስጦ ሲደጋግሙትና በረቀቀ ውዝዋዜ ሲያሸበሽቡት ነው የኖሩት እንጂ፣ ታሪካዊ ይዘቱንና ማኅበራዊ መልእክቱን ተንትነው በጽሑፍ አላቆዩንም፡፡ አሁን እኛ፤ ይህንን ለማድረግ መጀመር አለብን፡፡››

ይህ ከሠላሳ ዓመታት በፊት በታተመ አንድ የጥናት መጽሔት (ጆርናል) ላይ የታሪክ ምሁሩ ታደሰ ታምራት (ፕሮፌሰር) ስለ ስድስተኛው ምታመት ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሥራዎች በምልዐት አለመጠናቱ ያሳሰቡት ኃይለ ቃል ነበር፡፡ የቅዱስ ያሬድ ልሂቅነት ከዜማ ከማኅሌት ባለፈ ያለመተንተኑ ታሪካዊው ጥንተ ነገሩ ዘመኑና ትውልዱ እንዲያውቁት መጣና እንደሚገባም ያስተጋቡት የጥናት ደወል ነበር፡፡

1504 ዓመታት በፊት የኖረው ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን ልደቱ፣ ግንቦት 11 ቀን ደግሞ ዕረፍቱ (መስወሩ) የሚዘከርበት ነው፡፡ በተለያዩ ዘመናት በልደቱም ሆነ በመሰወሪያው ዕለት በተለያዩ ተቋማት የመታሰቢያ ዝግጅቶች ይብዛም ይነስም ሲቀርቡ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን ሺሕ ዓመት (ሚሌኒየሟን) በተቀበለችበት 2001 .. ዋዜማ፣ በጳጉሜን 2000 .. በሚሌኒየም አዳራሽ፣ 1500 ዓመተ ልደቱ በባህል ማዕከል ከዜማና ቅኔ ጋር በተያያዘ ዝክረ ያሬድ ተከናውኖም ነበር፡፡

Wednesday, May 24, 2017

የግዕዝ ቁጭት




በዘመኑ  በዓለም ከነበሩት ኃያላን መንግሥታት አንዱ ቀዳሚ የነበረው የአክሱም ዘመነ መንግሥት፣ በሥልጣኔው ጫፍ የነካ እንደነበር ቢወሳም፣ እስከዛሬ የአክሱም  ነገረ-ሥልጣኔ ከአምስት በመቶ በላይ አለመጠናቱን ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይ በሥነ ሕንፃ፣ ሥነ መድኃኒት፣ ቅርጻ ቅርጽ፣ አስተዳደር፣ የሥልጣን ሽግግር፣ የሥነ ከዋክብት፣ ንግድና  እርሻ፣  የባህር ላይ እንቅስቃሴ ጫፍ ለነካው ለዘመኑ ቴክኖሎጂም  ግራ የሚያጋቡ እንደሆኑ ምርምሮች ያመለክታሉ፡፡

የሥልጣኔውን ልዕልና ይመሰክሩ ዘንድ በተለይ የአክሱም ዘመነ መንግሥት በተቆረቆረበት መንደር ዛሬም ድረስ ቆመው የሚገኙት ከአንድ ድንጋይ የተጠረቡ ሰማይ ጠቀስ ሐውልቶቹ፣ በትግራይና በዛሬ ኤርትራ አካባቢ የሚገኙ በሺሕ የሚቆጠሩ ከተራራ የተፈለፈሉ የሕንፃ ሥራዎች፣ መቃብሮችና ከመሬት ወለል በታች በቁፋሮ በመገኘት ላይ  ያሉት (ከአክሱም ዘመንም ቀድመው የተሠሩ) ቤተመንግሥቶችና በውስጣቸው የሚገኙ ጥንታዊ ቁሳቁሶች የተመራማሪዎች ቀልብ እየሳቡ ሲሆን፣ አንድ ነገር ግን የተዘነጋ ይመስላል፡፡